TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ሺርካ

ባለፈው ህዳር ወር በርካታ ሰዎች በተገደሉበት ሺርካ ወረዳ ትላንት ታህሳስ 8 ቀን 2016 ዓ/ም ግድያ መፈፀሙ ተሰምቷል።

በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ሺርካ ወረዳ ጋላማ በሚባል አካባቢ ታህሣሥ 8 ቀን 2016 ዓ.ም 4 ኦርቶዶክሳውያን በታጣቂ  ኃይሎች መገደላቸውን የ " ማህበረ ቅዱሳን ቴሌቢዥን " ምእመናን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

አራቱ ምእመናን በጉዞ ላይ ሳሉ ከሚጓዙበት  መኪና በማስወረድ በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን ተጠቁሟል።

ከሟቾች መካከል በሺርካ ወረዳ አቡነ ገብረ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የአቋቋም  መምህር እንደሚገኙበት ተገልጿል።

እየተፈፀመ ያለውን ተከታታይ ግድያ ለማስቆም የመንግስት የጸጥታ አካል  ምንም አይነት እርምጃ እየወሰደ እንዳልሆነ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ቅዱስ ሲኖዶስ መሰል ጥቃቶች እንዲቆሙ ጥሪ ማቅረቡ ይታወቃል።

ባለፈው ህዳር ወር ከጨቅላ ህፃን አንስቶ እስከ 70 ዓመት አዛውንት እንዲሁም በርካታ የአንድ ቤተሰብ አባላት በዚሁ ወረዳ መገደላቸው ይታወሳል።

ከተፈፀሙ ግድያዎች ጋር በተያያዘ የኦሮሚያ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን መንግስት በአሸባሪነት የፈጀውን ' ሸኔ ' (እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሚለው ታጣቂ ቡድን) ተጠያቂ ማድረጉ አይዘነጋም።

ህፃን፣ አቅመ ደካማዎችን፣ ሴቶችን ሳይለይ #እየገደለ ያለው ይሄው ቡድን ነው ብሎ ነበር።

ታጣቂ ቡድኑ ግን ኃይላችን " በሰላማዊ ሰዎች ላይ እርምጃ አልወሰደም " በሚል ውንጀላውን አስተባብሎ የነበረ ሲሆን የክልሉ መንግሥት ይህ ኃይል የሚፈጸጸምማቸውን ጥቃት መካድ ባህሪው ነው ብሎ ነበር።

በሺርካ ወረዳ ከተፈፀሙ ግድያዎች ጋር በተያያዘ ውጥቶ በነበረው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ሪፖርት ላይ ፤ " የአካባቢው ነዋሪዎች አሁንም ተደጋጋሚ ዛቻ እየደረሳቸው መሆኑን ገልጸው መንግሥት በአስቸኳይ እንዲደርስላቸው ተማፅነው " እንደነበር መግለፁ የሚዘነጋ አይደለም።

@tikvahethiopia