TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Mekelle

አሜሪካ በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ የሚገኙ ዜጎቿን ለማስወጣት ጥረት እያደረገች ነው።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በትዊተር ገጹ ባሰራጨው "የጥንቃቄ መልዕክት" መቐለ የሚገኙ የአሜሪካ ዜግነት ያላቸውን ዜጎች ለማስወጣት ጥረት እየተደረገ መሆኑን አሳውቋል።

በመቐለ የሚኖሩ አሜሪካዊ ዜግነት ያላቸው ሰዎች ለደኅንነታቸው ተጠልለው እንዲቆዩ መስሪያ ቤቱ መክሯል።

በክልሉ ያሉ አሜሪካዊ ዜግነት ያላቸው ወይም በመቐለ የሚኖር #አሜሪካዊ ቤተሰብ ያላቸው ሰዎች ከመስሪያ ቤቱ ጋር ግንኙነት እንዲያደርጉ ተጠይቋል።

#WazemaRadio #USEmbassyAA

@tikvahethiopia