TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#USA

በአሜሪካ ሀገር ካሊፎርኒያ ግዛት ሳክራሜንቶ ከተማ በተከፈተ ተኩስ በትንሹ 6 ሰዎች ሲገደሉ 12 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ድንገተኛው የተኩስ እሩምታ መጠጥ ቤቶች እና ምግብ ቤቶች በሚበዙበት አካባቢ የተከፈተ ሲሆን ሰዎችም እራሳቸውን ለማዳን በየጎዳናዎቹ ሲሯሯጡ እና የድረሱልን ጥሪያቸውን ሲያሰሙ ነበር ተብሏል።

ፖሊስ በደረሰው ጥቆማ በቦታው ሲደርስ በርካታ ሰዎች በአካባቢው ተሰብስበው እንደነበር የገለፀ ሲሆን እስካሁን ድረስ ምንም አይነት ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር እንዳልዋለ አመልክቷል።

የሟቾች ቁጥር አሁን ከተጠቀሰውም በላይ ሊጨምር እንደሚችል ተገምቷል።

የከተማዋ አስተዳዳሪ የሆኑት ዴረል ሰቲንበርክ በጥቃቱ ሕይወታቸው ያለፈና ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ቁጥር ማሰብ በጣም አስቸጋሪ እንደሆነ ገልጸዋል።

አክለውም ፤ " በጦር መሳሪያ የሚፈጸሙ ጥቃቶች የከተማችን፣ የግዛታችን እንዲሁም የአገራችን ስጋት ነው። ይህንን ለመቀነስ የሚደረጉ ማንኛውም አይነት እርምጃዎችን እደግፋለው " ማለታቸውን ቢቢሲ በደረገፁ አስነብቧል።

እንደ Gun Violence Archive ድረገፅ መረጃ በአሜሪካ ሀገር ከጦር መሳሪያዎች ጋር በተያያዘ በየዓመቱ #አርባ_ሺህ (40,000) ሰዎች የሚሞቱ ሲሆን ይህ ደግሞ በመሳሪያዎች እራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎችን ያካታታል።

@tikvahethiopia
#USA

መሳሪያ በታጠቁ ሰዎች በርካቶች በሚገደሉባት ሀገረ አሜሪካ ከሰሞኑን ተፈፅመው በነበሩ ጥቃቶች ሰዎች ተገድለዋል ፤ ቆስለዋል።

ሰሞኑን በኒው ዮርክ ግዛት በፋሎ ከተማ አንድ ነጭ ታጣቂ ጥቁሮች የሚበረክቱበት መገበያያ ሥፍራ ገብቶ ጥቃት ፈፅሞ 10 ሰዎችን ገድሏል።

ይኸው ተጠርጣሪ 18 ዓመቱ ሱሆን ፔይተን ጌንድሮን ይባላል ጥቃቱን 320 ኪሎ ሜትር ተጉዞ መጥቶ መፈፀሙን ፖሊስ ገልጿል።

አሜሪካዊው ታጣቂ ጥቁሮችን ብቻ ነጥሎ ጥቃት መፈፀሙ ተነግሯል።

ጥቃቱ #በዘረኝነት መንፈስ የተፈፀመ ሊሆን ይችላል በሚልም ምርመራ እየተደረገበት ነው።

የበፋሎ ከተማ ከንቲባ ባይረን ብራውን ተጠርጣሪው "የቻለውን ያክል #የጥቁር_ነፍስ ለማጥፋት ነው የመጣው" ብለዋል።

ግለሰቡ ከጥቃቱ በኋላ በቁጥጥር ሥር የዋለ ሲሆን ጥቃቱን አልፈፀምኩም ሲል ቃሉን ሰጥቷል።

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ምንም እንኳ ምርመራው ባይጠናቀቅም " ይህን ዘረኛ ጥቃት እቃወማለሁ " ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

በሌላ በኩል ትላንት እሁድ አንድ የታጠቀ ሰው በደቡባዊ ካሊፎርኒያ ቤተክርስትያን ውስጥ ተኩስ ከፍቶ አንድ ሰው ገድሎ 5 ሰዎችን አቁስሏል። 4ቱ ሰዎች በፅኑ የቆሰሉ ናቸው።

ተጠርጣሪው እድሜው በስልሳዎቹ ሲሆን አሁን ላይ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ይገኛል።

እንደ Gun Violence Archive ድረገፅ መረጃ በአሜሪካ ሀገር ከጦር መሳሪያዎች ጋር በተያያዘ በየዓመቱ #አርባ_ሺህ (40,000) ሰዎች የሚሞቱ ሲሆን ይህ ደግሞ በመሳሪያዎች እራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎችን ያካታታል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA መሳሪያ በታጠቁ ሰዎች በርካቶች በሚገደሉባት ሀገረ አሜሪካ ከሰሞኑን ተፈፅመው በነበሩ ጥቃቶች ሰዎች ተገድለዋል ፤ ቆስለዋል። ሰሞኑን በኒው ዮርክ ግዛት በፋሎ ከተማ አንድ ነጭ ታጣቂ ጥቁሮች የሚበረክቱበት መገበያያ ሥፍራ ገብቶ ጥቃት ፈፅሞ 10 ሰዎችን ገድሏል። ይኸው ተጠርጣሪ 18 ዓመቱ ሱሆን ፔይተን ጌንድሮን ይባላል ጥቃቱን 320 ኪሎ ሜትር ተጉዞ መጥቶ መፈፀሙን ፖሊስ ገልጿል። አሜሪካዊው…
#US

በየጊዜው በርካቶች በታጣቁ ሰዎች በሚከፈት ተኩስ የሚገደሉባት ሀገረ አሜሪካ ትላንትም እጅግ በጣም ዘግናኝ የሚባል ጥቃት ተፈፅሞ 2 አዋቂዎችን ጨምሮ 19 ሕጻናት ተገድለዋል።

በአሜሪካ ቴክሳስ ግዛት አንድ የ18 ዓመት ወጣት በከፈተው የተኩስ እሩምታ 2 አዋቂዎችን ጨምሮ 19 ሕጻናት መገደላቸውን ተዘግቧል።

ድርጊቱ የተፈፀመው በደቡብ ቴክሳስ ግዛት፣ ዩቫልዲ ከተማ ሮብ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ነው አንድ ወጣት ድንገተኛ ተኩስ ከፍቶ ነው 19 ህፃናትን ጨምሮ 2 አዋቂዎችን የገደለው።

ከተገደሉት ሁለት አዋቂዎች አንዷ በዚያው ትምህርት ቤት የምታስተምር መምህርት ነበረች።

ፖሊስ እንዳለው ድርጊቱ የፈፀመው ወጣት የታጠቀው ኤአር-15 ከፊል አውቶማቲክ ጠመንጃ ነበር።

ወጣቱ መጀመርያ ሴት አያቱን ከገደለ በኋላ ነው ሕጻናቱን በግፍ የገደላቸው ተብሏል።

አንዳንድ መገናኛ ብዙኃን ወጣቱ በዚያው አካባቢ በሚገኝ አንድ ትምህርት ቤት የ2ኛ ደረጃ ተማሪ እንደሆነ እየዘገቡ ይገኛሉ።

የቴክሳስ ግዛት ገዥ ግሬግ አቦት ወጣቱ " ሳልቫዶር ራሞስ " እንደሚባልና መኪናውን ደጅ አቁሞ ወደ ትምህርት ቅጥር ግቢው ከገባ በኋላ አሰቃቂው ድርጊት እንደፈጸመ ተናግረዋል።

አሶሲየትድ ፕሬስ እንደዘገበው ከትምህርት ቤቱ በቅርብ የነበረ አንድ የድንበር ጠባቂ ፖሊስ የተኩስ ድምጽ ሰምቶ ወደ ትምህርት ቤቱ በመግባት ይህን ወጣት ታጣቂ ተኩሶ ባይገድለው ኖሮ የሟቾች ቁጥር ከዚህ በላይ ሊሆን ይችል ነበር።

እንደ Gun Violence Archive ድረገፅ መረጃ በአሜሪካ ሀገር ከጦር መሳሪያዎች ጋር በተያያዘ (በመሳሪያ እራሳቸውን የሚያጠፉትን ጨምሮ) በየዓመቱ #አርባ_ሺህ (40,000) ይሞታሉ።

(ኤፒ/ቢቢሲ - ፎቶ - ሶሻል ሚዲያ)

@tikvahethiopia
ቪድዮ ፦ በአሜሪካ ሀገር ቴክሳስ በምትሰኝ ግዛት በምትገኘው " አለን " ከተማ አንድ ታጣቂ በገበያ አዳራሽ ውስጥ በፈጸመው ጥቃት ስምንት (8) ሰዎችን በጥይት ገድሏል።

በታጣቂው ከተገደሉት ውስጥ #ሕጻናት ይገኙበታል።

ከተገደሉት በተጨማሪ ሰባት (7) ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው በሆስፒታል ህክምና እየደረገላቸው ሲሆን፣ ከመካከላቸው 3ቱ በጽኑ የተጎዱ ናቸው።

ታጣቂው በጅምላ ባገኘው ሰው ላይ በከፈተው ተኩስ ግድያውን የፈጸመ ሲሆን፣ በገበያ አዳራሹ ውስጥ የነበሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች ድጋፍ እንዲወጡ ተደርገዋል።

ታጣቂው እዚያው ጥቃቱን በፈጸመበት ስፍራ በፖሊሶች ተተኩሶበት የተገደለ ሲሆን፣ ጥቃቱን የፈጸመው ብቻውን እንደሆነ እንደሚታመን ቢቢሲ ዘግቧል።

እንደ Gun Violence Archive ድረገፅ መረጃ በአሜሪካ ሀገር ከጦር መሳሪያዎች ጋር በተያያዘ በየዓመቱ #አርባ_ሺህ (40,000) ሰዎች የሚሞቱ ሲሆን ይህ በመሳሪያዎች እራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎችን ያካታታል።

ቪድዮ ፦ Fox News

@tikvahethiopia