TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በቡራዩና አካባቢው ለንጹሃን ሞትና ንብረት ውድመት #ተጠያቂ ናቸው ተብለው የተያዙ ተጠርጣሪዎች ቁጥር 200 ደርሷል። (ፖሊስ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የማህበራዊ ሚዲያ ህግ እየተዘጋጀ ነው‼️

በማህበራዊ ድረ ገጾች የሚለጠፉ መረጃዎች #ትክክለኛነታቸውንና በህዝቦች መካከል #ግጭት የማይፈጥሩ መሆናቸውን #ለማረጋገጥ መንግስት ህጋዊ አሰራርን ሊተገብር ይገባል ሲሉ አስተያየታቸውን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የሰጡ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ተናገሩ።

ነዋሪዎቹ አክለውም ህጉ ትክክለኛነታቸው ሳይረጋገጥ በማህበራዊ ድረ ገጽ በሚሰራጩ መረጃዎች ምክንያት የሚከሰቱ ግጭቶችና #አለመግባባቶችን ከማስቀረቱም ባሻገር የዜጎችን #ትክክለኛ መረጃ የማግኘት መብት ለማረጋገጥ እድል ይፈጥራልም ብለዋል።

ከአስተያየት ሰጪዎች መካከል ወይዘሮ ተቋምወርቅ አሰፋ ይህን ብለዋል፦

"ፌስቡክ እውነትም ውሸትም አለው፤ በአሁኑ ሰዓት አልጠቀምም ብትል ከሚዲያ #ትርቃለህ እጠቀማለሁ ስትል ደግሞ #እውነታነቱ የቱ ጋር ነው ፌስቡክ አዘጋጆቹ ራሳቸው እነርሱ ናቸው የሚያውቁት መረጃውን የሚሰጠው አካል እውነታነቱ የቱጋ ነው ብሎ ሲያበቃ ሀሰተኛ መረጃ የሚያስተላልፉትን መንግስት #በህግ ሊከታተላቸው ይገባል˝ ብለዋል።
.
.
በሌላ በኩል...

በኢትዮጵያ ከማህበራዊ ሚዲያዎች አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ስርዓት ያለው አሰራር ለመፍጠር የሚያስችል ህግ #እየተዘጋጀ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር አበይ አህመድ በዚህ ሳምንት በህዝበ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር ጠቅሰዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም “የሚዲያ ነጻነት ሲባል በውሸት ስም ገፅ በመክፈት፣ ማንነትን በመደበቅ፣ ያልተገቡ ተግባራትን በማከናወን አይደለም” ሳይሆን ለአገርና ለህዝብ ግንባታ የሚውሉ ቁምነገሮችን በማሰራጨት መሆን ይገባልም ብለዋል።

ህጉ “በተደራጀ መልኩ ደመወዝ እየተከፈላቸው፤ አንዴ ኦሮሞ ሌላ ጊዜ ደግሞ አማራ፤ አንዱ ቦታ ሴት ፣ ሌላ ቦታ ደግሞ ወንድ ሌላም ሌላም በመሆን የሚሰሩ ሰዎችንም” #ተጠያቂ ለማድረግ ያለመ እንደሆነም ተናግረዋል።

የዚህ ዓይነቱን የማሕበራዊ ሚዲያ የሐሰት ፕሮፖጋንዳ ለመከላከልም ዋነኛው መፍትሔ ዋናዎቹ መገናኛ ብዙኃን ትክክለኛውን መረጃ ፈጥነው ለህዝብ ማድረስ መቻል መሆኑንም በአጽንኦት ገልጸዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መከላከያ ሚኒስቴር‼️

የሰራዊቱን አቅም ግንባታን መሰረት ያደረገ እና ሀገራዊ ለውጡን ማራመድ የሚችል ሪፎርም መደረጉን የመከላኪያ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ዛሬ በሰጠው መግለጫም መንግስት እየወሰደ ላለው የለውጥ እርምጃ የበኩሉን እንደሚወጣ ገልጿል።

በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ውስጥ በወንጀል የተጠርጣሩ አመራርና ፈጻሚዎች ጋር በተያያዘ ሰራዊቱን የሚፈርጁ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም አሳስቧል።

ተጠርጣሪዎችን የማጋለጥና በቁጥጥር ስር ማዋል ስራ የሚኒስቴሩ አንዱ የሪፎርሙ አካል ሆኖ እየተሰራበት መሆኑም ነው የተመላከተው።

ሰሞኑን በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን(ሜቴክ) እንዲሁም በሌሎች ተቋማት ውስጥ በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር በማዋልም ሚኒስቴሩ አብሮ እየሰራ መሆኑን በመከላከያ ሚኒስቴር የመከላከያ ኢንዱክትሪኖሽንና ህዝብ ግንኙነት ዋና ዳይሬክተር ሜጄር ጀነራል #መሀመድ_ተሰማ ገልጸዋል።

በህዝባዊ ወገንተኝነት ህዝብ በማገልገል ላይ የሚገኘው ሰራዊቱ ለእንዲህ አይነት የወንጀል ተግባር ራሱን መስዋት እስከማድረግ የሚታገል መሆኑንም ነው የተናገሩት።

ከላይ ከጠተቀሱት ተጠርጣሪዎች ጋር የመፈረጁን ተግባርም እንደሚያወግዝና ግለሰቦቹን #ተጠያቂ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

አሁን ሀገሪቱ ላይ የመጣውን አንጻራዊ ሰላምና መረጋጋት ወደ ተሻለ ምዕራፍ እንዲሻገር ሰራዊቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ ይሰራል ብለዋል።

ሀገራዊ ለውጡ በምንም አይነት መንገድ እንዳይቀለበስ የሚያስችል አቋም መፍጠር መቻሉንም የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሩ በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የሚታዩ ግጭቶችና አለመረጋጋቶች ለመቆጣጠር በተለያየ ቡድን የተዋቀረ ኮማንድ ፖስት መሰማራቱን እና በአንድ ወር ውስጥ ተጨባጭ ውጤት እንዲያመጡ አቅጣጫ ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል።

#በከፍተኛ_ትምህርት_ተቋማት አካባቢ የተፈጠሩ ችግሮች አሁን መረጋጋት ቢታይባቸውም፤ የተዛባ መረጃ #በሚሰራጩ ግለሰብና ቡድኖች ላይ
ህጋዊ #እርምጃ መውሰድ መጀመሩን ጠቁመዋል።


ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ የሚፈፀሙ የጥላቻ ንግግሮችን #ለመቀነስ እርምጃዎችን እንደሚወስዱ አስታወቁ፡፡ አጥፊዎችን #ተጠያቂ የሚያደርጉ #የህግ ማዕቀፎች ተግባራዊ ይደረጋሉም ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ አልጀዚራ
@tsegabwolde @tikvahethiopi
በትላንትናው ዕለት በጎንደር ከተማ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር አንዳንድ የንግድ ተቋማት ላይ #ጉዳት መድረሱን፤ የደረሰውን የጉዳት መጠንም የማጣራት ስራ መጀመሩን #የጎንደር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ኦፊሰር ኮማንደር ማረልኝ ወንድሙ ተናግረዋል። በጥፋቱ የተሳተፉ ግለሰቦችም በቀጣይ የማጣራት ስራ ከተከናወነ በኋላ በህግ #ተጠያቂ እንደሚደረጉም ገልፀዋል።

🗞ቀን ሃምሌ 2/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Tigray

ህወሓት ፤ ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ባወጣው መግለጫ " አምባገነን " ሲል የጠራቸው የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በትግራይ ዘግናኝ ግፍ እየፈፀሙ ነው ብሏል።

በአጠቃላይ የኤርትራ ጦር በደቡብ አፍሪካ የጦርነት ማቆም ስምምነት ከተፈረመ በኋላም በትግራይ እና በህዝቡ ላይ የሚያደርሰውን #ሁሉን_አቀፍ ጥቃት አጠናክሮ ቀጥሏል ሲል ከሷል።

የኢትዮጵያ መንግሥት #ኃላፊነቱን_እንዲወጣ ፤ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም ኢሳያስ አፈወርቂ በትግራይና በህዝቡ ላይ እየፈጸመው ያለውን ግፍ እና በደል በአስቸኳይ እንዲያስቆም እንዲያደርግ ፤ ከትግራይ እንዲወጣ እንዲያስገድዱ ፤ ሲፈጽመው ለነበረው ወንጀል #ተጠያቂ እንዲሆን እንዲያደርጉ ሲል ጥሪ አቅርቧል።

" ህወሓት " በዛሬው መግለጫው ያነሳቸው ነጥቦች ምንድናቸው ?

- በተፈረመው #የሰላም_ስምምነት መሰረት ጦርነት እንዲቆም ፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት እንዲከበር፣ የኤርትራና ሌሎችም ሃይሎች ከትግራይ እንዲወጡ ስምምነት ላይ ተደርሷል ብሏል።

- ህወሓት ፤ " አምባገነን " ሲል የጠራቸው የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ፤ በሰላም ስምምነቱ #እንዳልተደሰቱ ገልጾ ፤ " ወታደሮቹን ያስወጣል ተብሎ ቢጠበቅም ተጨማሪ ክፍሎችን (ኃይሎቹ) ወደ ትግራይ እያመጣ ነው " ብሏል። ይኸው ጦር በህዝባችን ላይ አሰቃቂ ወንጀል እየፈጸመ ይገኛል ሲል ገልጿል።

- የኤርትራ ጦር በሴቶቻችን ላይ ጾታን መሰረት ያደረገ እጅግ አረመኔያዊ ጥቃት እየፈፀመ ፤ ንፁሀን ዜጎችን እየጨፈጨፈ ፣ የህዝብና የግል ንብረት እየዘረፈ ወደ ኤርትራ እያጓጓዘ ፤ የተረፈውን ደግሞ #እያጠፋ እና እያቃጠለ ነው ፤ የትግራይ ቅርሶችም በከፍተኛ ደረጃ እየወደሙና እየተዘረፉ ነው ፤ በአጠቃላይ የኤርትራ ጦር በደቡብ አፍሪካ (ፕሪቶሪያ) የጦርነት ማቆም ስምምነት ከተፈረመ በኋላም በትግራይ እና በህዝቡ ላይ የሚያደርሰውን ሁሉን አቀፍ ጥቃት አጠናክሮ ቀጥሏል ብሏል።

- ህወሓት የኢትዮጵያ መንግሥት ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ፤ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም ኢሳያስ አፈወርቂ በትግራይ እና በሕዝቡ ላይ እየፈጸመ ያለውን ግፍ እና በደል #በአስቸኳይ_እንዲያስቆም ፤ ከትግራይ እንዲወጣም እንዲያስገድደው እንዲሁም በትግራይ ሲፈጽመው ለነበረው ወንጀል ሁሉ ተጠያቂ እንዲሆን ማደረግ አለበት ብሏል።

- ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በተለይም አፍሪካ ህብረት፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ፣ የአሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት በኢሳያስ አፈወርቂ " አምባገነን " ስርዓት ላይ ትክክለኛ ማዕቀብ እንዲጥልና ተጨባጭ እርምጃ እንዲወስድ ጥሪ አቅርቧል።

ይህንን የህወሓት ክስ በተመለከተ ከ "ኤርትራ" በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም።

የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት ጦርነት እንዲያበቃ ፤ ያሉት ችግሮችም #በሰላም እንዲፈቱ ፤ የሰብዓዊ ድጋፍ ያለገደብ ለተቸገሩት ዜጎች ሁሉ እንዲደርስ ፤ መሰረታዊ አገልግሎቶች ስራ እንዲጀምሩ ለማድረግ በደቡብ አፍሪካ እና ኬንያ (የስምምነቱ ማስፈፀሚያ ላይ) ስምምነት መፈረማቸው አይዘነጋም።

በናይሮቢ ስምምነት በትግራይ ክልል ያሉ ታጣቂዎችን ትጥቅ ማስፈታት የውጭ ኃይሎችን እና ከኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ውጭ የሆኑ ኃይሎችን ሁሉ ከክልሉ (ከትግራይ ክልል) ከማስወጣት ጋር #አብሮ እንደሚከናወን መገለፁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ከዘር ማጥፋት እልቂት ለማምለጥ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተሸሸጉ 2 ሺህ ቱትሲዎች እንዲገደሉ ትዕዛዝ በመስጠት የተጠረጠረው ግለሰብ ተያዘ። እ.አ.አ በ1994 በሩዋንዳ በነበረው የዘር ማጥፋት እልቂት፣ ከጥቃት ለማምለጥ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተሸሸጉ ሁለት ሺሕ #ቱትሲዎች እንዲገደሉ ትዕዛዝ አስተላልፏል በሚል የተጠረጠረው ግለሰብ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ መያዙን የሩዋንዳውን የዘር ማጥፋት የሚከታተለው፣ የተባበሩት…
" ከፍትሕ ማምለጥ እንደማይችሉ ማሳያ ነው "

ካለፉት 22 ዓመታ ጀምሮ ሽሽት ላይ የነበረውና በሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ወቅት ከዘር ማጥፋት እልቂት ለማምለጥ በቤተክርስቲያን የተሸሸጉ 2,000 (ሁለት ሺህ) ቱትሲዎች እንዲገደሉ ትዕዛዝ በማስተላለፍ የተጠረጠረው ፉልጌንሴ ካይሼማ መያዝ ምንም ያህል ጊዜ ቢወስድ እንዲህ አይነት ድርጊት የፈፀሙ ሰዎች #ከተጠያቂነት ማምለጥ እንደማይችሉ ማሳያ ነው ተብሏል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የግለሰቡን መታሰር መሰል ወንጀሎችን የፈፀሙ ከፍትህ ማምለጥ እንደማይችሉ ትልቅ መልዕክት የሚያስተላልፍ ነው ብለዋል።

ጉተሬዝ ፤ " እንዲህ አይነት ወንጀል ፈጽመዋል የተባሉ ሰዎች ከፍትህ ሊያመልጡ እንደማይችሉ እና ከሩብ ምዕተ አመት በኋላም ቢሆን #ተጠያቂ እንደሚሆኑ የሚያሳይ ኃይለኛ መልእክት ነው " ሲሉ ገልፀዋል።

እ.አ.አ በ1994 በሀገረ ሩዋንዳ በአክራሪ ሁቱዎች በተፈጸመ የዘር ማጥፋት፣ 800 ሺሕ የሚሆኑ ቱትሲዎች መገደላቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
" ' አክሲዮን እናሻሽጣለን ' የሚሉ ማስታወቂያዎችና ግለሰቦች ህገወጥ ናቸው " - የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ፤ " የአክሲዮን ድርሻ እናሻሽጣለን " የሚሉ ማስታወቂያዎችም ሆኑ ግለሰቦች ህገወጥ መሆናቸውን ህብረተሰቡ ይወቅልኝ አለ።

በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከፍተኛ የካፒታል ገበያ አማካሪ አቶ አሰፋ ስሞሮ ፤ " በማህበራዊ የትስስር ገጾች ላይ ከአክሲዮን ገበያ ጋር በተገናኘ #የድለላ ስራ እየሰሩ ያሉ #ህገወጥ ግለሰቦች መኖራቸውን መረጃውን አለን ነገር ግን አንዳቸውም ከባለስልጣኑ ፈቃድ አላገኙም " ብለዋል።

ባለስልጣን መ/ቤቱ ለጊዜው ፈቃድ መስጠት አለመጀመሩን የገለጹት ባለሙያው የፈቃድ መመሪያው ለፍትህ ሚኒስቴር መላኩን በማንሳት በሚደረጉ ቀጣይ ውይይቶች ይጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል፡፡

በዚህም በአሁኑ ወቅት ከባለስልጣኑ ፈቃድ ውጪ " አክሲዮን እናሻሽጣለን " የሚሉ ማስታወቂያዎችም ሆነ ግለሰቦች ህገወጥ መሆናቸውን ህብረተሰቡ ሊያውቅ ይገባል ሲል አስገንዝበዋል።

በተቀመጠው አዋጅ መሰረት የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች በሚል መጠሪያ ተቋሙ ፈቃድ እንደሚሰጥ በመግለጽ አስፈላጊው ቁጥጥርና ክትትል የሚደረግባቸው እንደሚሆኑም ከአሁኑ ጠቁመዋል፡፡

ባለስልጣኑ በይፋ ፈቃድ መስጠት ሲጀምርም በመሰል ህገወጥ ተግባራት የሚሳተፉ ግለሰቦችን በህግ #ተጠያቂ እንደሚያደርግም አሳውቋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ #የአሃዱሬድዮ ነው።

@tikvahethiopia