TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
* ዳንግላ

በዳንግላ ከተማ የሰዓት እላፊን ጨምሮ የተለያዩ ውሳኔዎች ተላለፉ።

የዳንግላ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት የተለያዩ ውሳኔዎችን ማሳለፉ ተገልጿል።

እነዚህም ፦

1. ማንኛውም ግለሰብ ከምሽቱ 3:00 ስዓት እስከ ንጋቱ 12:00 መንቀሳቀስ አይችልም፤ ለባለ ሶስት እግር ባጃጅ ፣ ሞተር፣ ዳማስ፣ የህዝብ ማመላለሻ፣ የጭነት መኪኖች ከምሽቱ 3:00 ስዓት እስከ ንጋቱ 12:00 ስዓት መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።

2. ከተፈቀደለት የመንግስት የፀጥታ ኋይል ውጭ የተመዘገበ ሆነ ያልተመዘገበ የጦር መሳሪያ የወገብም ሆነ የተከሻ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።

3. ድምፅ አልባ መሳሪያዎችን ስለታማ የሆኑ እንደ ጩቤ፣ገጀራ፣አንካሴ፣ ጦርና ፌሮ ብረት ወዘተ የመሳሰሉትን ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።

4. በህግ የሚፈለጉ ወይም ተጠርጣሪዎችን ሽፋን የሰጠ፣ የደበቀ ፣ የሀሰተኛ መረጃ ሰጥቶ ያሰመለጠ ያስጠይቃል ድርጊቱም የተከለከለ ነው።

5. በማንኛውም ቦታና ስዓት ጥይትም ሆነ ሮኬት ርችት መተኮስ የተከለከለ ነው።

6. የሠራዊቱን ሚሊታሪ(አልባሳት)
- የልዩ ኋይል
- የፓሊስ
- የመከላከያ ሠራዊት
- የፌዴራል ፓሊስ መልበስ የተከለከለ ነው።

7. ያልተፈቀደ ስብሰባዎችን ማለትም ያለ መንግስት እውቅና ውጭ ስብሰባ ማድረግ የተከለከለ ነው።

8. ማንኛውም ግለሰብ የፀጥታ ኋይል ለሚፈለገው የስራ ትብብር ያለ ቅድመ ሁኔታ የመተባበር ግዴታ አለበት ፤ ከሚሉት ናቸው።

በቀጣይ በፀጥታው ም/ቤት እየታዩ የሚጨመሩ ክልከላዎች የሚኖሩ ይሆናልም ተብሏል።

የዳንግላ ከተማ አስተዳደር የፀጥታው ም/ቤት ትላንት ያሳለፈው ውሳኔ በምን ምክንያት እንደሆነ በግልፅ የተብራራ ነገር የለም።

@tikvhahethiopia
#Update

ኦን-ላይን የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት ሐምሌ1/2014 ዓ.ም ሙሉ በሙሉ ይጀመራል ተብሏል።

ይህን ያሳወቀው የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ነው።

የኦንላይን የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት ጥር 2013 ዓ.ም ይፋ ተደርጎ እንደነበር ይታወሳል ነገር ግን በከፊል እንጂ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ አልተደረገም ነበር።

ከሐምሌ 1 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ ኦንላይን የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገልጿል።

ይህንን ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መሰራታቸውን ተነግሯል።

(ተጨማሪ ከላይ ያንብቡ)

@tikvahethiopia
#Update

ብፁዕ አቡነ አረጋዊ ለተጨማሪ ህክምና ወደ ዱባይ ተጓዙ።

ብፁዕ አቡነ አረጋዊ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትትርያርክ ልዩ ጽ/ት፣ የውጭ ግንኙነት ፣ የድሬዳዋና የጅቡቲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የጤና እክል አጋጥሟቸው በአዲስ አበባ በተለያዩ ሆስፒታሎች ህክምናቸውን ሲከታተሉ ቆይተዋል።

በኋላም ከሆስፒታል ወጥተው በመመላለስ ህክምናቸውን ቀጥለው የነበሩ ሲሆን በዛሬው ዕለት ለተጨማሪ ህክምና ወደ ዱባይ ማቅናታቸው ተገልጿል።

የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ህዝብ ግንኙነት መምሪያ፥ " ብፁዕነታቸው ጤናቸው ተስተካክሎ በቅርቡ ወደ መንበረ ጵጵስናቸው እንዲመለሱ ከመጸለይ ጋር በህክምናው ወቅት መልካሙ ሁሉ እንዲገጥማቸው ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ጽኑዕ ምኞቷን ትገልጻለች " ብሏል።

@tikvahethiopia
#EHRC

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በየደረጃው ያሉ የመንግሥት አስፈጻሚ አካላት እና ኃላፊዎች ላይ የቅርብ ክትትል በማድረግ ለሰብአዊ መብቶች መከበር አስተዋጽኦ ሊያደርጉ ይገባል ሲል ጥሪ አቀረበ።

ኮሚሽኑ ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት ተጠያቂነትን በማረጋገጥ፣ የሕግ በላይነትን በማስፈን፣ መንግሥትና የስራ አስፈጻሚ አካላቱ በመሉ ለሰብአዊ መብቶች መከበር፣ መጠበቅና መሟላት ያላቸውን ቁርጠኝነት እንዲያድሱና እንዲተገብሩ ልዩ ትኩረትና ክትትል ይሻል ብሏል። 

ኢሰመኮ ይህንን ያለው የ10 ወራት የሥራ ክንውን ሪፖርቱን ግንቦት 3 ቀን 2014 ዓ.ም. ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ፣ የፍትሕና የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበበት ወቅት።

(ዝርዝሩ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
' deferred letter of credit '

ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ የመጣውን የዋጋ ግሽበት ለማርገብና ኢኮኖሚ ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ለመቀነስ መንግሥት መሠረታዊ ፍጆታዎች በዱቤ ከውጭ እንዲገቡ መፍቀዱን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ ትናንት ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ስኳር፣ ዘይትና ስንዴን በዱቤ ወይም " ዲፈርድ ሌተር ኦፍ ክሬዲት " አሠራርን በመጠቀም ማስገባት ተፈቅዷል፡፡

ፈቃዱ የተሰጠው ለልማት ድርጅቶች ብቻ ሲሆን ባለፈው ወር 43 በመቶ የደረሰውን የምግብ ዋጋ ግሽበት ለማርገብ ይረዳል ተብሏል።

መንግሥት መሠረታዊ የፍጆታ ዕቃዎችን አቅርቦት ለመጨመር በማሰብ የፍራንኮ ቫሉታ አሠራርን ከመፍቀድ ባለፈ " ያለ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ " እንዲገቡ ፍቃድ መስጠቱ ይታወሳል፡፡

ይሁን እንጂ የተደረጉት ማስተካከያዎች ዋጋ ግሽበት ከመቀነስ አኳያ ያመጡት ለውጥ እምብዛም ነው፡፡

ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ5 ሊትር ዘይት ዋጋ ከ400 ብር በላይ ጭማሪ በማሳየት ከ1000 ብር በላይ የደረሰ ሲሆን አቅርቦቱም አነስተኛ መሆኑን ሸማቾች ያነሳሉ፡፡

በተመሳሳይ የስንዴና ስኳር አቅርቦት አነስተኛ ሲሆን በዋጋቸው ላይ ጭማሪ ታይቷል፡፡

ይህንን ችግር ለመፍታት በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ የሚመራው የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴው መሠረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች እንዲገቡ የፈቀደ ሲሆን ይህንን እንዲያከናውኑ ለጊዜው የተመረጡት የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓት ልማት ድርጅት እና የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን እንደሆኑ ጋዜጣው ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ አስነብቧል።

ሪፖርተር : https://telegra.ph/Reporter-05-11

@tikvahethiopia
#iጤና

• በስትሮክ፣ በአደጋ፣ እና በሌሎች በሽታዎች ምክንያት ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል ለተፈጠረ አለመንቀሳቀስ (Paralysis)
• እድሜ በመግፋት ለሚፈጠሩ ጉድለቶች እንደ አልዛይመርስ፤ ዲሜንሻ
• ከተለያዩ ቀዶ ጥገናዎች ለማገገም
• በሙሉ (Coma) ወይም በከፊል የንቃተ ህሊና መቀነስ ላላቸው ታካሚዎች እንክብካቤ
• ለካንሰር እና ተከታታይ የህክምና ክትትል ለሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች

👉 በ0901222233 ይደውሉልን
Telegram | FB | IG | Twitter 🌍
🏥 አድራሻችን ጀሞ ከ ጀሞ ሞል 200m ገባ ብሎ፡፡
#US

የአሜሪካው ፕሬዜዳንት በሀገራቸው ለሚታየው የዋጋ ግሽበት የሩስያን መሪ ቭላድሚር ፑቲንና የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ተጠያቂ አደረጉ።

ትላንት ጆ ባይደን ለሀገራቸው ህዝብ በሀገሪቱ የኢኮኖሚ ሁኔታ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በዚህ ማብራሪያቸው ለዋጋ ግሽበት የኮቪድ-19 ወረርሽኝንና ሩስያን ተጠያቂ አድርገዋል።

"ዛሬ እያየን ያለነው የዋጋ ንረት ሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች አሉ" ያሉት ባይደን አንደኛው አስከፊው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መሆኑን አስተዋል።

ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ "ፑቲን በዩክሬን ላይ የከፈተው ጦርነት ነው" ሲሉ ተደምጠዋል፤ ባይደን በመጋቢት ወር ከተመዘገበው የዋጋ ግሽበት 60% የሚሆነው ከነዳጅ የዋጋ ጭማሪ ጋር በተያያዘ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ባይደን ዩክሬንና ሩስያ በስንዴና በቆሎ ምርታቸው ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚይዙ በማስረዳት "የፑቲን ጦርነት የምግብ ዋጋ እንዲጨምር አድርጓል" ሲሉ የሩስያውን መሪያ ተጠያቂ አድርገዋል።

ከሪፖርተሮች በአሜሪካ ለሚታየው የዋጋ ግሽበት አስተዳደራቸው ኃላፊነት ይወስድ እንደሆነ ሲጠየቁ "ፖሊሲዎቻችን የሚያግዙ እንጂ የሚጎዱ አይመስለኝም" ሲሉ መልሰዋል።

ባይደን በሀገራቸው የሚታየው የዋጋ ግሽበት ሊፍታ የሚገበው ከፍተኛ ችግር መሆኑን በማንሳት ችግሩን ለመፍታት ልዩ ትኩረት አድርገው እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

ፕሬዜዳንቱ በትላንት ማብራሪያቸው "በእርግጥ የተወሳሰበ ነው። የአሜሪካ ዜጎች ሊረዱት እንደማይችሉ ግን እየጠቆምኩ አይደለም። እነሱ ይረዱታል፤ ጠረጴዛቸው ላይ ምግብ እንዲኖር ለማድረግ በቀን 8፣ 10 ሰዓታት እየሰሩ ነው" ብለዋል።

መቼ የምርቶች ዋጋ ይቀንሳል ለሚለው ባይደን ለመተንበይ ፍቃደኛ ሳይሆኑ የቀሩ ሲሆን የዋጋ ግሽበቱን ለመቆጣጠር ምን መስራት እንዳለብን እናውቃለን ብለዋል telegra.ph/US-05-11-2

@tikvahethiopia
#የትምህርትና_ስልጠና_ባለሥልጣን

ከባድ የመመሪያ ጥሰት ፈጽመው በተገኙ 24 የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰዱን የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አሳውቋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር በሚገኙ 108 የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና 147 ካምፓሶቻቸው ላይ ሚያዚያ 10 እና 11/2014 ዓ.ም ድንገተኛ ፍተሻ ማካሄዱን ባለስልጣኑ ገልጿል።

በዚህም ከባድ የመመሪያ ጥሰት ፈጽመው በተገኙ 24 የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ካምፓሶች ላይ የፕሮግራም፣ የካምፓስ እና የተቋም መዝጋት እርምጃ ተወስዷል፡፡

በተጨማሪም በ82 የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ቀላል የማስጠንቀቂያ እርምጃ መስጠቱን ባለስልጣኑ ገልጿል።

ተቋማቱ በቀጣይ የተገኝባቸው ክፍተቶች በማስተካከል በአስር የሥራ ቀናት ውስጥ ለባለሥልጣኑ ሪፖርት እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ተሰጥቷቸዋል፡፡

(የፕሮግራም፣ የካምፓስ እና የተቋም መዝጋት እርምጃ የተወሰደባቸው 24 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

እስካሁን ድረስ #አስተማማኝ የሆነና #ዘላቂ መፍትሄ ያልተገኘለት የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ዳግም ሌላ የከፋ እልቂት እንዳያስከትል ከፍተኛ ስጋትን ደቅኗል።

ከጥቂት ወራት በፊት ተደርሶ የነበረው ለሰብዓዊነት ግጭት የማቆም ውሳኔ መላ ህዝብ በተስፋ ሲጠብቅ የነበረውን ጥቂት የሰላም ጭላንጭል አሁን እየታየ ያለው የዳግም ጦርነትና ግጭት ሁኔታ የታየውን ተስፋ እንዳያጨልመው ስጋት ደቅኗል።

በእርግጥ ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት የማቆም ውሳኔ ተብሎ በታወጀበት ወቅት እንኳን በየአቅጣጫው ያሉትና ለዚህ ወገን እንወግናለን የሚሉ ሚዲያዎች ፣ አክቲቪስቶች፣ ፖለቲከኞች የጦርነት እና ግጭት ቅስቀሳዎች፣ ጥላቻንና የሰዎችን አእምሮ ለዳግም ጦርነት የማዘጋጀት ድርጊትና እቅስቀሳ አላቆሙም ነበር።

እስካሁን ባለው ጊዜ አቀራራቢ እና ሰላም ላይ ትኩረት ያደረጉ ስራዎች በአግባቡ አልተሰሩም ፤ ግጭት ቆመ ይባል እንጂ በተለይ በሚዲያ የሚሰራው ስራ ሰዎች ከጦርነት ስነልቦና እንዳይወጡ የሚያደርግ ነበር።

በተለያዩ አካላት እየተሞከሩ ነው ስለሚባሉት የሰላም ጥረቶች መላው ህዝብ ይሄ ነው የሚባል ዝርዝር መረጃ የለውም ፤ ይህንን ጥረት የሚያደርጉ አካላትም ለስራው እንቅፋት እንዳይሆነ መረጃውን ለመስጠት ባለመፈለጋቸው ከኃላ ለሰላም እና ችግርን በዘላቂነት ለመፍታት ስለሚደረገው ጥረት እና እንቅፋት ስለሆኑ ጉዳዮች በትክክል ማወቅም አልተቻለም።

ከሰሞኑ ግን ከፍተኛ የጦርነት ዝግጅቶችና ቅስቀሳዎች ፣ የሚዲያ ዘመቻዎች ከየአቅጣጫው ተጧጡፈው በመቀጠለቸው ለሰላም የነበረውን ተስፋ ዳግም እያደበዘዘው ይገኛል።

ሌላው በትግራይ ክልል ላለው በብዙ ሚሊዮን እርዳታ ጠባቂ ግጭት የማቆም ውሳኔ ከተደረሰ በኃላ በየቀኑ መግባት የነበረበት 100 ተሽከርካሪ ለምን እየገባ እንዳልሆነ ለዚህ ደግሞ ማን ? ምን ? እንቅፋት እንደሆነ በግልፅ የሚያብራራ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ድጋፍ አድራጊ ድርጅትም ብቅ አላለም።

የሆነው ሆኖ ግን አሁን ላይ በየአቅጣጫው የሚታየው የግጭት እና የጦርነት ቅስቀሳ ፣ ጥላቻን የመዝራት ዘመቻ ዳግም የከፋ እልቂት እንዳይመጣ የሚያሰጋ ሲሆን፤ ከግጭት እና ጦርነት ቀጠና ራቅ ያሉ አካላት ገና ከወዲሁ በሁኔታው የዩትዩብ ገንዘብ መሰብሰቢያ ፣ የፖለቲካ ትርፍ ማግኛ ማድረግ ጀምረዋል።

ከዚህ በፊት በነበረ ጦርነት ሳቢያ እጅግ የተዳከመው ኢኮኖሚ፤ አሁን በሩስያና ዩክሬን ጦርነት ምክንያት በዓለም ያለው ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚያዊ መናጋት በሀገር ውስጥ ዳግም ጦርነት ተደርጎ ኢኮኖሚው እንዳያንሰራራ ሆኖ እንዳይወድቅ ያስፈራል ፤ ይህ ደግሞ ይዞት የሚመጣው መዘዝ እጅግ የከፋ ነው።

@tikvahethiopia
#Google

ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጉግል #አፋን_ኦሮሞ እና #ትግርኛ ጨምሮ ከ300 ሚሊዮን በላይ የሚናገራቸውን 24 አዳዲስ ቋንቋዎች በጉግል መተርጎሚያ ዝርዝሩ ውስጥ አካቷቸዋል።

ከእነዚህ ውስጥ አስሩ ቋንቋዎች በአፍሪካ የሚነገሩ ሲሆን ከነዚህም መካከል አፋን ኦሮሞ ፣ ትግርኛ፣ ትዊ፣ ባምባራ፣ ክሪዎ፣ ሉጋንዳ ይገኙበታል።

በኢትዮጵያ እና በኬንያ ወደ 37 ሚሊዮን የሚጠጉ ነዋሪዎች አፋን ኦሮሞ የሚናገሩ ሲሆን ከ8 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የኤርትራና የትግራይ ተወላጆች ትግርኛን ይናገራሉ።

" ለዓመታት ጉግል መተርጎሚያ የቋንቋ ልዩነቶችን በማጥበብ በመላው ዓለም የሚገኙ ማህበረሰቦችን ለማገናኘት ረድቷል " ሲል የአሜሪካው ኩባንያ ገልጿል።

አክሎም አሁን ቋንቋቸው በአብዛኛው ቴክኖሎጂ ውክልና ያልተሰጣቸው ሰዎችን መርዳት ይፈልጋል ብሏል።

አሁን የተካተቱትን ቋንቋዎች ጨምሮ በጉግል ተርጓሚ የተካተቱ አጠቃላይ ቋንቋዎች ብዛት ወደ 133 ደርሷል።

አዲሶቹ የተካተቱት ቋንቋዎች የቴክኖሎጂ ምዕራፍን እንደሚወክሉ ገልጾም ምሳሌ ሳይኖር የሚተረጉም የማሽን መማሪያ ሞዴል እንደሚጠቀሙ አስፍሯል።

ይህ ኮምፒውተርን ለማሰልጠንና ትርጉሞቹን በማሰባሰብ የመረጃ ቋቱን ለማካበት የሚያገለግሉ በርካታ ሰዎች ለሌሏቸው ቋንቋዎች ጠቃሚ ሊሆን ይችላል ብሏል።

ነገር ግን ኩባንያው ቴክኖሎጂው ፍጹም እንዳልሆነ አምኗል።

https://telegra.ph/Google-05-12-3

#BBC/#Google

@tikvahethiopia
" በቦምባስ ከተማ በአኪሾ ጎሳ አባላት ባሕላዊ ሥነ ሥርዓት ላይ በክልሉ መንግሥት የፀጥታ አካላት የተወሰደ መጠን ያለፈ የኃይል አጠቃቀም ለሞትና የአካል ጉዳት ምክንያት ሆኗል " - ኢሰመኮ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በሶማሌ ክልል ፋፈን ዞን ጉርሱም ወረዳ ቦምባስ ከተማ መጋቢት 11 እና 12 ቀን 2014 ዓ.ም. በባሕላዊ ሥነ ሥርዓት የጎሳ መሪ (ሱልጣን) ለመምረጥ በተሰበሰቡ ሰዎች ላይ ግድያ እና የአካል ጉዳት ስለመፈጸሙ በደረሰው ጥቆማ መነሻነት ከሚያዝያ 7 እስከ 12 ቀን 2014 ዓ.ም. በቦታው በመገኘት  ምርመራ አድርጓል።

በዚህ መሰረት በአጠቃላይ በ2ቱ ቀናት በክልሉ ፀጥታ ኃይሎች እና በታጠቁ ግለሰቦች በተፈጸሙ ጥቃቶች 11 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን፣  ይኸውም  በታጠቁ ሰዎች የተፈጸመ ግድያ እና በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ከመጠን ያለፈ የኃይል አጠቃቀም (excessive use of lethal force) የደረሰ የሕይወት መጥፋት መሆኑን፤ በተጨማሪም ቢያንስ በ33 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ኮሚሽኑ በምክንያታዊ ሁኔታ አሳማኝ (reasonable ground to believe) ሆኖ እንዳገኘድ ገልጿል።

ኮሚሽኑ ምርመራውን ለማከናወን የአይን ምስክሮችን ፣ ተጎጂዎችን ፣ የተጎጂ ቤተሰቦችን እና የሀገር ሽማግሌዎችን በግል እና በቡድን በማነጋገር፣ ከሆስፒታል ምንጮች መረጃ በማሰባሰብ እንዲሁም ስለጉዳዩ ማብራሪያና ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ የሆኑ የክልሉ ኃላፊዎችን በማነጋገር ነው ምርመራውን ማካሄዱን የገለፀው።

ኢሰመኮ የክልሉ መንግሥት ለሟች ቤተሰቦች እና የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች ካሳ የከፈለ እንደሆነ የገለፀ ሲሆን ለተሟላ ፍትሕ የወንጀል ተጠያቂነት ሊረጋገጥ ይገባል ብሏል።

(ዝርዝሩን ከላይ ያንብቡ)

@tikvahethiopia