TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ተሳዳቢው ማነው? | ምክንያቱስ? |

በኢትዮጵያ ውስጥ ከምክንያታዊነት ይልቅ ስሜታዊነት፣ በሰከነ መንፈስ ከማሰብ ይልቅ ፈጥኖ መኮነንና ማውገዝ እየበዛ ነው፡፡ ይህ በሁሉም የሕይወታችን ዘርፍ ላይ የሚታይ ይመስላል። በማኅበራዊ ግንኙነታችንም ሆነ በማኅበራዊ ድረገጽ አጠቃቀማችን ላይ ምክንያታዊነት በስሜታዊነት ተበልጧል፡፡ በተለይ ስድብ፣ ከስድብም ክብረ-ነክ የሆኑ ቃላት ያጀቡት ስድብ የድረገጽ (የፌስቡክና የቲዊተር) ተጠቃሚዎች መገለጫ ከሆነ ዓመታት እየተቆጠሩ ነው፡፡ እንዲህ ያሉት ነገሮች፣ ጤናማ አከባቢንና ሰላማዊ ሁኔታዎችን አብዝተው ለሚሹ ሰዎች ስሜት የሚነካ ነው፡፡

ለዚህ ማሳያ ሩቅ መሄድ አይጠበቅብንም፡፡ ከፌስቡክ በሚሰራጩ ጽሑፎች ሥር የሚቀርቡትን ዛቻዎች፣ ማስፈራሪያዎችና ስድቦች ብቻ ማየት በቂ ነው፡፡ ሃሳቡን በምክንያታዊ መከራከሪያ ከማሸነፍ ይልቅ የስድብ ካራን ከሰጎባው የሚመዝ ቁጥሩ ትንሽ አይደለም፡፡ በጣም የሚገርመው ደግሞ ከርዕሰ ጉዳዩ ጋር (ከተለጠፈው ጽሁፍ ጋር ) የማይገናኙት ስድቦችን በአስተያየት መስጫ ቦታው ላይ የሚያስቀምጡ ከጥቂት በላይ መሆናቸው ነው፡፡

‹ሰዎች በማኅበራዊ ድረገጽ ለመሳደብ የሚዳርጋቸው ነገር ምንድን ነው?› የሚለው ጥያቄ በባለሙያዎች በተደጋጋሚ ብዙ ተብሎለታል፡፡ የአውሮፓ ሕብረት በሚያዚያ 2017 ባወጣው መረጃ ላይ ስድብ አዘል የማሕበራዊ ድረገጽ አስተያየቶች ሰዎችን እንደሽብር ላሉ መጥፎ ሀሳቦች የሚያነሳሳ እንደሆነ ይገልጽና፣ በማህበራዊ ድረገጾች ላይ ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል ሲል ይመክራል፡፡ የሕብረቱ ውሳኔ የተሳዳቢዎቹን ምክንያት አይገልጽም፡፡ ውጤቱ ወደ ሽብርተኝነት ያድጋል ሲል ማስጠንቀቁ ግን አልቀረም፡፡

እኛ ስድብ የምንለውን ጉዳይ ፈረንጆቹ ‹Hate Speech› ሲሉ ይጠሩታል፡፡ስለድረገጽ ስድቦች ጥናት ያደረጉ ሰዎች ሰዎች የሚሳደቡበት ምክንያት በተሳዳቢዎቹ አስተዳደግ ላይ ይወሰናል ይላሉ፡፡ የችግሩን መነሻ ወደ ስነልቦናዊ ትርጉም የሚወስዱት እነዚህ ተመራማሪዎች፣ሰዎች ያደጉበት ከባቢ ለስነምግባራዊነት የተመቸ ካልሆነ ተሳዳቢ ሊሆኑ እንደሚችሉ ያነሳሉ፡፡ከዚያም ለአንድ አከራካሪ ሀሳብ ከሞጋች ምክንያት ይልቅ ቀድሞ የሚመጣላቸው ስድብ ነው ይላሉ፡፡

ሌላኛው ጭፍን ጥላቻ ነው፦ አንድን አካል (ግለሰብ፣ቡድን፣የፖለቲካ ድርጅት፣ ተቋም ወዘተ) ያለበቂ ምክንያት መጥላት ከተጀመረ ጭፍን ጥላቻ ይባላል፡፡ከዚያም እርሱ የነካውንና ያየውን ሁሉ #ለማራከስና #ለማጥላላት ስድብ ጥቅም ላይ ይውላል፡፡

ለማኅበራዊ ድረገጽ ተሳዳቢዎች እንደሶስተኛ ምክንያት የሚጠቀሰው የአማራጭ ሃሳብ ማፍለቅ እጥረት ነው፦ አንድ ጉዳይ ላይ አስተያየት ለመስጠት የሚያስችል ዕውቀት ሳይኖር ሲቀርም ስድብ የአቅም ማነስን ለመሸፈን ይውላል፡፡ ሰዎች አንድን ጉዳይ በጭፍን ከመጥላታቸውም ባሻገር ሃሳብን በሃሳብ ለመሞገት የሚያስችል ዳራዊ ዕውቀት ሳይኖራቸው በሚቀር ወቅት የስድብ ካዝናቸውን ይከፍታሉ፡፡

ሰዎች ወደ #ፌስቡክ በመጡ ወቅት #ስድብን ለምን ይመርጣሉ ለሚለው ጥያቄ ብዙ አስረጂዎች ይቀርባሉ፡፡በርግጥ በኢትዮጵያ ያለው የማኅበራዊ ድረገጾች አጠቃቀም ወደ ስድብ ያደገበት ምክንያት #አልተጠናም፡፡ የሆነው ሆኖ ከላይ የተዘረዘሩት ዓለማቀፋዊ ምክንያቶች እኛንም መዳሰሳቸው አልቀረም፡፡

ይሁን እንጂ ጉዳዩን ከትምህርት ሥርዓታችን ጋር አገናኝተው አስተያየት የሚሰጡ ሰዎች አይጠፉም፡፡ለድሬ ቱዩብ ሃሳቡን ያጋራ (ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ) አንድ የስነ-ማኅበረሰብ ተመራማሪ እንደሚለው፣የፌስቡክና የሌሎች ማኅበራዊ ድረገጾች ላይ ስድብ ይዘው የሚቀርቡ ግለሰቦች የትምህርት ጥራቱ ያለበትን ደረጃ የሚያሳዩ ናቸው፡፡

እንደሚታወቀው የፌስቡክ ‹አካውንት› ለመክፈት የሚያስፈልገው ዋና ጉዳይ ማንበብና መጻፍ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥም ያለው ፌስቡክ ተጠቃሚ እነዚህን መሰረታዊ ሃሳቦች የሚያውቅና ቢያንስ የ8ኛ ክፍል ትምህርቱን ያጠናቀቀ (አንዳንዶች ዳያስፖራና ከ12ኛ ክፍል በላይ የሆነው ይበዛል ብለው ይሞግታሉ) ነው፡፡ ይሁን እንጂ በትምህርት ቤት በነበረበት ጊዜ #ኢሞራላዊና ከስነምግባር ያፈነገጡ ሃሳቦችን መሰንዘር ብልግና መሆኑን ሳያውቅ የወጣ በመሆኑ #ስድብን እንደማሸነፊያ ሀሳብ ይወስደዋል፡፡

ባለሙያው እንደሚሉት፣ እነዚህ ማንበብና መጻፍ በመቻላቸው ብቻ የፌስቡክ አካውንት የከፈቱ ሰዎች መከራከሪያ የሚሆን ምክንያታዊ ሐሳብ ስለሚቸግራቸው (Lack of alternative rationality) ስራቸው ስድብ ብቻ ይሆናል፡፡ እያንዳንዷን የፌስቡክና የቲዊተር ሃሰብም እየተከታተሉ፣ ሁሉም የፌስቡክ ሰው እንደነሱ ያስብ ዘንድ ይጠብቃሉ፤ ሁሉም ሰው #እነርሱ የሚጠሉትን #እንዲጸየፍ፣ የሚወዱትን ደግሞ እንዲወድ ይሻሉ፡፡ያንን ያላደረገውን #ይሰድቡታል፡፡ እነዚህ የስድብ ደርዘን መዝዘው የማይጨርሱ ሰዎች ያለፉበት የትምህርት ሥርዓት፣ ምክንያታዊነትን፣ የሰውን ሃሳብ ማክበርን፣ ሰውን ማክበርን፣ወዘተ አላስተማራቸውም፡፡

ይህንና ሌሎች ማስረጃዎችን እየጠቀሱ አስተያየት የሚሰጡ ብዙ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ለመሆኑ ማኅበራዊ ድረገጾቻችን ስለምን መከባበርን ሊያስተምሩን አልቻሉም? ስለምንስ መሰዳደብ በዛ? ይህስ ወዴት ያደርሰናል? የወቅቱ አንገብጋቢ ጥያቄ ይመስላል! 

Via መላዕክነሽ ሽመልስ በድሬቲዩብ (DIRETUBE)

#ሼር #share
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፌስቡክ ጦረኞች...

#የቃላት_ጦርነትና እስጥ አገባ ከሮና ገሮ ሲያበቃና ሲበጠስ ነው ሀገራት ወደ #ጦርነት ውስጥ የሚገቡት፡፡ ለዚህም ይመስላል የቻይናው ከሚኒስት መሪ የነበሩት ማኦ ዜዱንግ ጦርነት የፖለቲካ ትግሉ በሌላ መልኩ ቀጣይነት ነው ያሉት፡፡ ማሕበራዊ ድረገጾች ከፍተኛ የኃሳብ ፍልሚያ የሚካሄድባቸው ከጦርነት ያልተናነሱ አውድማዎች ናቸው፡፡ የማሕበራዊው ሚዲያ ጥይት ባይጮህበትም ከመድፍና ታንክ በላይ #በሰው_ሕሊና ውስጥ የሚያጓራ ከሚሳኤልም በላይ ተምዘግዝጎ የሚወነጨፍ፣ የሚጮህና አናዋጭ፤ በስሜታዊነት የሚነዳ ለጥፋትም የሚያነሳሳ ነው፡፡ #ፌስቡክ የኃሳብ ፍልሚያና ግብግብ የሚካሄድበት ጎራ መሆኑ በጀ እንጂ ሌላማ ቢሆን የከፋ እልቂትና ውድመት ሊያመጣ ይችል የነበረ የዘመኑ ሚዲያ ነው፡፡

ሙሉውን ፅሁፍ ያንብቡ👇

https://telegra.ph/የፌስቡክ-ጦረኞች-03-04
#ፌስቡክ

ለ1 ሳምንት #ከፌስቡክ እንድንርቅ የሚለው የመጀመሪያው ቅስቀሳ ለብዙዎች ጥቅም የሌለው መስሎ ታይቷቸዋል። ዋነኛ አላማ አድርጎት የነበረው በ7 ቀን ውስጥ የጥላቻ፣ ፣የጦርነት ቅስቀሳዎችን፣ የሽብር፣ የስድብ ፅሁፎችን ባለማየታችን አእምሮአችን የሚሰማውን ሰላም ለማስገንዘብ ነው። ቀጣዩ ስራችን እንደኛ ሰዎችን ሰላም እንዲሰማቸው አጠቃላይ ፌስቡክን በሰላም፣ አንድነት እና የፍቅር መልዕክቶች ማጥለቅለቅ ይሆናል። ሁላችንም ሀላፊነት አለብን ምክንያቱም ያለችን አንዲት ሀገር ብቻ ስለሆነች! በጥላቻ ሀገራችን ከመጥፋቷ በፊት እኛ የአቅማችንን እንሞክር።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር #አበረ_አዳሙ ለክልሉ ምክር ቤት ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በአማራ መገናኛ ብዙኻን ዛሬ ባስተላለፉት ማብራሪያ የሰኔ 15ቱ የባለ ሥልጣናት ግድያ ወንጀል ምርመራ እስካሁን ያልተጠናቀቀው ወንጀሉ ውስብስብና ምርመራው ዘርፈ ብዙ ስለሆነ መሆኑን ጠቅሰው፣ በቅርብ ዝርዝር ሪፖርት እናቀርባለን ብለዋል፡፡ ሴራውን በማክሸፋችን ክልላችን ከመፍረስ አድነነዋል፤ ባንቆጣጠረው ኖሮ ግን የባሰ ትርመስ ይፈጠር ነበር ብለዋል፡፡ እስካሁን በተደረሰበት ድምዳሜ ከጀርባ ስላሉ አካላት ይህ ነው ተብሎ የሚቀርብ ድምዳሜ እንደሌለ ተናግረዋል፡፡ አማራን በጎጥ ለመከፋፈል #ፌስቡክ ላይ የሚሰሩ ሃይሎች ግን ከባድ ችግር ስለፈጠሩብን መንግሥት ያግዘን ሲሉ ጥሪ አድርገዋል፡፡

Via #wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ፌስቡክ

ፌስቡክ ከሳውዲ አረቢያ ጋር የተገናኙ #የሃሰት ፕሮፓጋንዳ የሚሰራጭባቸው መለያዎችን የሚጠቀሙ አንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች እንዳሉ ደርሸበታለሁ በሚል መለያዎችን አገደ፡፡ ዘመቻው መካከለኛው መስራቅን እና ሰሜን አፍሪካ ላይ ያነጣጠረ እንደሁነና የመልዕክቱ ይዘት በአብዛኛውም በአረበኛ ቋንቋ የሚተላለፍ መሆኑን አረጋግጫለሁ ብሏል ፌስቡክ። እስካሁን ድረስም ከ 350 በላይ የሃሰት አካውንቶችን ዘግቻለሁ ብሏል። ሳውዲ ጉዳዩን አስመልክቶ እስካሁን ድረስ ምንም አይነት አስተያየት እንዳልሰጠች ተገልጿል።

Via ቢቢሲ/#ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ይህ ገፅ መረጃዎችን እና መልዕክቶች የሚያቀርበው ለቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ብቻ ነው!

የቲክቫህ ቤተሰቦች 1 ብለው ተነስተው በአስገራሚ ፍጥነት ከ470,000 በላይ ደርሰዋል። የቲክቫህ ቤተሰቦች ልዩ የሚያደርጋቸው ጥላቻን፣ ስድብን፣ ዘለፋን፣ ሰዎች ማዋረድን፣ የሰዎችን ስብዕና መንካትን፣ ያለ ተጨባጭ ማስረጃ መልዕክት መለዋወጥን፣ የሰዎችን ማንነት ማንቋሸሽን፣ ሰውን ከሰውነቱ ውጪ በሌሎች መመዘኛዎች ለክቶ መገምገምን ፈፅሞ አምርረው መቃወማቸው፤ ማውገዛቸው ነው!

የዚህ ቤተሰብ አባላት መረጃዎች ከዚህ ቀደም እንዴት እንደሚቀርብላቸው ጥንቅቀው ያውቃሉ። የሚሰራጭ መረጃ ከየት ከየት እንደሚቀርብላቸውም በአግባቡ ይረዳሉ። እያንዳንዱ ክስተት እንዴት ተመዝኖ እንደሚያቡት፣ ለሚመለከታቸው ሰዎችም መልዕክት እንዴት እንደሚደርስ፣ በዚህች ባልሰለጠነች ሀገር እና ወጣቷ ሁሉ ስሜታዊ በሆነባት ሀገር መረጃዎች ሌላ ቦታ ሊያመጡት የሚችለው ችግር ተፈትሾላቸው እንደሚቀርብም ጠንቅቀው ያውቃሉ።

በዚህ ገፅ ጉዳይ የሚመለከታቸው የቲክቫህ ቤተሰቦች ብቻ ናቸው። ሁሉም አካባቢ በሚባል ደረጃ የቤተሰቡ አባላት አሉ። ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የቲክቫህ ቤተሰቦች አሉ። ስቃያቸው ስቃያችን ነው፤ እንባቸው እንባችን ነው። ውጪ ሲያድሩ አብረን እያደርን ነው። ለሊት ሳይቀር ቁጭ ብለን የምናድረው የሀገራችን ሁኔታ አሳስቦን ነው፤ በያካባቢው ያሉ ቤተሰቦቻችን ጭንቀት እንቅልፍ ነስቶን ነው፤ የቤተሰባችን አባላት ችግር ሲገጥማቸው እያገዝን ነው። ለቤተሰቦቻችን ዋጋ እየከፈልን ነው!! ሁለት ዓመት ሙሉ አንድም ቀን አቋማችን ሳይዛነፍ ለአፍታ ከአጠገባችሁ ዞር ሳንል የአቅማችንን እያደረግን ነው። ኢትዮጵያ ቀና እንድትል ብቸኛው ተስፋችን ናችሁና።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን አሁን #ፌስቡክ ላይ ያለውን አካሄድ ይዘው ብቅ ያሉ የቲክቫህ እውነተኛ ቤተሰብ ያልሆኑ ሰዎች እንድንሳሳት፣ ከሰውነታችን ዝቅ እንድንል ፣ በተለይም አንድ ጥግ ይዘን ሰዎች በሰውነታቸው ሲበደሉ ብሄር እየጠራን እንድናጋግል፣ ሀገሪቷን ወደማያልቅ እልቂት እንድንመራት በሚመስል መልኩ የስድብ ናዳቸው እያወረዱብን ነው። ይህ ፈተና ለኛ ቀላል ነው። ቤተሰቦቻችን እነማን እንደሆኑ እናውቃለንና!

ስለ ትግራይ ክልል ስንናገር የሚከፋው፣ ስለ አማራ ክልል ስንናገር የሚከፋው፣ ስለ ኦሮሚያ ክልል ስንናገር የሚከፋው፤ ስለ ሙስሊም ወገኖቻችን ስንናገር የሚከፋው፣ ስለ ክርስቲያን ወገኖቻችን ስንናገር የሚከፋው፣ ስለ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ስንናገር የሚከፋው፣ ስለ ገዢው ፖርቲ ስንናገር የሚከፋው እና ከራሴ ውጪ ሌላው መስማት አልፈልግም፡ ዘውትር "እኔ ብቻ ልደመጥ፣ እኔ ብቻ ልሰማ" የሚሉ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት አይደሉም።

ስለ ትግራይ ክልል መረጃ ሲያይ የአማራ ህዝብ ጠላት፣ ስለ አማራ ክልል መረጃ ሲያይ የትግራይ ህዝብ ጠላት፣ ስለ ኦሮሚያ ክልል ሲያይ የአማራ ጠላት፣ ስለ አማራ ክልል መረጃ ሲያይ የኦሮሞ ህዝብ ጠላት እያለ በየፌስቡኩ እየፈረጀ የሚውል ሰው የቲክቫህ ቤተሰብ ሊሆን አይችልም። በሚነሱ ጉዳዮች ሁሉ ስድብ የሚቀድመውና ህዝቦችን ሳይቀር የሚያንቋሽሽ፣ ሁሉንም በጅምላ የሚፈርጅ፣ ለወደራሱ ማየት ትቶ የሰው ስህተት ሲፈልግ የሚውል ሰው እሱ የኛ ቤተሰብ አይደለም።

እኚ አካላት ዓላማቸው ግልፅ ነው እኛን ጥግ ማስያዝ፤ ይህ ደግሞ መቼም አይሳካም። መላው የቤተሰቡ አባላት በዚህ ጉዳይ አንደራደርም!!

የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ሁሉም ቦታ አሉ፣ በመቻቻል በአንድነት የሚያምኑ፣ መገፋፋትን የሚፀየፉ፣ አመዛዛኝ፣ ለሀገር አሳቢዎች፣ ነገ ምን ሊፈጠር ይችላል ብለው የሚጨነቁ፣ መረጃዎች የሚያደርሱትን ጉዳት የሚረዱ ናቸው።

ይህ ገፅ የሚመለከተው የቤተሰቡን አባላት ብቻ ነው!! ፌስቡክ ላይ የለመዳችሁበትን የመሰዳደብ እና የጥላቻ አካሄድ እኛ ጋር ለመለጠፍ አትሞክሩ፣ እየመጣችሁ ባትረብሹን ይመረጣል!!

መነሻችን መድረሻችንም ሰውነት ብቻ ነው!
ይህ ገፅ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች ብቻ ነው!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
* ጥንቃቄ

በTIKVAH-ETHIOPIA ስም በተዘጋጀ ሀሰተኛ የቴሌግራም አካውንት የማጭበርበር ስራ እየተሰራ በመሆኑ አባላት ጥንቃቄ እንድታደርጉ አደራ እንላለን።

የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ዛሬ ከሰዓት በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፁ አንዳንድ ህገወጥ ድርጅቶች የአስተዳደሩ ማስታወቂያ እንደሆነ በማስመሰልና በሀሰተኛ የቴሌግራም አካውንት ሀሰተኛ ማስታወቂያ እያሰራጩ መሆኑ ገልጿል።

ይህ ብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር የገለፀው ሀሰተኛ አካውንት በTIKVAH-ETHIOPIA ስም የተከፈተ ሀሰተኛና 25 ሺ ተከታዮች ያሉት ነው።

በዚህ ሀሰተኛ አካውንት ብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር የተለያዩ ሽልማቶች እንደሚሸልምና ሽልማቱም እስከ መስከረም 20 እንደሆነ የሚገልፅ ሀሰተኛ ማስታወቂያ ነው እየተሰራጨ ያለው።

አስተዳደሩ እንዲህ ዓይነት ሽልማቶች እንዳላዘጋጀ የገለፀ ሲሆን ህገወጦቹም በህግ እንደሚጠይቅ አሳውቋል።

ውድ የቲክቫህ አባላት ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስር ያሉት ትክክለኛ አካውንቶች የሚከተሉት ብቻ ናቸው ፦

1. TIKVAH-ETHIOPIA (ከ1.2 ሚሊዮን በላይ አባላት ያሉት)
2. TIKVAH-MAGAZINE (ከ250 ሺ በላይ አባላት ያሉት)
3. TIKVAH-SPORT (ከ140 ሺህ በላይ አባላት ያሉት)
4. TIKVAH-UNIVERSITY (ከ91 ሺ በላይ አባላት ያሉት)
5. TIKVAH-AFAAN OROMOO (ከ20 ሺ በላይ አባላት ያሉት)
6. TIKVAH-AID (ከ5 ሺህ በላይ አባላት ያለቱ)

ከዚህ በተጨማሪ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቴሌግራምና ከትዊተር ውጭ ምንም አይነት የ #ፌስቡክ አካውንት የለውም።

@tikvahethiopia
የኢትዮጵያው ከፍተኛ ባለስልጣን #ፌስቡክ መረጃዬን አሳልፎ ሰጠብኝ አሉ።

ዛሬ ምሽት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋ/ዳሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ''ሀክ ተደረጉ'' ከሚል ጹሑፍ ጋር ተንቀሳቃሽ ምስሎች ተለጥፈው ነበር።

ይህ ከሆነ ከደቂቃዎች በኃላ ዳሬክተሩ፥ ''ለግንዛቤያችሁ'' ብለው ባሰፈሩት መልዕከት ይፋዊ የፌስቡክ አካውንታቸው ''በውጭ አካላት ሃክ አልተደረገም'' ብለዋል።

የተለቀቀው ቪዲዮም ከ1 ዓመት በፊት ፌስቡክ የመልዕክት መላኪያ መተግበሪያ (Messenger) አማካኝነት ከጓደኞቻቸው ጋር ያወሩት እንደሆነ ገልጸዋል።

ዶ/ር ሹመቴ ግዛው ''ፌስቡክ መዝግቦ ያስቀመጠውን መረጃ (Password, Username) እንዴት አሳልፎ እንደሰጠና በዚህም ግለሰብንና ሀገርን ለማሳጣት የተደረገውን የቴክኖሎጂ ውንብድና በህግ አግባብ እንሄድበታለን'' ሲሉ በጹሑፋቸው ገልጸዋል።

በገጻቸው ላይ ለተለጠፈው ተንቀሳቃሽ ምስልም ፌስቡክን መረጃዬን አሳልፎ በመስጠቱ ነው ሲሉም አስረድተዋል።

''የኛ Username እና password እነርሱ ጋር ስለሚገኝ ይህንን ማድረግ ተገቢ አይደለም። ጠላትነታችን እዚህ የደረሰ አልመሠለኝም ነበር'' ይላል አጭር ያሰፈሩት ጹሑፍ።

ተንቀሳቃሽ ምስሉ ዳይሬክተሩ ለጓደኞቻቸው በፊት ለፊት ካሜራ ቀርጸው የላኩት ''አታስቀኑኝ በርሬ መጣለው'' የሚል መልዕክት የያዘ ሲሆን በገጻቸው ላይ በተደጋጋሚ ''ሹመቴ ግዛው ሀክ ተደረገ'' የሚል የሥላቅ መልዕክት ታክሎበት በገጹ ለደቂቃዎች ተለጥፎ ነበር።

አሁን ተንቀሳቃሽ ምስሎቹ ከገጹ የጠፉ ሲሆን ሂደቱን በህግ እንደሚከታተሉም ዶ/ር ሹመቴ አስታውቀዋል።

ዶ/ር ሹመቴ ከ2012 ጀምሮ የኢመደኤ ዋና ዳይሬክተር ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

ባለፉት ቀናት በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምክንያት ተቋርጠው የነበሩት #ቴሌግራም እና #ፌስቡክ መሰል የማህበራዊ ትስስር መተግበሪያዎች ትላንት ፈተናው መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ መደበኛ አገልግሎታቸው መመለሳቸውን ለማወቅ ተችሏል።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ኢንተርኔት እንደተዘጋ ተደርጎ የሚያሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሩስያ ፌስቡክን አገደች። ሩስያ በሀገሯ ውስጥ ፌስቡክ የተሰኘው የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት እንዳይሰጥ ሙሉ በሙሉ ዘግታዋለች። ሩስያ ከጥቅምት 2020 ጀምሮ ቢያንስ 26 በሚሆኑ የሩሲያ ሚዲያዎች እና የመረጃ ምንጮ ላይ መድልዎ መፈፀሙን ገልፃለች። በተጨማሪም በቅርብ ጊዜ ከክሬምሊን ጋር የተቆራኙ የሚዲያ ምንጮች RT Newsና Sputnik News በመላው አውሮፓ እንዲገደቡ መደረጉን አመልክታለች። ይህንንም…
#Instagram

ሩስያ ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ ኢንስታግራም እንደሚታገድ አስታወቀች።

በሜታ ኩባንያ ስር የሚተዳደረው ኢንስታግራም ከሰኞ ጀምሮ እንደሚታገድ ሩስያ ገልፃለች።

ይህ ውሳኔ የተላለፈው ሜታ ከዩክሬን ጦርነት ጋር ተያያዞ በፌስቡክ እና ኢንስታግራም ግጭት ቀስቃሽ ንግግሮች ‘ለተወሰነ ጊዜ’ እንደሚፈቀድ ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ ነው።

ሜታ በፌስቡክ እና ኢስታግራም ላይ " ሞት ለወራሪው ሩስያ፣ ሞት ለሩሲያ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን እና ሞት ለቤላሩሱ ፕሬዝደንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ " የሚሉ ልጥፎች በበርካታ አገራት ፈቅዷል እነዚህም አርሜኒያ ፣ አዘርባጃን ፣ ኢስቶኒያ ፣ ጆርጂያ ፣ ሃንጋሪ ፣ ላቲቪያ ፣ ሊቱዌኒያ ፣ ፖላንድ ፣ ሮማኒያ፣ ሩሲያ፣ ስሎቫኪያ እና ዩክሬን ናቸው።

ነገር ግን ድርጅቱ ንፁሃንን ኢላማ የሚያደርጉ ግጭትን ቀስቃሽ ንግግሮች እንደማይፈቅድ ገልጿል።

ሩስያ ፤ " ሜታ በፌስቡክ እና ኢስታግራም በዜጎቼ ላይ የጥቃት ጥሪዎች እንዲለጠፉ መፍቀዱ ከዚህ በፊት ተደርጎ የማይታወቅ ነው " ያለች ሲሆን በኢስታግራም በሩስያውያን ላይ የኃይል ጥቃት እንዲፈፀሙ ጥሪዎች እየተዘዋወሩ ነው ብላለች።

ይህን ተከትሎ ከሰኞ ጀምሮ ኢስታግራም በምድሪቱ ላይ እንደሚታገድ አሳውቃለች።

በሀገሪቱ ያሉ የኢንስታግራም ተጠቃሚዎች ባላቸው 48 ሰዓታት ውስጥ ፎቶ እና ቪድዮዎቻቸውን ወደ ሌላ ማህበራዊ ሚዲያ እንዲያዘዋውሩ እንዲሁም ለጓደኞቻቸው፣ ለተከታዮቻቸው እንዲያሳውቁ መልዕክት ተላልፏል።

ሩስያ ከዚህ በፊት #ፌስቡክ የተሰኘውን የሜታ ኩባንያ አካል የሆነውን የማህበራዊ ሚዲያ ማገዷ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
“ ማኅበራዊ ሚዲያዎች የልጆቻችንን አእምሮ እንዲበርዙ መፍቀድ የለብንም ” - ስፔንሰር ኮክስ

የአሜሪካ ሀገር " ዩታህ ግዛት " በታዳጊዎች ፌስቡክ፣ ቲክቶክ እና ኢነስታግራምን የመሰሉ ማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀማቸው ላይ ገደብ ጣለች።

ይህ በማድረግ አሜሪካ ውስጥ የመጀመሪያዋ ግዛት ሆናለች።

ትላንት ሀሙስ በፀደቀው ደንብ መሰረት ወላጅ ወይም አሳዳጊ ልጆቹ #ኢኒስታግራም#ፌስቡክ እና #ቲክቶክ ከመክፈቱ በፊት የወላጅ ይሁንታ ማግኘት ይኖርበታል።

የፀደቀው ደንብ ምን ይዟል ?

- የማኅበራዊ ሚዲያ አገልግሎት አቅራቢ ኩባንያዎች ለልጆች አገልግሎቱን ከማቅረባቸው በፊት #የወላጆችን ይሁንታ ማግኘት ይኖርባቸዋል።

- ወላጅ ወይም አሳዳጊ ልጆቹ #ኢኒስታግራም#ፌስቡክ እና #ቲክቶክ ከመክፈቱ በፊት የወላጅ ይሁንታ ማግኘት ይኖርበታል።

- ኩባንያዎች መተግበሪያዎቻቸው ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ አዳጊዎች ያለ ወላጅ ይሁንታ እንዳይከፍቱ ያደረጋሉ።

- ኩባንያዎቹ የአዳጊዎቹን የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም፣ ታሪክ፣ የለጠፏቸውን እና በግል #የተጻጻፏቸውን_መልዕክቶች ሁሉ ለወላጆች መስጠት ይገደዳሉ።

- የማኅበራዊ ሚዲያ አቅራቢ ኩባንያዎች የልጆቹን ፍላጎት እና ምርጫ መሠረት አድርገው #ማስታወቂያ በልጆቹ የማኅበራዊ ሚዲያ ሰሌዳቸው ላይ እንዳይለቁ ይገደዳሉ።

- ታዳጊዎች ማኅበራዊ ትስስር መድረኮችን ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት እስከ ንጋት 12፡30 ድረስ መጠቀም እንዳይችሉ ይደነግጋል።

ሕጉ ተግባራዊ መሆን የሚጀምረው ከሚቀጥለው ዓመት መጋቢት ጀምሮ ነው።

ይህን እርምጃ መውሰድ ያስፈለገው ማኅበራዊ የትስስር መድረኮች በልጆች #የአእምሮ_ጤና ላይ ከፍ ያለ መረበሽን እያደረሱ መሆኑ ከተደረሰበት በኋላ ነው ተብሏል።

የዩታህ ግዛት ገዢ ስፔንሰር ኮክስ በትዊተር ገፃቸው ላይ ፤ “ ማኅበራዊ ሚዲያዎች የልጆቻችንን አእምሮ እንዲበርዙ መፍቀድ የለብንም ” ሲሉ ጽፈዋል።

ከዩታህ በተጨማሪ ተመሳሳይ ሕጎች በቴክሳስ፣ በኦሃዮ፣ በአርካንሳስ፣ በኒው ጀርሲ እና በሊዊዚያና ግዛቶች እየተረቀቁ ነው መባሉን ቢቢሲ ዘግቧል።

Credit : #BBC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ምን አሉ ? የተ/ም/ቤት አባል ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ፦ " ጠ/ሚ ዐቢይ ወደ መንበረ ስልጣን ከወጡበት ከመጋቢት 2010 ዓ/ም ጀምሮ እየተወሳሰቡ የሄዱት የሀገራችን ፖለቲካዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች አሁን ላይ ወደ ሁለንተናዊ ቀውስ መሸጋገራቸውን ማሸፋፈን ወደማይቻልበት ደረጃ ደርሰዋል። ብልፅግና መራሹ መንግስትዎ ፦ - የኢትዮጵያ ህዝብ በሰላም ወጥቶ የሚገባበት ፣ - ነጋዴው…
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዶ/ር ደሳለኝ ምን ምላሽ ሰጡ ?

ኢትዮጵያ ቀውስ ውስጥ መሆኗና ለዚህም ተጠያቂው ገዢው ብልፅግና ፓርቲና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የወደቀ አመራር በመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከስልጣናቸውን #እንዲለቁና ስልጣናቸውን ለሚቋቋም ጊዜያዊ ሲቪል አስተዳደር እንዲያስረክቡ ፤ ፓርላማውም ተበትኖ ለምርጫ መንገድ እንዲጠርግ በሚል በዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ለተጠየቀው ጥያቄ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ምላሽ ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርቲያቸውና መንግሥታቸው ላይ ከታቃዋሚ ፓርቲ በኩል የቀረበውን ክስ በተመለከተ " እንዲህ ያለው ንግግር ለዛሬ #ፌስቡክ፣ ለዛሬ #ዩትዩብ ጥሩ ነው ፤ አቶ እንትና እንትና እንዲህ አደረጉ ለሚለው ለፌስቡክ ፍጆታ ጥሩ ነው ለትውልድ እና ሀገር ግን አይጠቅምም " ብለዋል።

" ቆም ብለን እኛ ማናየውን በማሳየት ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚጠቅመውን ሃሳብ ብናቀርብ ጠቃሚ ነው " ሲሉ ተደምጠዋል።

" በኢኮኖሚ፣ በሰላም እና በአንዳንድ ጉዳዮች የቀረቡትን የምንወስዳቸውና የምንሰራባቸው እንደሆነ ምንም ጥያቄ የለውም " ያሉት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ " በጥቅሉ ኢትዮጵያ ጨለማ ውስጥ ናት ከተባለ ግን ከሰሀራ በታች ካሉ ሀገራት በኢኮኖሚ 3ኛ ናት፣ ከምስራቅ አፍሪካ አንደኛ ናት ፣ ትላልቅ ተቋማትን እየገነባች ያለች ሀገርናት የሚል መልስ ሆኖ ያልቃል " ሲሉ ተናግረዋል።

ምርጫን በተመለከተ ፤ " ምርጫ ይካሄድ የሚለውን ሃሳብ በጣም አደንቃለሁ ፤ ብዙ ጊዜ የተቃዋሚዎች ችግር ምርጫ አይፈልጉም ዝም ብላችሁ ልቀቁና እኛ እንያዝ ነው የሚሉት ፤ አሁን ምርጫ ይደረግ የሚለው በጣም ጠቃሚ ነው ግን ሶስት ዓመት #መታገስ አለብን " ብለዋል።

" በየሳምንቱ ምርጫ ስለማይደረግ ፤ ሶስት አመት ታግሰን ያለንን ሃሳብ ይዘን ቀርበን እኛም ይዘን ቀርበን የኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈርደውን ፍርድ በፀጋ መቀበል ነው ፤ የዛሬ ሁለት ዓመት የፈረደውን ፍርድ አልተቀበልኩምና አሁን ፓርላማው ፈርሶ ምርጫ ካልተካሄደ አሁንም ፈርሶ ቢካሄድና ቢመረጥ ካልተመረጥን ይቀጥላል ጉዳዩ በየሁለት አመቱ ምርጫ ለማካሄድ አቅም ስለሚያንሰን በተቀመጠው መንገድ በ5 ዓመት እናደርጋለን " ብለዋል።

" ምርጫ ሲደረግ ያሉ ሀሳቦች ለህዝብ ቀርበው እኛ ህዝቡ በሚፈልገው ልክ ካላገለገልንና ካልጠቀምን ህዝቡ በምርጫው ሲቀጣን እጅ ስመን፣ ባንስምም እጅ ነስተን እናስረክባለን ፤ እስከዛ መታገስ ጥሩ ነው ፤ ፍርዱን ለህዝብ እንተወው " ሲሉ መልሰዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀገሪቱ ከገባችበት ቀውስ ጋር በተያያዘ ስልጣናቸውን እንዲለቁ በአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ህዝብ በመረጣቸው የምክር ቤት አባላት ሲጠየቁ የዛሬው ሁለተኛ ነው።

የምክር ቤት አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ ከወራት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣን በመልቀቅ " ላለው ችግር የመፍትሄው አካል ለመሆን አላሰቡም ወይ ? በሰብዓዊነት ላይ በተፈፀሙ እንዲሁም በማንነት ተኮር የዘር ማጥፋት ፣ የዘር ማፅዳት እና የማንነት ማሳሳት ወንጀሎች ተጠያቂ ለመሆን ምን ያህል ዝግጁ ኖት ? " የሚል ጥያቄ አቅርበው የነበረ።

በወቅቱ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ ኃላፊነት መውሰድ ካለብን በጋራ ቢሆን መልካም ስለሆነ " ስልጣን ብንለቅ " ነው የሚባለው ምክንያቱም መንግስት ማለት አስፈፃሚ ብቻ አይደለም የሚል ምላሽ ሰጥተዋቸው ነበር።

የዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ንግግር : https://t.iss.one/tikvahethiopia/79527

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia