TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በአፋር እና በሱማሌ ክልሎች #አዋሳኝ አካባቢዎች ምንም አይነት የፀጥታ ችግር እንዳይከሰት እንደሚሰሩ የሁለቱ ክልል ከፍተኛ ርዕሰ መሰተዳደሮች ገለፁ፡፡

የሱማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ሙስጠፋ_መሀመድ እና የአፋር ክልል ርዕሰ መሰተዳደር አቶ #አወል_አርባ ዛሬ በአዲስ አበባ በሁለቱ ክልሎች የፀጥታ ችግር መፍትሄ ዙሪያ ላይ ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም በሁለቱ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች አንድም ሰው እንዳይሞት እና ግጭት እንዳይከሰት የማድረግ ሰራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

የሰላም ሚኒስትር ዲኤታው አቶ #ዘይኑ_ጀማል በበኩላቸው ችግር በተፈጠረባቸው አካባቢዎች በአስቸኳይ የሀገር ሽማግሌዎች ቡድን እንዲቋቋምና ችግሩ በዘላቂነት ሊፈታ እደሚገባው ተናግረዋል፡፡ በአጠቃላይ ጉዳይ ላይም በህዝብ ለህዝብ #ውይይት ሊፈታ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ ክልሎቹ #ከማንነት እና #ከወሰን ጋር ያሉ ችግሮችን ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኙ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

Via ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
" ጉዳዩ ሳይከር ትኩረት ይሰጠው "

በኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎች ወሰን አካባቢ የፀጥታ ችግር እንዳለ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ገልጸዋል።

በዚህ የፀጥታ ችግር ሳቢያ ከሀረር ወደ ጅግጅጋ የሚወስደው መንገድ ማስተጓጎል እንደተፈጠረ አመልክተዋል።

በአካባቢው የሚገኝ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ፤ በኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልል አዋሳኝ ባቢሌ ዳከተ አካባቢ ግጭት መኖሩን ጠቁሞ በዚህም መንገድ መዘጋቱን አሳውቋል።

በአካባቢው በተፈጠረው ግጭት ጉዳት መድረሱን የጠቆመው የቤተሰባችን አባል አሁንም ችግሩ እንዳለ ጠቁመዋል።

ሌላ የቤተሰባችን አባል ፤ ከአዲስ አበባ ወደ ጅግጅጋ መስመር " ባቢሌ " አካባቢ ወይም በሁለቱ ክልሎች ወሰን መንገድ ላይ በተፈጠረ ግጭት የሰው ህይወት አልፏል ብለዋል።

" ልዩ ኮሌጅ " ተብሎ የሚጠራበት ስፍራ ትናንት በፀጥታ ችግር አንድ ሰው እንደሞተ በአይናችን አይተናል ሶስት ሰው ቆስሎ ሆስፒታል ገብተዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

ዛሬ የተረጋጋ ቢሆንም አልፎ አልፎ ተኩስ ይሰማል ጉዳዩ ሳይከር የምመለከተው የፌዴራል አካል እልባት ቢሰጠው መልካም ነው ሲሉ አሳስበዋል።

በግጭቱ ምክንያት መንገድ በመዘጋቱ ከትላንት አንስቶ መንገደኞች ከፍተኛ እግልት እንደገጠማቸውም ይኸው ቤተሰባችን ገልጿል።

" በበዓል ምክንያት ከስራ ወጥተን የምመለስበት ሰዓት ላይ እንዲህ አይነት ነገር መፈጠሩ በማህበረሰቡ ላይ ትልቅ ችግር እና በባቢሌ ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ስጋት ደቅኗል " ሲሉ ገልጿል።

ሌላው የቤተሰባችን አባል ፤ ባቢሌ መውጫ እና በባንባስ መካከል በተለምዶ " ዳከታ " እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በተፈጠረ ግጭት ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል።

ሁኔታው የነዋሪዎችን ደህንነት አደጋ ላይ እንደጣለው ጠቁመዋል። ግጭቱ ዛሬም ቀጥሎ እንደዋለ ገልጸዋል።

ችግሩ በሁለቱ ክልሎች መካከል የፍተሻ ቦታ ላይ #ከወሰን ጋር በተገናኘ የተፈጠረ እንደሆነ ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሚመለከታቸውን አካላት ለማነጋገር ጥረት ቢያዳርግም አልተሳካም።

@tikvahethiopia
ዓመታትን የፈጀው መንገድ . . .

" የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይገጥማቸው አማራጭ መንገዶችን ተጠቀሙ " - የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን

ግንባታው ከተጀመረ ዓመታትን ያስቆጠረው የቃሊቲ - ቱሉ ዲምቱ የመንገድ ፕሮጀክት አሁን ወደ መጠናቀቁ መድረሱ ተነግሯል።

ይህ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በደቡብ የአዲስ አበባ ክፍል እየገነባቸው ከሚገኙ የመንገድ ፕሮጀክቶች አንዱ የሆነው መንገድ ፤ ከደቡብና ከምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ወደ አዲስ አበባ ከተማ ለመግባትና ለመውጣት፣ ለረጅም ዓመታት ብቸኛው የወጪና ገቢ መተላለፊያ መስመር ሆኖ ሲያገለግል ነበር።

መንገዱን ያለውን የትራፊክ  እንቅስቃሴ በአግባቡ ማስተናገድ እንዲችል በሚል ግንባታ ከተጀመረ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን እንደሚለው ፤ ከመንገድ ፕሮጄክቱ አጠቃላይ ግንባታ ሂደት ከግማሽ በላይ የሚሆነው በተያዘለት የጊዜ ገደብ ተፈፅሞ በከፊል አገልግሎት መስጠት ችሏል።

ነገር ግን፦
- #ከፋይናንስ
- #ከወሰን_ማስከበር ጋር በተያያዘ በገጠሙ ችግሮች ምክንያት ቀሪው የግንባታ ሥራ በተፈለገው ልክ ሳይፈፀም መቆየቱን አመልክቷል።

ለችግሮቹ በተሰጠ መፍትሄ የፕሮጀክቱ ግንባታ ቀጥሎ አሁን ላይ ወደ ማጠናቀቂያው ምዕራፍ መሸጋገሩን አሳውቋል።

መ/ቤቱ በፕሮጀክቱ የግንባታ ሂደት ምክንያት የአካባቢው ነዋሪ ክረምት በጭቃ፣ በጋውን በአቧራ ሲፈተን እንደነበር ገልጿል።

በዚህ መንገድ ምክንያት የትራፊክ እንቅስቃሴው እንደ ኤሊ ጉዞ እያዘገመ ይጓዝ እንደነበረም ገልጾ አሁን ግን ወደመጠናቀቁ መድረሱን አሳውቋል።

አሁን ላይ ቀደም ሲል ተገንብቶ አገልግሎት እየሰጠ በቆየው የመንገዱ የቀኝ ክፍል ተደራቢ አስፋልት የማንጠፍ ስራ የተከናወነ ሲሆን፣ ከዚሁ ጎን ለጎን የእግረኛ እና የፔዳል ሳይክል መተላለፊያ መስመርና ቀሪ የማጠናቀቂያ ምዕራፍ ስራዎች በመከናወን ላይ ናቸው ብሏል።

ቃሊቲ ማሰልጠኛ የቀለበት መንገድ መሸጋገሪያ ላይ እየተሰራ የሚገኘውን የመንገድ ማገጣጠሚያ ግንባታ ጨምሮ ሌሎች ተያያዥ ስራዎች በጥቂት ጊዜያት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ይጠናቀቃሉ ብሏል።

አሸከርካሪዎች በግንባታው ምክንያት የትራፊክ መጨናነቅ ችግሮች እንዳይገጥማቸው አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ መልዕክት አስተለልፏል።

@tikvahethiopia