#UkraineCrisis
የሩስያ እና የዩክሬን ቁርሾ ምንድነው ?
ዩክሬን ወደ አውሮፓ ተቋማት NATO እንዲሁም አውሮፓ ህብረት የምታደርገውን እርምጃ ሩሲያ ስትቃወም ቆይታለች።
አሁን ደግሞ ዩክሬን #የምዕራቡ_ዓለም_አሻንጉሊት እንደሆነች እና በማንኛውም ሁኔታ ትክክለኛ ሃገር እንዳልነበረች ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ይገልፃሉ።
ዋና ፍላጎታቸው ደግሞ ዩክሬን የ30 ሃገሮች የመከላከያ ሃይል ጥምረት የሆነውን የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶን) እንደማትቀላቀል ምዕራባውያን ዋስትና እንዲሰጡ ነው።
እንደቀድሞዋ የ " ሶቪየት ሪፐብሊክ " አካል የነበረችው ዩክሬን ከሩሲያ ጋር ጥልቅ ማህበራዊ እና ባህላዊ ግንኙነት አላት። ሩስኪ በሰፊ የሚነገርባት ቢሆንም ሩሲያ እአአ በ 2014 ከወረረቻት ጊዜ ጀምሮ ግንኙነቶቹ ተበላሽተዋል።
እአአ በ2014 መጀመሪያ ላይ የሩሲያ ደጋፊ የነበሩት ፕሬዚዳንቷ ከስልጣን ሲወገዱ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ጥቃት ፈጸመች። ከዚያ ወዲህ የምስራቁ ጦርነት ከ14 ሺህ በላይ ሰዎችን ገድሏል።
ቀውሱ አሁን በምን ሁኔታ ላይ ነው ያለው ?
የሩሲያ ፕሬዝዳንት ፑቲን በዩክሬን ውስጥ ላሉ ተገንጣይ ግዛቶች እውቅና ሰጥተዋል ፤ እነዚህ ግዛቶች ዶኔትስክ እና ሉጋንስክ ይባላሉ።
ሩስያ በአማፂያን ቁጥጥር ስር በሚገኙ 2 የምስራቃዊ ዩክሬን ክልሎችን እንዲዘምቱ አዛለች፤ ምክንያት ? "ሠላምን ለማስፈን" እንደሆነ ነው የገለፀችው። የሩሲያ ጦር ወደ ሁለቱም ተገንጣይ የምስራቅ ዩክሬን ግዛቶች እንዲገባ የሚያስችል ስምምነትም በፕሬዝዳንት ፑቲን እና በአስገንጣይ ኃይሎች መካከል አለ።
የሩሲያ ፓርላማ የሀገሪቱ ጦር ከሩሲያ ውጪ እንዲሰማራ ፈቅዷል። ይህ ሁኔታ ነው ቀውሱን ያባባሰው እና አስፈሪ ያደረገው።
#BBC
@tikvahethiopia