TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#EHRC የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በተለያዩ አካባቢዎች በመንግሥት እና በታጠቁ ኃይሎች በሲቪል ሰዎች ላይ እየተፈጸሙ ያሉ ጥቃቶችን በቅርበት በመከታተል ላይ ይገኛል።  ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም. በምዕራብ ወለጋ ዞን ግምቢ ወረዳ ቡሌ ቀበሌ በመንግሥት እና በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (በተለምዶ ‘ኦነግ ሸኔ’) ታጣቂዎች መካከል ሲደረግ ከነበረው ውጊያ ጋር በተያያዘ በታጣቂው ቡድን በአካባቢው…
#ምዕራብ_ወለጋ

በምዕራብ ወለጋው ጥቃት የተገደሉት ብዙዎቹ ሴቶች እና ህፃናት መሆናቸውን የምዕራብ ወለጋ ቲክቫህ ቤተሰብ አባላት አሳውቀዋል።

አንድ ቤተሰቦቹ የተገደሉበት የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ፥ " የኔ ወንድም ሚስቱ 7 ወር ነፍሰጡር እና ልጁ 1 አመት 350 ቀን የሆናት ታውቃላችሁ ምን እንደሚላት 40 አመት በኃላ ክብርት ፕሬዝዳት ከድጃ መሃመድ ይላት ነበር ግን ያ ሳይሆን ቀርቶ ሰኔ 11/2014 አራት ነብስ ጠፋ " ሲል መልዕክቱ ልኳል።

ይኸው የቤተሰባችን አባል ንብረታቸው በጠቅላላ እንደወደመ በዚህ ሰአት የሞቱ ሰዎች አስክሬን እየተሰበሰበ እየተቀበረ መሆኑን ጨምሮ ገልጿል።

እናቴ አባቱ እንዲሁም እህቶቹ የት እንዳሉ እንደማይታወቅም አክሏል።

እስካሁን ትክክለኛውን የሟቾች ቁጥር ማወቅ እንዳልተቻለ ፤ አሁንም ከጫካ ውስጥ አስክሬን እየተገኘ መሆኑን የአካባቢው የቲክቫህ አባላት ገልፀዋል።

ወደ ስፍራው የመከላከያ ኃይል የተላከ ሲሆን አሁንም ተጨማሪ ኃይል ካልተላከ በሌላ ቀበሌ ሌላ ተጨማሪ ንፁሃንን ህይወት የሚቀጥፍ ጥቃት ሊሰነዘር ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን ገልፀዋል።

የመንግስት ተቀዳሚ ተግባሩ የዜጎችን ደህንነትና በሰላም የመኖር ዋስትና ማረጋገጥ ነውና ደህንነታቸውን እንዲያስጠብቅ ፤ ሌላ ጥቃት እንዳይፈፀም አስፈላጊውን ሁሉ እንዲያደርግ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ትላንት ጥቃት በተፈፀመበት አካባቢ ከፍተኛ የፀጥታ ስጋት በመኖሩ ነዋሪዎች ድጋፍ እንዲደረግላቸው እየጠየቁ መሆኑን ዛሬ ባወጣው አጭር መግለጫ መግለፁ ይታወቃል።

@tikvahethiopia