TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#EthiopianAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ' ቦይንግ 777-8 Freighter ' የተሰኘውን አዲስ የጭነት ማጓጓዣ አውሮፕላን ምርት ለመግዛት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ከቦይንግ አውሮፕላን አምራች ካምፓኒ ጋር መፈራረሙን አሳውቋል።

ስምምነቱ አየር መንገዱ በዓለም አቀፍ ደረጃ እያደገ ከመጣው የካርጎ ጭነት አገልግሎት ፍላጎት ይበልጥ ተጠቃሚ የሚያደርገው ሲሆን እያስመዘገበ የሚገኘውንም ዕድገት ቀጣይነት የሚያረጋግጥ መሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ስምምነቱን አስመልክተው “በአፍሪካ አቪየሽን መስክ ቀዳሚ አየር መንገድ እንደመሆናችን መጠን ይህንን አዲስ ፣ ዘመናዊና ነዳጅ ቆጣቢ የጭነት አውሮፕላን ከቦይንግ ካምፓኒ ለመግዛት የመግባቢያ ስምምነት በመፈራረማችን ደስታ ይሰማናል” ብለዋል።

አቶ ተወልደ ፥ “ይህ አዲሱ ቦይንግ777-8F የጭነት አውሮፕላን እያደገ የመጣውን የአየር መንገዱን የካርጎ ጭነት አገልግሎት በማስፋፋት አሁን ያሉትን 66 ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ለማሳደግ በእጅጉ ይረዳዋል” ሲሉም አክለዋል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EthiopianAirlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ ' ቦይንግ 777-8 Freighter ' የተሰኘውን አዲስ የጭነት ማጓጓዣ አውሮፕላን ምርት ለመግዛት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ከቦይንግ አውሮፕላን አምራች ካምፓኒ ጋር መፈራረሙን አሳውቋል። ስምምነቱ አየር መንገዱ በዓለም አቀፍ ደረጃ እያደገ ከመጣው የካርጎ ጭነት አገልግሎት ፍላጎት ይበልጥ ተጠቃሚ የሚያደርገው ሲሆን እያስመዘገበ የሚገኘውንም…
" ቦይንግ 777-8 Freighter "

- የኢትዮጵያ አየር መንገድ እጅግ ዘመናዊ እና በጣም ግዙፍ የሆኑ 5 777-8 የጭነት አውሮፕላኖችን ለመግዛት ከቦይንግ ኩባንያ ጋር ስምምነት ፈርሟል።

- አንዱ አውሮፕላን " 400 ሚልዮን ዶላር " ገደማ የሚሸጥ ሲሆን የመጫን አቅሙ ከጃምቦ ጄት (ቦይንግ 747-400) እኩል ነው፣ ነገር ግን በ30% ያነሰ ነዳጅ ይጠቀማል።

- በአንድ ጉዞ ከ118 ቶን በላይ የሚጭን ሲሆን ከ8,100 ኪሜ በላይ መብረር ይችላል።

- ቦይንግ ይህን አውሮፕላን ይፋ ያደረገው ከወር በፊት ሲሆን እንደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ላሉ ቋሚ ደንበኞቹ ለሽያጭ ቅድሚያ ሰጥቷል ተብሏል።

- አውሮፕላኑን ለመግዛት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአፍሪካ የቀረበ የመጀመርያው ተቋም ሆኗል። የኳታር አየር መንገድ 34 አዟል።

- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይህን አውሮፕላን ሲረከብ ካሉት አውሮፕላኖች ሁሉ ግዙፉ ይሆናል።

- ቦይንግ 777-8 በጣም ግዙፍ ከመሆኑ የተነሳ አንዳንድ አየር ማረፊያዎች ሊያስተናግዱት አይችሉም፣ ስለዚህ የክንፉ ጫፍ እንዲታጠፍ ሆኖ ተሰርቷል።

- አሁን ላይ አየር መንገዱ ዘጠኝ " 777 የቀድሞ ሞዴል " የጭነት አውሮፕላኖች አሉት፣ አዲሶቹ ሲመጡ አየር መንገዱን እንዲሁም ኢትዮጵያን የበለጠ የአቪዬሽን ማዕከል ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

Credit : ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት

@tikvahethiopia
አቶ እስክንድር ነጋ በፖሊስ ተይዘው ተወሰዱ።

የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዘዳንቱን አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ አባላት እና ደጋፊዎቹን፤ ፓሊስ በ3 መኪና ጭኖ እንደወሰዳቸው ገለፀ።

ፓርቲው " ክስተቱ የተፈጠረው በሰላማዊ መንገድ የካራማራን የድል በአል ለማክበር በሄዱ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ነው " ብሏል።

ከዚህ ክስተት ቀደም ብሎ ፕሬዚደንቱ አቶ እስክንድርን ጨምሮ የባልደራስ አመራሮች የካራማራ የድል በዓልን እንዳያከብሩ ተከልክለው እንደነበረ ፓርቲው ገልጿል።

አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ አባላትና ደጋፊዎቹ በአሁን ሰአት በልደታ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ እንደሚገኙም ፓርቲው አሳውቋል።

ክስተቱን በተመለከተ በፖሊስ የሚሰጥ ማብራሪያ ካለ ተከታትለን የምናሳውቅ ይሆናል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሰሜን ኮሪያ ሚሳኤል አስወነጨፈች። ትላንትና ለሊት ሰሜን ኮሪያ የተጠረጠረ ባላስቲክ ሚሳኤል ማስወንጨፏን የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አሳውቋል። ፅ/ቤቱ ተጨማሪ መረጃ ሲያገኝ ለህዝብ እንደሚያሳውቅ ገልጿል። ሚሳኤሉ ወደ ጃፓን ባህር አቅጣጫ መወንጨፉ ነው የተነገረው። ደቡብ ኮሪያ በበኩሏ ሰ/ኮሪያ ሚሳኤል ማስወንጨፏን ገልጻ ሚሳኤሉ በምስራቅ አቅጣጫ በኩል የተወነጨፈ ነው ብላለች። ባለፈው ጥር…
ሰሜን ኮሪያ ሚሳኤል አስወነጨፈች።

ትላንትና ለሊት ሰሜን ኮሪያ የተጠረጠረ ባላስቲክ ሚሳኤል ወደ ምስራቅ ባህር ማስወንጨፏን ጎረቤቶቿ እየገለፁ ይገኛሉ።

የደረሰ ጉዳት የለም።

ፒዮንግያንግ ይህ የሚሳኤል ማስወንጨፍ ሙከራዋ 2022 ከገባ ጊዜ አንስቶ 9ኛው መሆኑ ነው።

የአሜሪካ እና የደቡብ ኮሪያ የደህንነት ባለስልጣናት የሰሜን ኮሪያን እንቅስቃሴ በቅርበት እየተከታተሉት ነው ተብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አቶ እስክንድር ነጋ በፖሊስ ተይዘው ተወሰዱ። የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዘዳንቱን አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ አባላት እና ደጋፊዎቹን፤ ፓሊስ በ3 መኪና ጭኖ እንደወሰዳቸው ገለፀ። ፓርቲው " ክስተቱ የተፈጠረው በሰላማዊ መንገድ የካራማራን የድል በአል ለማክበር በሄዱ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ነው " ብሏል። ከዚህ ክስተት ቀደም ብሎ ፕሬዚደንቱ አቶ እስክንድርን ጨምሮ የባልደራስ አመራሮች የካራማራ…
#Update

" ፕሬዜዳንቱ እስክንድር ነጋ ብቻ ሲለቀቁ ሌሎቹ በሙሉ ለእስር ተዳርገዋል " - ባልደራስ ፓርቲ

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ከ25 በላይ አባላቱ እንደታሰሩ አስታወቀ።

ይህን ያሳወቀው ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ ነው።

ዛሬ የካቲት 26 የሚከበረውን የ " ካራማራ የድል " በዓል ለማክበር በ " ድላችን ሀውልት " የተገኘው የባልደራስ ቡድን ወደ አደባባዩ እንዳይገባ ከተደረገ በኋላ፣ የቡድኑ አባላት በሙሉ ወደ ልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደዋል ሲል አመልክቷል።

ባልደራስ ፓርቲ ፤ ፕሬዘደንቱ እስክንድር ነጋ ብቻ ሲለቀቁ ሌሎቹ በሙሉ ለእስር ተዳርገዋል ሲል አሳውቋል።

አባላቱ ምንም አይነት የህግ ጥሰት ሳይፈጽሙ፣ ከህግ ውጭ መታሰራቸውን የገለፀው ባልደራስ አጠቃላይ ታሰሩብኝ ያላቸውን አባላት ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል።

ከእነዚህ መካከል የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ስንታየሁ ቸኮል ፣ አስቴር ስዩም ፣ አስካል ደምሌ ይገኙበታል።

(ሙሉ የስም ዝርዝር ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ተስማምተዋል ዛሬ ሀሙስ በቤላሩስ በተካሄደው 2ኛ ዙር ውይይት ሩስያ እና ዩክሬን ሰላማዊ ዜጎች ከዩክሬን የውጊያ ቀጠና የሚወጡበትን መንገዶች ለማመቻቸት ተስማምተዋል። የዩክሬን ፕሬዝዳንት ረዳት የሆኑት ሚካሂል ፖዶሊያክ " 2ቱም ወገኖች በጊዜያዊ የተኩስ አቁም የሰብአዊነት ኮሪደሮችን በጋራ ማቋቋም ላይ መግባባት ላይ ደርሰዋል። እነዚህንም ኮሪደሮችን ለማደራጀት ሩሲያ እና ዩክሬን በቅርቡ የግንኙነት…
#Update

የሩስያ እና ዩክሬን ስምምነት ተግባራዊ ሆነ።

ከቀናት በፊት ሩስያ እና ዩክሬን ባካሄዱት 2ኛው ዙር የሰላም ድርድር ወቅት የሰብዓዊ ኮሪደር እንዲከፈትና ሰላማዊ ሰዎች እንዲወጡ ለማድረግ ጊዜያዊ የተኩስ አቁም እንዲደረግ መስማማታቸው ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ ዛሬ ረፋድ ጀምሮ በሩሲያ ጦር ኃይል የተከበቡ #ማሪዮፖል እና #ቮልኖቫክሃ የሚባሉ ከተሞች ላይ ጊዜያዊ የተኩስ አቁም መታወጁን ሩስያ ገልፃለች።

ዩክሬንም ይህን አረጋግጣለች።

ጊዜያዊ የተኩስ አቁሙ በከተሞቹ ያሉ ሰላማዊ ሰዎች ለቀው እንዲወጡ እድል ለመስጠት መሆኑን የሩሲያ የመከካከያ ሚኒስቴር አመልክቷል።

የሰላማዊ ሰዎች መተላለፊያ ለማመቻቸት የተደረሰው ይኸው ጊዜያዊ የተኩስ አቁም የሚመለከተው በደቡብ ምሥራቅ ዩክሬን የሚገኙትን ሁለቱን ከተሞች ብቻ እንደሆነ ሚኒስቴሩ ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ፕሬዜዳንቱ እስክንድር ነጋ ብቻ ሲለቀቁ ሌሎቹ በሙሉ ለእስር ተዳርገዋል " - ባልደራስ ፓርቲ ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ከ25 በላይ አባላቱ እንደታሰሩ አስታወቀ። ይህን ያሳወቀው ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ ነው። ዛሬ የካቲት 26 የሚከበረውን የ " ካራማራ የድል " በዓል ለማክበር በ " ድላችን ሀውልት " የተገኘው የባልደራስ ቡድን ወደ አደባባዩ…
#Update

የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ከተያዙበት አመራሮች እና አባላት መካከል ከፓርቲው ፕሬዜዳንት አቶ እስክንድር ነጋ በተጨማሪ ፣ አቶ ስንታሁ ቸኮል፣ ወ/ሮ ቀለብ ስዩም እና ወ/ሪይ አስካል ደምሌ ከእስር የተለቀቁ መሆኑን አሳውቋል።

ፓርቲው በአሁን ሰዓት 33 አባለቱ በእስር ላይ እንዳሉ ገልጿል።

ቢኒያም ታደሰ እና ሳሙኤል ዲሚትሪ የሚባሉ አባላቱ ሰግሞ ከሌሎቹ እስረኞች ተነጥለው ጊዮርጊስ የሚገኘው አዲስ አበባ ፖሊስ መወሰዳቸውን አመልክቷል።

በሌላ በኩል በፖሊስ ቁጥጥር ስር ያሉት እስረኞች እህልና ውሃ እንዳይገባላቸው ተከልክለዋል ሲል ገልጿል። ፖሊስ ይህን ለምን እንደሚያደርግ ሲጠየቅም " ከላይ በመጣ ትዕዛዛ ነው " የሚል ምላሽ እንደሰጠው ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ ጠቅሷል።

(ባልደራስ በአሁን ሰዓት በእስር ላይ ይገኛሉ ያላቸው አባላቱ ከላይ የተዘረዘሩት ናቸው)

@tikvahethiopia
" ሩስያን አውግዙ " - አሜሪካ

አሜሪካ የአፍሪካ ሀገራት ሩሲያ በዩክሬን እያደረገች ያለውን " ወታደራዊ ተልዕኮ " እንዲያወግዙ ጥሪ አቀረበች።

አሜሪካ ፥ ምንም እንኳን የአፍሪካ ሀገራት የተመድን የውሳኔ ሃሳብ ቢደግፉም አሁንም ሌሎች ሀገራት ሩሲያን ማውገዝ አለባቸው ብላለች።

በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ኃላፊ ሞሊ ፊ ዩክሬናውያን የአፍሪካን ድጋፍ እንደሚፈልጉ አስታውቀዋል።

አሜሪካ በዓለም አቀፍ መድረክ የአፍሪካ ድምጽ አስፈላጊ መሆኑን እንደምታምን ገልፃለች።

ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ አሁን ላይ በአንድ ላይ ሆኖ ድምጹን እያሰማ መሆኑን የገለጸችው አሜሪካ፤ ይህም ሉዓላዊነትን፣ ግዛታዊ አንድነትን፣ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ መፍታትን እንዲሁም የንጹሃንን ህይወት መታደግን የሚጠይቅ እንደሆነ አስታውቃለች፡፡

መረጃውን ቪኦኤን ዋቢ አድርጎ ያስነበበው አል ዓይን ኒውስ ነው።

@tikvahethiopia
#BAANKII_GADAA

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለ " ገዳ ባንክ " በመስራች ባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ የተመረጡትን 11 የቦርድ አባላት ሹመት አጽድቋል።

በዚህም፦
1. ዶ/ር ብርሃኑ አሰፋ
2. አቶ ዋስይሁን አመኑ
3. አቶ ሐምዲኖ ሜዴሶ
4. አቶ ሀይሉ ኢፋ (የኦሮሚያ ክልል የልማት ድርጅት ተቆጣጣሪ ባለሥልጣንን በመወከል)
5. ኢ/ር አብዶ ገለቶ
6. ዶ/ር ሀሰን ሁሴን
7. አቶ ሙለታ ደበል
8. አቶ ሽፈራው ሩፌ
9. ወ/ሮ ሰሚራ አብደላ
10. አቶ አላዛር አዱላ
11. ዶ/ር ደገፋ ዱሬሳ የቦርድ አባላትነታቸው ጸድቋል።

ብሔራዊ ባንክ የቦርድ አባላቱ ሥራ መጀመር የሚችሉ መሆኑን ያስታወቀ ሲሆን በተቻለ ፍጥነት በባንክ የሥራ አመራር፤ በኮርፖሬት አስተዳደር፤ በውስጥ ቁጥጥር፤ በስጋት አስተዳደር፤ በባንክ ህግ ማዕቀፍ ላይ ተገቢውን ስልጠና እንዲወስዱ አሳስቧል።

More : @tikvahethmagazine
የጋራ ግብረ ኃይሉ ማሳሰቢያ ሰጠ።

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ቡድኖችና ግለሰቦች ሰሞኑን በሀገሪቱ በታላቅ ድምቀት በተከበሩ የአድዋ ድል በዓልን እና በዛሬው ዕለት ተከብሮ በዋለው የካራማራ ድል በዓል ላይ በመገኘት በሀገራችን ብሄር ብሄረሰቦችና በህዝብ መካከል ግጭት ለመቀስቀስ ሞክረዋል አለ።

ይህን ያለው ዛሬ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ነው።

ግብረኃይሉ ፥ " ደከመን ሰለቸን ሳይሉ የህዝቡን ሰላምና ደህንነት ሌት ተቀን የሚጠብቁ የፀጥታ አካላትን ክብር አስፀያፊ ስድቦችን በመሳደብ ደፍረዋል " ብሏል።

ከፀጥታ ኃይሎች ጋር አላስፈላጊ ግጭት ውስጥ ለመግባት ያልፈነቀሉት ድንጋይ አልነበረም ሲል ገልጿል።

ነገር ግን የፀጥታ ኃይሎች ሁሉንም ትንኮሳዎች በትግስት በማለፍ በዓላቱ በሰላምና በድምቀት እንዲከበሩ ማድረጋቸውን ገልጿል።

ግብረ ኃይሉ ውስን የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ቡድኖች እና ግለሰቦች የሚፈልጉትን በግልፅ ህግና ስርዓት ተከትለው ማድረግና ሐሳባቸውን በነፃና በዴሞክራሲያዊ መንገድ በተፈቀደላቸው ስፍራ ማራመድና መፈፀም ሲችሉ ብሄርን ከብሄር፣ ሀይማኖትን ከሀይማኖት ጋር ለማጋጨት ስራዬ ብለው ሌት ተቀን በህቡዕ እና በግልጽ ጭምር እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን ደርሼበታለሁ ብሏል።

እነዚህ ውስን የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ቡድኖችና ግለሰቦች ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ሲል ግብረ-ኃይሉ አሳስቧል።

ማንም ከህግ በላይ ስላልሆነ ህግ ጥሰን ድርጊታችንን እንቀጥላለን የሚሉ ከሆነ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ እንዲሁም በህግ ተጠያቂ እንደሚያደርጋቸው የጋራ ግብረኃይሉ አስጠንቅቋል።

የጋራ ግብረ ኃይሉ በመግለጫው ላይ ውስን የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ቡድኖችና ግለሰቦች ያላቸውን በስም አልገለፀም።

@tikvahethiopia
#CBE

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከዚህ ቀደም በተቀመጠው ቀነ ገደብ መረጃቸውን ያላሟሉ ደንበኞቹን ሒሳባቸውን ማንቀሳቀስ እንዳይችሉ አደረገ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ መሰረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያወጣውን መመሪያ ተከትሎ መረጃቸውን ያላሟሉ ደንበኞቹን ሒሳባቸውን ማንቀሳቀስ እንዳይችሉ አግዷል።

ባንኩ የደንበኞቹን መረጃ የማደራጀት እና የማጥራት ስራ እ.ኤ.አ እስከ የካቲት 27 ቀን 2022 ድረስ መሰራቱ እና በርካታ ደንበኞቹም መረጃቸውን ወቅታዊ ማድረጋቸውን ገልጿል።

ቀሪ መረጃቸውን ወቅታዊ ያላደረጉ ደንበኞቹ ወደ ማንኛውም የባንኩ ቅርንጫፍ እስከ አርብ መጋቢት 2 ቀን 2014 ብቻ በመሄድ ሒሳባቸውን ማንቀሳቀስ የሚያስችል መረጃ እንዲሰጡ ጠይቋል።

ከመጋቢት 2 ቀን 2014 ዓ.ም በኋላ ባሉት ቀናት ማንኛውንም የባንክ አገልግሎት (የሞባይል ባንኪንግ ፣ የኢንተርኔት ባንኪንግ እንዲሁም የኤቲኤም እንዲሁም የፖስ አገልግሎት) ማግኘት አይችሉም ብሏል።

Via : @tikvahethmagazine
#UKRAINE #NATO

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮልድሚር ዜሌንስኪ ዛሬ በመዲናቸው ኬዬቭ ሆነው በቴሌቪዥን ለህዝባቸው ባሰሙት ንግግር ላይ የተናገሩት ፦

" ...ምዕራባውያን መሪዎች ሩሲያ አገራችንን ልትወር መሆኗን ያውቁ ነበር፤ ፑቲን ከተሞቻችንን በቦምብ እንዲደበድቡ ፈቅደዋል።

በዩክሬን ላይ ጥቃት እንደሚፈጸም እና ጉዳትም የማይቀር መሆኑን እያወቀ NATO ሆን ብሎ የዩክሬን ሰማይ ለበረራ ዝግ እንዳይሆን አድርጓል።

የNATO መሪዎች ዛሬም ከበረራ ነጻ የሆነ ቀጠና ውሳኔን ባለማሳለፋቸው ምክንያት ተጨማሪ የዩክሬን ከተሞች እና መንደሮች በቦምብ እንዲደበደቡ ፈቅደዋል።

NATO ዩክሬንን ለመከላከል እርምጃ ባለመውሰዱ በጦርነቱ ምክንያት ለሚሞቱ የአገራችን ዜጎች ሕይወት ተጠያቂ ነው። "

ለምንድነው NATO የዩክሬንን አየር ማይዘጋው ?

NATO በምድርም ሆነ በአየር ወደ ዩክሬን የመግባት ፍላጎት የለውም።

ለNATO ውሳኔ ምዕራባውያን ባለሥልጣናት እንደምክንያት የሚያስቀምጡት በዩክሬን ከበረራ ነጻ የሆነ ቀጠና ከተከለለ የNATO አውሮፕላኖች ጥሰት በሚፈጽሙ የሩሲያ ተዋጊ አውሮፕላኖች ላይ ጥቃት መሰንዘር ይችላሉ።

ይህ ደግሞ 3ኛው የዓለም ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል ስጋት አላቸው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UKRAINE #NATO የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮልድሚር ዜሌንስኪ ዛሬ በመዲናቸው ኬዬቭ ሆነው በቴሌቪዥን ለህዝባቸው ባሰሙት ንግግር ላይ የተናገሩት ፦ " ...ምዕራባውያን መሪዎች ሩሲያ አገራችንን ልትወር መሆኗን ያውቁ ነበር፤ ፑቲን ከተሞቻችንን በቦምብ እንዲደበድቡ ፈቅደዋል። በዩክሬን ላይ ጥቃት እንደሚፈጸም እና ጉዳትም የማይቀር መሆኑን እያወቀ NATO ሆን ብሎ የዩክሬን ሰማይ ለበረራ ዝግ እንዳይሆን…
" ዩክሬን በዚሁ ከቀጠለች ሀገርነቷን ልታጣ ትችላለች " - ቭላድሚር ፑቲን

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዛሬ በነበራቸው ስብሰባ የዩክሬንን አመራሮች " አሁን እያደረጉ ያሉትን ድርጊት ማድረጋቸውን ከቀጠሉ ዩክሬን ሀገርነቷን ልታጣ ትችላለች " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ፑቲን ፥ " አሁን ያሉት አመራሮች እየሰሩት ያለውን ስራዎች ከቀጠሉ የዩክሬን ግዛትን የወደፊት ሁኔታ አደጋ ላይ እንደሚጥሉ መረዳት አለባቸው " ያሉ ሲሆን " ይህ ከሆነ እራሳቸው ተጠያቂ ሊሆኑ ይገባል " ብለዋል።

ዛሬ በነበራቸው በዚሁ ስብሰባ ላይ ቭላድሚር ፑቲን ምዕራባውያን አገሮች በሩሲያ ላይ የጣሉትን ማዕቀቦች " ጦርነት ከማወጅ ጋር ተመሳሳይ ነው " ብለውታል።

በሌላ በኩል ፑቲን በዩክሬን ሰማይ ላይ የበረራ ክልከላን ለመጣል የሚደረግ ሙከራ በዓለም ላይ አስከፊ የሆነ መዘዝ ያስከትላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ፕሬዜዳንቱ ፤ በዩክሬን ሰማይ የበረራ ክልከላ ለማድረግ የሚሞክር የትኛውም ኃይል በጦርነቱ ውስጥ ተሳትፎ እንዳደረገ እንደሚታይ እና እንዲህ ያለው እርምጃ ለአውሮፓ እና ለዓለም አስከፊ መዘዝ የሚያስከትል መሆኑን ነው የገለፁት።

ፕሬዜዳንት ፑቲን ፤ በድጋሜ አላማቸው የሩሲያኛ ተናጋሪ ማህበረሰቦችን ከጥቃት መከላከል፤ ዩክሬን ገለልተኝት እንዲሁም ለሩሲያ ስጋት እንዳትሆን ማድረግ መሆኑ አስታውቀዋል።

@tikvahethiopia