TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ወላይታ ሶዶ🔝

ለዘመናት በአንድነትና በፍቅር የቆዩ በወላይታና ሲዳማ ብሔረሰቦች መካከል ተከስተው የነበረውን አለመግባባትን በማስወገድ በፍቅር፣ በይቅርታና በዕርቅ አንድነታቸውን ዳግም እንዲቀጥሉ የሚያስችል #የዕርቀ_ሰላም_ኮንፈረንስ በወላይታ ሶዶ ተካሂዷል፡፡

ኮንፈረንሱ ከቀናት በፊት በሲዳማ ዞን የተጀመረ ሲሆን በተቀመጠለት መርሃ ግብሩ መሠረት በወላይታ ሶዶም ከሁለቱም ብሔረሰብ የመንግስት ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የኃይማኖት አባቶችና ከተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች የተወከሉ በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተደርጓል፡፡

የወላይታ ዞን ተጠባባቂ አስተዳደር አቶ #ዳጋቶ_ኩምቤ በኮንፈራንሱ መክፈቻ እንደተናገሩት በወላይታና ሲዳማ ብሔረሰብ መካከል ያለው አንድነት ከብረት የተጠናከረ ነው፤ በመሆኑም ዛሬ በሚናደርገው መድረክ አንድነታቸውን እናስቀጥላለን እንጅ አንፈጥርም ብለዋል፡፡ ስለሆነም ተከስተው የነበረውን አለመግባባትን በማስወገድ፤ ያለፈውን በመተው ወደፊት በመጓዝ ሁላችንም በሁሉም ዘርፍ አስፈላጊ ለሆነው ሠላም ዘብ መቆም ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ ርዕሰ መስተዳደር አቶ #ሚሊዮን_ማትዎስ በኮንፈረንሱ ተገኝተው እንደተናገሩት ሁለቱም ብሔረሰቦች ሠላም ፈላጊ ናቸው፡፡ ከዚህ በኋላ የህዛባችን ሠላም የሚያደፈርሱ የትኛውም ኃይል ለሠላም ጤንቅ ናቸውና ፈልፍለን እያወጣን ለሁለቱም ህዝቦች ጋራ ተጠቃሚነት፣ ለሠላምና ለዴሞክራሲ መስፈን እንሠራለን ብለዋል፡፡

የኢፌዴሪ ሠላም ሚኒስተር ወ/ሮ #ሙፈሪያት_ካሚል እንደተናገሩት ስለ ሠላም የሁለቱም ህዘቦችና ሽማግሌዎች ያዉቃሉ፤ ጥበብ ጥበበኞች ዘንድ ትገኛለች፤ ዕዉቀትም በአስተማር ዘንድ፡፡ በመሆኑም ዛሬ በሁለቱ ህዝቦች ሠላም ፍላጎት መሠረት የዕርቅ ማዕድ ተቋዳሽ ሆነናል፡፡ ለሁላችንም እንኳን ደስ አለን ብለው የወላይታና ሲዳማ አንድነት አይበጠስም፣ አይሰበርም ይልቁንስ ሊበጥስ የሚጥር ኃይል ይበጠሳል እንጅ በማለት አንድነት ይበልጥ ይጠናከራል ብለዋል፡፡

በፕሮግራሙ ገልለተኛ አካል የሆነ የዕርቅ ሽማግሌም ከሐምሌ 23/2010 ዓ.ም ጀምረው የተሠራውን የዕርቅ ሂደቱንና ከሁለቱም ህዝቦች በኩል የተነሱና በጋራ መስማማት የተዳረሱ ጉዳዮችን በሪፖርት መልክ አቅርበዋል፡፡ በተነሱ ሀሳቦችም ሁለቱም በኩል የተገኑ ሽማግሌዎች ይቀር መባባላቸውን ዕርቅና ፍቅር እናውርድ ብለው በመስማማታቸው መሠረት ዕርቁ ልፈፀም መቻሉንም አስረድተዋል፡፡

ሽማግሌዎችም ከሁሉ በላይ ከጌታ ጋር ያለንን አንድነታችን ስናጣክር ሌላው ሁሉ ይሆናል የመንግስት አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችን ወደ ፈጣር እንቅርብ ፣ ያለፈውን እንተው ወደ ፊት እንጓዝ በማለት መክረዋል፡፡

በመድረኩም ከሁሉም ቤተ ክርሲቲያን የተገኙ መሪዎችም የፀሎትና ቃል ስብከት ፕሮግራም አድርገዋል ይህም የወላይታና ሲዳማ የጥንት መሠረቱ ወንጌል ነው ሲሉም አሳስበዋል፡፡

በመጨረሻ ከሁለቱም ብሔረሰብ ተሳታፊዎች ሀሳባቸውን የሰጡት ላለፈው ይቅር ተባብለዋል፡፡ በመሆኑ የባህላዊ ዕርቅ ሥርዓትም ተደርጓል፡፡

ምንጭ፦ የወላይታ ሶዶ ከተማ ባ/ቱ/መ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወላይታ~ሲዳማ!

የሲዳማ ብሔር የሀገር ሽማግሌዎች በሰኔ 8 2010 ዓ.ም በሀዋሳ እና አከባቢው በተከሰተው ግጭት ሕይወታቸውን ያጡ የወላይታ ብሔር ተወላጆች ቤተሰብ ላይ ለቅሶ በመድረስ #አጽናንተዋል፡፡

ረጅም ዘመናትን የዘለቀው የሁለቱ ህዝቦች #ትስስር ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የሟች ቤተሰቦች ገልጸዋል፡፡

የሲዳማ ብሔር የሀገር ሽማግሌዎች በሐዋሳና አከባቢዋ በተፈጠረው ግጭት ልጆቻቸውንና ዘመዶቻቸውን በሞት ለተለዩ ቤተሰቦች ላይ ለቅሶ በደረሱበት ወቅት ከሟች ቤተሰቦች አንዳንዶቹ እንደተገለጹት ሁለቱ ህዝቦች ለረጅም ዘመናት በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ተሳስረው፣ ተቻችለውና ተከባብረው የኖሩ ህዝቦች ናቸው፡፡

በሁለቱ ህዝቦች መካከል ግጭት እንዲፈጠር የሚቀሰቅሱ አካላት ሊገስጹ ይገባል ብለዋል፡፡

በሰኔ 8 2010 ዓ.ም በሀዋሳ እና አከባቢው በተከሰተው ግጭት የሰው ህይወት በመጥፋቱ እጅግ ማዘናቸውን የሟች ቤተሰቦች ገልፀው እርቀ ሰላም እንዲወርድ ከፍተኛ ጥረት ላደረጉ በየደረጃው የሚገኙ አመራር አካላት፣ አስታራቂ ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ #ዳጋቶ_ኩምቤ እንደተናገሩት የወላይታ እና የሲዳማ ህዝቦች ለዘመናት ተከባብረውና ተቻችለው አብረው የኖሩ ህዝቦች ናቸው፡፡

የሁለቱ ህዝቦች ታሪካዊ ትስስር በአንድ መድረክ ተነግሮ የሚያልቅ አይደለም ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በሁለቱ ህዝቦች መካከል በተከሰተው ግጭት ክቡር የሆነው የሰው ህይወት ከመጥፋቱም በላይ በሰው አካል ላይ ጉዳት ያደረሰ፣ በርካታ ንብረት የወደመበት እና በርካታ ሰው የተፈናቀለበት መሆኑን አስታውሰዋል፡፡

ይህ ጥፋት ሁለቱንም ህዝቦች የማይወክል ጥቂት ቡድኖችና ግለሰቦች የራሳቸውን ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥቅም ለማግኘት ሆን ብለው ግጭቱ የብሔር ይዘት እንዲኖረውና የህዝቦቹ ትስስር #እንዲሻክር ያደረጉት ነው ብለዋል፡፡

#የሲዳማ_ብሔር የሀገር ሽማግሌዎች እንደተናገሩት በወላይታ ሶዶ በመገኘት ወገኖቻቸውን በሞት ላሰጡ ቤተሰቦች ላይ ለቅሶ ለመድረስና ለማጽናናት የመጡበት ዋናው ዓላማ የሁለቱ ህዝቦች ዘመን ተሻጋሪ ግንኙነታቸውንና አብሮነታቸውን ለማደስ ነው፡፡

የወላይታ እና የሲዳማ ህዝቦች ረጅም ዘመን የቆየው አንድነትና አብሮነት ቀጣይነት አንዲኖረው ለማድረግ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ የሀገር ሽማግሌዎቹ አስታውቀዋል፡፡

የሁለቱ ህዝቦች አንድነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ለማድረግ የሟች ቤተሰቦችን የማጽናናት ሥራ በባህላዊ የዕርቅ ስርዓት ተከናውኗል፡፡

በተመሳሳይ በዛሬው ዕለት ታህሳስ 25 ቀን 2011 ዓ.ም የወላይታ ብሔር የሀገር ሽማግሌዎች ወደ ሐዋሳ በማቅናት በሲዳማ ብሔር በኩል በግጭቱ ሕይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች ላይ ለቅሶ በመድረስ እንደሚያጽናኑ ይጠበቃል፡፡

ምንጭ፦ Wolaita ZONE Culture,tourisim and Governmental Communication Affairs Office
@tsegabwolde @tikvahethiop
#አርባምንጭ

በወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ #ዳጋቶ_ኩምቤ የተመራ ከፍተኛ አመራር በጋሞ "ዩ-ማስቃላ" ክብረ-በዓል ላይ ለመታደም አርባ ምንጭ ከተማ ገብቷል፡፡ አመራሮቹ አርባ ምንጭ ሲገቡ የጋሞ ዞን አስተዳዳሪ ደማቅ አቀባበል አደርገውላቸዋል፡፡ የሁለቱም ዞን አስተዳዳሪዎች የሁለቱን ወንድማማች ህዝቦች ግንኙነት ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እንደሚሰሩ የተገለፀ ሲሆን በህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱ ዙሪያ እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ተነጋግረዋል፡፡ የጋሞ ዞን አቻቸው በተመሣሣይ በወላይታ የጊፋታ በዓል ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

Via #GMN
@tsegabwolde @tikvahethiopia