TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኦነግ/WBO‼️

የ'ኦነግ' የቅበላ ቀነ ገደብ ተጠናቋል!
(*የልዩ ሁነት #አምስት የመጨረሻ ቀናት አሉ)
.
.
ከመንግሥት ጋር በተፈጠረው ያለመግባባት ዳግም በውጊያና የተለያዩ ግጭቶች ላይ የቆየው የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት የከበረውን የገዳ ሥርዓት መርሖዎችና ሕጎች መሰረት አድርጎ ለቀረበው ጥሪና የሰላም አዋጅ ላለፉት ሶስት ቀናት ሲደረግለት የቆየው አቀባበል ትላንት ምሽት 12:00 ላይ መጠናቀቁን የእርቀ ሰላሙ የቴክኒክ ኮሚቴ ይፋ አድርጓል።

በመንግሥት እና በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት መካከል እርቀ ሰላም ለማውረድ፤ በኦሮሚያ አባገዳዎች፣ በሀደ ሲንቄዎች(Haadha Siinqee)፣ በአገር ሽማግሌዎች፣ በምሁራንና ለሰላም መስፈን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሲያደርጉ በቆዩ በርካታ ዜጎች እንቅስቃሴ ጥረቱ መልካም ፍሬ አፍርቶ #በጫካ የነበረው ሠራዊት ላላፉት ሦስት ቀናት በኦሮሚያ 12 ዞኖችና 22 ወረዳዎች አቀባበል ሲደረግለት ቆይቷል።

ጥር 14 ቀን 2011 ዓ.ም በአምቦ ዩኒቨርሲቲ በአባገዳዎች #የሰላም_አዋጅ ታውጆ የእርቀ ሰላም ኮሚቴ የተቋቋመ ሲሆን ጥሪው በጎ ምላሽ አግኝቶ ሠራዊቱ መሳርያውን ለአባገዳዎችና ለቴክኒክ ኮሚቴው በማስረከብ ባሕላዊ አቀባበል፣ ባርኮት(Muuda) እና ፍቅራዊ ክብካቤ እየተደረገለት ቆይቷል።

ከነገ ጀምሮም በተዘጋጀለት ካምፕ በመግባት በሰላም ተጠሪዎች፣ በሕግ ባለሙያዎች እና በሌሎች ምሁራን የተለያዩ ስልጠናዎች መውሰድ ይጀምራል። ከሁለት ወር በማይበልጠው በዚህ ቆይታ የሠራዊቱ አባላት እንደየፍላጎታቸው እና ችሎታቸው ስልጠና ወስደው በመስካቸው የሚመደቡ ሲሆን በቆይታቸውም በአባገዳዎች፣ በቴክኒክ ኮሚቴው አባላትና በሰላም ተጠሪዎች አያያዛቸው የሚጎበኝ ይሆናል።

እስካሁን በነበረው ሂደትና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የቴክኒክ ኮሚቴው የፊታችን እሁድ ተገናኝቶ አጠቃላይ ምክክርና ግምገማ የሚያደርግ ሲሆን ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

በተያያዘ ዜና -- በ'ልዩ ሁነት' በቀነ ገደቡ መግባት ላልቻሉ የሠራዊቱ አባላት ተጨማሪ #አምስት ቀን የተሰጠ ሲሆን በእነዚህ ጊዜያት በየወረዳው የሰላም ክፍሎች በመገኘት #መሳርያቸውን ማስረከብና ወደካምፕ ገብተው ለቀጣይ ሰላማዊ ሕይወታቸው ጠቃሚ የሆኑትን #ስልጠናዎች መውሰድ እንደሚችሉ ተገልጿል።

Via Gulale Post
@tsegabwolde @tikvahethiopia