#እንድታውቁት
በኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ 6710 ከA/B/C/D ወደ " OK " መቀየሩን አሳውቆናል።
በኢትዮ ቴሌኮም ድጋፍ ለልብ ሕሙማንን የሚለገስበት 6710 አጭር የፅሁፍ መልዕክት ከዚህ በፊት ከ1 ብር እስከ 100 ብር ድጋፍ የሚደረግበት A/B/C/D አማራጭ ወደ “OK” ተቀይሯል።
አሁን ላይ አንድ ጊዜ ብቻ " OK " ብሎ ወደ 6710 በመላክ እና በመመዝገብ በቀን አንድ ብር ድጋፍ ማድረግ ይችላሉ፡፡
#6710_OK📨
#አንድ_ብር_ለአንድ_ልብ!💖
ይህንን መልዕክት በማጋራት ለብዙሃን ያድርሱ።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#US በየጊዜው በርካቶች በታጣቁ ሰዎች በሚከፈት ተኩስ የሚገደሉባት ሀገረ አሜሪካ ትላንትም እጅግ በጣም ዘግናኝ የሚባል ጥቃት ተፈፅሞ 2 አዋቂዎችን ጨምሮ 19 ሕጻናት ተገድለዋል። በአሜሪካ ቴክሳስ ግዛት አንድ የ18 ዓመት ወጣት በከፈተው የተኩስ እሩምታ 2 አዋቂዎችን ጨምሮ 19 ሕጻናት መገደላቸውን ተዘግቧል። ድርጊቱ የተፈፀመው በደቡብ ቴክሳስ ግዛት፣ ዩቫልዲ ከተማ ሮብ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት…
#አሜሪካ
በአሜሪካ ኦክላሆማ ግዛት ቱልሳ በተሰኘች ከተማ ሆስፒታል ውስጥ በተከፈተ ተኩስ አራት ሰዎች መገደላቸውን እና በርካቶች መቁሰላቸውን ፖሊስ ገልጿል።
ትኩስ እንደከፈተ የተጠረጠረው እና ጠመንጃ እና ሽጉጥ ታጥቆ የነበረው ግለሰብ መሞቱንም ፖሊስ አረጋግጧል።
ፖሊስ ጥቃቱ በተሰነዘረበት ቅዱስ ፍራንሲስ ሆስፒታል በሦስት ደቂቃ የደረሰ ሲሆን በጥቃቱ የሚጎዱ ሰዎችን ቁጥር ለመቀነስ በስፍራው በአስቸኳይ መድረሱ ተገልጿል።
ትላንት ረቡዕ በተፈጸመው በዚህ ጥቃት በርካቶች መቁሰላቸውንም ባለሥልጣናት አረጋግጠዋል።
የቱልሳ ከተማ ምክትል የፖሊስ ኃላፊ ኤሪክ ዳላግሊሽ " አሁን ላይ አራት ሲቪል ሰዎች የሞቱ ሲሆን፣ ጥቃት አድራሹም ሞቷል " ብለዋል።
እስካሁን ማንነቱ ያልተለየው ጥቃት አድራሽ እራሱ ሳያጠፋ እንዳልቀረ ተገምቷል።
ተጠርጣሪው ሁለት መሳሪያዎችን ታጥቆ የነበረ ሲሆን " አንደኛው ረዝም ያለ፣ ሌላኛው ደግሞ የእጅ ሽጉጥ ነው በስፍራው የተገኘው " ብለዋል የፖሊስ ኃላፊው።
#ቢቢሲ

Audio
#Olusegun_Obasanjo
ከቀናት በፊት ትግራይ ክልል ፤ መቐለ የነበሩት እና ከዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ጋር ምክክር ያደረጉት በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዜዳንት ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት መቋጫ እንዲያገኝ እንዲሁም ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ እየተደረገ ያለውን ጥረት በተመለከተ ከBBC Focus on Africa ጋር ያደረጉት ቃለምልልስ ከላይ በድምፅ ተያይዟል።
(3.3 MB)

#ባሌ_ሮቤ
በጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ለሥራ ጉብኝት ባሌ ሮቤ ገብቷል።
በጉብኝቱ ከጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተጨማሪ ፦
➡️ ሰሞኑን ትግራይ ክልል መቐለ የነበሩት የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ፣
➡️ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ፣
➡️ የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ተወካይ ኡስማን ዲዮን እንዲሁም የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተሳታፊ ናቸው።
የልዑካን ቡድኑ በባሌ ዞን እየተከናወኑ ያሉ የግብርና ሥራዎችን ተዘዋውሮ ይመለከታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

#Update #ችሎት የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ፤ " ሁከት እና ብጥብጥ በማነሳሳት " ወንጀል ተጠርጥሮ በእስር ላይ በሚገኘው በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ የ10 ቀናት የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል። የጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ የምርምራ ጊዜውን የፈቀደው የተከሳሽ ጠበቃ ያቀረቡትን መከራከሪያ እና የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ነው። የምርመራ ጊዜው ከግንቦት 19 ቀን…
" የግራ ዓይኑ ስር አብጦ የለበሰው ቲ-ሸርት ተቀዶ አግኝተነዋል " - ታሪኩ ደሳለኝ (የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ወንድም)
በእስር ላይ የሚገነው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለለኝ ደብደባ እንደተፈፀመበት ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ ገልጿል።
የጋዜጠኛ ተመስገን ወንድም የሆነው ታሪኩ ደሳለኝ ፤ ዛሬ ግንቦት 25/2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ፖሊስ በተለምዶ 3ተኛ ወንድሙን ጋዜጠኛ ተመስገንን ለመጠየቅ ፖሊስ ጣቢያ ተገኝቶ እንደነበር ገልጿል።
" በዚህ እስር ቤት በታሳሪና በጠያቂ መካከል በሁለት ሾቦ የተጋረደ ከ10 ሜትር የሚበልጥ ርቀት አለ " የሚለው ታሪኩ " በታሳሪና በጣያቂ መካከል ባለው ርቀት የተነሳ፣ ንግግር ለማድረግ እጅግ አዳጋች ነው። አጠቃላይ ነገሩ መጯጯህ ነው " ብሏል።
" ጋዜጠኛ ተመስገን ከዚህ በፊት በእስር ቤት እያለ ባጋጠመው በጆሮ ህመም ምክኒያት በዚህ ግር ግር ውስጥ ጆሮው ለመስማት ያዳግተዋል " ሲል አክሏል።
ይሄ በመሆኑ ጋዜጠኛ ተመስገን ለፖሊሶቹ " ትንሽ ቀረብ ብሎ ቢያወራኝ " ሲለው ፖሊሱ በእጁ የማመናጨቅ ምልክት እንዳሳየው ተመስገንም ድጋሜ ለማስረዳት ሲሞክር አንዱ ፖሊስ ከነበረበት ከጠያቂ ቦታ ሌላው ፓሊስ ከእስረኛቹ መቆሚያ ደረጃ ላይ በመውረድ ለሁለት ተመስገንን አብረውት ከቆሙት እስረኞች መካከል ጎትተው በማውጣት በቦክስ፣ በጫማ ጥፊ ለሁለት እንደደበደቡት ታሪኩ አስረድቷል።
" ይህ ሲሆን የሌሎች እስረኛ ጠያቂ ቤተሰቦችና እስረኞችም አይተዋል። " ያለው ወንድሙ ታሪኩ " ድብደባውን እየፈፀሙ ወደ እስራኛ ክፍል ሳይሆን ወደ ሌላ ቦታ ይዘውት ሄደዋል "ብሏል።
ከቆይታ በኃላ በቢሮ ውስጥ ጋዜጠኛ ተመስገንን እንዳገኘው የሚገልፀው ታሪኩ " የግራ ዓይኑ ስር አብጦ የለበሰው ቲ-ሸርት ተቀዶ አግኝተነዋል " ሲል ሁኔታውን አሳውቋል።

#ባሌ_ሮቤ በጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ለሥራ ጉብኝት ባሌ ሮቤ ገብቷል። በጉብኝቱ ከጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተጨማሪ ፦ ➡️ ሰሞኑን ትግራይ ክልል መቐለ የነበሩት የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ፣ ➡️ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ ➡️ የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ተወካይ ኡስማን ዲዮን እንዲሁም የፌደራል…
#Update
ለስራ ጉብኝት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር ባሌ ሮቤ የሚገኙት የቀድሞው የናይጄሪያው ፕሬዝደንት ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ በሲናና ወረዳ በ3 ሺህ 200 ሔክታር መሬት ላይ በክላስተር የለማውን የሥንዴ ሰብል ጎብኝተዋል፡፡
ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነች የሚገኘው ስራ አበረታች እና ለበርካታ የአፍሪካ ሀገራት ተሞክሮ መሆን የሚችል ተግባር መሆኑን ኦባሳንጆ በጉብኝቱ ወቅት ተናግረዋል፡፡
የአፍሪካ ሀገራት ለግብርናው ዘርፍ ትኩረት ሰጥተው ከሰሩ የምግብ ዋስትናቸውን ከማረጋገጥ ባሻገር ምርታቸውን ለውጭ ገበያ በማቅረብ ኢኮኖሚያቸውን ሊያሻሽሉ እንደሚችሉ ገልፀዋል፡፡
በወረዳው በዘንድሮ የበልግ እርሻ 42 ሺህ 901 ሔክታር መሬት በስንዴ ሰብል መሸፈኑን ከሲናና ወረዳ ግብርና ፅ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
(የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ)

#Germany #Ethiopia
ጀርመን በኢትዮጵያ መንግሥት ጥያቄ ከቀረበላት አገራዊ የምክክር ሂደቱን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኗን አሳውቃለች።
ሀገሪቱ ይህን ያሳወቀችው ኢትዮጵያ በሚገኙት አምባሳደሯ ነው።
በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ስቴፋን አወር ለኢዜአ በሰጡት ቃል ፤ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር የአገሪቷን መሰረታዊ ችግሮች ለመፍታት ጥሩ የመፍትሔ አማራጭ ነው ብለዋል።
በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ጥያቄ ከቀረበላት የፌዴራል ስርዓት የምትከተለው ጀርመን በሚቻለው አቅም ሁሉ አገራዊ የምክክር ሂደቱን ለመደገፍ ዝግጁ ናት ሲሉ አረጋግጠዋል።
" በኢትዮጵያ የሚስተዋሉትን ውስጣዊ ችግሮች በመፍታት መፍትሔ ለማበጀት በጋራ መምከር ያስፈልጋል " ያሉት አምባሳደሩ " ኢትዮጵያ የምታካሂደው አገራዊ ምክክር ሁሉንም አሳታፊና አካታች ሆኖ ሲካሄድ ልዩነቶችን በመነጋገርና በመፍታት በቀላሉ ብሔራዊ መግባባት መፍጠር ያስችላል " ብለዋል።
በአገራዊ ምክክሩ ለጋራ ችግሮች መንስኤ የሆኑ ጉዳዮች ምንድን ናቸው? የሚለውን ቁልፍ ጥያቄ በማንሳትና በግልጽ መነጋገር የጋራ መፍትሔ ማምጣት ይቻላል ሲሉም አክለዋል።
አምባሳደር ስቴፈን ፤ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን የምክክር ሂደቱን ሁሉን አቀፍ ለማድረግ እየሰራ መሆኑ የሚደነቅ ነው ብለዋል።
#ENA

#Kenya ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር በምትዋሰንበት ድንበር አቅራቢያ በርካታ የፀጥታ ኃይሎችን አሰማርታለች። በሀገሪቱ የማርሳቢት ግዛት ውስጥ በተቀሰቀሰ የጎሳ ግጭት ምክንያት በርካታ ሰዎች መገዳላቸውን ተከትሎ ነው በሺዎች የሚቆጠሩ ፖሊሶችና የፀጥታ ኃይሎች የተሰማሩት። የሀገሪቱ መንግስት ለተፈጠረው የፀጥታ ችግር ድርቅ፣ ፖለቲካዊ ቅስቀሳ እና ከኢትዮጵያ የጦር መሳሪያ በቀላሉ መገኘቱ ነው ብሏል። የኬንያ…
#Update
በማርሳቢት የተጣለው ሰዓት እላፊ ተራዝሟል።
ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር በምትዋሰንበት ድንበር አቅራቢያ #ማርሳቢት የተጣለው የሰዓት እላፊ በ30 ቀን እንዲራዘም መወሰኑን የኬንያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል።
ከዚህ ቀደም የኬንያ መንግሥት በማርሳቢት ከፍተኛ ቁጥር ያለው የፀጥታ ኃይል ማሰማራቱና ለአንድ ወር የሰዓት እላፊ አዋጅ ማወጁ እንዲሁም ትጥቅ እንደሚያስፈታም መግለፁ አይዘነጋም።
ከሳምንታት በፊት በማርሳቢት ከተማ አረመኔያዊ የተባለ ግድያ መፈፀሙ በዚህም የአካባቢው አስተዳዳሪን ጨምሎ ሌሎችም መገደላቸው ይታወሳል።

#ችሎት
ሌ/ኮሎኔል ሰጠኝ ካሳይ፣ ኮለኔል ፍጹም አብርሃ፣ ሻለቃ ዋልታንጉስ ተስፋው እና ሻለቃ ክንድያ ግርማይ ከእስር እንዲፈቱ ታዘዘ።
4ቱ የሜቴክ የቀድሞ አመራሮች ከተከሱሰበት የሙስና ወንጀል ክስ ከእስር እንዲፈቱ ታዟል።
ትዕዛዙን ያስተላለፈው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።
አራቱ አመራሮች በፍርድ ቤቱ ከተወሰነባቸው የእስራት ቅጣት በላይ በእስር በመቆየታቸውና የእስር ጊዜያቸውን በማጠናቀቃቸው ነው እንዲፈቱ የታዘዘው።
አመራሮቹ የኃይል ትራንስፎርመር እና ባለ ሶስት ፌዝ ተርሚናል ኮኔክተር ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለማቅረብ የተገባ ውል ላይ ያለጨረታ ግዢ ፈጽመዋል ተብለው በዓቃቤ ህግ በቀረበባቸው የሙስና ክስ በወንጀል ህግ 32 /1 ሀ እና የሙስና ወንጀል አዋጅ. ቁ 881/2007 አንቀጽ 91 ሀና ለ ንዑስ አንቀጽ 3 መሰረት በየደረጃው እንዲከላከሉ ብይን ተሰጦ ነበር።
ፍርድ ቤት ፤ ተከሳሾቹ ያቀረቡትን የመከላከያ ማስረጃ ከመረመረ በኋላ በዓቃቤ ህግ ያቀረበውን ማስረጃ በተገቢው አልተከላከላችሁም ሲል የጥፋተኝነት ፍርድ አስተላልፎባቸው ነበር።
በዚህም ፍርድ ቤቱ ሻለቃ ክንድያ ግርማይን 2 ዓመት ከ9 ወር እስራትና 400 ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጡ የወሰነ ሲሆን፤ ቀሪዎቹ ሦስት ተከሳሾች ደግሞ በ3 ዓመት እስራትና 500 ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል።
ይሁንና ተከሳሾቹ በፍርድ ቤት ከተወሰነባቸው የእስራት ጊዜ በላይ ከጥቅምት 30 ቀን 2011 ዓ/ም ጀምሮ በእስር በማሳለፋቸውና የእስር ጊዜያቸውን በማጠናቀቃቸው ከእስር እንዲፈቱ ታዟል።
ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ

#አቢሲንያ_ባንክ
Be A Legend!
Pay with your BoA Visa card like Drogba!
የአቢሲንያ ባንክን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻነል ይቀላቀሉ! https://t.iss.one/BoAEth

#Gambella
ትናንት ከቀኑ 10 ሰዓት ገደማ በጋምቤላ ወረዳ ጎሊ በሚባል አካባቢ በተፈፀመ ጥቃት በእርሻ ሥራ ላይ የነበሩ 2 ሰዎች (አንድ ወንድ እና አንድ ሴት) ሲገደሉ 3 ሠዎች (2 ወንድ እና አንስ ሴት) ታፍነው መወሰዳቸውን የጋምቤላ ክልል አሳውቋል።
ክልሉ ለጥቃቱ የጋምቤላ ነፃነት ግንባር (ጋነግ) ተብሎ የሚጠራውን ቡድን እና በህ/ተ/ም/ቤት በአሸባሪነት የተፈረጀውን " ሸኔ " / እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እያለ የሚጠራውን የታጠቀ ቡድን ተጠያቂ አድርጓል።
የክልሉ መንግስት የፀጥታ ሀይሎች ጥቃት አድራሾቹ ላይ እርምጃ ለመውሰድ ክትትል እያደረጉ እንደሚገኝ ገልጾ ህብረተሰቡ ተገቢውን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ ማቅረቡን ከክልሉ ኮሚኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያሳያል።

ፎቶ፦ የጥምረት ለሴቶች ድምጽ በሀገራዊ ምክክር አስተባባሪ ኮሚቴ ከኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጋር #የሴቶችን_ውክልና ለማረጋገጥ እና በሀገራዊ ምክክሩ ውስጥ የሴቶችን ድምፅ ማካተት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውጤታማ ውይይት አድርጓል።
Via Timran / ትምራን
@tikvahethiopia
Via Timran / ትምራን
@tikvahethiopia