TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Worebabo📍

በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 609 የብሬን ጥይትና ሌሎችን ህገ ወጥ ቁሳቁሶችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የወረባቦ ፖሊስ ጽ/ቤት አስታወቀ።

ፖሊስ ፤ በወረባቦ ወረዳ በቀን 05/7/2014 ህገ ወጥ መሳሪያዎችና እቃዎች ጭኖ ከጭፉራ አቅጣጫ ወደ ሃይቅ ዋናውን መንገድ ይዞ ሲመጣ የነበረ " ኮድ 3 B38052 AA " የሆነ የጭነት አይሱዙ ቢሲቲማ ከተማ ኬላን በመጣስ ለማምለጥ የሞከረ ቢሆንም የጸጥታ ሃይሎች ባደረጉት ክትትል በ02 ቀበሌ ሃራ መገጠያ አካባቢ ከሌቱ 10:00 አካቢቢ በቁጥጥር ስር መዋሉን አስረድቷል።

መኪናው በቁጥጥር ውስጥ ሲውል ፦
👉 39 ካርቶን ጎልዴን ሲጋራ፥
👉 33 ካርቶን የሺሻ አፕል፥
👉 305 የክላሽ ጥይት፥
👉 609 የብሬን ጥይት ፥
👉 10 የቱርክ ጥይት፥
👉 22 የUNHCR የእርዳታ ኬንዳ እና 11 ብርድልሶች በጸጥታ አካሉ ተይዟል ተብሏል።

የመኪና አሽከርካሪ የተሰወረ ሲሆን 3 ተጠርጣሪዎችና መኪናው በቁጥጥር ስር መዋሉም የወረባቦ ፖሊስ ጽ/ቤት አስታውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ይፈለጋል የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከላይ በምስሉ ላይ ያለውን ግለሰብ በወንጀል እንደሚፈልገው አሳውቋል። ግለሰቡ የተለያዩ ሀሰተኛ መታወቂያዎችን በማውጣትና በመጠቀም ከተለያዩ ባንኮች ብር አጭበርብሮ በማውጣት ወንጀል እንደሚፈለግ ነው ፖሊስ የገለፀው። ፌዴራል ፖሊስ ተጠርጣሪውን የሚመለከት ማንኛውም መረጃ ካልዎት እንዲያሳውቁ ጥሪ ያቀረበ ሰሆን ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግ ጠይቋል። ስልክ…
#ተይዟል

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከጥቂት ቀናት በፊት በጥብቅ ሲፈልገው የነበረ ግለሰብ መያዙን አሳውቋል።

ፖሊስ የካቲት 29 ቀን 2014 ዓ/ም ባወጣው ማስታወቂያ ከላይ በምስሉ ላይ የሚታየውን ግለሰብ በወንጀል እንደሚፈልገው ገልጾ ነበር።

ግለሰቡ የተለያዩ ሀሰተኛ መታወቂያዎችን በማውጣትና በመጠቀም ከተለያዩ ባንኮች ብር አጭበርብሮ በማውጣት ወንጀል እንደሚፈለግ ነበር ፖሊስ ገልጾ የነበረው።

ዛሬ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ እንዳሳወቀው ግለሰቡ በተለያዩ ስሞች በመጠቀም ለመሰወር ቢሞክርም በህብረተሰቡ ጥቆማ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል።

@tikvahethiopia
#Tigray

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ከትግራይ የሰብዓዊ ድጋፍ ጋር በተያያዘ መግለጫ አውጥቷል።

ሚኒስቴሩ በመግለጫው የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት የትግራይ ክልልን ሰብአዊ ችግር ለመፍታት በአፋር መስመር የሰብአዊ ድጋፍ የሚያደርሱ ተሽከርካሪዎች በተቀላጠፈ ሁኔታ እንዲንቀሳቀሱ በማመቻቸት ገንቢ የሆነ ሚና ሲጫወት መቆየቱን እና አሁንም ሚናውን መቀጠሉን ገልጿል።

በዚህም መሰረት ዛሬ መጋቢት 17 (እኤአ) 20 የጭነት ተሽከርካሪዎች ምግብ እና 3 ነዳጅ ጫኝ ተሽከርካሪዎች ከሰመራ ወደ መቐለ መንቀሳቀስ ጀምረዋል ሲል አሳውቋል።

የሰብዓዊ ዕርዳታውን ከፍ ለማድረግ እና የክልሉን መሰረታዊ ፍላጎቶች ለማሟላት በየቀኑ ወደ ትግራይ የሚያቀኑት የጭነት ተሽከርካሪዎች ቁጥር 40 ለማድረስ እንደሚሰራ አመልክቷል።

በተጨማሪም 17 አጋሮች መድሃኒትን (ክትባትን ጨምሮ) የህክምና ቁሳቁሶችን እና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦትን ወደ ትግራይ ክልል እንዲያስገቡ ፍቃድ አግኝተዋል ብሏል።

ሚኒስቴሩ በመግለጫው 11 አጋሮች 275 ሺ 192 ኪ.ግ የሚመዝኑ የህክምና ግብአቶችን በአየር በረራ ማድረሳቸውን ገልጿል።

ሚኒስቴሩ በአፋር ክልል በድጋሚ በተፈፀመው ጥቃት ከ700,000 በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው እና በአባአላ በኩል ወደ ትግራይ የሚወስደው የሰብአዊ እርዳታ መስመር እንዲዘጋ ማድረጉን አመልክቷል። ጥቃቱ በአፋር ክልል ቂሊቤቲ ረሱ ዞን ወደ 5 ወረዳዎች ከፍ ብሎ ከ300,000 በላይ ሰዎችን እንዲፈናቀሉ ማደረጉን ገልጿል።

ከሰመራ 38 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሰርዶ 43 ምግብ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ቆመው እንደሚገኙም ሚኒስቴሩ አመልክቷል።

ሆኖም ግን ዛሬ ከተደረጉት ጥብቅ ጥረቶችና ውሳኔዎች በተጨማሪ የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ያለውን የሰብአዊ ችግር ለመፍታት ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል።

@tikvahethiopia
#Update

አሜሪካ የሶማሊያን 'የዲሞክራሲ ሂደት አደናቀፉ' ባለቻቸው ተጨማሪ ሶማሊያውያን ላይ የቪዛ ዕገዳ ጥላለች።

ሀገሪቱ ይህን ያሳወቀችው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቷ አማከኝነት ነው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንክን ትላንት ባወጡት መግለጫ የሶማሊያ መንግሥት የምክር ቤታዊ ምርጫ ሂደቱን ማክሰኞ እአአ መጋቢት 15 /2022 ሊያጠናቅቅ ራሱ ያወጣውን ቀነ ገደብ ተግባራዊ ሳያደርግ መቅረቱን ተከትሎ የዲሞክራሲ ሂደቱን በማደናቀፍ ተጠያቂ ወይም ተመሳጣሪ ናቸው በተባሉ ተጨማሪ ሰዎች ላይ አሜሪካ የቪዛ ማዕቀብ እርምጃ መውሰዷን አሳውቀዋል።

አንቶኒ ብሊንከን ምንም እንኳን ባለፉት ጥቂት ሳምንታት አበረታች እርምጃ የታየ ቢሆንም አሁንም ያልተያዙ ከሠላሳ ስድስት በላይ ክፍት የምክር ቤት መቀመጫዎች እንዳሉ አመልክተዋል።

የምርጫው ሂደት መዛባት ላይ እንዲሁም ዲሞክራሲያዊ ተቋማትን የሚደግፉ እና ሂደቱ ግልጽ እንዲሆን የሚጥሩ ጋዜጠኞች እና ተቃዋሚ ፓርቲ አባላት የወከባ የእስር እና የጥቃት ዒላማ እየተደረጉ መሆኑን የሚያመለክቱ ተዓማኒ ሪፖርቶች መውጣታቸውን ቀጥለዋል ሲሉም አንቶኒ ብሊንከን መግለፃቸውን ቪኦኤ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
ፎቶ : ኩሪፍቱ ሪዞርትስ አዋሽ ፓርክ ውስጥ ያስገነባውን አዲስ ቅርንጫፍ ከትላንትና በስቲያ አስመርቋል።

የአዋሽ ፏፏቴዎች ላይ የተገነባው ይህ የኩሪፍቱ ሪዞርት ለፓርኩ ተጨማሪ የቱሪስት መዳረሻ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

የኩሪፍቱ ሪዞርትስ ባለቤት አቶ ታዲዮስ ጌታቸው ፤ አዲሱ የአዋሽ ሪዞርታቸው እንደከዚህ ቀደሞቹ ሁሉ በአከባቢው ያሉ ተፈጥሯዊ የግንባታ ቁሶችን መጠቀሙን አስረድተውናል።

የግንባታ ሂደቱ 11 ወራት መፍጀቱንም ጠቁመዋል።

ከዚህም በተጨማሪ በሰው ኃይል ደረጃ ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ በአከባቢው ያሉ አቅሙ ያላቸውን ዜጎች መርጦ በማሰልጠን ወደ ሥራ ማስገባታቸውን አቶ ታዲዮስ ገልጸውልናል።

ኩሪፍቱ በስሩ አሁን ላይ ሦስት ሺ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር ችሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከዓመት በኋላ ከቤታቸው ውጪ መታየታቸው ተሰምቷል። አቶ ዳውድ ዛሬ ረፋድ ላይ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር ስብሰባ ለመቀመጥ ወደ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አምርተው እንደነበር ቢቢሲ ዘግቧል። ምርጫ ቦርድ ከቀናት በፊት የኦነግ የረጅም ጊዜ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ አንድ ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ ከቤታቸው እንዳይወጡ ተከልክለው በቁም…
#OLF

የኦነግ ከፍተኛ ከፍተኛ አመራር አባል እና የሊቀመንበሩ አቶ ዳውድ ኢብሳ ከፍተኛ አማካሪ ዶ/ር ሽጉጥ ገለታ ለዶቼ ቨለ የተናገሩት ፦

" ... የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከአንድ ዓመት በላይ ለሚሆን ጊዜ በመኖሪያ ቤታቸው ታግተው ሰው ሄዶ ሊጠይቃቸው እንዲሁም እሳቸውም ወጥተው ሰው ማግኘት በማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ ነበሩ።

ከረጅም ጊዜ በኋላ ይህንኑን የተረዳው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማጣራት አድርጎ ነገሩ ትክክል አይደለም በማለት መንግስት እንዲፈታቸው መጠየቁ የሚታወስ ነው፡፡

ይህንኑን ሂደት ተከትሎ ይመስላል ከቀናት በፊት ሊቀመንበሩ የካቲት 30 ቀን 2014 ለመጀመሪያ ጊዜ ከዚያ ከሚኖሩበት ጊቢው ወጥተው በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመገኘት ከቦርዱ ሃላፊዎች ጋር የኦነግ ጽ/ቤት ስለመዘጋቱ፣ በእስር ላይ የሚገኙ የፓርቲው አመራሮች ለደህንነታቸው አስጊ በሆነ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን እና በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

በመሆኑም ከቀደመው ሁኔታ በተሻለ መንቀሳቀስ ጀምረዋል፡፡ "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#OLF የኦነግ ከፍተኛ ከፍተኛ አመራር አባል እና የሊቀመንበሩ አቶ ዳውድ ኢብሳ ከፍተኛ አማካሪ ዶ/ር ሽጉጥ ገለታ ለዶቼ ቨለ የተናገሩት ፦ " ... የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከአንድ ዓመት በላይ ለሚሆን ጊዜ በመኖሪያ ቤታቸው ታግተው ሰው ሄዶ ሊጠይቃቸው እንዲሁም እሳቸውም ወጥተው ሰው ማግኘት በማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ ነበሩ። ከረጅም ጊዜ በኋላ ይህንኑን የተረዳው የኢትዮጵያ…
#OLF

አቶ ዳውድ ኢብሳ አሁን ላይ ያገኙት የመንቀሳቀስ ነጻነት ወደ ፈለጉበት መሄድ የሚያስችላቸው እና በስልክ የፈለጉትን ሰው ደውለው የሚገናኙበት ነው ?

የዶ/ር ሽጉጥ ገለታ (የአቶ ዳውድ ከፍተኛ አማካሪ) ለዶቼ ቨለ የሰጡት ምላሽ ፦

" .... እኔ የማውቀው መንቀሳቀሳቸውን እንጂ ከዚህ በፊት የሚጠቀሙበት ስልካቸውን በመቀማታቸው ለጊዜው አግኝተናቸው ማውራት አልቻልንም፡፡

ይሁንና አስፈላጊ የሆኑ አንዳንድ ቦታዎችን ለመድረስ እድሉን እንዳገኙ ነው ለጊዜው የምናውቀው፡፡

ይሄ ለውጥ ምርጫ ቦርዱ ደብዳቤውን ከፃፈ ወዲህ ያየነው መልካም የሚባል ለውጥ ነው፡፡

ከ7 ቀናት በፊት ጀምሮ የተሻለ የመንቀሳቀስ ሁኔታ ቢኖርም ሙሉ በሙሉ በነጻነት የመሄድ ነገር አለ የሚል መደምደሚያ ግን የለንም።

" ... ለውጡ መልካም ነው፡፡ ይህ ቀጥሎ ሊቀመንበሩ ሙሉ በሙሉ ነጻ እስኮሆኑ እና በተለያዩ ህመሞች በእስር ቤት እየተሰቃዩ ያሉት እንደነ ሚካኤል ቦረን፣ ከኔሳ አያና እንዲሁም ከ አቶ ባቴ ዑርጌሣ ጋር በአንድ ስፍራ የነበሩ እንዲሁም ስንቴ ፍርድ ቤት ያሰናበተው እና ከ2 ዓመት በላይ ታስሮ የሚገኘው አብዲ ረጋሳ እና ሁሉም የኦነግ አባላትና አመራሮች ተለቀው ቢሮው ቢንቀሳቀስ ለሁሉም ሰላም መልካም ነው፡፡

የፖለቲካ አውዱንም ያሰፋል፡፡

አሁን የተመለከትነው መነሻ ይመስለናል፡፡ መቀጠል ያለበት ነው ብለን እናምናለን፡፡ በዚህ ሂደት ድምጻችን ላያሰሙልን የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች እና ሚዲያዎች በህዝባችን ስም ምስጋና ለማቅረብ እንወዳለን፡፡ "

@tikvahethiopia
#ATTENTION

ከ8 ወር በላይ ወደ ቄያቸው ያልተመለሱት የገደማይቱ ተፈናቃዮች የመፍትሄ ያለ እያሉ ነው።

በገደማይቱ ሀምሌ 17 ቀን በነበረው ግጭት ምክንያት ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ በርካታ ዜጎች እስካሁን ወደ ቄያቸው መመለስ አልቻሉም።

እነዚህ ዜጎች በየመጠለያው ካምፕ እና በየዘመድ አዝማዶቻቸው ቤት ተጠልለው ወራት ማለፋቸውን ገልፀውልናል።

" ዞር ብሎ የሚያየን እና የሚጠይቀን አጥተናል " ያሉት እነዚሁ ወገኖች ለ20 እና 30 ዓመታት ከኖሩበት ቀያቸው ቢፈናቀሉም አሁን ድረስ ምላሽ የሚሰጥ እንዳላገኙ ተናግረዋል።

በወቅቱ በርካታ ሰዎች መገደላቸውና ሴቶችም ከፍተኛ እንግልት እና ስቃይ እንደደረሰባቸው ያስታወሱት እነኚህ ወገኖች የነበራቸው ሁሉ ንብረት እንደወደመ እና ተዘርፎ በየከተማው ሲሸጥ እንደነበር አስረድተዋል።

የፌዴራል መንግስትን መፍትሄ እንዲሰጠብ ለመጠየቅ ጥረት ብናደርግም አሁን ቆዩኝ ጦርነት ነው እያለን ለወራት በየቤተክርስቲያኑ ፣ በዘመድ አዝማድ ቤት እና በየመጠለያ ጣቢያው በየሜዳው ወድቀን ቆይተናል ብለዋል።

የተፈናቀለው ሰው ቁጥር በርካታ መሆኑን የሚገልፁት እነኚሁ ወገኖች ድምፃቸው እንዲሰማላቸው ፣ ትኩረትም እንዲሰጣቸው፣ የኢትዮጵያ መንግስትም መፍትሄ ይፈልግላቸው ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከወራት በፊት ከነበረው ግጭት ጋር በተያያዘ ሁኔታው ሲከታተል እንደነበረ አስታውሶ ከዛ በኃላ ተፈናቃዮች ስለሚገኙበት ሁኔታ ወቅታዊ መረጃ እንደሚያደርሰን አሳውቋል።

ምላሹ እንደደረሰን የምንልክላችሁ ይሆናል።

@tikvahethiopia
የፕሬዜዳንቱ ማስጠቀቂያ 🍱

የፈረንሳዩ ፕሬዜዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በዩክሬን ጦርነት የተከሰተው አለመረጋጋት በሚቀጥሉት ከ12-18 ወራት ውስጥ በአፍሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ ያሉ ሀገራትን ወደ ከፍተኛ የምግብ ቀውስ ሊያስገባ ይችላል ሲሉ አስጠነቀቁ።

ፕሬዜደንቱ ይህን ማስጠንቀቂያ የሰጡት ለሁለተኛ የስልጣን ዘመን በስልጣን ላይ ለመቆየት ከሚያደርጉት የምርጫ ውድድር ጋር በተያያዘ በፓሪስ ከተማ የፖለቲካ ፕሮግራማቸውን ባሳወቁበት ወቅት ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃላቸው ነው።

ማክሮን ፤ " በዩክሬን ጦርነት ምክንያት በሚቀጥሉት ከ12-18 ወራት ውስጥ በተለይም በሩሲያ ላይ በጣም ጥገኛ በሆነ ሀገሮች [ በአፍሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ ] ከፍተኛ የምግብ ቀውስ ያጋጥመናል " ያሉ ሲሆን አውሮፓ ለዚህ ፈተና ዝግጁ መሆን አለባት ለራሷ ለአውሮፓ እና ለአጋሮቿ " ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" በትምህርት ሚኒስቴር የተቆረጠው ማለፊያ ነጥብ የአካባቢውን ነባራዊ ሁኔታ እና ችግር ታሳቢ ያላደረገ ነው " - አቶ አለሙ ደባሽ በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በጋዝጊብላ ወረዳ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ 229 ተማሪዎች 30 ተማሪዎች ወይም 13 በመቶ ብቻ ማለፋቸውን የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት አስታውቋል። በወረዳው ቤላ አምባ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለፈተናው ከተቀመጡ 44 የተፈጥሮ…
" ...ትምህርት ሚኒስቴር ለዩኒቨርሲቲ መግቢያ የወሰነው ማለፊያ ነጥብ በዞኑ ያለውን ሁኔታ ከግምት ያስገባ አይደለም " - የሰሜን ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ

በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ዞን ለዩኒቨርሲቲ መግቢያ ካስፈተኑ 42 ትምህርት ቤቶች በስድስት ትምህርት ቤቶች የተፈተኑ 679 ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት አላመጡም፡፡

ጊራና ፣ ቃሊም ፣ ኩል መሰክ ፣ ጉርጉር ደብረሮሀ ፣ ሀናመኳት ደብረሲና እና ክበበው 2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መኾናቸው ተገልጿል፡፡

የሰሜን ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ባለሙያ ወይዘሮ ሙሉ አዳነ ዞኑ ከ5 ወራት በላይ ጦርነት ሲካሄድበት በመቆየቱና አሁንም ቀጣናው ሙሉ በሙሉ ሰላሙ ባልተረጋገጠበት ተማሪዎች ለፈተና በቂ ዝግጅት ሳያገኙ ፈተና መውሰዳቸውን አስረድተዋል፡፡

አክለው " በጦርነቱ ምክንያት ከደረሰው ሥነ ልቦና ጉዳት ሳያገግሙ ተማሪዎች ፈተና መውሰዳቸው ተገቢ አለመኾኑን የገለጹት ወይዘሮ ሙሉ ትምህርት ሚኒስቴር ለዩኒቨርሲቲ መግቢያ የወሰነው ማለፊያ ነጥብ ይኸንን ግምት ውስጥ ያላስገባ ነው " ብለዋል፡፡

በዞኑ 9 ሺህ 710 ተማሪዎች ተፈትነው 3 ሺህ 657 ተማሪዎች ብቻ ናቸው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ማለፊያ ነጥብ ያመጡት።

ምንጭ፦ አሚኮ

@tikvahethiopia
''...በውጤት እና መቁረጫ ነጥቡ ዙሪያ አስፈላጊው ማብራሪያ እንዲሰጥ ለሚኒስቴር መስሪያቤቱ ጥያቄ አቅርቤ ምላሽ እየጠበኩ ነው'' የአበክመ ት/ቢሮ

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2013 ዓ/ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ የፈተና በውጤት እና መቁረጫ ነጥቡ ዙሪያ አስፈላጊው ማብራሪያ እንዲሰጥ ለሚኒስቴር መ/ቤቱ ጥያቄ አቅርቤ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ዛሬ ተገቢው ማብራሪያ እንደሚሰጥ ገልጾልኛል ሲል አስታውቋል።

ቢሮው ''ብሔራዊ ፈተና በሁለቱም ዙር በሰላማዊ መንገድ እንዲሰጥ የሚፈለግብንን ሁሉ አድርገናል። ከ12ኛ ክፍል ፈተና አኳያ የክልሉ ድርሻም ይሄው ነው።'' ሲል ነው በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ያሰፈረው።

''የአንደኛው ዙር ፈተና እንደተጠናቀቀ በሚቀጥለው ቀን ለሀገር አቀፍ ፈተናዎች ድርጅት በወቅቱ ፈተና ተሰርቋል እየተባለ በማህበራዊ ሚዲያ ሲስራጭ በነበረው የተለያየ መረጃ ምክንያት የፈተና ውጤት ትንተናው በጥንቃቄ እንዲታይ በፅሁፍ ጥያቄ አቅርበናል። ሌሎች ጠቃሚ ሀሳቦችንም በወቅቱ አቅርበናል።'' ሲል ገልጿል።

አክሎም በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በኩል አስፈላጊው ማብራሪያ ከተሰጠ በኋላ በትምህርት ቢሮው በኩል የሚፈለጉ መረጃዎች ካሉ መረጃዎችን ሳልደብቅ ገልጻለሁ ብሏል።

''የተማሪዎች ውጤት ለዞኖች፣ ወረዳዎች እና ትምህርት ቤቶች በግልፅ የተላለፈ ስለሆነ ለመሸፋፈን የሚፈልግ አካልም የለም መሸፋፈንም አይቻልም።'' ማለቱን ከቢሮው ገጽ ተመልክተናል።

@tikvahethiopia
" ከ20 ሺህ በላይ የተማሪዎች ቅሬታዎች ላይ ምላሽ ተሰጥቷል " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የፈተናዎች አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ ከፈተና እርማት እና ቅሬታዎች ጋር በተያያዘ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ም/ዋ/ዳይሬክተሩ በመግለጫቸው የፈተናው እርማት ከሰው ንክኪ ነፃ በሆነ መልኩ በጥንቃቄ የተከናወነ ቢሆንም በሁለተኛው ዙር ፈተና እርማት ላይ የቴክኒክ ችግር ማጋጠሙን እና እርማት መደረጉን ገልፀዋል፡፡

የእርማት ችግሩ የተፈጠረው በ 559 ባልበለጡ ተማሪዎች ላይ እንደሆነ እና ዳግም ምልከታ ተደርጎ መሰተካከል እንደተደረገም ጨምረው ገልፀዋል፡፡

የፈተና እርማት ችግር ማጋጠሙ የተገኘውም የፈተናዎች አገልግሎት ባደረገው ምርመራ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

ቅሬታዎችን በተመለከተም ተማሪዎች ሳይጉላሉ ባሉበት ቦታ ሆነው ቅሬታቸውን ለመፍታት የ ሚያስችል ስርዕት ተዘርግቶ መሰራቱን ገልፀዋል፡፡

በስርዓቱም ከ 20ሺህ በላይ ተማሪዎች ቅሬታቸውን አቅርበው ምላሽ መሰጠቱንም ነው የተናገሩት፡፡

በተደጋጋሚ የሚነሱ የፆታ እና የስም ስህተቶች በትምህርት ቤቶች አካባቢ የተፈጠረ ክፍተት እንጂ የፈተናዎች አገልግሎት ክፍተት አለመሆኑን ም/ዋ/ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡

በዘንድሮው አመት የተፈታኝ ተማሪዎች መብዛት እና በአገራችን ውስጥ ካሉት 47 ከፍተኛ ት/ት ተቋማት ውስጥ አሁን 43 ቱ ከፍተኛ የት/ት ተቋማት ብቻ የሚቀበሉ ስለሆነ ይህም የዩኒቨርስቲ ቅበላ አቅም አነስተኛ እንዲሆን በማድረጉ መግቢያ ነጥቡን ከፍ እንዳደረገውም ተገልጿል፡፡

በዚህ ምክኒያት በዘንድሮው አመት ፈተናውን ከወሰዱት ውስጥ 25 ፐርሰንት ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲ እንደሚገቡ ተነግሯል፡፡

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

@tikvahethiopia