TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" የሀብት ምዝገባ መረጃው ለህዝብ ክፍት ይደረግ " የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የፌዴራል ሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን #በተሿሚዎች፣ #በተመራጮች ወይም #በመንግሥት_ሠራተኞች ላይ እያከናወነ ያለው የሀብት ምዝገባ መረጃ ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ ጠይቋል። በ2002 ዓ/ም በወጣው የሀብት ማሳወቂያና ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 668/2002 ድንጋጌ መሠረት፦ 👉 የአገሪቱ ፕሬዚዳንት፣ 👉 ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣…
" ... የተመዘገበ የሀብት መጠንን ለህዝብ ይፋ ለማድረግ ህጉ አይፈቅድም " - የፌደራል የስነ ምግባር እና የፀረ ሙስና ኮሚሽን

የፌደራል የስነ ምግባር እና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ፤ በባለስጣናት እና በመንግሥት ሠራተኞች ላይ እያከናወነ ያለው የሀብት ምዝገባ መረጃ ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ በርካታ ዜጎች እና ተቋማት እየጠየቁ እንደነበር እና አሁንም እየጠየቁ እንደሆነ ይታወቃል።

ከጥቂት ቀናት በፊትም የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የፌዴራል ሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን #በተሿሚዎች#በተመራጮች ወይም #በመንግሥት_ሠራተኞች ላይ እያከናወነ ያለው የሀብት ምዝገባ መረጃ ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ መጠየቁም ይታወሳል።

ይህን በተመለከተ ለምን ኮሚሽኑ የተመዘገበን ሀበት ለህዝብ ይፋ እንደማያደረግ ተጠይቆ ምላሽ ሰጥቷል።

ኮሚሽኑ ለጥያቄው ምላሽ የሰጠው ለአሀዱ ሬድዮ ጣቢያ ነው።

የኮሚሽኑ የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተስፋዬ ሻሜቦ ለሬድዮ ጣቢያው ፤ " የሀብት ምዝገባ እና ማሳወቅ አዋጅ 668 ህዝባር 2002 ላይ በተደነገገዉ መሰረት የተመዘገበን ሀብት ማየት ለሚፈልግ የትኛዉም ሰዉ መጥቶ የሚጠይቅ ከሆነ ህጉ በሚፈቅደዉ አሰራር መሰረት ይስተናገዳል " ብለዋል።

" ሆኖም ግን የተመዘገበን ሀብት ለሁሉም ህዝብ ይፋ ማደረግን ህጉ ይከለክላል " ሲሉ ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ የተመዘገበን ሀብት በህጋዊ መንገድ ለሚጠይቁ አካላት የማሳየት ስራን እየሰራ መሆኑን ገልፀው " የተመዘገበን ሀብት ትክክል ነዉ አይደለም የሚለዉን ለመለየት የሚፈለጉ ዜጎች በህጋዊ መልኩ የሚጠይቁ ከሆነ እና ተመዘገበዉ ሀብት እዉነተኛ አለመሆኑን የሚጠቁሙበት አጋጣሚ ካለ የሀብቱን አንድ አራተኛ እንዲያገኙ ይደረጋል " ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው አስረድተዋል።

#Credit_Ahadu

@tikvahethiopia