TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
‹‹አማራ ክልል ውስጥ ወንጀል ሠርተው ሌላ ክልል #እንደበቃለን ብለው የሚያስቡ ካሉ #ተስፋቸውን ይቁረጡ፡፡›› የአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ #ዮሐንስ_ቧያለው
.
.
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ቧያለው በክልሉ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር እና በሰሜን ሸዋ ዞን በተከሰተው #ግጭት ዙሪያ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በግጭቱ ሕይወታቸውን ባጡ ወገኖች እና በደረሰው የንብረት ውድመት አዴፓ ማዘኑን የገለፁት አቶ ዮሐንስ ለተጎጅ ቤተሰቦችና ወገኖች #መፅናትን ተመኝተዋል፡፡

ጉዳቱ ከመድረሱ በፊት የክልሉ መንግሥት ሥጋቱን ያውቀው እንደነበር ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱም ‹‹እንደስጋት በክልሉ የፖለቲካ ኃይሎች ግጭትን ለዓላማቸው መጠቀሚያ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ግምቶች ነበሩን፤ ግን ከገመትነው #የፈጠነ ሆኖብናል›› ብለዋል። ይህን ያክል የንብረት እና የሰው ሕይወት ጠፍቷል ለማለት የቴክኒክ ቡድኑ የጥናት ምላሽ እንደሚጠበቅም ተናግረዋል፡፡

ሕዝቡ ሕግና ሰላምን በማስጠበቅ ረገድ በአዴፓ እና በክልሉ መንግሥት እምነት አጥቷል የሚሉ ሐሳቦች ይደመጣሉ በእናንተ በኩል ምን ግምገማ አለ? ተብሎ ከጋዜጠኞች ለተነሱ ጥያቄዎችም አቶ ዮሐንስ ‹‹እንዲያውም አሁን ሕዝቡ በአዴፓ ላይ ከፍተኛ #እምነት የጣለበት ወቅት ነው፤ አዴፓ በሕዝቡ አመኔታ ማግኘቱን ተከትሎ #ለመነጣጠል የሚፈልጉ ኃይሎች የፈጠሩት ሴራ በመሆኑ ሕዝቡ ከጎናችን ሊሆን ይገባል›› ብለዋል፡፡ ‹‹በተለያዩ አካባቢዎች የተፈጠሩ ግጭቶች የአዴፓ እና የአማራ ሕዝብ አንድነት የሚያስፈራቸው ኃይሎች የፈጠሩት ሴራ ነው›› በማለትም ተናግረዋል፡፡

ሕዝቡ መራር በሆነው በዚህ ጊዜ #አብሮነቱን እንዲያጠናክር የጠየቁት አቶ ዮሐንስ ‹‹አማራ ክልል ውስጥ ወንጀል ሠርተው በሌላ ክልል እንደበቃለን ብለው የሚያስቡ ካሉ ተስፋቸውን ይቁረጡ፤ ከአጐራበች ክልሎች እስከ ፌዴራል መንግሥት ድረስ ወንጀለኞችን ለመያዝ በጥምረት እየሠራን ነው›› ብለዋል፡፡ በክልሉ መሠል ችግር እንዳይከሰት ብቁ ዝግጅት እንደተደረም ተናግረዋል፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia