TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ተክለብርሃን አምባዬ ኮንስትራክሽን🔝

በአዲስ መልክ በመሰራት ላይ ባለው የኮተቤ ካራ የመንገድ ፕሮጀክት በግንባታ ላይ ያለ ድልድይ አርማታ እየተሞላ ባለበት ወቅት ድልድዩን ለመስራት የሚያግዝ መወጣጫ የካቲት 11 ቀን 2011 ዓ.ም በመደርመሱ በሰራተኞች ላይ ከቀላል እስከ ከባድ ጉዳት እንዲደርስ #ምክንያት ሆኗል፡፡

የመንገድ ፕሮጀክቱ ስራ ተቋራጭ ተክለ ብርሀን አምባዬ ኮንስትራክሽን የተጎጂዎችን ህይወት ለማትረፍ የተሳተፉ አካላትን #ለማመስገን ባዘጋጀው ፕሮግራም በተጎጂዎቹ ላይ የሞትና ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስ የአካባቢው ማህበረሰብ፣ የፖሊስ አባላት፣ የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ሰራተኞች፣ የህክምና ባለሙያዎች እና ሌሎች የህብረተሰብ አካላት ከፍተኛ ርብርብ በማድረጋቸው ከፍተኛ #ምስጋና አቅርቧል፡፡

በአደጋው በአንድም ሰው ላይ የሞት አደጋ እንዳልደረሰ እና የተጎዱ ሰራተኞች የህክምና እርዳታና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኙ ያሥታወቀው ስራ ተቋራጩ አደጋው ባጋጠመበት ወቅት የአካባቢው ነዋሪዎችና የተለያዩ አካላት አፋጣኝ ትብብር ማድረጋቸው የከፋ ችግር እንዳይፈጠር አስችሏል ብሏል፡፡

የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ #ሰይፉ_አምባዬ በአደጋው እና በደረሰው ጉዳት በጣም አዝነናል፤ የአደጋው ምንጭም በገለልተኛ አካል እየተጠና ይገኛል ብለዋል፡፡

በምስጋና ፕሮግራሙ ላይ የተገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችም በቀጣይ ተመሳሳይ አደጋዎች እንዳይደገሙ ስራ ተቋራጮች ቅድመ ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ሞገስ ጥበቡ በበኩላቸው የስራ ላይ አደጋዎች ባለስልጣኑን እንደሚያሳስበው ገልፀው መንገድ የምንገነባው ለህብረተሰቡ ልማትና ዕድገት በመሆኑ ስራዎች ሲከናወኑ የህብረተሰቡንና የሰራተኞችን ደህንነት ማዕከል አድርገው መሆን አለበት ብለዋል፡፡

ኢ/ር ሞገስ አክለውም የኮተቤ ካራ የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ መጓተቱ በአካባቢው ማህበረሰብ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ጫና እየፈጠረ በመሆኑ የግንባታ ስራውን ማጠናቀቅ በሚቻልበት ዙሪያ ከስራ ተቋራጩ ጋር በልዩ ሁኔታ ተነጋግረን ስምምነት ላይ ደርሰናል ብለዋል፡፡

በመጨረሻም ኢ/ር ሞገስ በድልድዩ ስራ ያጋጠመው አደጋ መንስኤ ጥናት እንደተጠናቀቀ ለህብረተሰቡ ይፋ የሚደረግ መሆኑን ገልፀው ጉዳት የደረሰባቸው ሰራተኞች ወደ ጤንነታቸው እንዲመለሱ አስፈላጊ የሚባለውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል፡፡

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን
@tsegabwolde @tikvahethiopia