TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በአዲስ አበባ ከተማ ሊቆም ነው የተባለው የእቴጌ ጣይቱ ሀውልት #ውሸት ነው ብሏል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር። በነገው ዕለት የመሰረት ድንጋይ ሊጣል ነው የተባለውም ውሸት መሆኑን ከከተማ አስተዳደሩ ተሰምቷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከኢንጂነር ታከለ ኡማ ቢሮ አዲስ ስታንዳርድ ሰማሁት እንዳለው የእቴጌ ጣይቱ ሀውልት ሊቆም መሆኑና የመሰረት ድንጋይ ነገ ይቀመጣል መባሉም #ውሸት መሆኑን አረጋግጧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለተማሪዎች‼️የዩኒቨርሲቲ ምደባ መጥቷል እየተባለ የሚወራው ወሬ #ውሸት ነው። እስካሁን በዚህ ጉዳይ ኤጀንሲው ያለው ነገር የለም።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አብዲ ኢሌ‼️

የቀድሞው የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ #አብዲ_መሐመድ የቀረበባቸው ክስ “የተቀነባበረ ውሸት ነው” አሉ። አቶ አብዲ ይህን ያሉት ጉዳያቸውን እየተመለከተ ላለው ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት ነው።

ችሎቱ ለዛሬ ቀጠሮ ይዞ የነበረው አቶ አብዲን ጨምሮ በ47 ተጠርጣሪዎች ላይ የቀረበባቸውን ክስ በንባብ ለማሰማት ነበር። የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በተጠርጣሪዎቹ ላይ በይፋ ክስ የመሰረተው ባለፈው ረቡዕ ጥር 22 የነበረ ቢሆንም የተከሳሽ ጠበቆች በችሎት ባለመገኘታቸው የክስ ንባቡ ለዛሬ ተላልፏል። ጠቅላይ አቃቤ ህግ ተከሳሾቹ በሐምሌ 2010 ዓ. ም. በሶማሌ ክልል 59 ሰዎች እንዲገደሉ እና 412 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት እንዲወድም አድርገዋል በሚል ነው ክሱን ያቀረበው።

በዛሬው የችሎት ውሎ ክሳቸውን ያደመጡት አቶ አብዲ ክሱን ተረድተውት እንደሆነ በመሐል ዳኛው ሲጠየቁ “ሆን ተብሎ የተቀነባበረ #ውሸት መሆኑ ገብቶኛል” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። የእርሳቸውን ምላሽ ተከትሎ ችሎቱን ሞልተው የነበሩ ታዳሚዎች በሹክሹክታ ሲጠያየቁ እንደነበር በስፍራው የተገኘው የጀርመን ራድዮ ዘጋቢ ታዝቧል። ፍርድ ቤቱ ከአቶ አብዲ ውጭ የሌሎችን ተከሳሾች ምላሽ ያላደመጠ ሲሆን ከክስ መቃወሚያ ጋር ደርቦ ለመስማት ለመጪው የካቲት 20 ቀጠሮ ሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱ በዛሬው ውሎው የተከሳሽ ጠበቆች በክሱ ላይ ያቀረቡትን አቤቱታም አድምጧል። በክሱ ውስጥ የምስክሮች ዝርዝር አለመካተቱን ያነሱት የተከሳሽ ጠበቆች በተገቢው ሁኔታ “እንድንከላከል አያስችለንም” ሲሉ ተቃውመዋል። አቃቤ ህግ ምላሹን በጽህፈት ቤት በኩል እንዲያስገባ ያዘዘው ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ላይ ብይን ለመስጠት ለየካቲት 6 ቀጥሯል።

በዛሬው ችሎት አብዛኞቹ ተከሳሾች በአካል አለመቅረባቸውን ዘጋቢያችን ተመልክቷል። ፍርድ ቤቱ ባለፈው ሳምንት ባስቻለው ችሎት ፖሊስ ያልተያዙ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር እንዲያውል የአምስት ቀናት ጊዜ ፈቅዶ ሰጥቶ ነበር። የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ለፖሊስ የደረሰው ከትላንት በስቲያ መሆኑን አቃቤ ህግ ዛሬ ለፍርድ ቤቱ ገልጿል። “ከቦታው ርቀት አንጻር በቂ ጊዜ ይሰጠን” ሲልም በዛሬው ችሎት አመልክቷል።

ምንጭ:- የጀርመን ድምፅ ራዲዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር የተሰጠ መግለጫ፦

"የለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር የከተማውን ፕላን ለማስጠበቅ አረንጓዴ ቦታዎችን፣ ወንዝ ዳርቻዎችን፣ አስተዳደሩ ካሳ ከፍሎባቸው ቤት የተሰራባቸውን እና ባለሃብቶች #ከተፈቀደላቸው በላይ የያዙትን ቦታ ላይ የተሰሩትን ቤቶች ዛሬ ማፍረሱ ይታወቃል። ሆኖም በFB ገጽ ላይ Etiopian DJ የኢትዮጵያ ሙዚቃ የቤቶችን ፈረሳ በተመለከተ #በብሄር ላይ የተመሰረተ ፈረሳ ነው፣ ሚዲያ እንዳይገባ ተከልክሎአል ከሁሉ በላይ ደግሞ ሁለት ሰው #ሞቶል እንዲሁም ቆስለዋል በማለት FB ላይ የለጠፈው ነገር ፍጹም #ውሸት እና በብሔር ላይ የተመሰረተ ፈረሳ የለለ ሚዲያዎችም የነበሩ እና አንድም ሰው እንኮን ሊሞት የቆሰለም ያልነበረ መሆኑን ከተቆቆመው ኮማንድ ፖስት ማረጋገጥ ተችሎል።በመሆኑም Ethiopian Dj ም ሆነ ለሎች በ FB ላይ የምለጥፉ ከእንደዚህ አይነት ድርጊት ብርቁ መልካም ነው እንላለን።"

©ኤልያስ መሰረት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወ/ሮ #ሙፈሪያት_ከሚል

"በሰላም ሚኒስትር እና የደህዴን ሊቀመንበሯ ሙፈርያት ካሚል ላይ የግድያ ሙከራ ተደረገ" ተብሎ እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ እውነትነት የራቀ መሆኑ የሰላም ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ሄርሜላ ሰለሞን ለአለም አቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ተናገሩ። ዳይሬክተሯ ወሬውን ለማጣራት ወ/ሮ ሙፈርያት ጋር ከደወሉ በሁዋላ ይህንን ብለዋል፦

"ሚኒስትሯ ቀኑን ሙሉ ሀዋሳ ስብሰባ ላይ ነው የዋሉት። እንኳን ሙከራ ሊደረግ ለመሞከር እድል የሚኖርበት ሁኔታ አልነበረም። ለማንኛውም የተባለው ሙሉ ለሙሉ #ውሸት ነው ብለው ሚኒስትሯ እራሳቸው አሁን በስልክ ነግረውኛል። ምንም የተለየ ነገር አልተፈጠረም።"

ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የክልሉ ባለስልጣን መረጃው ፌክ ኒውስ ነው ሲሉ ለጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ተናግረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethuopia
#ATAYE

ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ ከተማ አካባቢ በተፈጠረ ግጭት የሰው ሕይወት መጥፋቱ ይታወቃል። መንግስት “ለግጭቱ ተጠያቂው ኦነግ ነው” ሲል ገልፆአል።

ኦነግ በበኩሉ ተከታዩን ምላሽ ሰጥቷል፦

“አጣዬ #ኦነግ ምን ሊሰራ #ይመጣል፣ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሰራዊት እንደሌለው ብዙ ጊዜ መላልሰን ተናግረናል በመሆኑም ስሞታው #ውሸት ነው” የኦነግ ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ አደባ

Via ዶቼ ቬለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AAU

ጋዜጠኛ ጌትነት ተስፋዬ - ተኩስ ነበረ የተባለው #ውሸት ነበር በሚል ዳግም በፌስቡክ ገፁ ባወጣው መረጃ አስተካክሏል። በተማሪዎች ስም እኛም እናመሰግናለን!
-------
ጥቃቅ የሚመስሉ ነገር ግን ወላጆችን የሚያስጨንቁ መረጃዎች ስላሉ ጋዜጠኞችም ሚዲያዎችም ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ መረጃ ቢያቀብሉ ይመረጣል!! ትላንት ፋና ብሮድካስቲንግ በፌስቡክ ገፁ ይዞት የወጣው የተሳሳተ መረጃ በርካታ ቤተሰቦቻችን ላይ ጭንቀት ፈጥሮ ነበር።

@tikvahethiopia @tikvahethiopia
ብልፅግና ፓርቲና የ‹ባለ አደራ መንግሥት›...

ሕወሓት፤ ብልፅግና ፓርቲ በ2012 ዓ/ም እንደሚደረግ ከሚጠበቀው አገር ዐቀፍ ምርጫ በፊት ከተመሰረተ ኢትዮጵያ በባለ አደራ መንግሥት መመራት አለባት አለ፡፡ ከቀናት በፊት ሊቀመንበሩ ደብረፂዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) ብልፅግና ፓርቲን መመስረቱም ሆነ ኢሕአዴግን የማፍረሱ ሒደት ሕጋዊ መንገዱን አልተከተለም በሚል ኢትዮጵያ ከምርጫ በፊት በባለ አደራ ልትመራ ትገደዳለች ማለታቸው ይታወሳል፡፡

በተመሳሳይ ኅዳር 18 ምሽት በትግራይ ቴሌቪዥን ቆይታ የነበራቸው የሕወሓት እና ኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ጌታቸው ረዳ ይህንኑ ሀሳብ ደግመውታል፡፡
ኢሕአዴግ አራቱን ብሔራዊ ድርጅቶች የማፍረስ ስልጣን አልተሰጠውም የሚሉት ጌታቸው፤ በሐዋሳው ጉባኤ ሀላፊነቱ ተሰጥቶታል የሚባለው #ውሸት ነው ሲሉ የሰላ ትችት ሰንዝረዋል፡፡

‹‹ብልፅግና ፓርቲ ውኅድ ሳይሆን አዲስ ፓርቲ ነው በማለትም›› ብልፅግናን መስርተው አሁን ባለው የመንግሥትነት ቦታ እንቀጥላለን ካሉ፤ ያን ጊዜ ሕግ የሚፈታው ጉዳይ ይሆናልም ብለዋል፡፡ በመሆኑም ብልፅግና ፓርቲ ኢህአዴግን መውረስ አይችልም፤ የብልፅግና ፓርቲ እየሄደበት ያለው ሂደትም ጨፍላቂ ነው ሲሉ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፡፡ በአንጻሩ ብልፅግና ፓርቲ ሕጋዊ ሂደቶችን ተከትሎና ኢሕአዴግን አዋኅዶ እየተፈጠረ መሆኑን በተደጋጋሚ የሚናገሩት የኢሕአዴግ ሊቀመንበር ዐቢይ አሕመድ፤ አዲሱ ውህድ ፓርቲ እውነተኛ ፌደራሊዝምን የሚተገብር እንጂ ጨፍላቂ አይደለም ሲሉ ይደመጣሉ፡፡

(አሃዱ ቴሌቪዥን)

@tikvahethiopia @tikvahethipiaBpt
በደቡብ ሱዳን የቲክቫህ አባላት!

ደቡብ ሱዳን ውስጥ የሚገኙ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት በሀገሪቱ ውስጥ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እጅግ በሚያስፈራ ሁኔታ እየተሰራጨ እንደሆነ ገልፀውልናል።

ሀገሪቱ የምታደርገው ምርመራ ትንሽ ቢሆንም በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ግን ከፍጥነት እየጨመረ ነው ሲሉ አሳውቀውናል።

አንዳንድ የሀገሪቱ ሰዎች ኮሮና ቫይረስ የሚባለው #ውሸት ነው፣ አሉባልታ ነው፣ እንዲህ የሚባል በሽታ የለም ፤ ጥቁሮችን አይዝም የሚል አመለካከት አላቸው ብለዋል።

በሀገሪቱ ወረርሽኙን ለመከላከል የሚሰራው ስራ ደካማ ነው ፤ ቁጥራቸው በርካታ ባለስልጣናት ሳይቀሩ በቫይረሱ ተይዘዋል።

በሀገሪቱ ባለፉት ሳምንታት ብቻ በርካታ ሰዎች (የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ሳይቀሩ) ሞተዋል ግን በምን ምክንያት እንደሆን አይገለፅም ሲሉ ያለውን ሁኔታ አስረድተውናል።

አካላዊ ርቀት፣ እጅን አዘውትሮ በሳሙና መታጠብ፣ በአንድ ቦታ አለመሰባሰብ፣ ሌሎችም ቫይረሱን የመከላከያ መንገዶች ተግባራዊ አይደረጉም ይህ ሁኔታ የጤና ስርዓቷ እጅግ ደካማ በሆነው ደቡብ ሱዳን ከፍተኛ ዋጋ ማስከፈሉ አይቀርም ሲሉ ያደረባቸውን ስጋት ገልፀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia #Sudan የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያ እና ሱዳንን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ በአረብኛ ቋንቋ ባሰራጩት መልዕክት የሱዳንና የኢትዮጵያ ህዝቦች ወንድማማቾች መሆናቸውን ገልፀው በሁለቱ ሀገራት መካከል ችግር መኖሩ ግልፅ ነው ብለዋል። ነገር ግን ሁለቱ ሀገራት እነዚያን ችግሮች ለመፍታት ሊጥሩ እና ሊተባበሩ ይገባል ሲሉ ገልፀዋል። ኢትዮጵያ እና ሱዳንን ለማጋጨት የሚፈልጉ…
#Update #Ethiopia #Sudan

" መረጃው ውሸት ነው " - ዶ/ር ለገሰ ቱሉ

" በእግረኛ የሚመጡ ከሆነ የአካባቢው ታጣቂ በተጠንቀቅ ቆሟል " - አቶ አብራራው ተስፋ

" ሱዳን ትሪቡን " የተባለው የሱዳን ሚዲያ የሱዳን ጦር ሰራዊት ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ኃይሎች ተወሰደብኝ ያለውን እርምጃ ለመበቀል የይገባኛል ጥያቄ በሚናሳበት የአልፋሽጋ አካባቢ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ስር የነበሩ " ካላ ላባን " እና " በረከት " የተባሉ አካባቢዎችን ተቆጣጥሯል ሲል ዘግቧል።

በዘገባውም ላይ የሱዳን ጦር በርካታ የኢትዮጵያ የጦር ተሸከርካሪዎች ላይ ጉዳት እንዳደረሰ  / እንዳቃጠለ ፣ ወታደሮችንም እንደማረከ ገልጿል።

ዛሬ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ቃላቸውን የሰጡት የኢፌድሪ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስተር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ መረጃው #ውሸት እንደሆነ አረጋግጠዋል።

በሌላ በኩል በም/ጎንደር ዞን ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ የሱዳን ጦር አካባቢው እንዳይለማ አልሞ አሁንም ድረስ ከእርቀት መድፍ እየተኮሰ እንደሆነ የወረዳው የሰላምና ደህንነት ኃላፊ አቶ አብራራው ተስፋ ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል ገልፀዋል።

አንድ የአካባቢው ነዋሪም የሱዳን ጦር ትንኮሳውን በአካባቢው ትናንት ማምሻውን ቀጥሎ እንደነበር አስረድተዋል፡፡ 

መድፍ ከእርቀት ከመተኮስ ያለፈ ነገር እንደሌለ የሚናገሩት የወረዳው የሰላምና ደህንነት ኃላፊ ፥ " በእግረኛ የሚመጡ ከሆነ የአካባቢው ታጣቂ #በተጠንቀቅ_ቆሟል ነው " ያሉት፡፡ 

ህብረተሰቡ በሚተኮሱት ከባባድ መሳሪያዎች ከመደናገጥ ይልቅ ተደራጅቶ ዘልቀው የሚመጡ ከሆነ እየጠበቀ እንደሆነ ነው ለሬድዮ ጣቢያው ያስረዱት፡፡

@tikvahethiopia