TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ... ሁሉም ወገን ቀውስን ከሚያባብስ ድርጊት ታቅቦ ግጭቱን ለመፍታት ሁልንተናዊ የሰላም መንገዶችን ሊጠቀም ይገባል " - ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

የኢትዮጵያ 🇪🇹 ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ በዩክሬን ቀውስ ውስጥ ሁሉም ወገኖች ግጭትን ከሚያባብሱ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ ጠየቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዩክሬን ውስጥ የተፈጠረውን ቀውስ በተመለከተ ዛሬ ባስተላለፉት መልዕክት " ኢትዮጵያ በቅርቡ ካለፈችበት ጦርነት ተነስታ ስለ ጦርነት ጉዳት የምታካፍለው ሰፊ ልምድ አላት " ብለዋል።

ዶ/ር ዐቢይ ፥ " የኢትዮጵያ ልምድ ጦርነት ቤተሰብን ፣ ማህበረሰብ ብሎም የሀገርን ኢኮኖሚን ክፉኛ የሚጎዳ፣ አጥፊ ነው " ሲሉ ገልፀዋል።

ጦርነት የሚያደርሰውን ቁሳዊ ጉዳት መጠገን ቢቻልም በማህበረሰብ ላይ ጥሎት የሚያልፈውን ጠባሳ ግን ለማከም ከባድ መሆኑን አመልክተዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፥ " ኢትዮጵያ #የዩክሬን ወቅታዊ ቀውስ በቅርበት እየተከታተለች ነው " ያሉ ሲሆን ግጭቱን የሚያባብሱ ሁኔታዎች እንደሚያሳስባት ገልፀዋል።

ሁሉም ወገኖች ቀውስን ከሚያባብስ ድርጊት ታቅበው ግጭቱን ለመፍታት ሁልንተናዊ የሰላም መንገዶችን እንዲጠቀሙ ጠይቀዋል።

በአካባቢው ላይ #ሰላም እንዲሰፍን ያላቸውን ምኞት መግለፃቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#Bank_of_Abyssinia

በብዙ ምክንያቶች የዐሥራት በኲራት ግዴታችንን ሳንወጣ የቀረንና ማድረግ እየፈለግን ያልፈጸምን በርካቶች ነን።

አቢሲንያ ባንክ ያለብንን ሃይማኖታዊ ግዴታ እያስታወሰ በየወሩ ዐሥራታችንን እንድናወጣ ያቀረበልን ምርጥ መፍትሔ ዐሥራት በኲራት ልዩ የሒሳብ ደብተር።

በየወሩ እንዲያወጡ የሚያስችል የዐሥራት በኲራት ሒሳብ። የአቢሲንያ ባንክን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻነል ይቀላቀሉ! https://t.iss.one/BoAEth
የትራፊክ ቅጣት መክፈያ 👉 6050

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የትራፊክ ደንብ ተላላፊ አሽከርካሪዎች የቅጣት ክፍያ ስርዓትን የሚያቀላጥፍ እና የሚያዘምን አዲስ አሰራርን ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ዛሬ ይፋ አድርጓል።

የትራፊክ ህግ ተላላፊ አሽከርካሪዎች የትራፊክ ቅጣት ክፍያን ለመፈፀም በኢትዮ-ቴሎኮም የተዘጋጀው 6050 አጭር ቁጥር መጠቀም ይችላሉ ተብሏል።

አዲስ ይፋ የተደረገው የትራፊክ ቅጣት ክፍያ ስርዓት በ6050 አጭር ቁጥር በመጠቀም ትራፊክ ፖሊሶች እና የኤጀንሲው የቁጥጥር ባለሙያዎች በወረቀት ይደረግ የነበረውን አሰራር እንደሚያስቀር ተገልጿል።

ቅጣቱን በሞባይል ስልክ ለተቀጪው በማድረስም መንጃ ፈቃዱ ሳይያዝበት ወይም ታርጋው ሳይፈታበት ጥፋቱን በፈፀመበት ቦታ ክፍያውን መፈፀም ያስችለዋል ተብሏል።

የትራፊክ ደንብ ቅጣት ክፍያን በቴሌብር አማካኝነት መክፈል የሚያስችለው ይህ አገልግሎት ወይም አሰራር ለዘመናት አድካሚ የነበረውን በወረቀት ላይ ያተኮረ የቅጣት ክፍያ አፈጻጸምን የሚያስቀር ነው ተብሎለታል።

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ

@tikvahethiopia
" ሩስያ ያቀደችውን ታሳካለች " - ቭላድሚር ፑቲን

የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ከፈረንሳዩ አቻቸው ኢማኑኤል ማክሮን ጋር 90 ደቂቃ ያህል የፈጀ የስልክ ውይይት አድርገዋል።

በዚሁ ወቅት ፑቲን ሞስኮ ዩክሬን ውስጥ በምታካሂደው ዘመቻ ያቀደችውን ታሳካለች ብለዋል።

ፑቲን አስተዳደራቸው የኪዬቭን ወታደራዊ እንቅስቃሴ በማስቆም ለሩሲያ ደኅንት ወታደራዊ ስጋት እንዳትሆን እናደርጋለን ስለማለታቸው የሩሲያ መንግሥት አስታውቋል።

ሩሲያ የዩክሬንን ወታደራዊ እንቅስቃሴ የማስቆም እና ገለልተኛ የማድረግ ዓላማ ማሳካት ትችላለች ሲሉ ቭላድሚር ፑቲን ለኢማኑኤል ማክሮን ተናግረዋል።

በተጨማሪ ቭላድሚር ፑቲን ኪዬቭ ድርድርን ለማዘግየት ጥረት የምታደርግ ከሆነ የሞስኮ ፍላጎቶች ይጨምራሉ ሲሉ መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

ፎቶ ፦ፋይል

@tikvahetiopia
#ድርቅ

በኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎች ያለው የድርቅ ሁኔታ ፦

#Oromia 📍

• በቦረና እና ምስራቅ ባሌ ዞኖች ባሉ 14 ወረዳዎች ብቻ 61 ትምህርት ቤቶች በድርቅ ምክንያት ተዘግተዋል።

• በምስራቅ እና ምዕራብ ሀረርጌ ፣ በቦረና ፣ በምዕራብ ጉጂ ፣ በምዕራብ አርሲ እና ባሌ ዞኖች በሚገኙ 70 ወረዳዎች ውስጥ በ605 ቀበሌዎች 2.8 ሚሊዮን ሕዝብ የመጠጥ ውኃ ይፈልጋል።

• 257 ሺ እንስሳት አቅም አንሷቸዋል።

• በቦረና እና ምስራቅ ባሌ ዞኖች አካባቢዎች ከ 3.1 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ድጋፍ ይሻሉ። ከነዚህ ውስጥ 8 ሺህ 244ቱ በአዲሱ ድርቅ ተጠቂ የሆኑ ናቸው።

• የውኃ ችግር ለማቃለልል 100 ውኃ ጫኝ ቦቴዎች ውኃ እያሰራጩ ይገኛሉ።

• ለ2ቱ ዞኖች 254 ሺህ ኩንታል እህል ለ853 ዜጎች ተልኳል።

#Somali📍

• 915 ት/ቤቶች ከሥራቸው ተስተጓጉለዋል። ከነዚህ 316ቱ ሙሉ በሙሉ ተዘግተዋል።

• በ83 ወረዳዎች 3.1 ሚሊዮን ሕዝብ ለውኃ እጥረት ተጋልጧል።

• 2.4 ሚሊዮን ሕዝብ ለምግብ እጥት ተጋልጧል። ከእነዚህ እና አጠቃላይ 3 ሚሊዮን 360 ሺህ ሕዝብ የምግብ ድጋፍ እንደሚሻም ተናግረዋል።

• ከሀምሌ እስከ የካቲት ባለው የድርቅ ጊዜ 864 ሺህ 43 እንስሳት መሞተዋል።

• 58 ሺህ 305 ሰዎች በድርቁ ተጠቅተዋል። እነዚህ ሰዎች ወደ ሌሎች ድርቅ ወዳልተከሰተባቸው አካባቢዎች እንዲሄዱ ተደርጓል።

• መንግሥት ከመስከረም እስከ ጥር ድረስ ለ1.7 ሚሊዮን ሰዎች 530 ሺ ኩንታል እህል እንዲከፋፈል አድርጓል።

• አሁን ላይ 159 የውኃ መጫኛ ቦቴዎች ለ 81 ወረዳዎች ውኃ እንዲያሰራጩ እየተደረገ ነው።

[ የብሄራዊ አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን 👉 ለጀርምን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ የሰጠው መረጃ ]

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA #USA

የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን #አሜሪካ በአዲስ አበባ ለሚገኘው ኤንባሲዋ ጉዳይ እንዲያስፈፅሙላት በኃላፊነት ቦታ ላይ ካስቀመጠቻቸው አምባሳደር ትሬሲ ጃኮብሰን ጋር ተወያይተዋል።

በዚሁ ውይይት ወቅት አቶ ደመቀ ፤ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት የማጠናከር ከፍ ያለ ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን አገራዊ ምክክር ኮሚሽን መቋቋሙን እና ኮሚሽነሮችም መሾማቸውንና በቅርቡ ሁሉን አቀፍ ምክክር እንደሚጀመር ገልፀዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/ETHIOPIA-USA-03-03
TIKVAH-ETHIOPIA
" ሩስያ ያቀደችውን ታሳካለች " - ቭላድሚር ፑቲን የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ከፈረንሳዩ አቻቸው ኢማኑኤል ማክሮን ጋር 90 ደቂቃ ያህል የፈጀ የስልክ ውይይት አድርገዋል። በዚሁ ወቅት ፑቲን ሞስኮ ዩክሬን ውስጥ በምታካሂደው ዘመቻ ያቀደችውን ታሳካለች ብለዋል። ፑቲን አስተዳደራቸው የኪዬቭን ወታደራዊ እንቅስቃሴ በማስቆም ለሩሲያ ደኅንት ወታደራዊ ስጋት እንዳትሆን እናደርጋለን ስለማለታቸው…
" ከእኔ ጋር ቁጭ ብለህ ተነጋገር " - ቮልድሚር ዜኔንስኪ

የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ከሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር በቀጥታ ለመነጋገር ጠያቄ አቀረቡ።

ዜሌንስኪ ይህን ጥያቄ ያቀረቡት ዛሬ አመሻሽ ላይ በሰጡት መግለጫ ነው።

ፕሬዜዳንቱ ፤ " ጦርነቱን ለማቆም #ብቸኛው አማራጭ ከፑቲን ጋር በቀጥታ መነጋገር ነው " ብለዋል።

ዜሌንስኪ ለፑቲን ባስተላለፉት መልዕክት ፥ " ሩሲያን እያጠቃን አይደለም፤ ለማጥቃትም እቅዱ የለንም። ከእኛ ምንድነው የምትፈልገው ? መሬታችንን ትልቀቅ " ብለዋል።

ፕሬዜዳንቱ አክለው ፤ " ከእኔ ጋር ቁጭ ብለህ ተነጋገር። 30 ሜትር ሳይርቅ " በማለት ፑቲን ከፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ጋር በረዥሙ ጠረጴዛቸው ፊት ለፊት ያደረጉትን ንግግር አስታውስዋል።

ዜሌኒስኪ በመግለጫቸው ላይ #ምዕራባውያን ተዋጊ አውሮፕላኖችን እንዲሰጧቸው ጠይቀዋል።

" የአየር ክልሉን መዝጋት የማትችሉ ከሆነ ፤ አውሮፕላኖችን ስጡኝ " ሲሉ ነው ዜሌንስኪ የጠየቁት።

ምዕራባውያን የሩሲያ ተዋጊ አውሮፕላኖችን በዩክሬን ላይ ጥቃት እንዳያደርሱ የዩክሬንን አየር ክልል እንዲዘጉ ሲጠየቁ ቆይተዋል።

ዜሌንስኪ ፤ " በቀጣይ ሩሲያ ላትቪያ ፣ ሊትዌኒያ እና ኢስቶኒያን ልትወር ትችላለች " ሲሉ መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

በሌላ መረጃ ፥ የሩስያ እና ዩክሬን ሁለተኛው ዙር የሰላም ድርድር ዛሬ በቤላሩስ ተጀምሯል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ከእኔ ጋር ቁጭ ብለህ ተነጋገር " - ቮልድሚር ዜኔንስኪ የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ከሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር በቀጥታ ለመነጋገር ጠያቄ አቀረቡ። ዜሌንስኪ ይህን ጥያቄ ያቀረቡት ዛሬ አመሻሽ ላይ በሰጡት መግለጫ ነው። ፕሬዜዳንቱ ፤ " ጦርነቱን ለማቆም #ብቸኛው አማራጭ ከፑቲን ጋር በቀጥታ መነጋገር ነው " ብለዋል። ዜሌንስኪ ለፑቲን ባስተላለፉት መልዕክት ፥ " ሩሲያን…
#ተስማምተዋል

ዛሬ ሀሙስ በቤላሩስ በተካሄደው 2ኛ ዙር ውይይት ሩስያ እና ዩክሬን ሰላማዊ ዜጎች ከዩክሬን የውጊያ ቀጠና የሚወጡበትን መንገዶች ለማመቻቸት ተስማምተዋል።

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ረዳት የሆኑት ሚካሂል ፖዶሊያክ " 2ቱም ወገኖች በጊዜያዊ የተኩስ አቁም የሰብአዊነት ኮሪደሮችን በጋራ ማቋቋም ላይ መግባባት ላይ ደርሰዋል። እነዚህንም ኮሪደሮችን ለማደራጀት ሩሲያ እና ዩክሬን በቅርቡ የግንኙነት እና የትብብር መንገዶችን ይፈጥራሉ " ሲሉ ተናግረዋል።

የሩሲያው ልዑካን ቡድን መሪ ቭላድሚር ሜዲንስኪ ያለውን ሂደት አረጋግጠዋል። ሁለቱ ወገኖች የሲቪሎችን ህይወት ለማዳን " ዋናውን ጉዳይ " እንደፈቱ ተናግረዋል።

ተደራዳሪዎቹ በወታደራዊ እና በሰብአዊ ጉዳዮች እንዲሁም ወደፊት በሚደረጉ የፖለቲካ ዕርቅ ጉዳዮች ላይ የጋራ አቋም መያዛቸውንም ቭላድሚር ሜዲንስኪ ገልፀዋል።

የዩክሬን ወገን ድርድሩ የሚጠብቁትን ውጤት እንዳላመጣ ገለፀው የሚቀጥለው ዙር ድርድር በቅርብ ጊዜ ይካሄዳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ማሳወቃቸውን አር ቲ ኒውስ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
ሩብል📉

የምዕራባውያን ማዕቀብ እጅጉን የበረታባት ሩስያ የመገበያያ ገንዘቧ የሆነው #ሩብል ከአሜሪካ #ዶላር አንፃር በእጅጉ ቀንሷል።

አሁን ላይ 1 የሩስያ ሩብል $0.0085 ከ1 የአሜሪካ ሳንቲም በታች ወይም አንድ የአሜሪካ ዶላር በ117.18 የሩስያ ሩብል እየተመነዘረ ነው።

አንድ የአሜሪካ ዶላር በሩስያ ሩብል ሲመነዘር ፦

• ከአንድ ወር በፊት : 76.2 ሩብል
• ከአንድ ሳምንት በፊት : 81.4 ሩብል
• ከአንድ ቀን በፊት : 108.5 ሩብል
• አሁን : 117.18 ሩብል

ምዕራባውያን አንዳንድ የሩሲያ ባንኮች #ስዊፍት የተሰኘውን ዓለም አቀፍ የገንዘብ ማዘዋወሪያ ስርዓትን እንዳይጠቀሙ አግደዋቸዋል።

እገዳውን ተከትሎ ነው የሩሲያው ሩብል በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ደረጃ ዋጋው የወረደው።

ምዕራባውያን በሩስያ ባንኮች ላይ ጠንካራ የሆኑ ማዕቀቦችን ጥለዋል ፤ የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክም 630 ቢሊዮን ዶላር ከማንቀሳቀስ ታግዷል።

አሁንም የምዕራባውያኑ ሀገራት በሩስያ ላይ እየጣሉት ያለው ጠንካራ ማዕቀብ የሩስያን ኢኮኖሚ እንደሚያሽመደምደው እና ከዓለም አቀፉ ስርዓት እንደሚገፋው ተንታኞች እየተናገሩ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ዐቢይ_ፆም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዐቢይ ፆምን በማስመልከት ፥ " መላው ኦርቶዶክሳዊያን ወርሃ ጾሙን ፈጣሬ ዓለማት መድሃኔዓለም ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ፍጹም ምህረቱን እንዲያወርድልን በመጸለይ ልናሳልፈው ይገባል " ስትል መንፈሳዊ መልዕክቷን አስተላልፋለች። አራተኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ…
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ አርፈዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።

የቅዱስነታቸውን ሽኝት በተመለከተ ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ ተሰብስቦ በሚያስተላልፈው ውሳኔና በሚያወጣው መርሐ ግብር መሰረት የሚፈጸም መሆኑን የኢኦተቤ ህዝብ ግንኙነት አሳውቋል።

አራተኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ህመም አጋጥሟቸው በሀሌሉያ ሆስፒታል በህክምና ላይ እንደነበሩ መገለፁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#DrAbiyAhmed

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ በአራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ እረፍት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ " አራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ማረፋቸውን በመስማቴ ጥልቅ ኀዘን ተሰምቶኛል። " ብለዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ፥ ተለያይተው የነበሩት ሁለቱ ሲኖዶሶች አንድ እንዲሆኑ ቅዱስነታቸው ወሳኙን ሚና መጫወታቸውን አስታውሰዋል።

" ነገሮችን በአርምሞ እየተመለከቱ ሀገራችንን በጸሎት ያግዙ ነበር። " ያሉት ጠቅለይ ሚኒስትሩ " በዚህ ወቅት እርሳቸውን ማጣት ከባድ ጉዳት ነው። ለሁላችንም መጽናናትን እመኛለሁ " ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ አርፈዋል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል። የቅዱስነታቸውን ሽኝት በተመለከተ ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ ተሰብስቦ በሚያስተላልፈው ውሳኔና በሚያወጣው መርሐ ግብር መሰረት የሚፈጸም መሆኑን የኢኦተቤ ህዝብ ግንኙነት አሳውቋል። አራተኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ…
#Update

ቅዱስ ሲኖዶስ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ሥርዓተ ቀብር እሑድ እንዲፈጸም ወስኗል።

የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ 4ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ ሥርዓተ ቀብር እሑድ ዕለት እንዲፈጸም ውሳኔ አሳልፏል፡፡

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ሥርዓተ ቀብር በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚከናወን ተገልጿል።

@tikvahethiopia
Situation_Report_Northern_Ethiopia_Humanitarian_Update_3_Mar_2022.pdf
3.1 MB
#UNOCHA

PDF የሰሜን ኢትዮጵያ ወቅታዊ የሰብዓዊ ድጋፍ ሁኔታ ሪፖርት።

@tikvahethiopia