TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AutismDay

" ምሉዕ ፋውንዴሽን " የኦቲዝም ቀንን ትላንት ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር አከበረ። የትላንቱ መርሐግብር '' ተለየው እንጂ አላነስኩም '' በሚል መሪ ቃል ነው የተከበረው።

በ2013 ዓ/ም የተመሰረተው የበጎ አድራጎት ማኅበሩ ፤ በኦቲዝምና ሌሎች ልዩ ፍላጎት የሚያስፈልጋቸው ልጆች፤ ታዳጊዎች እና ወላጆቻቸው ያማከለ የልህቀት ማዕከል ሲሆን በውስጡም ቤተመጻሕፍት ፣ የክህሎት ማስጨበጫ ፣ የልዩ ፍላጎት ልጆች ወላጆች ውይይት የሚያደርጉበትና ሌሎች ማኅበረሰብ ተኮር ስራዎችን የያዘ ነው።

በወ/ሮ ትዕግስት ኃይሉና አቶ ክንፈ ፅጌ የተመሰረተው ማኅበሩ የበኩር ልጃቸው በኦቲዝም ጥላ ስር የሚኖር ታዳጊ በመሆኑ በየትምህርት ቤቱ፣ በህጻናት መጫወቻ ስፍራዎች እንዲሁም በተለያዩ የህዝብ ተቋማት ላይ ያጋጠማቸውን ውጣ ውረዶች ሌሎች እንዳይጎዱበት ለማገዝ መቋቋሙን ሰምተናል።

በተጨማሪም በልጆቻቸው አካላዊ፣ አዕምሮአዊ እና ስነ-ልቦናዊ እድገት ላይ የነበረውን ውስንነት ለመቅረፍ የተጠቀሙባቸውን መንገዶች እና በዘርፉ ያካበቷቸውን ልምዶች ለሌሎች ለማጋራት በማሰብ የመኖሪያ ቤታቸውን ክፍት በማድረግ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች እንዲገለገሉበት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡

ኦቲዝም የአዕምሮ ዕድገት መዛባት መንስዔ በውል ባይታወቅም የልጆቹን ዕምቅ አቅም በመፈለግና በማውጣት የተሻለ ዜጋ እንዲሆኑ ማስቻል ይቻላል።

በአፍሪካ የኦቲዝም የአዕምሮ መዛባት ችግር ስርጭት በስፋት ባይጠናም ከሰሀራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት በዕድገት ችግር ውስጥ ካሉ ከመቶ ልጆች ውስጥ ከ 11 -33 የሚሆኑት በኦቲዝም የአዕምሮ ዕድገት መዛባት ውስጥ እንደሚኖሩ ግን አንዳንድ ጥናቶች ይጠቁማሉ።

@tikvahethiopia