TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
የእስራኤልና ፍልስጤሙ ሃማስ ጦርነት በቀጣይ ምን ይዞ ይመጣ ይሆን ?

ዋና ነጥቦች ፦

▪️ሃማስ ፤ " ወራሪ " ናት በሚላት #እስራኤል ላይ  ወታደራዊ ኦፕሬሽን ማካሄድ መጀመሩንይህ ኦፕሬሽንም #ፍልስጤማውያን ባለፉት አስርት ዓመታት ውስጥ ለደረሰባቸው ግፍ ሁሉ ምላሽ እንደሆነ ገልጿል።

▪️ እስራኤል ፤ " አሸባሪ " የምትለው የሃማስ ቡድን ጥቃት መክፈቱ ከባድ ስህተት መሆኑን በመግለፅ ለእያንዳንዱ ድርጊቱ የከፋ ዋጋ እንደሚከፍልበት ፤ ለሚመጣው ነገር  ሁሉ ኃላፊነቱን እንደሚወስድ ገልጻለች። ሃማስ ላይም መጠነ ሰፊ የአፀፋ እርምጃ ጀምራለች።

▪️እስካሁን ከእስራኤል ከ700 በላይ ከፍልስጤም ከ400 በላይ ሰዎች አልቀዋል።

በእስራኤል እና ሃማስ ጦርነት ሀገራት እና መሪዎች አቋማቸውን እያንፀባረቁ ናቸው።

አንዳንዶቹ በግልፅ ሃማስን " የሽብር ቡድን " እንደሆነ ገልፀው ጥቃቱን ሲያወግዙ አንዳንዶቹ ደግሞ በሁለቱም በኩል ግጭት ቆመ በእርጋታ ነገሮች እንዲፈቱ እየጠየቁ ነው።

እስራኤል አጋሮቿ ሁሉ የተከፈተባትን ጥቃት በግልፅ እንዲያወግዙ ትሻለች።

በወታደራዊና ኢኮኖሚ አቅማቸው ጠንካራ የሆነ የዓለም ሀገራት ምን አቋም ነው የያዙት ?

🇺🇸አሜሪካ - የእስራኤል ወዳጇ #አሜሪካ የ ' ሃማስን ' ጥቃት የአሸባሪዎች ጥቃት ነው በማለት በግልፅ ጥቃቱን አውግዛ ለእስራኤል ሁሉን አቀፍ ድጋፍ አደርጋለሁ ብላለች። ወታደራዊ ድጋፍም ልካለች።

🇫🇷ፈረንሳይ - የሃማስን ጥቃት " የአሸባሪዎች ጥቃት " ስትል ገልጻ ከእስራኤል ጎን እንዳሆነች ገልጻለች።

🇩🇪ጀርመን -ጥቃቱን አውግዛ ከእስራኤል ጎን መሆኗን ገልጻለች። ሃማስንም አሸባሪ ስትል ጠርታለች።

🇮🇳ሕንድ-እስራኤል የተፈፀመባት ጥቃት የአሸባሪዎች ጥቃት ነው ብላ ከእስራኤል ጎን መሆኗን ገልጻለች።

🇬🇧ዩናይትድ ኪንግደም - በእስራኤል ላይ " የሽብር " ጥቃት መፈፀሙን ገልጻ ሀገሪቱ እራሷን የመከላከል መብት አላት ብላለች። ከእስራኤል ጎን እንደሆነችም ገልጻለች።

_

🇮🇷ኢራን - " የፍልስጤም ህዝብ #ራሱን_የመከላከል መብት አለው " ብላ የሃማስን ጥቃት በግልፅ " አኩሪ ተግባር " ስትል አወድሳለች።  " ፍልስጤም እና እየሩሳሌም " ነፃ እስኪወጡ ከፍልሥጤም ተዋጊዎች ጎን እንቆማለን ብላለች።
_

🇨🇳ቻይና- ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት እንዲረጋጉ ፤ ራሳቸውን እንዲቆጣጠሩ እና ጦርነቱን በአስቸኳይ እንዲያቆሙ እንዲሁም ሲቪሎች እንዲጠበቁ ፤ የሁኔታውን እንዳይባባስም እንዲሰሩ አሳስባለች።

ቤጂንግ የሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ የቻይና አቋምን በተመለከተ እስራኤል ሃማስ ላደረሰው ጥቃት ከቻይና ጠንካራ ውግዘት ጠብቃ ነበር ብሏል።

ቻይና የሃማስ ታጣቂ ኃይልን እንደ አሸባሪ ድርጅት ሳይሆን እንደተቃዋሚ ኃይል ነው የምታየው።

🇸🇦 ሳዑዲ አረቢያ - ሀገሪቱ በቅርቡ ከእስራኤል ጋር ያላትን ግንኙነት ለማደስ እየተንቀሳቀሰች ሲሆን አሁን የተቀሰቀሰው ጦርነት በአስቸኳይ እንዲቆም ጥሪ አቅርባለች። ሁለቱም ወገኖች ግጭት እንዲያቆሙና ሲቪሎችም እንዲጠበቁ አሳስባለች።

🇦🇪የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ (UAE) - ያለው ሁኔታ እጅግ እንዳሳሰባት በመግለፅ ግጭት እንዲቆም እና ሲቪሎች እንዲጠበቁ ስትል ጥሪ አቅርባለች።

🇹🇷ቱርክ - በእስራኤልና ፍልስጤም ሃይሎች መካከል የሚካሄደውን ጦርነት ለማረጋጋት ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እንደምታደርግ አቋሟን ገልጻለች። ለሁለቱ ሀገራት መፍትሄ ቀጣናዊ ሰላም ማስፈን ብቸኛ መንገድ ነው ብላለች። አሁን ላይ ያለው ከፍተኛ ውጥረት እንዲረግብ እንደምትሰራ ነው የገለፀችው።

🇷🇺 ሩስያ - ሩስያ በአቸኳይ #ተኩስ_እንዲቆም ጥሪ አቅርባለች።

_

አፍሪካውያን ምን አሉ ?

- የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር የሆኑት ሙሣ ፋኪ ማሃማት " የእሥራዔል-ፍልስጥዔም ቋሚ ውጥረት ዋናው ምክንያት የፍልስጥዔም ህዝብ መሠረታዊ መብቶቹን፣ በተለይም ነፃና ሉዓላዊ መንግሥት መነፈጉ ነው " ብለዋል። ሁለቱ ኃይሎች ግጭት አቁመው ወደ ድርድር ጠረጴዛ ይቅርቡ ብለዋል።


- የዩጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቨኒ " በእሥራዔል እና በፍልስጤም መካከል እንዳዲስ ግጭት መቀስቀሱ የሚያሳዝን ነገር ነው። ለምን ሁለቱም ወገኖች የሁለት መንግስት መፍትሄን ተግባራዊ አያደርጉም? በተለይ ደግሞ ሰላማዊ ዜጎችን እና ተዋጊ ያልሆኑ አካላት በታጣቂዎች ዒላማ መደረጋቸው መወገዝ አለበት " ብለዋል።

- #ኬንያ በፕሬዜዳንቷ በኩል ባወጣችው መግለጫ እስራኤል ላይ የተፈፀመው የሽብር ጥቃት መሆኑን በመግለፅ ከእስራኤል ጎን እንደሆነች ገልጻለች።   በተጨማሪ ግጭቱ እንዲበርድ እና እስራኤልም ፍልስጤምም ከወታደራዊ እንቅስቃሴ እንዲቆጠቡ ብላለች።

የUN ፀጥታ ም/ቤት ስብሰባ በምን ተጠናቀቀ ?

ትላንትና ምሽት የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት በእስራኤል - ጋዛ ጦርነት በዝግ አስቸኳይ ስብሰባ ቢቀመጥም አባል ሀገራቱ መስማማት ስላልቻሉ የጋራ መግለጫቸውን ማውጣት አልቻሉም።

አሜሪካ 15ቱ የፀጥታው ምክር ቤት አባላት #ሃማስን አጥብቀው እንዲያወግዙ መጠየቋ ተሰምቷል።

የአሜሪካው ከፍተኛ ዲፕሎማት የሆኑት ሮበርት ዉድ ፤ " የሃማስን ጥቃት ያወገዙ ብዙ አገሮች አሉ። ሁሉም እንዳልሆኑ ግልፅ ነው " ያሉ ሲሆን " እኔ ምንም ሳልናገር ከመካከላቸው አንዱን ማወቅ ትችላላችሁ " ሲሉ ሩስያ ጥቃቱን ካላወገዙት ውስጥ እንደሆነች ተናግረዋል።

መረጃዎቹ ከዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን የተሰባሰቡ ናቸው።

@tikvahethiopia