TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ድርቅ

በኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎች ያለው የድርቅ ሁኔታ ፦

#Oromia 📍

• በቦረና እና ምስራቅ ባሌ ዞኖች ባሉ 14 ወረዳዎች ብቻ 61 ትምህርት ቤቶች በድርቅ ምክንያት ተዘግተዋል።

• በምስራቅ እና ምዕራብ ሀረርጌ ፣ በቦረና ፣ በምዕራብ ጉጂ ፣ በምዕራብ አርሲ እና ባሌ ዞኖች በሚገኙ 70 ወረዳዎች ውስጥ በ605 ቀበሌዎች 2.8 ሚሊዮን ሕዝብ የመጠጥ ውኃ ይፈልጋል።

• 257 ሺ እንስሳት አቅም አንሷቸዋል።

• በቦረና እና ምስራቅ ባሌ ዞኖች አካባቢዎች ከ 3.1 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ድጋፍ ይሻሉ። ከነዚህ ውስጥ 8 ሺህ 244ቱ በአዲሱ ድርቅ ተጠቂ የሆኑ ናቸው።

• የውኃ ችግር ለማቃለልል 100 ውኃ ጫኝ ቦቴዎች ውኃ እያሰራጩ ይገኛሉ።

• ለ2ቱ ዞኖች 254 ሺህ ኩንታል እህል ለ853 ዜጎች ተልኳል።

#Somali📍

• 915 ት/ቤቶች ከሥራቸው ተስተጓጉለዋል። ከነዚህ 316ቱ ሙሉ በሙሉ ተዘግተዋል።

• በ83 ወረዳዎች 3.1 ሚሊዮን ሕዝብ ለውኃ እጥረት ተጋልጧል።

• 2.4 ሚሊዮን ሕዝብ ለምግብ እጥት ተጋልጧል። ከእነዚህ እና አጠቃላይ 3 ሚሊዮን 360 ሺህ ሕዝብ የምግብ ድጋፍ እንደሚሻም ተናግረዋል።

• ከሀምሌ እስከ የካቲት ባለው የድርቅ ጊዜ 864 ሺህ 43 እንስሳት መሞተዋል።

• 58 ሺህ 305 ሰዎች በድርቁ ተጠቅተዋል። እነዚህ ሰዎች ወደ ሌሎች ድርቅ ወዳልተከሰተባቸው አካባቢዎች እንዲሄዱ ተደርጓል።

• መንግሥት ከመስከረም እስከ ጥር ድረስ ለ1.7 ሚሊዮን ሰዎች 530 ሺ ኩንታል እህል እንዲከፋፈል አድርጓል።

• አሁን ላይ 159 የውኃ መጫኛ ቦቴዎች ለ 81 ወረዳዎች ውኃ እንዲያሰራጩ እየተደረገ ነው።

[ የብሄራዊ አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን 👉 ለጀርምን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ የሰጠው መረጃ ]

@tikvahethiopia
#ALERT🚨

" ሰባ ሰባት እንኳን አንዲህ አልነበረም "

ሰሀላ ሰዬምት ወረዳ በከባድ ድርቅ መመታቱ ተገልጿል።

በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ስር ያለው ሰሀላ ሰዬምት ወረዳ 13 ቀበሌዎች አሉት።

ወረዳው የ2015/2016 የምርት ዘመን #ድርቅ ክፉኛ መትቶታል።

ወረዳው በከፊል አርብቶ አድር የሚታወቅ ሲሆን ከማሳው በሚያገኛት ጥቂት ኩንታል እህል በይበልጥ ለገለባው ዋጋ ሰጥቶ በእንሰሳቱ ኑሮውን የሚገፈ አርሶና አርብቶ አደር አካባቢ ነው።

በወረዳው ከፍተኛ የእንስሳት ሀብትም ይገኛል።

ጠቅላላ ካለው የእንስሳት ሀብት የዳልጋ ከብት 104,430፣ የጋማ ከብት 22,121 በግ እና ፍየል 465,428 ይገኙበታል።

ከዚህ ውስጥ ለድርቅ የተጋለጡ የዳልጋ ከብት 92,430፣ የጋማ ከብት 16,121፣ በግ እና ፍየል 396,760 ናቸው።

ወደአጎራባች ዞን የተሰደዱ የዳልጋ ከብት 20,328 ፣ በግ እና ፍየል 116,900 ሲሆኑ እስካሁን በድርቅ ምክንያት የሞተ የዳልጋ ከብት 1320 ፣ የጋማ ከብት 71 በግ እና ፍየል 2457 ናቸው።

በወረዳው ከ52 ሺህ በላይ ህዝብ የሚኖርበት ሲሆን 46ሺ የሚሆነው አፋጣኝ እርዳታ ካለገኘ አደጋ ውስጥ እንደሆነ የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ ብሩ ተናግረዋል።

አቶ ሲሳይ፤ " ምንም እንኳን ድርቅ ቢሆንም ከዚህ በፊት ለእንስሳት የሚሆን ሳር አይጠፋም ነበር። ዛሬ ግን የተቃጠለ መሬት ብቻ ነው የሚታየው፤ ለጥርስ ስጋ ማውጫ የሚሆን የሳር ስንጥር እንኳን አይታይም፤ የወረዳው ነዋሪዎች እንደነገሩን እንደ ወረዳችን እንዲህ አይነት ድርቅ አይተን አናውቅም፤ ሰባሰባት እንኳን አንዲህ አልነበረም " በማለት የድርቁን አስከፊነት ገልጸዋል።

በወረዳው የአርሶ አደሩ ማሳ ርቃኑን ቀርቷል፣ እንስሳት ቆዳቸው ከስጋቸው መጣበቅ ብቻ ሳይሆን ነፍሳቸው በጣዕረሞት ላይ ናት፣  ህጻናት፣ እናቶችና አረጋውያን በርሀብ ተገርፈው ነፍሳቸው ከጉንጫቸው ተጣብቃ ይዛቸው ልትጠፋ አፋፍ ላይ ነች። ተሎ መድረስ ካልተቻለ አሳዛኝ ክስተት በሰሀላ ሰዬምት ወረዳ ሊከሰት ይቻላል።

የአስተዳደሩ የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽ/ቤት ጉዞ አዘጋጅቶ የነበረ ሲሆን የብሄረሰቡ ከፍተኛ አመራሮችና አንዳንድ ግብረሰናይ ድርጅቶች በወረዳው ተገኝተው ቀበሌዎቹን ጎብኝተው ከነዋሪዎች ጋር ውይይት አድርገው ነበር።

የቀበሌው ማህበረሰብ በውይይቱ ላይ " ከእግዚአብሄር በታች መንግስት ነበር ለሰው ልጅ ዋስትና፣ ዛሬ ግን መንግስትም ፊቱን አዞረብን " ብለዋል።

" በዚህ ሳምንት ውስጥ የሚበላ ካልቀረበ ልጆቻችን አናገኛቸውም ፤ አሁንም ቢሆን አንዲት እንጀራ ለ10 ሰው ነው የምንሻማው፤ ከዛ ውጭ ግን ጨው በውሀ በጥብጠን ነው የምንጠጣው " ብለዋል።

እስካሁንም በወረዳው በርሀብ ምክኒያት የ2  ሰዎች ሂይወት አልፏል ሲሉ አሳውቀዋል።

እንስሳትን በተመለከተ " በወረዳችን ትንሽ እህል ካገኘን እንሰሳ ስለምናረባ ከብት እና ፍየሎቻችንን ሸጠን እህል ስለምንሸምት ብዙም አያሳስበንም ነበር፤ ዘንድሮ ግን ለከብቶችም ሆነ ለፍየሎችና በጎች የሚሆን የሚጋጥ ሳር ስለሌለ ተስፋ አስቆርጦናል " ብለዋል።

የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ምህረት መላኩ፤ የተለያዩ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ቃል ከመግባት የዘለለ በመንግስት በኩልም ምንም የቀረበ ነገር የለም።

ለክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽ/ቤት ሪፖርት ከማድረግ ባለፈ የችግሩን አሳሳቢነት ብንገልጽም እስካሁን የተሰጠ ምላሽ የለም ብለዋል።

መረጃው ከዋግኽምራ ኮሚኒኬሽን ነው የደረሰን።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ድርቅ #ትግራይ

" ከምበላባቸው ቀናት #ጦሜን የማድርባቸው ቀናት ይበዛሉ " - የሰንዓለ ነዋሪ

" በድርቅ ምክንያት 6 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል ፤ ... 89 ከመቶ ነዋሪ በከባድ የደርቅ አደጋ ላይ ይገኛል " -  ዒስራ ዓዲ ወጀራት ወረዳ

በትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ዒስራ ዓዲ ወጀራት ወረዳ ባጋጠመው ድርቅ ምክንያት 6 ሰዎች መሞታቸውን የወረዳው የኢኮኖሚ ዘርፍ ፅህፈት ቤት አስታወቀ።

ፅ/ቤቱ ፤ በወረዳው ቀበሌ ገበሬ ማህበራት ያጋጠመው ድርቅ በጊዜው ካልተገታ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር ይችላል ሲል አስጠንቅቋል።

ወ/ሮ ኣልጋነሽ ከበደ በወረዳው የሰንዓለ ነዋሪ የእድሜ ባለፀጋ ናቸው።

ወ/ሮ ኣልጋነሽ ፤ ከማሳቸው የሚያገኙት ገቢ ከአመት አመት ስለማይመግባቸው ድሮውኑ በሴፍትኔት እገዛ ሲተዳደሩ ነበር።

በጦርነቱ ምክንያት የሴፍትኔት አገልግሎት በመቆሙ የዘንድሮ ድርቅ መቋቋም አቅቷቸዋል። በዛ ላይ አህታቸው በረሃብ ምክንያት በመሞትዋ ሁለት ልጆችዋን የመንከባከብ ሃላፊነት በእሳቸው ላይ ወድቀዋል።

ወ/ሮ ኣልጋነሽ ችግሩ የሚይዙት የሚጨብጡት አሳጥቷቸው ከሚበሉባቸው ጦማቸው የሚያድሩባቸው ቀናት እንደሚበዙ ተናግረዋል።

ከወረዳዋ ሰንዓለ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ብቻ ድርቅ ባስከተለው ችግር ቄያቸው ጥለው ከተሰደዱ 40 የቤተሰብ አስተዳዳሪዎች አንድዋ ወ/ሮ ፎቴን ኣባዲ ናቸው።

በድርቁ ምክንያት ከማሳቸው ያገኙት ገቢ ባለመኖሩ ፣ በዛ ላይ ከምግባረ ሰናይ ተቋማትና መንግስት የሚሰጥ እርዳታ በመቆሙ ቤታቸው ቆልፈው እግራቸው ወደ መራቸው ተሰደዋል። 

ድርቅ ባስከተለው ረብ አስከአሁን 6 ሰዎች መሞታቸው የሚገልፁት የወረዳው የኢኮኖሚ ዘርፍ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ሃሪፈያ ግደይ ፤ የወረዳው 89 ከመቶ ነዋሪ በከባድ የደርቅ አደጋ ላይ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።  

የምግባረ ሰናይ ድርጀቶች የፌደራልና የክልሉ መንግስታት ችግሩ በመረዳት ቶሎ እንዲደርሱ ጥሪ ያቀረቡት ሃላፊዋ ፣ በተለይ እናቶችና ህፃናት ታሳቢ ያደረገ አስቸኳይ መፍትሄ እንዲደረግ ማሳሰባቸውን የትግራይ ቴሌቪዥንን ዋቢ በማድረግ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ዘግቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በትግራይ ያጋጠመው ደርቅ የሚመለከት ተከታታይ መረጃዎችን በማቅረብ ላይ ሲሆን ፤ በክልሉ ምስራቃዊ ዞን ሶስት ወረዳዎች ባጋጠመ የድርቅ አደጋ የበርካታ ሰዎች ህይወት ማለፉን የክልሉ የመንግስት አካላት መናገራቸውን መዘገቡ ይታወሳል።
                      
@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
" እስካሁን ባለኝ መረጃ በረሃብ ምክንያት የሚሞት ሰው የለም " - ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለህ/ተ/ም/ቤት እየሰጡት ባለው ማብራሪያ ፤ " እስካሁን ባለኝ መረጃ በረሃብ ምክንያት የሚሞት ሰው የለም " ሲሉ ተናግረዋል። " በትግራይ የተወሰነ አካባቢ ፣ በአማራ የተወሰነ አካባቢ ፣ በኦሮሚያ ፣ ምስራቁ ክፍልም እንዲሁ ድርቅ አለ " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " ይህ ምንም ጥያቄ…
#ድርቅ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድርቅን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ " አሁን የተከሰተው ከ77ም ያልተናነሰ ነው " በሚል ከዚህ ቀደም የተሰጡ አስተያየቶችን ኮነኑ።

" የሚታረስ መሬት እያለን የሰው ጉልበት እያለን ድህነንት እና ልመናን ጌጥ አናድርገው " ያሉት ዶ/ር ዐቢይ አህመድ " ተቸግረዋል ሊያልቁ ነው ሲሉን እንደ ሽልማት አንውሰደው ኮሮና መጣ ሊረግፉ ነው አሉ ረገፍን እንዴ ? አልረገፍንም ሟርት ነው። ጦርነት ስንጀምር ታስታውሳላችሁ ረሃብ ረሃብ ረሃብ አሉ እውነት ነው እንዴ ? " ሲሉ ተናግረዋል።

" በአንድ በኩል መዘናጋት የለብንም ችግር ሲመጣ ተረባርባን እንፍታው " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " 6 ወር ያልፍና የታለ የሞተ ሰው ፣ የተባለው የታለ ሲባል ማፍር ያመጣል " ብለዋል።

" አንዳንዱ ከ77 ያልተናነሰ ድርቅ አለ ይላል ማለትም 1 ሚሊዮን ገደማ ሰው ይሞታል ማለት ነው ፤ አንድ ሚሊዮን ካልሞተ እየዋሸ ነው ሰውየው እኛ ደግሞ 1 ሚሊዮን ሳይሆን አንድም እንዳይሞት አቅማችን በፈቀደ እንፍጨረጨራለን ከአቅም በላይ ከሆነስ ? እሱ ምን ይደረጋል " ብለዋል

አሁን ኢትዮጵያ ባለችበት ሁኔታ ከተረባረበች ቢያንስ ሰው እንዳይሞት የማድረግ አቅም እንዳላት ተናግረዋል።

ከወራት በፊት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የአደጋ መከላከያ እና ዝግጁነት ኮሚሽን ኮሚሽነር ገብረሕይወት ገ/እግዚአብሔር (ዶ/ር) ፤ በትግራይ የከፋው ድርቅ የተከሰተው በ1951 እና በ1977 እንደነበርና አሁን ያጋጠመው ከዚህም በላይ እንደሆነ ተናግረው ነበር።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በቅርቡ ፤ " በትግራይ ረሃብ እና ሞት እያንዣበበ ነው "  ያሉ ሲሆን ከ1977 በኋላ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ እጅግ የከፋ ድርቅ ነው የተከሰተው ሲሉ ተናግረው ነበር።

በእድሜ የገፉ አዛውንቶችም በክልሉ ቴሌቪዥን ቀርበው መሬት እህል አላበቅል እንዳላቸውና ሁኔታው ከ1977 የከፋ እንደሆነ መናገራቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia