TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"እኔ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሹም እንጂ የአንድ #ብሔር ተወካይ አይደለሁም። እኔ #ወታደር ነኝ። ወታደር ደግሞ ብሔር የለውም። የሀገር ጠባቂ እንጂ የብሔር ጉዳይ አስፈፃሚ አይደለም" ጄነራል ሰዓረ መኮንን

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲስ አበባ⬇️

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የነዋሪዎች ምዝገባና የመታወቂያ አሰጣጥ መመርያ ቁጥር 3/2010 በማሻሻል፣ #ብሔር_የማይጠቀስበት መታወቂያ ለነዋሪዎች መስጠት ሊጀምር ነው፡፡

የተሻሻለው መመርያ የከተማውን ነዋሪዎች የመታወቂያ አሰጣጥ ከማነዋል ወደ ዲጂታል የሚያሸጋግርና በአሻራ የተደገፈም ስለሚሆን፣ በሐሰተኛ ሰነድ መታወቂያ የያዙ ግለሰቦችን መለየት ያስችላል ተብሏል፡፡

ይህንን አሠራር ተግባራዊ ለማድረግ በክፍላተ ከተሞችና በወረዳዎች የሚገኙ አመራሮችና ሠራተኞችን ያካተተ ሥልጠና፣ ቅዳሜ ነሐሴ 19 ቀን 2010 ዓ.ም. ተሰጥቷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች መታወቂያ ብሔርን የሚጠቅስ በመሆኑ፣ ይህም ከአንድነት ይልቅ ልዩነቶችን የሚያጎላ ስለሆነ በተገኘው አጋጣሚ ቅሬታ ሲቀርብበት ቆይቷል፡፡

ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ሥልጣን በያዙ ማግሥት ይህንን ጉዳይ በሚመለከት እንደገለጹት፣ የመታወቂያ ጉዳይ ቀላል ቢመስልም ከፍተኛ ቅሬታ እየተነሳበት በመሆኑ አሰጣጡን ማስተካከል ይገባል፡፡

በዚህ መሠረት መመርያው የተሻሻለ በመሆኑ በመታወቂያ አሰጣጥ ላይ በሁለት መሠረታዊ ጉዳዮች ለውጥ ያመጣል ተብሏል፡፡

የመጀመሪያው በመታወቂያ ላይ ከብሔር ስያሜ ይልቅ #ኢትዮጵያዊ ሲባል፣ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ አሰጣጡ ዲጂታል ስለሚሆን ሕገወጦችን መለየት እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡ በተለይ ሕገወጥ ጥቅም የሚሹ ግለሰቦች፣ በተለያዩ ዘዴዎች መታወቂያ በማውጣት ሲያገኙ የቆዩትን ጥቅም እንደሚያስቀር ታምኗል፡፡

ለአብነት በክልል ከተሞች የግል መኖሪያ ቤት እያላቸው በሕገወጥ መንገድ  የአዲስ አበባ ነዋሪነት መታወቂያ በመያዝ ኮንዶሚኒየም ቤት የተቀራመቱትን ዕርምጃ መውሰድ ያስችላል ተብሏል፡፡

የተሻሻለው መመርያ የኮምፒዩተር አመዘጋገብ፣ የነዋሪዎች ምዝገባ ሒደት፣ የነዋሪዎች መታወቂያ ይዘትና የመሸኛ ጉዳይን በዝርዝር ይዟል ተብሏል፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቅርቡ #ብሔር የማይጠቀስበት ዲጂታል መታወቂያ ለነዋሪዎቹ መስጠት ይጀምራል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሀዋሳ ከተማ⬆️

በከተማዋ #ብሔር ተኮር መጠራጠር እንዲሰፍን በበሮች ላይ ቀለም በመቀባት የተሰራው ስራ በህብረተሰቡ እና በመንግስት ንቃት መክሸፉን የሀዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ #ስኳሬ_ሹዳ ገለፁ፡፡

ምክትል ከንቲባው ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ከፊታችን ባለው መስከረም 17 ለሚከበረው የመስቀል ባዓል ለመላው የእምነቱ ተከታዮች #የእንኳን_አደረሳችሁ መልዕከት አስተላልፈዋል፡፡

ከመስከረም 18 እስከ 21 በሀዋሳ ከተማ ለሚካሄደው የደኢህዴን 9ኛ ጉባኤ እንዲሁም ከመስከረም 23 እስከ 25 ‹‹በልማታዊ ዴሞክራሲ ማዕቀፍ የለውጥ እንቅስቃሴያችንን በማስቀጠል የኢትዮጵያን ህዳሴ እናረጋግጥ›› በሚል መሪ ቃል በከተማዋ ለሚካሄደው የኢህአዴግ 11ኛ ጉባኤ ለመላው የድርጅቶቹ አባላትና ደጋፊዎች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውንም አስተላልፈዋል፡፡

በከተማችን ባለፉት 3 ቀናት በተለያየ አካባቢ በተለይም በታቦር፣ በምስራቅና በመናህሪያ ክፍለ ከተማ የተለያዩ ቀለሞችን በመኖሪያ ቤት በሮች ላይ #በመቀባትና ቀለሙን ተከትሎ የብሔር ግጭት ሊኖር እንደሚችል በማስመሰል በተነዛ ወሬ የከተማዋ ህዝብ መጠነኛ ጭንቀት ውስጥ እንደገባ ይታወቃል፡፡

ይህን አአስመልክቶ የከተማ አስተዳደሩ ከክልሉና ከፌደራል የፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር ሰፊ #የፀጥታ ጥበቃና የጥናት ስራ ሲሰራ መቆየቱን የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አቶ ስኳሬ ሹዳ ገልፀዋል፡፡

በዚህም መሰረት በከተማው በግለሰቦች መኖሪያ ግቢ በሮች ላይ የተቀባ ቀለም መኖሩን ማረጋገጥ እንደተቻለም አቶ ስኳሬ ገልጸዋል፡፡

እነዚህ ቀለሞች አንደኛው የከተማ አስተዳደሩ ማዘጋጃ ቤት የቤቶች ደረጃ ምዝገባ ስራ ክፍል የቀባው ሲሆን ሁለተኛው በከተማዋ በቆሻሻ ማንሳት ስራ የተሰማሩ ማህበራት ገንዘብ የከፈሏቸውን ነዋሪዎች ካልከፈሉት ለመለየት የቀቡት መሆኑን ለመለየት እንደተቻለ ምክትል
ከንቲባው ገልፀዋል፡፡

ከዛ ውጪ የተለየ ፍላጎት ያላቸው ቡድኖች ህዝቡን ለማሸበርና የከተማዋን ገፅታ ለማጉደፍ እንዲሁም በህዝቦች መካከል መተማመንና አብሮነት እንዳይኖር በማድረግ ብሔር ተኮር ጥርጣሬ ለማሳደር የቀቡት ቀለም መኖሩንም ለማረጋገጥ ተችሏልም ብለዋል፡፡

በሀገር ደረጃ የተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ እንዳይቀጥል ለማድረግና እንዲቀለበስ ፍላጎት ያላቸው ሀይሎች በተለያየ ጊዜና ቦታ ሲያደርጉት ከነበረው እንቅስቃሴ አንዱ እንደሆነም #ለመረዳት እንደተቻለ አቶ ስኳሬ ገልፀዋል፡፡

በመሆኑም በተደረገው ክትትል ወቅት እኩይ ተግባር ማስፈፀሚያ የሆኑና ገንዘብ የሚከፈላቸው በልመና መስክ የተሰማሩ ጥቂት ግለሰቦች ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉበት ሁኔታ መኖሩን የገለፁት መክትል ከንቲባው ከእነርሱ ውጭ ከሌላ አካባቢ በመምጣት አልጋ
በመከራየት ስለት ነገሮችን ይዘው ሲንቀሳቀሱ የተያዙ ፀጉረ ልውጦች መኖራቸውንም በመጠቆም ነው፡፡

ቀለም በበራቸው የተቀባባቸው ነዋሪዎችም ያለምንም ልዩነት አልፎ አልፎ የተቀባባቸው መሆኑም ተረጋግጧል፡፡ በዚህም በከተማው
የሚኖሩ የደቡብ ብሔረሰቦች ላይ ብቻ ሳይሆን በከተማዋ በሚገኙ ሌሎች የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች በር ላይም መቀባቱ ተረጋግጧልም ብለዋል ምክትል ከንቲባው፡፡

እነዚህ አካላት ላይ በመደረግ ላይ ያለው ምርመራ ውጤቱ ለህዝብ ይፋ የሚደረግ ነው ያሉት አቶ ስኳሬ በአሁኑ ወቅት የፀጥታ ሀይሉና ህብረተሰቡ በአንድ ላይ በመሆን አከባቢውን በንቃት እየጠበቀ መሆኑን ተከትሎ በከተማዋ ከተራ ሽብር እና ወሬ በስተቀር የተከሰተ አንዳችም ችግር አለመኖሩን ጠቁመዋል፡፡

በመሆኑም ከፊታችን ያለው የመስቀል በዓልም ይሁን በጉጉት የሚጠበቀው የደኢህዴንና የኢህአዴግ ጠቅላላ ጉባኤን በከተማዋ ለማክበር ምንም አይነት የፀጥታ ችግር እንደማይገጥም ገልጸው የከተማው ነዋሪዎችና ወደ ከተማዋ የሚመጡ እንግዶች ስጋት እነዳይገባቸው
አሳስበዋል፡፡

ውበት ለከተማችን፤ ስኬት ለህዝባችን…!

©የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹ወንጀለኛ የማንም #ብሔር ተወካይ አይደለም፡፡›› ጠቅላይ አቃቤ ሕግ

በሙስና 27 ሰዎች፣ በሰብዓዊ መብት ጥሰት ደግሞ 36 ሰዎች በአጠቃላይ ከ63 በላይ ተጠርጣሪዎች ተይዘዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ🔝

በተማሪዎች መካከል ሁከትና ብጥብጥ እንዲፈጠር በሚያነሳሱ አካላት ላይ መንግስት አስፈላጊውን #እርምጃ ሊወስድ እንደሚገባ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጠየቁ።

ተማሪዎች የተሳሳተ መረጃን ሳያረጋግጡ ለሌሎች ከማስተላለፍ ተግባር መቆጠብ እንደሚገባቸውም የሐይማኖት አባቶች አስገንዝበዋል።

በዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች መካከል ሰሞኑን በተፈጠረው አለመግባባት ዙሪያ ከተማሪዎችና ባለድርሻ አካላት ጋር  ትናንት በዩኒቨርሲቲው ዋናው ግቢ ውይይት ተካሄዷል፡፡

በውይይቱ ከተሳተፉት መካከል የ2ኛ ዓመት የማኔጅመንት ተማሪ ሐና ይመር እንደገለፀችው በተቋሙ ሁከትና ግርግር የሚፈጥሩ አካላት የማንኛውንም ብሔር እይወክሉም፡፡

”የተከሰተው ችግርም የግል ጥቅማቸውን ለማሳካት ያሰቡ ሐይሎች ተግባር እንጂ የተማሪው ፍላጎት ባለመሆኑ ድርጊቱን እናወግዛለን” ብላለች።

በግቢው ጸብ ሲፈጠር ወደ ቡድንና #ብሔር የመቀየሩ ነገር እየጎለበተ ስለሚገኝ ተማሪው ከዚህ ዓይነቱ ተግባር #ሊቆጠብ እንደሚገባም ጠቁማለች፡፡

ተቋሙም በትምህርታቸው ተገቢውን ውጤት ሳያገኙ ተሰናብተው እያለ ተመዝግበው የሚገኙ ተማሪዎችና  #በጥበቃ ስራ ላይ አድሏዊ አሰራር የሚፈጽሙ የጸጥታ ሐይሎችን ተግባር መገምገም እንደሚገባው ተናግራለች።

”ወንጀለኛ ተማሪ ብሔርን #አይወክልም፤ ጥፋት የፈጸሙ የየትኛውም ብሔር ተማሪዎች ለህግ መቅረብ አለባቸው” ያለው ደግሞ የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪ ፉዓድ መሀመድ  ነው፡፡

ተማሪዎችም ሰላማዊ የመማር ማስተማር ስራን ለማደፍረስ የሚጥሩ አካላትን ተግባር ማውገዝና የህግ የበላይነትን የማስከበር ስራን ማጠናከር እንደሚገባቸው አሳስቧል፡፡

የ3ኛ ዓመት የህግ ተማሪ ሙፍቲ መንዛ እንደተናገረው ተግባሩ በአገሪቱ የተጀመረውን የለውጥ እንቅስቃሴ ለማደናቀፍ የታቀደ ሴራ በመሆኑ ተማሪው ተግባሩን ማውገዝ ይገባዋል፡፡

”ዩኒቨርሲቲውም አመራሩ፣ አገልግሎት ሰጪውና ሌሎች አካላት በተማሪዎች መካከል መከፋፈል እንዲፈጠር ምክንያት የሚሆኑ አሰራሮችን ሊገመግም ይገባል” ብለዋል።

የውይይቱ ተሳታፊ የሐይማኖት አባት መላዓከ ሰላም ማንደፍሮ በበኩላቸው “ተማሪው የሀይማኖት አባትና የአገር ሽማግሌዎች የሚያስተላልፉትን መልዕክት በተግባር ማዋል ይገባል፤ በተለይ ደግሞ  ተማሪዎች የተሳሳተ መረጃን ሳያረጋግጡ ለሌሎች ከማስተላለፍ መቆጠብ አለባቸው” ሲሉ ገልፀዋል፡፡

”በተማሪዎች መካከል ልዩነትን የሚፈጥሩ አካላት ተግባር የሐይማኖት አባቶች ያወግዛሉ” ያሉት ደግሞ ሼህ አብዱለጢፍ መታን ናቸው፡፡

ተማሪዎችም ቀያቸውን ለቀው ለመጡለት የመማር ማስተማር ዓላማ ቅድሚያ ሰጥተው እኩይ ተግባራትን በጋራ መዋጋት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል፡፡

በውይይቱ ላይ  የተገኙት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የርዕሰ መስተዳድሩ የክልልና የፌዴራል ግንኙነት አማካሪ አቶ #ባዘዘው_ጫኔ እና የብረታ ብረት እና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱላዚዝ መሐመድ በተቋሙ በተከሰተው የጸጥታ ችግር ማዘናቸውን ገልፀዋል፡፡

ድርጊቱ እንዳይባባስ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ የግቢው ማህበረሰብ፣ የጸጥታ አካላትና ተማሪዎች ምስጋና አቅርበዋል።

በቀጣይም ተግባሩ የተማሪዎች አለመሆኑን በመረዳት ሁሉም የተቋሙ ተማሪ አንድነትን በማጠናከርና አኩሪ እሴቶችን በማጎልበት እኩይ ተግባሮች መታገልና የፍቅር መቻቻልና የይቅርታን ባህልን ማዳበር እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ተወካይ ፕሬዝዳንት ዶክተር #ጀማል_ዩስፍ ችግሩ የተፈጠረው በአገሪቱ የተጀመረውን ለውጥ የማይፈልጉ አካላት በተማሪዎች መካከል ልዩነት በመፍጠር የራሳቸውን ዓላማ ለማሳካት ያቀዱት ሴራ መሆኑን ገልፀዋል።

ተማሪዎችም በአመራሩም ሆነ በጸጥታ አስከባሪ ሐይሎች ላይ ያነሷቸው ችግሮችን ለመፍታት ዩኒቨርሲቲው ከምንጊዜውም በላይ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል፡፡

የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ የጥፋቱ አካል የሆኑ ተማሪዎች በህግ እንደሚጠየቁም ተናግረዋል፡፡

በውይይቱ የተቋሙ፣ የፌዴራልና የክልል ተወካይዎች፣ የሐይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌሎች፣ የጸጥታ አካላትና ተማሪዎች የተገኙ ሲሆን በእለቱም እርስ በርስ ተጋጭተዋል የተባሉት ተማሪዎች #እርቅ ፈጽመዋል።

በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ህዳር 11 ቀን 2011 ዓ ም ከምሽቱ 1 ሰዓት በተከሰተ አለመግባባት በአምስት ተማሪዎች ላይ የአካል ጉዳት ደርሷል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ሁሉም ነገር #ሰላም ነው፡፡›› ተማሪዎች

በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ነገሮች #እንደቀድሞው ወደ #ሰላማዊ ሁኔታ መመለሱን የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ያነጋገራቸው ተማሪዋች ገልጸዋል። የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች መካከል አቡ አንዳርጌ ‹‹አሁን ላይ ሁሉም ነገር ሰላም ነው፡፡ ወደ ዩኒቨርሲቲው ከተመለስኩ በኋላ የተለወጡ ነገሮችን አስተውያለሁ›› ብሏል፡፡

አብዛኛው የዩኒቨርሲቲው ግቢ #የአጥር ግንባታ መጠናቀቁንና የፀጥታ ጥበቃውም ተሻሽሎ እንዳገኘው ነው ተማሪ አቡ ለአብመድ ያስታወቀው፡፡ ብዙዎቹ ከዩኒቨርሲቲው ርቀው የነበሩ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እየተመለሱ ስለመሆናቸውም ተናግሯል፡፡

በዩኒቨርሲቲው ውስጥ እንደ ከዚህ ቀደሙ #ብሔር ለይቶ አንድ ላይ የመንቀሳቀስ ልምድ መቅረቱን መታዘቡንም ገልጿል፡፡ ‹‹ፖሊስ እንደበፊቱ በሁሉም አቅጣጫ ሳይሆን በበር ይገባል፡፡ መታወቂያ አሳይቶ የመግባት ልምድም ዳብሯል›› ነው ያለው ተማሪ አቡ፡፡ ‹‹የወደፊቱን ባላውቅም አሁን የሚታየው እንቅስቃሴ ጥሩ ነው፤ ከፍተኛ መሻሻል አለ›› ነው ያለው፡፡

ተማሪ ቤተልሔም ኃይሉም የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ሰላም የተሻሻለ መሆኑን ነው ያረጋገጠችው፡፡ ‹‹ከምዝገባው ቀን አሳልፈን በመገኘታችን የገንዘብ ቅጣት ተጥሎብናል፡፡ በነበረው ግርግር ምክንያት በተቀሰቀሰው እሳት ቃጠሎ መታወቂያ የጠፋባቸው ተማሪዎች አሁን ላይ እየተጉላሉ ነው፤ የፀጥታው ጉዳይ ግን አሁን ሰላማዊ ነው›› ስትል ለአብመድ በስልክ ተናግራለች፡፡

ሌላኛዋ የዩኒቨርሲቲው ተማሪ ብስኩት አለማየሁም የፀጥታ ችግሮች ተስተካክለው በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ሰላማዊ ሁኔታ መፈጠሩን ተናግራለች፡፡ የተጀመረው ሰላማዊ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም አሳስባለች፡፡

በምዝገባ ወቅት መታወቂያ ባለመያዛቸው መቸገራቸውን የተናገሩ ተማሪዎችን ጉዳይ በተመለከተ ምላሽ የሰጡት የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ሪጅስትራር አቶ መኩሪያው አበራ ‹‹መንገድ ተዘግቶ ከመቆየቱ ጋር ተያይዞ የራሱ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድሯል፤ ችግሩን ተረድተን ለምዝገባው እስካሁን እያስተናገድን ነው፡፡

የጠፋባቸውን መታወቂያ ለማውጣትም ይሁን ለምዝገባ ሁሉም ነገር አልጋ ባልጋ ባይሆንም እንኳ በፊት የነበረውን አሠራርና ሥርዓት ተከትሎ ምላሽ እየተሰጠ ነው›› ብለዋል፡፡

የቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር መርሻ አሻግሬ ተማሪዎች አስቀድሞ ከጥር መጀመሪያ አንስቶ ወደ ዩኒቨርሲቲው እንዲገቡና የመማር ማስተማር ሂደት እንዲጀመር ተገልጾላቸው እንደነበር ነው ዶክተር መርሻ የተናገሩት፡፡ ነገር ግን ‹‹በስጋት ምክንያት ወደ ዩኒቨርሲታችን ያልመጡ ተማሪዎች ካሉ ትምህርት እያመለጠ ነውና ይመለሱ፤ በቅጣት እስከ መጭው ዓርብ መመዝገብ ይችላሉ›› ሲሉም አሳስበዋል፡፡

በፀጥታውም ዙሪያ የተጠናከረ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን አንስተው የተማሪዎችን ግንዛቤ ለማሻሻል ውይይቶችና ስልጠናዎች እየተሰጡ መሆኑን ምክትል ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል፡፡ ‹‹የባከነውን የትምህርት ጊዜ ለማካካስ የትምህርት የጊዜ ሰሌዳውን በመከለስ እስከ ሐምሌ መጨረሻ ድረስ የመማር ማስተማር ሂደት ለመቀጠል ተስማምተናል›› ነው ያሉት አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንቱ፡፡

ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደቱ እንዲደናቀፍ በማድረግ በግጭት የተሳተፉ የአስተዳደር ሠራኞችም ሆኑ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው እርምጃ እንደተወሰደባቸውና ለሕዝብ ይፋ እንደተደረገም ዶክተር መርሻ አስታውቀዋል፡፡ በሕግ መጠየቅ ያለባቸው በሕግ እንዲጠየቁ መንግሥት እየሠራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረ የፀጥታ ችግር ትምህርት ተቋርጦ የአማራ ክልል ተወላጅ ተማሪዎች ለሳምንታት በባሕር ዳር መቆየታቸውና የአማራ ክልል ተወላጅ ተማሪዎች በቅርቡ እንዲወጡ እስከተደረገበት ጊዜ ድረስ በባሕር ዳር መቆየታቸው በቅርቡ ወደ ዩኒቨርሲቲው መመለሳቸው የሚታወስ ነው፡፡ የዩኒቨርሲቲው የፀጥታ ሁኔታ መስተካከሉን በመጠራጠር እስካሁን ወደ ዩኒቨርሲቲው ያልተመለሱ ተማሪዎች መኖራቸውንም አብመድ አረጋግጧል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia