TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#BALE "የባሌ ጊነር መንገዶች ተዘግተዋል። የከተማይቱ ወጣቶች ሰላማዊ ሰልፍ እያደረጉ ይገኛሉ።" መሃመድ/Tikvah Family/
@tsegabwolde @tikbahethiopia
#ADAMA #JIMMA #BALE_ROBE

ከተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ዛሬ በአዳማ ከተማ የሰላም ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው። በኮንፈረንሱ ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳና ከተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡

በተመሳሳይም በደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ ካሉ ዞኖችና ከተሞች የተውጣጡ ነዋሪዎች ተሳታፊ የሆኑበት የሰላም ኮንፈረንስ በጅማ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው። በሰላም ኮንፈረንሱ ላይ ከጅማ፣ ቡኖ በደሌ፣ ኢሉ አባቦር ዞን፣ ባሌ ሮቤ እና ከጅማ ከተማ የተውጣጡ ከ1 ሺህ 600 የሚልቁ ነዋሪዎች ከክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር በመምከር ላይ ናቸው። በውይይቱ ላይ የኦዲፒ ማዕከላዊ ኮሚቴ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ እንዳሉት፥ በጥፋት ድርጊቶች ውስጥ የተሳተፉ አካላትን ለህግ በማቅረብ የህግ የበላይነት ይረጋገጣል።

ባሌ ሮቤ ላይ በተደረገው ውይይት የተገኙት የገቢዎች ሚኒስትሯ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው ሰሞኑን የተፈጸመው ድርጊት ህብረተሰቡን እንደማይወክል ተናግረዋል። አያይዘውም እንደዚህ አይነት ዋጋ መክፈል እንደማያስፈልግ ጠቅሰው፥ ችግሮች ሲከሰቱ መመካከርና መደማመጥ አስፈላጊ ነው ብለዋል። ውይይቱ በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የታየውን የሰላም እጦት ችግር ከመሰረቱ ይፈታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከኦሮሚያ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Bale📍

የረመዷን ፆም ባለፈው ቅዳሜ ተጀምሯል። ይህን ታላቅ ወር ህዝበ ሙስሊሙ በጾም በዱአ እያሳለፈ ይገኛል።

በባሌ ዞን በድርቅ ውስጥ ያሉ የማኅበረሰብ ክፍሎች ግን " የሚጠጣ ና የሚበላ ስላሌለን ለዘንድሮ ለረመዳን ፆም ሰግተናል " ሲሉ ያለውን ችግር ያስረዳሉ።

የራይቱ ገልቢ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት ሀጂ አሊዪ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ በሰጡት ቃል ፥ "እንደዚህ ዓይነት ሁኔታ አይተን አናውቅም። ባሌ የጥጋብ ሀገር ፣ ሌሎችን የምትቀልብ ሀገር ነበረች። አሁን የሚበላ እና የሚጠጣ የለንም። ድጋፍ የማይደርስልን ከሆነ ለመፆም እንቸገራለን" ብለዋል።

አባታችን ሃጂ አሊዪ የረመዳን ወር ውስጥ እንደዚህ አይነት ችግር ገጥሞን አያውቅም ያሉ ሲሆን "የኛ ህዝብ ረመዳንን በደስታ ለመቀበል ይጠብቁ ነበር፣ አሁን ግን በስጋት የተሞላ ነው" ብለዋል።

ሌላኛው የዚሁ አከባቢ ነዋሪ የሆኑት አቶ አብዱራህማን ሃጅ አሊዪ፥ "ፈጣሪ በተዓምራቱ መፍትሔ ከበጀልን እንጂ፣ በዚህ እጥረት ውስጥ ሆነን እንፆማለን ለማለት እንደ ራይቱ ይከብዳል" ሲሉ ያስረዳሉ።

በደርቅ በተጎዳችው በባሌ ዞን በምትገኘው የራይቱ ወረዳ ወደ 60 ሺ ከሚገመቱ ከብቶች ከግማሽ በላይ እንዳለቁ እና ሌላው ደግሞ መሰደዱን ከዞኑ አስተዳደር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

በአጠቃላይ ድርቁ በተከሰተባቸው የኦሮሚያ አከባቢዎች እስካሁን 800 ሺ የሚጠጉ ከብቶች የሞቱ ሲሆን 300 ሺ የሚሆኑ ከብቶች ደግሞ መድከማቸውን የቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ ኃላፊ አቶ ሙስጠፋ ከድር ተናግረዌ።

ሀጂ አሊዪ ከሰሞኑ የተወሰነ ዝናብ መዝነቡን ጠቁመው ዝናቡ ቀጥሎ ቢዘንብ የምንዘራው ዘር ፣ የምናርስበት ከብት ፤ የምንቆፍርበት ጉልበት የለንም ሲሉ የሚመለከተው አካል እንዲተባበራቸው ጠይቀዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/BALE-04-05

@tikvahethiopia