TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"በቅርቡ አደጋ የደረሰበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር 302 ከመረጃ ሳጥን (FDR & CVR) ሙሉ መረጃው #በተሳካ ሁኔታ መገልበጥ ተችሏል። በስፍራው የሚገኙ ባለሞያዎቻችንና አሜሪካዉያን ኤክስፐርቶች የመረጃውን #ትክክለኝነት አረጋግጠዋል። የኢትዮጵያ መንግስት መረጃዎቹን የተረከበ ሲሆን እስካሁን በነበረው ሂደት የአደጋው መንስኤ #ከኢንዶንዢያው በረራ 610 ጋር የሚመሳሰል ሆኖ ተገኝቷል። በቀጣይ በሚደረግ ዝርዝር ትንተና መሰረት በአንድ ወር ውስጥ ለህዝብ ይፋ ይሆናል፡፡ በእስካሁኑ ሂደት የፈረንሳይ መንግስት ላደረገው ትብብር ማመስገን አንወዳልን።" -- Dagmawit Moges

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#MoE

አገር አቀፍ ፈተናዎች የሚሰጡባቸው እና የምረቃ ቀናት እንዲሁም የሬሜዲያ ፈተና ወጤት አያያዝ ላይ ቅያሪ ተደርጓል።

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ግንቦት 9 ቀን 2015 ዓ/ም ያስተላለፈውን ሴርኩላር በተመለከተ ከዩኒቨርሲቲዎችና ከክልል ት/ቢሮ አመራሮች ጋር በድጋሚ ግንቦት 22 ቀን 2015 በበይነ-መረብ ውይይት አድርጓል።

በውይይቱ መሰረትም ፦

- ፈተናዎች የሚሰጡባቸው ቀናት፣

- የተማሪዎች ምረቃ በዓል፣

- የሪሜዲያል ፈተና ውጤት አያያዝ በተመለከተ ቅያሪ መደረጉን ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች፣ ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ ለሁሉም የክልል ትምህርት ቢሮዎች በፃፈው ደብዳቤ ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተፈርሞ የተላከውን ደብዳቤ #ትክክለኝነት ከሚመለከታቸው አካላት አረጋግጧል።

በዚህም ፦

- በ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል አጠናቀው ፈተና በመውሰድ በልዩ ሁኔታ የሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ ለሆኑ ተማሪዎች ለአንድ ሴሚስተር የተሰጠው ትምህርት በማዕከል የጋራ ፈተና ተዘጋጅቶ ለተቋማት እንዲላክ ፤ ተቋማት ፊተናውን የማስተዳደር ውጤት የመግለፅና በ2016 ፍሬሽማን ፕሮግራም ለመከታተል ብቁ ሆነው የተገኙት (ማለትም በተቋማት የውስጥ ፈተና 30 ከመቶ፣ #በማዕከል የተዘጋጀው ፈተና 70 ከመቶ) ተደምሮ በድምሩ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡቱን እንዲያሳወቁ፣ ይህ አጠቃላይ ሂደት እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ እንዲጠናቀቅ ትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ አስቀምጧል።

- በ2015 ዓ/ም የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የተመዘገቡ በግልና በመንግስት ተቋማት የሚገኙ እጩ ምሩቃንና ባለፉት ዓመታት የህግ መውጫ ፈተና ወስደው የማለፊያ ውጤት ያላስመዘገቡት ተማሪዎች የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የመፈተኛ ማእከላት ውስጥ ፈተናው ከሐምሌ 3 እስከ 8 ባሉት ቀናት ተሰጥቶ ውጤት ሐምሌ 10 ቀን የሚገልጽ ይሆናል ተብሏል።

- የተማሪዎችን ምረቃ በተመለከተ ከሐምሌ 11 እስከ ሐምሌ 16 ቀን ባሉት ቀናት ውስጥ ማካሄድ የሚቻል መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር የገለፀ ሲሆን በመርሃ-ግብሩ ላይ የሚሳተፉት የመውጫ ፈተናውን ያለፉ ተማሪዎች #ብቻ ናቸው ብሏል።

- የ2015 የ12ኛ ከፍል ማጠቃለያ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ 30 የሚሰጥ ሆኖ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከሐምሌ 16 ቀን ጀምሮ ለዚሁ ሥራ ብቻ ዝግጁ እንዲሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ አስቀምጧል።

(ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሚመለከተው የትምህርት ሚኒስቴር አካል ትክክለኝነቱን ያረጋገጠው ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኦዲት የተሰበሰበው ገቢ #ትክክለኛነቱን ለማረጋገጥ ሂሳብ ኦዲት ሲደረግ በኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት #በዶላር የተሰበሰበ 1.3 ሚሊዮን ገቢ ትክክለኝነቱን ማረጋገጥ #አልተቻለም። የፌዴራል ዋና ኦዲተር ማንኛውም ገቢ ተገቢ ማስረጃ ሳይሟላ በገቢ መመዝገብ ፍጹም ትክክል እንዳልሆነ አስገንብዝቦ የገቢ ማስረጃዎች በትክክል ተደራጅቶ እንዲያዝ ተገቢው ማስተካከያም እንዲደረግና እርምጃ እንዲወሰድ አሳስቧል።…
#ኢትዮጵያ #ኦዲት

በ11 መስሪያ ቤቶች 43.5 ሚሊዮን ብር #ምንም ማስረጃ ሳይኖር ወጪ ተደርጓል።

በ2015 የበጀት ዓመት መ/ቤቶች የተፈቀደላቸውን በጀት በአግባቡ ወጪ ማድረጋቸውን / በአግባቡ መጠቀማቸውን ፣ ተገቢ ማስረጃ መቅረቡንና ሂሳቡ በትክክል መመዝገቡን ለማጣራት ኦዲት ተደርጓል።

በዚህም ፥ ምንም አይነት ማስረጃ ሳይቀርብ በወጪ የተመዘገበ ክፍያ / ሂሳብ ተገኝቷል።

በ11 መ/ቤቶች 43.5 ሚሊዮን ማስረጃ ሳይኖረው በወጪ ሂሳብ የተመዘገበ ሲሆን ማስረጃም ባለመቅረቡ ትክክለኛነቱን ማረጋገጥ አልተቻለም።

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን 17.4 ሚሊዮን
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ባለስልጣን 8.7 ሚሊዮን
የመንገድ ደህንነትና መድህን ፈንድ አገልግሎት 8.7 ሚሊዮን
ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ 4.4 ሚሊዮን
የኢትዮጵያ አካል ድጋፍ አገልግሎት 3.3 ሚሊዮን ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

ከዚህ ባለፈ ፤ በወጪ ለተመዘገቡ ክፍያዎች የተሟላ ማስረጃ መቅረቡን ለማረጋገጥ በተደረገው ኦዲት በ 48 መ/ቤቶች የተሟላ ማስረጃ ሳይቀርብ 44 ሚሊዮን 440 ሺህ በወጪ ተመዝግቦ ተገኝቷል።

የተሟላ ማስረጃ ሳይዙ ወጪ ከመዘገቡት መካከል ፦
🔴 ማዕድን ሚኒስቴር 5 ሚሊዮን 719 ሺህ
🔴 ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ 5 ሚሊዮን 716 ሺህ
🔴 የጤና ሚኒስቴር 4 ሚሊዮን 677 ሺህ
🔴 ገንዘብ ሚኒስቴር 3 ሚሊዮን 34 ሺህ
🔴 በስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ገዋኔ የግብርና የቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ 2 ሚሊዮን 450 ሺህ
🔴 የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት 2 ሚሊዮን 185 ሺህ ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

የፌዴራል ኦዲተር መስሪያ ቤት ፤ ማስረጃ ካልቀረበ የሂሳቡን #ትክክለኝነት_ማረጋገጥ_እንደማይቻል ፤ የወጪ ማስረጃ ላልቀረበላቸው ክፍያዎች የወጪ ማስረጃ እንዲቀርብላቸው የማይቀርብላቸው ከሆነ #ገንዘቡ_ተመላሽ እንዲደረግ አሳስቧል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia