TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውሃ አሞላል ዙሪያ የተቋቋመው የባለሙያዎች ቡድን ሪፖርት ላይ የኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ የውሃ ሚኒስትሮች በአዲስ አበባ #እየተወያዩ ነው። በውይይቱ ላይ የኢፌዴሪ የውሃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ፣ የሱዳን የውሃ ሀብት፣ የኤሌክትሪክና የመስኖ ሚኒስትር ኢንጂነር ከድር ጋስመዲን እና የግብፅ የውሃ ሀብትና የመስኖ ሚኒስትር ዶክተር መሀመድ አብዱላቲ እየተሳተፉ ይገኛሉ።

©ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚር #ዐቢይ_አሕመድ በአሁኑ ጊዜ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር #እየተወያዩ ይጋኛሉ። ይህ ታሪካዊና በኢትዮጲያ የፖለቲካ ታሪክና ትርክት አይነተኛ የውይይት መድረክ ከጥቂት ወራት በፊት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋባዥነት ከተደረገው የቀጠለ ነው። ከዛሬው ውይይት አስተባባሪ አንዱ የሺዋስ አሰፋ እንዳሉት የመድረኩ ዋና አላማ በዚህ የፖለቲካው ሽግግር ወቅት የፖለቲካ አመለካከትን በሰላማዊ ሁኔታ መለዋወጥ ልምድን ለማሰደግ ነው። ከ4 የፖለቲካ ድርጅት አመራሮችም የውይይት ጽሁፍ ይቀርባል።

ምንጭ፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ🔝

#የኤርትራ ፐብሊክ ዲፕሎማሲና የባህል ልኡክ አባላት #ከሀዋሳ_ከተማ ነዋሪዎች ጋር #እየተወያዩ ይገኛሉ።

ፎቶ፦ Sofi
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደንቢ ዶሎ...

የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከቄለም ወለጋ ዞን ከተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች እና ከደንቢ ዶሎ ነዋሪዎች ጋር #እየተወያዩ ይገኛሉ፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia