TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ItsMyDam #ItsOurdam #GERD

"እኔ እናት ነኝ ለልጄ የተሻለች አገር እፈልጋለሁ! ሰላም እፈልጋለሁ! ለዚህም ካለኝ ላይ ለህዳሴው የምችለውን አድርጌያለሁ። ተማሪ ሆኜ የ3 ወር ቁርሴን፣ ሠራተኛም ሆኜ የ3 ወር ደሞዜን ሰጥቻለሁ። በህዳሴው የመጣ በአይኔ መጣ! ወገኖቼ እኛ እርስ በእርስ ሰንባላ ለጠላት ደስታ ነው፡፡ ሁሉንም ትተን አንድ ሆነን ስለ ህዳሴው እንቁም! የአድዋን ድል ማክበር ብቻ ሳይሆን አድዋን እንድገም መባላት ትተን ለሠላም ለብልፅግና እናብር ያኔ ጠላትም ይፈራናል።" - #GenetHailu

#ItsMyDam #ItsMyBlood
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ItsMyDam #ItsOurDam #GERD

"የኅዳሴ ግድብ ድርድር ከምርጫ በኋላ ይከናወን" - አቶ ጃዋር መሀመድ

ምርጫ 2012 እስከሚካሄድ ድረስ ኢትዮጵያ ከኀዳሴ ግድቡ ድርድር እንድትወጣ ፖለቲከኛ አቶ ጃዋር መሀመድ ጥሪ አቀረቡ። ዩናይትድ ስቴትስ ምርጫውንና በቅርቡ በአበዳሪ የገንዘብ ተቋማት ለኢትዮጵያ ቃል የተገባውን ብድር በጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ላይ ጫና ለማሳደር እየተጠቀመችበት ነው ብለዋል ፖለቲከኛው።

በዋሽንግተን ዲሲ በተደረገው የመጨረሻው ዙር ድርድር ላይ ኢትዮጵያ እንዳትሳተፍ ጠቅላይ ሚንስትሩ መወሰናቸው ትክክል ነበር ያሉት ፖለቲከኛው ፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ በአቋማቸው ሊፀኑ ይገባል ብለዋል።

ግብፅና ሱዳን አስቸጋሪ የአገር ውስጥ ጉዳይ በገጠማቸው ወቅት ድርድሩ ተቋርጦ እንደነበረ ያስታወሱት አቶ ጃዋር መሃመድ፤ ኢትዮጵያ ያሉባትን አንገብጋቢ የአገር ውስጥ ጉዳዮች (ምርጫው 2012ን ጨምሮ) እስከምታጠናቅቅ ድርድሩ ላልተወሰነ ጊዜ ሊራዘም ይገባል ብለዋል። መንግሥት የድርድሩን ጉዳይ ወደ አፍሪካ ኀብረት በመውሰድ የአባል አገራቱን ድጋፍ እንዲሰበስብም አቶ ጃዋር መሃመድ መክረዋል።

[አሐዱ ቴሌቪዥን]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ItsMyDam #ItsOurDam #GERD

የኢትዮጵያ መንግሥት የታላቁ ህዳሴ ግድብ የውኃ አሞላል እና አለቃቀቅን የተመለከተ ሰነድ አዘጋጅቶ ለድርድር እንደሚያቀርብ ሪፖርተር ጋዜጣ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጭ ገለፁልኝ ብሎ ዘግባል።

በአሜሪካ እና በዓለም ባንክ አመቻችነት የግድቡን የውኃ አሞላል እና አለቃቀቅን በተመለከተ ሲደረግ የቆየው ድርድር ውጤት የኢትዮጵያን ጥቅም የሚጎዳ በመሆኑ፣ የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን የአገሪቱን ሉዓላዊነትና ጥቅም የሚያስከብር የድርድር ሰነድ እንዲያዘጋጅ በመንግሥት ታዞ ሰነዱን በማዘጋጀት ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ከተደራዳሪ ቡድኑ በተጨማሪ የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የዓለም አቀፍ ሕግ ስምምነት ባለሙያዎች፣ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለሙያዎች፣ ከተለያዩ የአገር ውስጥና የውጭ ዩኒቨርስቲዎች የተወጣጡ ኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች ሰነዱን በማዘጋጀት ሒደት ላይ ሌት ተቀን እየሠሩ እንደሚገኙ ማረጋገጥ ተችሏል።

More https://telegra.ph/reporter-03-01

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#ItsMyDam #ItsOurDam #GERD

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ /አብን/ በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ ያወጣው መግለጫ፦ https://telegra.ph/NAMA-03-01

ኢዜማ የታላቁ ህዳሴ ግድብን አስመልክቶ ያወጣው መግለጫ፦ https://telegra.ph/EZEMA-03-01

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#ItsMyDam #ItsOurDam #GERD

ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በዛሬው ዕለት በተከበረው 124ኛው የዓድዋ ድል በዓል ተገኝተው ካደረጉት ንግግር የተወሰደ፦

"ሰሞኑን የህዳሴው ግድብ አስመልክቶ የቀረበው የውል ሰነድ ቆምብለን ከውጫሌው ውል በመማር በውሉ የሰፈሩ ሓሳቦችና ቃላቶች፣ በሉኣላዊነታችን ላይ የመጡ ከዛም አልፎ ለሌላ ጂኦፖለቲካዊ ዓላማ ማስፈፀሚያ ገፀ በረከትና እጅ መንሻ ሆኖ እንዳያገለግል በከፍተኛ ጥንቃቄና ሓላፊነት መፈፀም ይገባል።”

#TPLF
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ItsMyDam #ItsOurDam #GERD

የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ [ኢሕአፓ] በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በጋራ ከመንግስት ጋር እንዲቆም ጥሪ አቅርቧል። የፓርቲውን ሙሉ መግለጫ ከላይ አንብቡ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ItsMyDam #ItsOurDam #GERD

የህግ ባለሞያው ሼክስፒር ፈይሳ ስለግድቡ፦

ግብፆች በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ አንድ ነው የሆኑት፤ ተማሪውም፣ አዋቂውም፣ ህፃኑም፣ አስተማሪውም፣ ሀብታሙም፣ ድሃውም በአንድ ቃል ነው መንግስታቸውን የሚደግፉት። መንግስታቸው ደግሞ ይሄን ካላደረገ መንግስታቸውን የሚቃወሙትም በአንድ ቃል ነው።

እኛም እንደዛው መሆን አለብን። የግብፆችን ማስጠንቀቂያ አይታችሁ ከሆነ፤ ወይም በፌስቡክ፣ በሶሻል ሚዲያ የነሱ ፀሃፊዎች የሚሉትን ካያችሁ ለምንድነው ጦርነት፣ የኛ ወታደሮች ምንድነው የሚሰሩት በአስቸካይ ኢትዮጵያ እንቢ ብላለች ጦርነት መክፈት አለብን፤ መዋጋት አለብን አልሲሲ ጀነራሉ እሱ ነው ፊት እየሰጣቸው ያለው ነው የሚሉት።

እኛም አንድ መሆን አለብን ብዙ ሰዎች በግድቡ ላይ ይሄ ግድብ መጀመሪያውን አስፈላጊ አይደለም ይላሉ፤ አዎን! ሊሆን ይችላል መጀመሪያ በማን ተጀመረ፣ ለምን ተጀመረ እሱን አለፍን አሁን ላይ ደርሰናል፤ በአሁን ሰዓት ግድቡ 60 እና 70 በመቶ ደርሶ ወደኃላ መመለስ የሚባል ነገር አይሰራም። ብዙ ሀብት የፈሰሰበት፣ ብዙ ስራ የተሰራበት ግድብ ነው። ግድቡ መቀጠል ነው ያለበት። ይሄ ደግሞ ጥቅማችን ነው። አንድ ላይ ሆነን መቀጠል አለብን።

#AtkeltiAsefa
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ItsMyDam #ItsOurDam #GERD

በመጪው ክረምት በሕዳሴ ግድቡ የውሃ መሙላት እንደሚጀመር እና የግድቡ ግንባታ በተያዘለት ጊዜ መሰረት እንደሚቀጥል የውኃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የውኃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ በግድቡ ሁለት ተርባይኖች የሚጀመረው የቅድመ ሀይል ማመንጨት ስራም በተያዘለት እቅድ መሰረት እንደሚጀመርም አስታውቀዋል፡፡

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ያለበትን ደረጃ እና ሂደት እንዲሁም የድርድር ሁኔታ ላይ በጠቅላይ ሚንስትር ፅ/ቤት መግለጫ ተሰጥቷል፡፡

በመግለጫው ላይ የተገኙት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በበኩላቸው አሜሪካ የግድቡን ሙሌት በተመለከተ ያወጣችው መግለጫ ፈፅሞ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

አሜሪካ የተፋሰሱ አገራት በራሳቸው ወደ ስምምነት እንዲደርሱ ግፊት በማድረግ በጎ ሚናዋን ብቻ እንድትወጣ ኢትዮጵያ እንደምትፈልግ እና በሌላ ተፅዕኖ የሚሆን ነገር እንደሌለም ሚንስትሩ አረጋግጠዋል።

#ኢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ItsMyDam #ItsOurDam #GERD

የኅዳሴ ግድብ ድርድር ሁሉም ወገኖች መደመጣቸውን፣ አሜሪካም ወገንተኛ አለመሆኗን ለማረጋገጥ ምን እያደረጋችሁ ነው ተብለው የተጠየቁት የአሜሪካ ግምዣ ቤት ሴክሬታሪ ስቴቨን ምኑችን ጥያቄውን በቀጥታ ሳይመልሱ ቀርተዋል።

የኔቫዳው የኮንግረስ አባል ስቴቨን ሖርስፎርድ ሚዛናዊ ብትሆኑ ኢትዮጵያ ወደ ድርድሩ ልትመለስ ትችላለች ብዬ አስባለሁ ሲሉ ለምኑችን ነግረዋቸዋል።

ከግብጽ በተጨማሪ ሱዳን ከስምምነት ሳይደረስ ግድቡ በውኃ ሊሞላ አይገባም የሚል አቋም እንዳላት ምኑችን በአሜሪካ ኮንግረስ Ways & Means Committee ኮሚቴ ተናግረዋል። ኮሚቴው ከውጭ ግንኙነት ጋር የማይቀራረብ የመንግሥት በጀት ላይ አተኩሮ የሚሰራ ነው።

#EsheteBekele #LamFilmona

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ItsMyDam #ItsOurDam

ምክክር ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ [ምክክር ፓርቲ] በዛሬው ዕለት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ 'በአባይ ጉድብ ድርድር ዙሪያ' የመንግስትን አቋም እንደሚደግፍ ገልጿል።

#TikvahFamily
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia