TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ መንግስት እርዳታ ወደ' ትግራይ ክልል' እንዲገባ የህወሓት ታጣቂዎች የያዟቸውን የአፋር ክልል አካባቢዎች ለቀው ሊወጡ ይገባል ሲል አስገነዘበ። መንግስት ለሰብዓዊነት ሲባል መንግስት ግጭት የማቆም ውሳኔ ማሳለፉ ከትግራይ ክልል በኩልም በጎ ምላሽ መሰጠቱ ይታወሳል። ነገር ግን ውሳኔ ከተላላለፈበት ቀን አንስቶ እስከ ዛሬ ምንም አይነት ሰብዓዊ እርዳታ ወደ ትግራይ ክልል ሊገባ እንዳልቻለ…
" አፋር ውስጥ ጦርነቱ ቀጥሎ በሌላው የኢትዮጵያ ክፍል ሰላም ሊኖር አይችልም " - አቶ ሰዒድ ሙሳ ኢብራሒም (የኤሬብቲ ጎሣ መሪ)

አፋር ክልል ውስጥ የቀጠለው ጦርነት " ለሰብዓዊነት ሲባል በታወጀው ግጭት ማቆም ውሳኔ " ላይ አደጋ መደቀኑን ዲፕሎማቶች ተናግረዋል።

ሮይተርስ ፤ አፋር ውስጥ ጦርነቱ መቀጠሉን 2 የሰብአዊ ርዳታ ሠራተኞች እንዳረጋገጡለት አስነብቧል።

በአፋር 6 ወረዳዎች በትግራይ ኃይሎች መያዛቸውን ዘገባው ገልጿል።

የአፋር ኤሬብቲ ጎሣ መሪ አቶ ሰዒድ ሙሳ ኢብራሒም ለሮይተርስ በሰጡት ቃል፥ " አፋር ውስጥ ጦርነቱ ቀጥሎ በሌላው የኢትዮጵያ ክፍል ሰላም ሊኖር አይችልም " ሲሉ ተናግረዋል።

የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር አህመድ ሃሪፍ ፤ በትግራይ ኃይሎች ተይዘዋል ካሉት 6 ወረዳዎች 2ቱ ውስጥ ጦርነቱ መቀጠሉን፤ በክልሉ መዳረሻ ላይም በከፍተኛ ሁኔታ የትግራይ ኃይሎች እየተበራከቱ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የህወሓት ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ በሰጡት ቃል በተጠቀሱት አካባቢዎች ውጊያ የለም ሲሉ አስተባብለዋል።

በአፋር ክልል አቅራቢያ ተዋጊዎቻቸውን እያሰፈሩ ነው ስለመባሉ ግን ማስተባበያ አልሰጡም ሲል ሮይተርስ ገልጿል። (Reuters.com / Deutsche Welle)

በሌላ መረጃ በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ የአሜሪካ ጉዳይ አስፈፃሚ አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን ከአፋር ክልል ፕሬዜዳንት ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸው ታውቋል።

አምባሳደር ጃኮብሰን ፤ አሜሪካ በጦርነት ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል የገለፁ ሲሆን አቶ አወል አርባ ህወሓት እያደረሰ ነው ያሉትን ስቃይ የዓለም ህብረተሰብ በፅኑ ሊያወግዘው ይገባል ብለዋል።

@tikvahethiopia
#GreyImport

ውፍረትን እና ቦርጭን መቀነስ ይፈልጋሉ?
ሙሉ ከወገብ በላይ (ቦዲ) - 950ብር
የቦርጭ ብቻ -650  ብር
ቦርጭን በአጭር ጊዜ የሚቀንስ እና ማራኪ-ቁመና የሚያላብስ ።

ስልክ፦ 0913979706 ያሉበት ድረስ ከነፃ ማድረሻ ጋር!    
ተጨማሪ : የቴሌግራም አድራሻችን ይጎብኙ
( ክልል ከተሞች እንገኛለን ) @አ.አ = ቦሌ መዳሃንያለም
#AtoGelesaDilbo

በኢህአዴግ የሽግግር ወቅት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀ መንበር የነበሩትና በአሁኑ ወቅት የፓርላማ አባሉ አቶ ገላሳ ዲልቦ በድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት መለያታቸውን ቤተሰቦቻቸው ገልፀዋል።

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አንዱ መስራች የሆኑት አቶ ገላሳ ዲልቦ ባለፈው ዓመት በነበረው ምርጫ የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ጎላኦዳ ቁምቢ መልካ በሎ ወረዳዎችን በመወከል በግል ተወዳድረው በማሸነፍ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ነበሩ።

አቶ ገላሳ ዲልቦ ፤ ለረጅም ዓመታት በስደት ኑሯቸውን በለንደን አድርገው የነበሩ ሲሆን ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ በውጭ አገራት የነበሩ ተቃዋሚ ኃይሎች ጥሪ ማድረጋቸውን ተከትሎ ወደ አገር ቤት ከተመለሱ አንጋፋ ፖለቲከኞች መካከል አንዱ ነበሩ።

አቶ ገላሳ ፤ የተወለዱት ምሥራቅ ወለጋ ነቀምቴ ከተማ ሲሆን አንደኛ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እዚያው ነበር የተከታሉት።

በአውሮፓውያኑ 1974 አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የገቡ ቢሆንም የመጀመሪያ ዓመት ትምህርታቸውን ሳይጨርሱ ደርግ ሥልጣን መቆጣጠሩን ተከትሎ ለትግል ወደ ሶማሊያ መሄዳቸውን በወቅቱ ተናግረው ነበር።

ሆኖም የሶማሊያ መንግስት ወደ ሀገር ስለመለሳቸው በአገር ቤት የነበረውን የትጥቅ ትግል መቀላቀላቸውንና የትግል ሕይወታቸውም በዚያው እንደተጠነሰሰ በአንድ ወቅት ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በሽግግሩ ወቅት የኦነግ ሊቀ መንበር የነበሩት አቶ ገለሳ ፤ ከኦነግ ፓርቲ የወጡት በአውሮፓውያኑ 1998 የኦነግ መከፋፈልን ተከትሎ ሲሆን፣ "አባኦ ቃማ ጨኡምሳ" የሚባል ሌላኛውን የኦነግ ፓርቲን መስርተው በሊቀ መንበርነት ለረጅም ዓመታት ማገልግለላቸውን ቢቢሲ አስታውሷል።

አቶ ገለሳ ትላንት ለሊት በድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AtoGelesaDilbo በኢህአዴግ የሽግግር ወቅት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀ መንበር የነበሩትና በአሁኑ ወቅት የፓርላማ አባሉ አቶ ገላሳ ዲልቦ በድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት መለያታቸውን ቤተሰቦቻቸው ገልፀዋል። የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አንዱ መስራች የሆኑት አቶ ገላሳ ዲልቦ ባለፈው ዓመት በነበረው ምርጫ የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ጎላኦዳ ቁምቢ መልካ በሎ ወረዳዎችን በመወከል በግል ተወዳድረው…
#DrAbiyAhmed

የአቶ ገለሳ ዲልቦ ህልፈትን ተከትሎ የኢትዮጵያው ጠ/ሚ ሀዘናቸውን ገልፀዋል።

" አቶ ገለሳ ከተማሪዎች ንቅናቄ ጀምሮ ለኦሮሞ ሕዝብ ነጻነት እና እኩልነት ታግለዋል ያሉት " ዶ/ር ዐቢይ ፤ " በተለይ ሶማሌ በነበራቸው የትግል ቆይታ ብዙ መከራ እና ችግር እንዳሳለፉ አጫውተውኝ ነበር " ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፥ " በቅርቡ በለውጡ አመራር በተደረገላቸው ግብዣ የሰላማዊ ትግል ጉዞ መርጠው ወደ ሀገራቸው ተመልሰው በሰላማዊ መንገድ መታገል ከመጀመራቸውም ባሻገር በ2013 ምርጫ በግል ተወዳድረው የፓርላማ አባል ለመሆንም ችለዋል " ሲሉ ገልፀዋል።

" በትግል ውጣ ውረድ ውስጥ የገጠማቸውን በጎ እና ክፉ ለማሄስ እና ወጣቶች ከሁለቱም እንዲማሩ ለማድረግ ይተጉ ነበር " ያሉት ዶ/ር ዐቢይ ፤ " አቶ ገላሳ ዝምተኛ፤ አስተዋይ፤ ምክንያታዊ እና ለሰላማዊ ንግግር እጅግ የሚያመች ሰብእና የተላበሱ ግለሰብ ነበሩ ፤ ያጣናቸው ይበልጥ በሚያስፈልጉን ጊዜ ነው። " ሲሉ ገልፀዋቸዋልም

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AtoGelesaDilbo በኢህአዴግ የሽግግር ወቅት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀ መንበር የነበሩትና በአሁኑ ወቅት የፓርላማ አባሉ አቶ ገላሳ ዲልቦ በድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት መለያታቸውን ቤተሰቦቻቸው ገልፀዋል። የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አንዱ መስራች የሆኑት አቶ ገላሳ ዲልቦ ባለፈው ዓመት በነበረው ምርጫ የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ጎላኦዳ ቁምቢ መልካ በሎ ወረዳዎችን በመወከል በግል ተወዳድረው…
#Update

የአቶ ገለሳ ዲልቦ ስርዓተ ቀብር የፊታችን ቅዳሜ በቅድስት ስላሴ ካቴድራል እንደሚፈፀም የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ገለፀ።

አቶ ገላሳ ከኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባልነታቸው ባለፈ በምክር ቤቱ የኢንዱስትሪ እና ማዕድን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ም/ሰብሳቢም ነበሩ።

በአቶ ገላሳ ዲልቦ ህልፈት ሀዘኑን የገለፀው ም/ቤቱ የቀብር ስነ-ስርዓታቸው የፊታችን ቅዳሜ መጋቢት 24/ 2014 ዓ.ም በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#CHINA #USA

ቻይና ለአሜሪካ ባለስልጣት የቪዛ አገልግሎት ላለመስጠት ወሰነች።

ይህ ውሳኔ አሜሪካ ለቻይና ባለሰልጣናት ቪዛ እንደማትሰጥ ከገለፀች በኃላ በቻይና የተሰጠ ተመሳሳይ የአፀፋ ምላሽ ነው።

አሜሪካ ሰኞ ዕለት በሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ረገጣዎች ላይ እጃቸው አለበት ባለቻቸው የቻይና ባለስልጣናት ላይ ነው የቪዛ እገዳ ጥላ ነበር።

መረጃው የአል ዓይን ኒውስ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MinjarShenkora📍 በምንጃር ሸንኮራ በተፈፀመ ጥቃት የሰው ህይወት አለፈ። በወረዳው " አሞራ ቤት ቀበሌ " ላይ ታጣቂዎች ፈፀሙት በተባለው ጥቃት በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል። ጥቃቱ ከኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ በሆነዉ አሞራቤት ቀበሌ " አዉራ ጎዳና መንደር ትናንት ከሰዓት የተፈፀመ ሲሆን የሰው ህይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል ከሚል መረጃ ውጭ ምን ያህል የሚለው አልታወቀም። …
የአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ምን አሉ ?

የኦሮሚያ ክልል ባወጣው መግለጫ መጋቢት 20 ቀን 2014 በምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ ቆርኬ/አውራ ጎዳና ምንጃር ውስጥ ይንቀሳቀሳሉ ያላቸው " ጽንፈኛ ኃይሎች " በጉዞ ላይ በነበሩ የህዝብ ሚሊሻና የፌዴራል ፖሊስ ላይ ዘግናኝ ጥቃት ፈፅመዋል ብሏል።

ክልሉ ፤ " ...እነዚህ ጽንፈኛ ኃይሎች የፈፀሙት እኩይ ተግባርና ሴራ የአማራና የኦሮሞ ህዝቦች ዘላቂ አብሮነትና ሁለንተናዊ ብልጽግና ጉዞን ለማደናቀፍ የተወጠነ የጥፋት ዕቅድ አካል መሆኑን እንገነዘባለን " ብሏል።

ከሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ጋር በመተባበርም በህግ ፊት አቅርበን ተገቢና ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ለማድረግ በቁርጠኛ ነን ሲል አሳውቋል።

ከአማራ ክልል ጋር በመሆንም ጥቃቱ በደረሰበት ቦታ ላይ ክትትል በማድረግ ወንጀለኞችን ህግ ፊት ለማቅረብ እየተሠራ ነው ብሏል።

የአማራ ክልል በበኩሉ " ጽንፈኞችና ፀረ ሰላም " ናቸው ያላቸው የጥፋት ኃይሎች በአማራ ክልል ሕዝብ እና በአጎራባች ክልል ህዝብ መካከል ግጭት ለመፍጠርና የክልሉን ህዝብ ማኅበራዊ እረፍት ለመንሳት በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች ግጭት ለማጫር ተንቀሳቅሰዋል፤ እየተንቀሳቀሱም ይገኛሉ ብሏል።

እነዚህ ኃይሎች ፦

👉 በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ጃዊ ወረዳ ክልሉ በሚዋሰንባቸው የቤኒሻንጉል ክልል መተከል ዞን በላያ እና አካባቢው፤

👉 በሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ በመልካ ጅሎና ሲናናጆ ቀበሌ

👉 በማእከላዊ ጎንደር ዞን በአንድ አንድ አካባቢዎች በወንድማማቾችና እህትማማቾች መካከል በአንድነትና በፍቅር ለሺ ዘመናት አብሮ በኖረው የአማራ ህዝብ መካከል እንዲሁም ከኦሮሞ እና ከጉሙዝ ሕዝብ ጋር የግጭት ሙከራ አድርገዋል ብሏል።

ያንብቡ : telegra.ph/Oromia-Amhara-03-30

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ምን አሉ ? የኦሮሚያ ክልል ባወጣው መግለጫ መጋቢት 20 ቀን 2014 በምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ ቆርኬ/አውራ ጎዳና ምንጃር ውስጥ ይንቀሳቀሳሉ ያላቸው " ጽንፈኛ ኃይሎች " በጉዞ ላይ በነበሩ የህዝብ ሚሊሻና የፌዴራል ፖሊስ ላይ ዘግናኝ ጥቃት ፈፅመዋል ብሏል። ክልሉ ፤ " ...እነዚህ ጽንፈኛ ኃይሎች የፈፀሙት እኩይ ተግባርና ሴራ የአማራና የኦሮሞ ህዝቦች ዘላቂ አብሮነትና…
#Update

🗣 የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ቦሰት ለቪኦኤ ፦

" አውራ ጎዳና የምትባለው የአሞራ ቤት ቀበሌ መንደር ነች። ሰው ከፊል አርሶ አደር የሆነ በንግድም ጭምር የሚተዳደር ነው።

በዕለቱ ጥዋት አካባቢ አንዳንድ ምልክቶች ነበሩ 4 ሰዓት አካባቢ ጀምሮ ከዛ በኃላ ወደ ቀን 7 ሰዓት አካባቢ ጀምሮ መሳሪያ የጫኑ በልዩ ልዩ በአይሱዙ ፣ በመሳሰሉ መኪናዎች ጭነው የመጡ ሰዎች አልፍ ሲልም የመንግስት ተሽከርካሪ ጭምር የተጠቀሙ ሰዎች ናቸው የመጡት።

የቡድን መሳሪያም አጥምደው ነው የመጡት መጀመሪያ ላይ በአውራ ጎዳና ከተማ ውስጥ አለፉ ከዛ መጨረሻ ላይ ዳር ላይ ሲደርሱ የፌዴራል ፖሊስ ምንድነው ሲላቸው መጀመሪያ እሱን ገደሉ ከዛ ተመልሰው ወደ ማህበረስቡ ገቡና ወደ 8 ሰዓት አካባቢ በጣም የጦፈ ጦርነት ውስጥ ነበር የተገባው።

አመሻሽ 12 ሰዓት አካባቢ ነው ተኩስ እየቆመ የመጣው ፤ ድንገቴ ስለሆነ ሰውም ባላሰበበት ሰዓት ስለሆነ ከባድ ችግር ነበር የነበረው።

እንደምንም ብሎ የአካባቢው ማህበረሰብ እራሱን ለማዳን ጥረት አድርጎ ሴቶች እና ህፃናትን አሽሽቶ ሌላውን አካል እዛው ባለበት ለማድረግ ተሞክሯል።

የአካል ጉዳት ፣ የሞት ፣ የንብረት ጉዳት ና መፈናቀል ጭምር ነው የተፈጠረው። "

🗣 በኦሮሚያ ክልል የምሥራቅ ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አባቡ ዋቆ ለቢቢሲ ፦

" ... ከአጎራባቹ የአማራ ክልል አካባቢ የመጣ ታጣቂ ቡድን በዞኑ የፀጥታ ኃይሎች ላይ ጥቃት ፈጽሞ ጉዳት አድርሷል።

የብሔር ግጭት መፍጠር የሚፈልጉ በኦሮሚያ እና አማራ ድንበር ላይ የሚንቀሳቀስ የተደራጀ ጽንፈኛ ኃይል ሊሆን ይችላል።

ጥቃት ፈጻሚው ቡድን ማንነቱ የማይታወቅ ነው።

በጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸው የፀጥታ አባላት ለሥራ ጉዳይ ተሰማርተው በቡድን እየተመለሱ ሳለ ነው በተፈጸመባቸው ድንገተኛ ጥቃት ከመካከላቸው 18ቱ የተገደሉት እና 15 ደግሞ የቆሰሉት። "

🗣 የምሥራቅ ሸዋ ፖሊስ አዛዥ ኤቢሳ አሰፋ ለኦቢኤን ፦

አዛዡ ፤ በጥቃቱ 26 ሰዎች ተገድለዋል ብለዋል ፤ ጥቃቱን ያደረሰውን ቡድን ማንነት አልገለፁም። ነገር ግን የተደራጀ እና ዘመናዊ ጦር መሳሪያ የታጠቀ ነው " ሲሉ ግምታቸውን አስቀምጠዋል።

@tikvahethiopia
#NewsAlert

የነዳጅ ትራንስፖርት ባለንብረቶች ማኅበር የሥራ ማቆም አድማ ለማድረግ የጊዜ ገደብ ማስቀመጡ ተሰማ።

የማህበሩ አባላት ዛሬ በዋቢ ሸበሌ ሆቴል ባደረጉት ጠቅላላ ስብሰባ በተደጋጋሚ መንግስት ቸልተኛ በመሆኑ የነዳጅ አመላላሽ ቦቴ ቁጥር ከ3500 በ20 እጅ ቀንሷል ብለዋል።

ጅቡቲ ደርሶ መልስ 25,000 ብር እየከሰሩ መሆኑንና ይኸም የሆነውም የብር ዋጋ በመውረዱና መለዋወጫ በመወደዱ መሆኑንም ተናግረዋል።

በመሆኑም መንግስት በአስር ቀናት ውስጥ መፍትሄ የማይሰጣቸው ከሆነ የሥራ አድማ እንደሚጠሩ ማስታወቃቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረችው ፅጌሬዳ ግርማይን በመግደል የተከሰሰው ተማሪ በወንጀለኛ ሕግ 539/1 ራሱን እንዲከላከል ብይን ተሰጦታል። በሕግ ጥላ ስር የሚገኘው ተከሳሹ፤ በጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዳዩን እየተከታተለ እንደሚገኝ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሕግ አገልግሎት ዳይሬክተር መርኪያ መንገሻ @tikvahuniversity ተናግረዋል። " ከባድ ግድያ በመፈጸም የወንጀል…
#Update

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረችው ፅጌሬዳ ግርማይን በመግደል የተከሰሰው ተማሪ የመከላከያ ማስረጃ እንዲያቀርብ ለመጋቢት 28 ቀን 2014 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጥቶታል።

በሕግ ጥላ ስር የሚገኘው ተከሳሹ ብሩክ በላይነህ፤ በአርባ ምንጭ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዳዩን እየተከታተለ ይገኛል።

ማክሰኞ መጋቢት 20/2014 ዓ.ም ፍርድ ቤት የቀረበው ተከሳሹ፤ "የሚፈልጋቸው ምስክሮቹ በአካባቢው ባለመኖራቸው ምክንያት" የመከላከያ ማስረጃ ማቅረብ ሳይችል ቀርቷል።

በመሆኑም ፍ/ቤቱ ተለወጫ ቀጠሮ ለመጋቢት 28/2014 ዓ.ም እንደሰጠው የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሕግ አገልግሎት ዳይሬክተር መርኪያ መንገሻ ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል።

ጥር 23/2014 ዓ.ም የተገደለችው የ20 ዓመቷ ተማሪ ፅጌሬዳ ግርማይ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሆቴልና ቱሪዝም ማኔጅመንት የ2ኛ ዓመት ተማሪ ነበረች፡፡

More : @tikvahuniversity
#Update

የሞጆ - ሀዋሳ ፈጣን የመንገድ ፕሮጀክት አካል የሆኑት ፦
👉 በክፍል ሶስት ባቱ - አርሲ ነጌሌ 57 ኪ.ሜ
👉 በክፍል አራት የአርሲ ነጌሌ - ሀዋሳ 52 ኪ.ሜ የአስፓልት ኮንክሪት የዲዛይን እና ግንባታ ፕሮጀክቶች በመስክ የስራ ቅኝት መጎብኘታቸው ተገልጿል።

ቅኝቱ በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ሀብታሙ ተገኘ እና በሌሎች የተቋሙ ስራ ሀላፊዎችና በሚመለከታቸው አካላት ነው የተካሄደው።

በዚህም ወቅት እየተከናወኑ የሚገኙ ወቅታዊ የግንባታ ስራ እንቅስቃሴዎች እና ቀጣይ ስራዎች የተገመገሙ ሲሆን ፕሮጀክቶቹ በተቀመጠላቸው ጊዜ ግንባታቸው እንዲጠናቀቅ ለማስቻል ከስራ ተቋራጮቹና ከአማካሪ ድርጅቶች ጋር ምክክር ተደርጓል፡፡

በቀጣይም የሚከናወኑ ስራዎችን በተመለከተም የተቋሙ ኢንጅነር ሀብታሙ ተገኘ የስራ አቅጣጫዎችን አስቀምጠቄ።

በሁለቱም የፍጥነት መንገድ ፕሮጀክቶች ስራ ላይ የሚያጋጥሙ ውስንነቶችን በመፍታት ግንባታው ይበልጥ በፍጥነትና በሚገባ መልኩ እንዲከናወን ለማስቻልም የሚደረገውን ጥረት እንደሚቀጥልም አመላክተዋል፡፡

የሞጆ - ሀዋሳ የፈጣን መንገድ አካል የሆኑት ክፍል አንድ ሞጆ - መቂ እና ክፍል ሁለት መቂ - ባቱ ከዚህ ቀደም ግንባታቸው ተጠናቅቆ ለትራንስፖርት አገልግሎት ክፍት መደረጉ ይታወሳል።

ምንጭ፦ ERA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የሞጆ - ሀዋሳ ፈጣን የመንገድ ፕሮጀክት አካል የሆኑት ፦ 👉 በክፍል ሶስት ባቱ - አርሲ ነጌሌ 57 ኪ.ሜ 👉 በክፍል አራት የአርሲ ነጌሌ - ሀዋሳ 52 ኪ.ሜ የአስፓልት ኮንክሪት የዲዛይን እና ግንባታ ፕሮጀክቶች በመስክ የስራ ቅኝት መጎብኘታቸው ተገልጿል። ቅኝቱ በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ሀብታሙ ተገኘ እና በሌሎች የተቋሙ ስራ ሀላፊዎችና በሚመለከታቸው አካላት…
ሞጆ 🛣 ሀዋሳ !

የባቱ - አርሲ ነጌሌ ግንባታ ፦

👉 በእስራኤሉ SBI international holdings A.G /ኤስ ቢ አይ ኢንተርናሽናል ሆልዲንግስ ኤ.ጂ ነው/ የሚነናወነው።

👉 የማማከርና ቁጥጥር ስራውን ኩንውሀ ኢንጂነሪንግ እና ኮንሰልቲንግ ከኮሪያ ኤክስፕረስ ኮርፖሬሽን ጋር በጋራ እያከናወኑ ነው።

👉 ለፕሮጀክቱ ማስፈፀሚያ የሚሆነው ሶስት ቢሊየን ሶስት መቶ አምስት ሚሊየን ሁለት መቶ አርባ ሶስት ሺህ ብር እየተሸፈነ የሚገኘው ከአለምባንክ በተገኘ ፋይናንስ ነው፡፡

👉 የአፈር ቆረጣ ስራ፣ ሰብ ቤዝ ስራዎች፣ የስትራክቸር ፣የውሀ ማፋሰሻ ፣ የአቃፊ ግንብ፣ ትላልቅ የድልድይ ግንባታ፣ ማሳለጫዎችና ማቋረጫዎች እና የክሬሸር ስራ በመከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡

👉 21 ኪ.ሜ የDBM/ ለመጨረሻ የአስፋልን ንጣፍ ስራ ዝግጁ የማድረግ ስራ ተጠናቋል/ ።

አርሲ ነጌሌ - ሀዋሳ የሚዘልቀው የመንገድ ክፍል ፦

👉 ሚገነባው የስራ ተቋራጭ cccc ቻይና ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ነው።

👉 የማማከርና የቁጥጥር ስራውን ቤጂንግ ኤክስፕረስ ዌይ ሱፐር ቪዥን ካምፓኒ ሊሚትድ ከውሀን ጄአይኦኬ ኢንጅነሪንግ ኮንሰልታንሲ ሊሚትድ ጋር በጋራ በመሆን እየሰሩት ነው ፡፡

👉 መንገዱን ለመገንባት የሚውለውን ወጪ አምስት ቢሊየን አንድ መቶ አርባ ዘጠኝ ሺህ ብር በቻይናው ኤግዚም ባንክ 85 በመቶ እና 15 በመቶ በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፈን ነው፡፡

👉 በአርሲ ነጌሌ - ሀዋሳ የመንገድ ፕሮጀክት የአፈር ቆረጣ እና ድልዳሎ ስራ፣ የአፈር ቆረጣ እና ሙሌት፣የስትራክቸር ስራዎች፣ የሰብ ቤዝ ስራ፣ የውሀ ማፋሰሻ ቱቦዎች ቀበራ ፣ የድልድይ ግንባታ፣ የጠጠር ንጣፍ ስራዎች እየተሰሩ ናቸው፡፡

👉 የ3 ነጥብ 4 ኪ.ሜ ለመጨረሻ የአስፋልት ንጣፍ ስራ ዝግጁ የማድረግ ስራ የDBM ተጀምሯል።

#ERA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ማለፊያ ነጥብ ይፋ ሆነ። የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዴኤታ ሳሙኤል (ዶ/ር) ለጋዜጠኞች የ12ኛ ክፍል መለቀቂያ ፈተና መቁረጫ ነጥብ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። በሁለት ዙር ለተሰጠው የመልቀቂያ ፈተና የተሰጠው የማለፊያ ነጥብ የተለያየ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በዚህም መሰረት በመጀመሪያ ዙር ፈተናቸውን የወሰዱ የተፈጥሮ ሳይንስ እና የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች…
#ETHIOPIA

የ2013 የ12ኛ ክፍል ፈተና በሁለት ዙር ተሰጥቶ ውጤት እና የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ከሆነ ቀናት ተቆጥሯል።

የፈተናው ውጤት እና የመቁረጫ ነጥቡ በተለያዩ ተማሪዎች/ወላጆች፣የትምህርት ቢሮና መምሪዎች ዘንድ ቅሬታ ፈጥሮ ትልቅ አጀንዳ መሆኑ ይታወቃል።

መንግስት ለቅሬታዎች ምላሽ እንዲሰጥም ግፊት እየተደረገ ነው።

የትምህርት ሚኒስቴር በበኩሉ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ምደባ ለማድረግ ተማሪዎች ማስተካከል ያለባቸውን መረጃዎች እንዲያስተካክሉ ያስቀመጠው ቀነ ገደብ መጋቢት 19 ላይ ተጠናቋል።

ተማሪዎች ግን መቼ ተመድበው ትምህርት እንደሚጀምሩ እስካሁን አይታወቅም።

በውጤት እና መቁረጫ ነጥብ ላይ ከተነሳው ቅሬታ ባለፈ ወደዩኒቨርሲቲ መግባት የሚያስችላቸውን ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው ሳይገቡ ሌላው ቀርቶ የት እንደሚማሩ ሳያውቁ ለመቀመጥ ተገደዋል፤ ይህም ከፍተኛ ጫና እያሳደረ ይገኛል።

መንግስት እየተነሱ ላሉ ቅሬታዎች ያለውን ምላሽ በፍጥነት እንዲሰጥና ሌሎች ውጤት የመጣላቸውና ወደ ዩኒቨርሲቲ መቀላቀል ያለባቸውን ተማሪዎች በፍጥነት ወደ ትምህርት እንዲያስገባ ከወላጆችና ተማሪዎች እየተጠየቀ ይገኛል።

ይህ ዓመት ሊጠናቀቅ ጥቂት ወራት የቀረው ሲሆን እስካሁን ተማሪዎች አልተመደቡም፤ ዩኒቨሲቲዎችም መቼ ጥሪ እንደሚያደርጉ አይታወቅም።

የኮቪድ19 ወረርሽኝ በሀገሪቱ ከተነሳ ጊዜ አንስቶ በኃላም በሰሜን ኢትዮጵያ የተነሳው ጦርነት የኢትዮጵያ የትምህርት ስርዓት ላይ እያሳደረ ያለው ተፅእኖ ከባድ ሆኖ ቀጥሏል።

በትግራይ ተማሪዎች የ2012ና የ2013 ፈተናን አልወሰዱም የ2014 ይወስዳሉ ተብሎ አይታሰብም።

በሀገር ደረጃም የትምህርት መርሃግብሩ ቀድሞ ወደነበረበት ሊመለስ አልቻለም። ይህ ትውልዱ ላይ ትልቅ ተፅእኖ የሚያሳድር በመሆኑ መፍትሄ ያሻዋል።

@tikvahethiopia