TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ፌደራል ፖሊስ⬇️

የህዝቡን #ደህንነት እና #ሰላም ለመጠበቅ ሲል መንግስት አስፈላጊውን #እርምጃ እንደሚወስድ የፌደራል ፖሊስ ገለፀ።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ከሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማል በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው ላይ የመንግስት ትእግስት #ገደብ እንዳለው በመግለፅ #ጉልበተኞችን እንደማይታገስ አስታውቀዋል።

አሁን ላይ እየተስተዋሉ ያሉት #ሁከቶች #በሁለት የፖለቲካ ድርጅቶች ስም የተቀነባበሩ መሆናቸውን ኮሚሽነር ጀነራሉ ጠቁመዋል።

ባለፉት ሦስት ቀናት በቡራዩና አካባቢው ብዛት ያላቸው ወንጀለኞች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን በመጠቆም፥ በተለያዩ ቦታዎች ተዘርፈው የነበሩ ንብረቶችን የማሰባሰብ ስራ መሰራቱንም ነው ያስታወቁት።

በአጠቃላይም በቡራዩ ከ300 አስከ 400 የሚደርሱ ተጠርጣሪዎች ሲያዙ በአዲስ አበባ ደግሞ ከ300 በላይ ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን ገልጸዋል፡፡

በአዲስ አበባ #ገንዘብ ተከፍሏቸው ብሄርን ከብሄር ለማጋጨት እንዲሁም ብሄርን መሰረት ያደረጉ ስድቦችንም ጭምር በማሰራጨት #የተጠረጠሩ ግለሰቦች መያዛቸውንም አንስተዋል።

ይህ ድርጊት #በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባና በአርባ ምንጭ መታየቱን ጠቅሰዋል።

ኮሚሽነሩ በቡራዩና አካባቢው የተፈፀመውን ግድያ ለማውገዝ በርካታ ሰላማዊ ሰው መውጣቱን ጠቅሰው #የተወሰኑ ቡድኖች ግን አዝሚሚያቸው ሌላ ነበር ብለዋል።

ከእነዚህ የተወሰኑ ግለሰቦች መካከልም #ቦምብ ይዘው የነበሩ በህብረተሰቡ ትብብር መያዛቸውን ገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በፒያሳና በመርካቶ #ለዝርፊያ የሚቃጡ ግለሰቦች እንደነበሩ ነው የጠቀሱት።

የተወሰኑት የጸጥታ ኃይሎች ደግሞ ጠብመንጃ ለመንጠቅ ሙከራ ያደረጉ ሲሆን በዚህም ከጸጥታ ኃይሉ ጋር #ግብግብ ገጥመው ነበር ብለዋል።

ይህንንም ተከትሎ የአምስት ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን፥ ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች መቁሰላቸውን ገልጸዋል።

በአጠቃላይ ይህ ግርግር ሆን ተብሎ የተጀመረውን ለውጥ #እንዳይሳካ #ታስቦበት የተከናወነ መሆኑን ነው ያነሱት።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia