TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ተጠርጣሪዎቹ ፍርድ ቤት ቀርበዋል‼️

በሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል #ተጠርጥረው ዛሬ በፌዴራሉ ፍርድ ቤት ቀርበው የነበሩት 34 ሰዎች ለነገ ተቀጠሩ።

በጎሃ አጽብሃ መዝገብ የተካተቱ ተጠርጣሪዎች ናቸው ዛሬ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው ጉዳያቸው ለነገ የተቀጠረው።

ፍርድ ቤቱ በዛሬው ውሎው ፖሊስ በተጠርጣሪዎቹ ላይ አቅርቦት የነበረውን አዳምጦ ከቀረቡት 36 ተጠርጣሪዎች መካከል ሁለቱ በዋስ እንዲወጡ ፈቅዷል።

16ቱ ተጠርጣሪዎች መንግስት ጠበቃ እንዲያቆምላቸው የፈቀደው ፍርድ ቤቱ ፖሊስ በተጠርጣሪዎች ላይ ተጨማሪ ምርመራ ለማድረግ የጠየቀውን የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ለመፍቀድ ለነገ ለነገ ቀጥሯል።

ተጠርጣሪዎቹ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ የማረሚያ ቤትና የፖሊስ አባልና ሃላፊ ሆነው ባገለገሉበት ወቅት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጽመዋል በሚል ተጠርጥረዋል።

ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ እንዳስረዳው ተጠርጣሪዎቹ በሽብር የተፈረጁ ግለሰቦችን በማፈን፣ ስውር እስር ቤት አስገብቶ ኢሰብአዊ የሆነ ድርጊት እንዲፈጸምባቸው ማድረጋቸውን ለፍርድ ቤቱ ገልጿል።

በጳጉሜ 2006 ዓ.ም የኢትዮጵያና ናይጄሪያ እግር ኳስ ቡድን ጨዋታ ባደረጉበት ዕለት ቦንብ አፈንድተዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎችን በማሰቃየትና የአንድ ሰው ህይወት እንዲያልፍ ማድረግና ሌሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸማቸውን ፖሊስ ለፍርድ ቤት አስረድቷል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሻለቃ መስፍን በቁጥጥር ስር ዋሉ‼️

የብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ህብረት ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ የቀድሞ ምክትል ስራ አስኪያጅ ሻለቃ #መስፍን_ስዩም በሙስና ወንጀል #ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ሻለቃ መስፍንን ፖሊስ ትላንት ፍርድ ቤት ይዟቸው ቀርቦ የነበረ ቢሆንም ተጠርጣሪው የተያዙበትን ምክንያት እንደማያውቁ ለፍርድ ቤቱ በመግለጻቸው የተጠረጠሩበትን ወንጀል በመርማሪ ፖሊስ ተነግሯቸው ለሰኞ ታህሳስ 8 ቀን 2011 እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

ፖሊስ እንደገለጸው ሻለቃ መስፍን በ7 ሚሊዮን 952 ሺህ 767 ብር የመንግስት ሃብት እንዲባክን በማድረግ ወንጀል ተጠርጥረዋል።

”በተጨማሪም በመጣራት ላይ ያለ 481 ሺህ ብር በላይ ሃብት እንዲባክን አድርገዋል” ተብሏል።

ምንጭ፦ ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በተለያዩ ወንጀል #ተጠርጥረው በህግ ቁጥጥር ስር ለዋሉና ሲፈለጉ ለነበሩ 4 ሺህ 382 ግለሰቦች #የምህረት የምስክር ወረቀት መሰጠቱን የአማራ ክልል ጠቅላይ አቃቢ ህግ መስሪያ ቤት ገልጿል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በምዕራብ ኦሮሚያ በነበረው #ሁከት ተሳትፈዋል የተባሉ የመንግስት አመራሮች እየተመረመሩ ነው!
.
.
.
በምዕራብ ኦሮሚያ ዞኖች ባለፉት ወራት በነበረው የፀጥታ ቀውስ ሀላፊነታቸውን አልተወጡም ተሳትፎም አድርገዋል ተብለው የተጠረጠሩ አንድ መቶ ያህል የክልሉ አመራሮችና የፀጥታ አካላት ላይ ምርመራ እየተካሄደ ሲሆን ስምንት መቶ የሚጠጉ ፖሊሶችም ስልጠና እንዲወስዱ እየተደረገ ነው።

ባለፉት ወራት የምዕራብ ወለጋ፣ ምስራቅ ወለጋ ፤ ሆሮ ጉዱሩ እና ቄለም አካባቢዎች በኦሮሞ ነፃነት ግንባር ታጣቂዎችና በመንግስት የፀጥታ ሀይሎች መካከል ከፍተኛ ግጭት እንደነበረ ይታወሳል። በዚህ ግጭት ደግሞ የዞኑ አመራሮችን ከመግደል እስከ ባንኮች ዘረፋ የሚደርስ ሰፊ ወንጀል መፈጸሙ በክልሉ መንግስት መግለጫ የተሰጠበት እንደነበርም አይዘነጋም፡፡በተለይ አባቶርቤ ተብሎ የሚጠረ ህቡዕ ቡድን የተለያዩ ግለሰቦችን በመግደል ድርጊት ተሰማርቶ እንደነበርም መንግስት ራሱ ይፋ አድርጓል።

አሁን አካባቢው ላይ በኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) እና በኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) መካከል የተፈጸመውን እርቅ ተከትሎ አንጻራዊ ሰላም የወረደ መስሏል፡፡ ሁለቱን ወገኖች በማሸማገል ስራ ላይ የነበሩት አባ ገዳዎች እና ሃደ ሲንቄዎችም( እናቶች) ውጥረት እና ግጭት ሲንጣቸው በነበሩ ዞኖች ተንቀሳቅሰው ባሳለፍነው ሳምንት ሁኔታውን መቃኘታቸው ይታወቃል፡፡ ታጥቀው የነበሩ የኦነግ አባላትንም ትጥቅ በማስፈታት ወደተዘጋጀላቸው ካምፕ እንዲገቡ እየተደረገ ነው። ከሁሉም በላይ ግን የጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ እና የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ #ለማ_መገርሳ አካባቢው ድረስ በመጓዝ ያደረጉት ጉብኝት እና ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር የነበራቸው ውይይት ይበልጥ በስፍራው የሰላም አየር መንፈስ መጀመሩን ለማመላከት የታሰበ ይመስላል፡፡

አሁን ይህ ውጤት ይገኝ እንጂ ለወራት የተስተዋለውን ግጭት ያባባሰው እና ለቁጥጥር አዳጋች ያደረገው ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ የክልሉ የጸጥታ አካላት #በሁከቱ መሳተፋቸው መሆኑን ዋዜማ ሬድዮ መረጃ አግኝቻለሁ ብሏል፡፡ በተለይ አባቶርቤ ተብሎ ሲንቀሳቀስ በነበረው የህቡዕ ቡድን ውስጥም ሆነ አከባቢው ላይ በነበረው ሁከት የቀጥታ ተሳትፎ ነበራቸው ተብለው የተጠረጠሩ ከ800 በላይ የኦሮሚያ ክልል የፖሊስ አባላት በአሁኑ ወቅት አምቦ በሚገኘው ሰንቀሌ ወታደራዊ ማሰልጠኛ የተሃድሶ ስልጠና እየተሰጣቸው እንደሚገኝም ጭምር ነው ራድዮ ጣቢያው አረጋግጫለሁ ብሎ የዘገበው፡፡

ዋዜማ ራድዮ ከምንጮቼ ሰማሁ እንዳለው ይበልጥ #ሁከቱን_በመምራት በማደራጀትና በማስተባበር #አባቶርቤ በተሰኘው ቡድን ውስጥም በቀጥታ በመሳተፍ ደግሞ በ100 ግለሰቦች ላይ ምርመራ እየተካሄደባቸው ይገኛል፡፡ ከነዚህ መካከልም #የዞን_አመራሮች እና #በፖሊስ_አመራርነት ደረጃ የሚገኙ መኖራቸው ጭምርም ታውቋል፡፡

አካባቢውን ያረጋጋሉ ተብለው ከአዲስ አበባ የተላኩት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አመራርም #ተጠርጥረው በምርመራ ላይ ናቸው፡፡

ምንጭ፦ ዋዜማ ራዲዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተጠርጣሪዎቹ በዋስ እዲወጡ ተፈቀደ‼️

ፍርድ ቤቱ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በፈጸሙ ተጠርጣሪዎች ላይ በምስክርነት የቀረቡ ግለሰቦችን ፎቶ በማንሳት በማህበራዊ ድረ ገጽ ሲለጥፉ በቁጥጥር ስር ውለዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች የጠየቁትን የዋስትና ጥያቄ ተቀበለ። ተጠርጣሪዎቹ ሃጎስ ግርማይ እና ተወልደ ውበት የተባሉ ግለሰቦች ሲሆኑ፥ በፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ወንጀል ችሎት ለሁለተኛ ጊዜ ቀርበዋል።

መርማሪ ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል ፈጽመዋል ተብለው በምርመራ ላይ በሚገኙ ግለሰቦች ላይ ምስክርነት በመስጠት ፍርድ ቤት ቅድመ ምርመራ ላይ እያሉ፥ ፎቷቸውን በማንሳት በማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ በመለጠፍ መጠርጠራቸውን ተከትሎ ሲያደርግ የቆየውን ምርመራ ማጠናቀቁን እና የምርመራ መዝገቡን ለአቃቤ ህግ ማስረከቡን ለችሎቱ ገልጿል።

ተጠርጣሪዎቹ በበኩላቸው ፍርድ ቤቱ ዋስትና እንዲፈቅድላቸው አመልክተዋል። ፍርድ ቤቱም የተጠርጣሪዎቹን የዋስትና ጥያቄ በመቀበል በሁለት ሺህ ብር ዋስ እንዲወጡ ፈቅዷል።

በሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል #ተጠርጥረው በምርመራ ላይ ከሚገኙትና ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ተጠርጣሪዎች ውጭ፥ ከ16 በላይ መርማሪ ፖሊሶችና የማረሚያ ቤት አስተዳደር ሰራተኞች #የመብት_ጥሰት ወንጀል ተጠርጣሪ ግለሰቦች ላይ ክስ መመስረቱ ይታወሳል።

Via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከንቲባው እየተፈለጉ ነው...

የብቸና ከተማ ከንቲባ #ከሰሞኑን ከተፈጠረው ግጭት ጋር ተያይዞ #ተጠርጥረው እየተፈለጉ ሲሆን እስካሁን በቁጥጥር ሥር አልዋሉም። እስካሁን ምክትል ከንቲባው፣ የንግድ፣ የገቢዎች፣ የሲቪል ሰርቪስ፣ የቅሬታ ሰሚ፣ የማዘጋጃ ቤትና የገንዘብና ኢኮኖሚ ጽሕፈት ኃላፊዎችና አፈ-ጉባኤ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia