TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) መሪ አቶ ዳውድ ኢብሳ ቦሌ አየር ማረፊያ ሲደርሱ ከሰጡት አስተያየቶች ዋና ዋና ነጥቦች:-

• መንግስት ይህ ለውጥ #በሰላማዊ መንገድ እንዲሄድ ለዚህ በር ስለከፈተ ይህ ለውጥ ግቡ እንዲመታ ተሳትፎ ለማድረግ ነው ወስነን የመጣነው፡፡

• ከህዝቡ ጋር ሰላማዊ የትግል መንገድ ስነ ስርዓት አካሄድ ላይ ውይይት የማድረግ እቅድ አለን፡፡

• ይህ ለውጥ ግቡን የሚመታበት ሁኔታ ላይ ከመንግስት ጋር #ውይይት እናደርጋለን፡፡

• ተፎካካሪ ፓርቲዎች #ሰላማዊ ትግል ውስጥ መከተል ያለባቸው ስነ ስርዓቶች ላይ ውይይት እናደርጋለን፡፡

#የሕግ የበላይነት እንዲሰፍን ሁሉም #ተሳትፎ እንዲያደርግ እንሰራለን፡፡

• የረጅም ጊዜ እቅዳችን በኢትዮጵያ ውስጥ ዘላቂ የዴሞክራሲ ስርዓት እንዲሰፍንና ህዝቡ በራሱ መሪዎቹን እንዲመርጥ ማድረግ ነው፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጨፌ ኦሮሚያ🔝

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ #ለማ_መገርሳ የ6 ወራት የስራ አፈጻጸምን ለጨፌ ኦሮሚያ ያቀረቡ ሲሆን፣ በሪፖርታቸው የመሬት ወረራና ሕግ ወጥ ግንባታን ለመከላከል ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልጸው፣ ህዝቡ #የሕግ_የበላይነትን የማስከበር ሂደት ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡ በክልሉ ተከስቶ የነበረውን የጸጥታ ችግር ለመፍታት ባለፉት 6 ወራት በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን አቶ ለማ ተናግረዋል፡፡

የክልሉ መንግስት #ሰላም_እንዲኖር እየሰራ ቢሆንም በክልሉ አንዳንድ አከባቢዎች የጸጥታ ችግሮች መከሰታቸውን የገለጹት አቶ ለማ፣ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ችግሩ እንዲከሰት ያደረጉ አካላትን ወደ ሕግ የማቅረብ ስራዎች እየተሰሩ ናቸው ብለዋል፡፡

በተለይ በጉጂና በምዕራብ ጉጂ ዞኖች የተከሰቱትን #የጸጥታ_ችግሮች በትዕግስትና በሳል አመራር በመስጠት ሁኔታው ወደ #ሰላም እንዲመጣ መደረጉን አቶ ለማ በሪፖርታቸው ገልጸዋል፡፡ ህዝቡ ከመጣው ለውጥ ተጠቃሚ እንዲሆን ለማድረግ ስራዎች መሰራታቸውንም አቶ ለማ ገልጸዋል፡፡ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት በተሰራው ስራ የተለያዩ ፓርቲዎች ወደ አገር ገብተው የፖለቲካ እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆናቸው በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡

#OBNLive

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢንሳ የቀድሞ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሌተናል ኮሎኔል ቢኒያም ተወልደ ዋስትና ታገደ!

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት ሐምሌ 29 ቀን 2011 ዓ.ም. በ30,000 ብር ዋስ ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ የሰጠ ቢሆንም፣ ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ ለይግባኝ ሰሚው ችሎት ይግባኝ አቅርቦ እንዲታገድ አድርጓል፡፡

በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው #በእስር ላይ የሚገኙት ቀድሞ የኢትዮጵያ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) ምክትል ዳይሬክተር ሌተና ኮሎኔል ቢኒያም ተወልደ፣ በተመሠረተባቸው ክስ እንዲከላከሉ ብይን ተሰጥቶባቸው ነበር፡፡ የሙስና ወንጀሎች አዋጅ ቁጥር 881/2007፣ አዋጅ ቁጥር 780/2005፣ አዋጅ ቁጥር 591/2007 የወንጀል ሕግ 808 ተላልፈዋል በማለት ዓቃቤ ሕግ እንደ ክሱ በማስረዳቱ በአምስት ክሶች  እንዲከላከሉ ብይን ተሰጥቶ ነበር፡፡

የተጠቀሱባቸው #የሕግ ድንጋጌዎች #ዋስትና እንደማይከለክሉ በማስረዳት ሌተና ኮሎኔል ቢኒያም በጠበቃቸው አማካይነት ፍርድ ቤቱ የዋስትና መብታቸውን እንዲጠብቅላቸው ጠይቀው ነበር፡፡ ዓቃቤ ሕግ በተከሳሹ ላይ የተጠቀሱት ሕጎች ከ15 ዓመታት በላይ ሊያስቀጧቸው እንደሚችሉ በመግለጽ፣ የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቅ እንዲደረግ ተከራክሮ ነበር፡፡

ፍርድ ቤቱ የዋስትና ጥያቄው የሕግ ክልከላ ያለበት ነው ወይስ አይደለም የሚለውን መርምሮ፣ የዓቃቤ ሕግን መቃወሚያ ውድቅ በማድረግ በ30,000 ብር ዋስትና እንዲለቀቁና ዓቃቤ ሕግ ይግባኝ የሚል ከሆነ በማለት አሥር ቀናት ለመጠባበቂያ ሰጥቶ ነበር፡፡ ዓቃቤ ሕግም ይግባኙን ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አቅርቦ ‹‹ያስቀርባል›› በመባሉ፣ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ትዕዛዝ እስከሚሰጥ ዋስትናው መታገዱ ታውቋል፡፡

Via Reporter
@tsegabwolde @tikvahethiop
#ETA

" ማንኛውም የግል ትምህርት ወይም ስልጠና ተቋም #የመምህርነት እና #የህግ ትምህርት ዘርፎችን ማስተማር አይችልም "

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ፤ ባዘጋጀው የከፍተኛ ትምህርትና የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዘርፍ ፈቃድ አሰጣጥ ረቂቅ መመሪያ ላይ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወይም የስልጠና ተቋማት በሁሉም መርሃ ግብሮች #የሕግ እና #የመምህርነት ትምህርት ዘርፎችን #አሁንም ማስተማር እንደማይችሉ ተገልጿል።

ከዚህ በፊትም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሁሉም መርሃግብሮች የሕግ እንዲሁም የመምህርነት ትምህርት እንዳይሰጡ የተደረገ ሲሆን አሁንም በአዲሱ መመሪያ የሕግ እና የመምህርነት ትምህርት መስጠት አይችሉም ተብሏል።

ሌሎች በአዲሱ የከፍተኛ ትምህርትና የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዘርፍ ፈቃድ አሰጣጥ #ረቂቅ መመሪያ ላይ ምን ተካቷል ?

- ማንኛውም ተቋም አዲስ ፕሮግራም ለመከፈት ወይም ነባሩን ፕሮግራም ለማስቀጠል የፍላጎት ዳሰሳ፣ የገበያ ጥናት እና ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ እውደ ጥናት ማካሄድ ይኖርበታል፡፡

- ለማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት የፕሮግራም ፈቃድ የሚሰጠው ባለስልጣኑ (የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን) የሚያወጣቸውን መስፈርቶች አሟልተው ሲገኙ ብቻ ይሆናል፡፡

- የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚከፍቷቸው ፕሮግራሞች ባለስልጣኑ (የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን) የሚያወጣቸውን የመመዘኛ መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

- ለማንኛውም ተቋም የሚሰጥ ፈቃድ የሚያገለግለው በባለስልጣኑ (የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን) ተገምግሞ ለተፈቀደለት ካምፓስና የትምህርት መስክ ብቻ ይሆናል።

- ማንኛውም ተቋም የጤና የትምህርት መስኮችን መስጠት የሚችለው በመደበኛ መርሃ ግብር ብቻ ይሆናል፡፡

- ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም በርቀት ትምህርት መርሃ ግብር ማስተማር የሚችለው ከድንበር ተሻጋሪ ወጪ በመጀመሪያ ዲግሪ ብቻ ይሆናል።

- ማንኛውም የግል ትምህርት ወይም ስልጠና ተቋም #የመምህርነት እና #የህግ ትምህርት ዘርፎችን ማስተማር አይችልም፡፡

- ማንኛውም የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋም የትኛውንም ስልጠና በርቀት መርሃ ግብር ለማሰልጠን የሚቀርብ የፈቃድ ጥያቄ የማይስተናግድ ይሆናል።

- ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም #በህክምና_ዶክትሬት እና #በስፔሻሊቲ ትምህርት ፈቃድ ለማግኘት ተቋሙ #የህክምና_ሆስፒታል ሊኖረው ይገባል።

- በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ በተቋም ደረጃ የጸደቀ ስርዓተ ትምህርት የፈቃድ ጊዜው ሳያበቃ የስርዓተ ትምህርት ወይም የዲግሪ ስያሜ ለውጥ ካለባለስልጣኑ ፈቃድ ወጪ ማድረግ አይችልም።

- በሀገር ደረጃ በትምህርት ፖሊሲ ስርዓተ ትምህርቱ እስካልተቀየረ ድረስ በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ በተቋም ወይም በካምፓስ ደረጃ የጸደቀ ስርዓተ ትምህርት የፈቃድ/ፈቃድ እድሳት ጊዜው እስካላበቃ ድረስ በሌሎች ካምፓሶች መተግበር ወይም መጠቀም ይችላል።

- የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በበየነ መረብ ወይም በርቀት ትምህርት መርሃ-ግብር ፈቃድ ሲጠይቁ በባለስልጣኑ (የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን) ስርዓተ-ትምህርቱ ቀድሞ መገምገም እና ተገቢ ማስተካከያ ተደርጎ መፅደቅ ይኖርበታል።

- ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም በብሎክ ኮርስ ትምህርት ለመስጠት ያለው አመቺነትና ተገቢነት እንዲሁም የትምህርት ጥራት ላይ የሚኖረውን ተፅህኖ ከግምት በማስገባት ስርዓተ ትምህርቱ ከጸደቀ በኃላ ሊተገብር ይችላል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ያገኘው ከትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን መሪ አስፈፃሚ ሕይወት አሰፋ ነው።

@tikvahethiopia
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር በመጪው ሰኔ ወር የሚሰጠው የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ን በድጋሜ ለሚወስዱ ተፈታኞች መልዕክት አስተላልፏል።

1ኛ. በሰኔ 2015 ዓ / ም እና በየካቲት 2016 ዓ / ም ተፈትነው የነበረና አሁን በድጋሜ ለመፈተን ማመልከት ለሚፈልጉ፤

2ኛ. ከሰኔ 2015 ዓ.ም በፊት #የሕግ_መውጫ_ፈተና ወስደው የማለፍያ ነጥብ ያለገኙ አሁን በድጋሚ ለመውሰድ ለሚፈልጉ ስም ዝርዝራቸው ከቀድሞ ዩኒቨርስቲያቸው ለትምህርት ሚኒስቴር የተላከላቸው አመልካቾች፤

ምዝገባው እስከ ግንቦት 25/ 2016 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑን ገልጿል።

ተፈታኞች በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ብቻ ምዝገባውን እንዲያጠናቅቁ ተብሏል።

ሚኒስቴሩ ፦

➡️ ከላይ ከተገለጸው ጊዜ ውጭ የሚቀርቡ የምዝገባ ጥያቄዎች ተቀባይነት እንደማይኖራቸው አሳስቧል።

➡️ በሰኔ 2015 ዓ / ም እና በየካቲት 2016 ዓ / ም ተፈትነው የማለፊያ ውጤት ያልመጡ አሁን በድጋሜ መፈተን የሚፈልጉ አመልካቾች የሚጠበቅባቸውን የአገልግሎት ክፍያ በቴሌ ብር ብቻ መፈጸም አለባቸው ተብሏል።

➡️ ከሰኔ 2015 ዓ/ም በፊት ለሕግ መውጫ ፈተና ተቀምጠው በድጋሜ ለመፈተን የሚፈልጉ አመልካቾች ስም ዝርዝራቸው ከቀድሞ ዩኒቨርሲቲያቸው መላኩን በማረጋጥ የሚጠበቅባቸውን #የአገልግሎት_ክፍያ ለዚሁ ጉዳይ ብቻ በተከፈተው የንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር ➡️1000553176097 ገቢ በማድረግ ደረሰኙን በግልፅ በሚታይ #ስካን_ኮፒ በማድረግ በ [email protected] ኢሜል አድራሻ እንዲልኩ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM