TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ። በ2013 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ሊሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ፈተና በተለያዩ ሀገራዊ ምክንያቶች ወደ 2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተሸጋግሮ በሁለት ዙር መሰጠቱ ይታወቃል። የመጀመሪያው ዙር የሲቪክስ ፈተና በሁሉም ትምህርት ቤቶች በሚባል ደረጃ የውጤት መመሳሰልና ግሽበት ታይቶበታል። ስለሆነም የሲቪክስ የፈተና ውጤት ለዩኒቨርስቲ መግቢያ መወዳደሪያነት #እንዳያገለግል…
#ማሳሰቢያ

የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አውንታዊ ድጋፍ ለሚሹ አመልካቾች student.ethernet.edu.et በመግባት ማመልከት እንደሚችሉ ገልጿል።

በተመሳሳይም በውጤታቸው ላይ ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎች result.neaea.gov.et በመግባት እና Compliant የሚለውን በመጫን ቅሬታቸውን በፎርሙ ላይ በመሙላት ማቅረብ ይችላሉ ሲል አሳውቋል።

ኤጀንሲው ምላሹን በማመልከቻ ቅጹ ላይ በሚያስቀምጡት አድርሻ እንደሚያሳውቅ የገለፀ ሲሆን በአካል ወደ ኤጀንሲው መምጣት አያስፈልግም ብሏል።

@tikvahethiopia
#WeCare

በተለያዩ የህክምና ዘርፍ ስፔሻሊስት የሆኑ ዶክተሮችን ኦንላይን በቪድዮ፣ በድምጽ አልያም በ አጭር መልእክት ማግኘት የሚያስችል አዲስ አገልግሎት ተጀመረ።

ለራስዎ ፣ ለልጅዎ ወይም ለቤተሰቦ የሚሰማዎትን ህመም ወይም አጠራጣሪ ነገር በ WeCare መተግበሪያ በሙያው የተካኑ ሐኪሞችን በፍጥነት በማማከር እፎይታ ያግኙ!

መተግበሪያውን ለማውረድ : https://play.google.com/store/apps/details?id=com.icare.patient

አጠቃቀሙን ለመረዳት ቻናሉን @wecareet ይቀላቀሉ

ለበለጠ መረጃ : 9394 በመደወል ማብራሪያ ይጠይቁ!
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሰዎች_ለሰዎች ሰዎች ለሰዎች (Menschen for Menschen) ድርጅት በ2014/15 በጀት ዓመት 15 ሚሊዮን ዩሮ መድቧል። በዶ/ር ካርል ሄይንዝ በም እ.ኤ.አ 1981 ዓ.ም የተመሰረተው ሰዎች ለሰዎች (Menschen for Menschen) ድርጅት በ2014/15 በጀት ዓመት በአርባ ዓመት ታሪኩ ከፍተኛውን በጀት መመደቡን አስታውቋል። በዚህም 15 ሚሊዮን ዩሮ ማለትም 900 ሚሊዮን ብር በጀት…
#ሰዎች_ለሰዎች

ሰዎች ለሰዎች ድርጅት በኢትዮጵያ በቆየባቸው 40 ዓመታት ከ7 ቢሊዮን ብር በላይ ለልማት አውሏል።

ሰዎች ለሰዎች (Menschen für Menschen) ድርጅት የኢትዮጵያ እውነተኛ ወዳጅ በሆኑት በዶ/ር ካርል ሄይንዝ በም ተቋቁሞ ላለፉት 40 ዓመት የተለያዩ የልማት ሥራዎችን እና ድጋፎችን ሲያከናውን ቆይቷል።

ድርጅቱ እስካሁን በኢትዮጵያ በቆየባቸው 40 ዓመታት ከ7 ቢሊዮን ብር በላይ ለልማት ማዋሉን ጠቅሷል። በዚህም 6 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዊያን ተጠቃሚ መሆን እንዲችሉ ማድረጉን ገልጿል።

በዚህ ዓመት በታሪኩ ከፍተኛውን በጀት መድቦ በአምስት የተለዩ ተግባራት ላይ እንደሚሰራ የሰዎች ለሰዎች ድርጅት የጀርመን ሥራ አመራር ቦርድ ተጠሪ ዶክተር ሰባስቲያን ብራንዲስ ትላንት በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ጠቅሰዋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/MFM-02-23
#UkraineCrisis

የሩስያ እና የዩክሬን ቁርሾ ምንድነው ?

ዩክሬን ወደ አውሮፓ ተቋማት NATO እንዲሁም አውሮፓ ህብረት የምታደርገውን እርምጃ ሩሲያ ስትቃወም ቆይታለች።

አሁን ደግሞ ዩክሬን #የምዕራቡ_ዓለም_አሻንጉሊት እንደሆነች እና በማንኛውም ሁኔታ ትክክለኛ ሃገር እንዳልነበረች ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ይገልፃሉ።

ዋና ፍላጎታቸው ደግሞ ዩክሬን የ30 ሃገሮች የመከላከያ ሃይል ጥምረት የሆነውን የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶን) እንደማትቀላቀል ምዕራባውያን ዋስትና እንዲሰጡ ነው።

እንደቀድሞዋ የ " ሶቪየት ሪፐብሊክ " አካል የነበረችው ዩክሬን ከሩሲያ ጋር ጥልቅ ማህበራዊ እና ባህላዊ ግንኙነት አላት። ሩስኪ በሰፊ የሚነገርባት ቢሆንም ሩሲያ እአአ በ 2014 ከወረረቻት ጊዜ ጀምሮ ግንኙነቶቹ ተበላሽተዋል።

እአአ በ2014 መጀመሪያ ላይ የሩሲያ ደጋፊ የነበሩት ፕሬዚዳንቷ ከስልጣን ሲወገዱ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ጥቃት ፈጸመች። ከዚያ ወዲህ የምስራቁ ጦርነት ከ14 ሺህ በላይ ሰዎችን ገድሏል።

ቀውሱ አሁን በምን ሁኔታ ላይ ነው ያለው ?

የሩሲያ ፕሬዝዳንት ፑቲን በዩክሬን ውስጥ ላሉ ተገንጣይ ግዛቶች እውቅና ሰጥተዋል ፤ እነዚህ ግዛቶች ዶኔትስክ እና ሉጋንስክ ይባላሉ።

ሩስያ በአማፂያን ቁጥጥር ስር በሚገኙ 2 የምስራቃዊ ዩክሬን ክልሎችን እንዲዘምቱ አዛለች፤ ምክንያት ? "ሠላምን ለማስፈን"  እንደሆነ ነው የገለፀችው። የሩሲያ ጦር ወደ ሁለቱም ተገንጣይ የምስራቅ ዩክሬን ግዛቶች እንዲገባ የሚያስችል ስምምነትም በፕሬዝዳንት ፑቲን እና በአስገንጣይ ኃይሎች መካከል አለ።

የሩሲያ ፓርላማ የሀገሪቱ ጦር ከሩሲያ ውጪ እንዲሰማራ ፈቅዷል። ይህ ሁኔታ ነው ቀውሱን ያባባሰው እና አስፈሪ ያደረገው።

#BBC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UkraineCrisis የሩስያ እና የዩክሬን ቁርሾ ምንድነው ? ዩክሬን ወደ አውሮፓ ተቋማት NATO እንዲሁም አውሮፓ ህብረት የምታደርገውን እርምጃ ሩሲያ ስትቃወም ቆይታለች። አሁን ደግሞ ዩክሬን #የምዕራቡ_ዓለም_አሻንጉሊት እንደሆነች እና በማንኛውም ሁኔታ ትክክለኛ ሃገር እንዳልነበረች ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ይገልፃሉ። ዋና ፍላጎታቸው ደግሞ ዩክሬን የ30 ሃገሮች የመከላከያ ሃይል ጥምረት…
#Ukraine

አሁን ምን እየሆነ ነው ያለው ?

- ዩክሬን ፕሬዝዳንት ፑቲን አገሪቱን ሙሉ በሙሉ ለመውረር እንቅስቃሴው ተጀምሯል ብላለች።

- ዛሬ ማለዳ የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮላድሚር ዜለንስኪ ሩሲያ በአገራቸው ላጥ ጥቃት መክፈቷን አሳውቀዋል። የሚሳአኤል ጥቃት መፈጸሙን አረጋግጠዋል። ሩሲያ ዛሬ ማለዳ ላይ የከፈተችው ጥቃት ኢላማ ያደረጉት የዩክሬን መሰረተ ልማቶችና የድንበር ጥበቃዎች ላይ ነው ብለዋል። የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ሰራዊቱ ጥቃት መሰንዘሩን አረጋግጦ ኢላማዎቹ ከተሞች ላይ ሳይሆኑ የዩክሬን ወታደራዊ መሰረተ ልማቶች፣ የአየር መከላከያ እና የአየር ኃይል ተቋማት መሆናቸውን ገልጿል።

- ሩሲያ በማንኛውም ቀን "አውሮፓ ውስጥ ትልቅ ጦርነት" ልትጀምር እንደምትችል የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ አስጠንቅቀው ሩሲያውያን እርምጃውን እንዲቃወሙት ጠይቀዋል። ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ለመነጋገር ያደረጉት ሙከራ አለመሳካቱን አስታውቀዋል። "ከሩሲያ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ጋር የስልክ ንግግር ለማድረግ ሞከርኩ። ውጤቱ ዝምታ ሆነ" ብለዋል ዜለንስኪ። ሩሲያ ወደ 200 ሺህ የሚጠጉ ወታደሮች እና በሺዎች የሚቆጠሩ የውጊያ መኪናዎች በዩክሬን ድንበር እንዳሏት ተናግረዋል። ሩሲያውያን በዩክሬን ጉዳይ እየተዋሹ መሆኑን ጠቅሰው ጥቃትን እንዲቃወሙ ተማፅነዋል።

- የቭላድሚር ፑቲን በምስራቃዊ ዩክሬን #ዶንባስ ክልል ወታደሮቻቸው ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ እንዲያካሂዱ አዘዋል። በሩሲያ የሚደገፉ አማጺያኖች ጋር እየተዋጉ የሚገኙ የየክሬን ወታደሮች መሳሪያቸውን አስቀምጠው ወደቤታቸው እንዲመለሱ ጥሪ አስተላልፈዋል። ዩክሬንን የመቆጣጠር እቅድ እንደሌላቸው የገለጹ ሲሆን ነገር ግን ማንኛውም አካል ሩሲያ ላይ አደጋ የሚጭር ነገር ካደረገ ምላሻችን ፈጣን ነው ብለዋል።

#BBC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የአዲስ አበባ ከተማ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ ከዚህ ቀደም በሃገር አቀፍ ደረጃ በታወጀው የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ታግደው የነበሩ አገልግሎቶች ከሰኞ የካቲት 14 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ እንደሚጀምሩ አሳውቋል። ኤጀንሲው ፥ ከ #አዲስ_የነዋሪነት_መታወቂያ_አገልግሎት ውጭ ከሰኞ የካቲት 14/2014 ጀምሮ የታገዱ አገልግሎቶች እንደሚጀምሩ እና በሁሉም ክ/ከተማ በየወረዳው በተዘጋጀ…
#Update

በአዲስ አበባ ከተማ ተቋርጦ የቆየው የአዲስ የነዋሪነት መታወቂያን የመስጠት አገልግሎት ከወረዳ ወረዳ በሚደረግ የመሸኛ አሰጣጥ ብቻ አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚቻል የአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነት ምዝገና እና መረጃ ኤጀንሲ አስታውቋል።

የኤጀንሲው ከፍተኛ አማካሪ አቶ መላክ መኮንን ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 በሰጡት ቃል " በያዝነው ሳምንት ተቋርጦ የነበረው የመታወቂያ ምትክ እና እድሳት አገልግሎት በሁሉም ወረዳዎች አገልግሎት መስጠት ጀምሯል " ብለዋል።

ከዚሁ በተጨማሪ ተቋርጦ የቆየው ከወረዳ ወረዳ በመሸኛ አማካኝነት ሲሰጥ የነበረው አዲስ የነዋሪነት መታወቂያ አገልግሎት በዛሬው እለት መጀመሩን ተናግረዋል።

አቶ መላክ መኮንን " ከተለያዩ የክልል ከተሞች የሚመጡ መሸኛዎችን በመቀበል የሚሰጠው አዲስ የነዋሪነት መታወቂያ አገልግሎት ገና አልተጀመረም " ያሉ ሆን " አገልግሎቱን ከሳምንት በኋላ ለማስጀመር እየተሰራበት ነው " ብለዋል።

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ukraine አሁን ምን እየሆነ ነው ያለው ? - ዩክሬን ፕሬዝዳንት ፑቲን አገሪቱን ሙሉ በሙሉ ለመውረር እንቅስቃሴው ተጀምሯል ብላለች። - ዛሬ ማለዳ የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮላድሚር ዜለንስኪ ሩሲያ በአገራቸው ላጥ ጥቃት መክፈቷን አሳውቀዋል። የሚሳአኤል ጥቃት መፈጸሙን አረጋግጠዋል። ሩሲያ ዛሬ ማለዳ ላይ የከፈተችው ጥቃት ኢላማ ያደረጉት የዩክሬን መሰረተ ልማቶችና የድንበር ጥበቃዎች ላይ ነው ብለዋል።…
የዩክሬን ቀውስ አስከፊውን የዓለም ጦርነት ይዞ እየመጣ ይሆን ?

🇷🇺 የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን 🗣

" ዶንባስ ክልል ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ተጀምሯል። የወታደራዊ ዘመቻው ዋነኛ ዓላማ ላለፉት 8 ዓመታት በኬይቭ በሚገኘው መንግስት የዘር ጭፍጨፋ ሲፈፀምባቸው የነበሩ ሰዎችን ነፃ ማውጣት ነው። "

🇺🇦 የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ 🗣

" ሩሲያ በማንኛውም ቀን አውሮፓ ውስጥ #ትልቅ_ጦርነት ልትጀምር ትችላለች። ሩሲያውያን እርምጃውን ሊቃወሙት ይገባል። ከሩሲያ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ጋር የስልክ ንግግር ለማድረግ ሞከርኩ፤ ውጤቱ ዝምታ ሆነ። ሩሲያ ወደ 200 ሺ የሚጠጉ ወታደሮችና በሺዎች የሚቆጠሩ የውጊያ መኪናዎች በዩክሬን ድንበር አሏት። ሩሲያውያን በዩክሬን ጉዳይ እየተዋሹ ነው ስለሆነም ጥቃቱን ሊቃወሙ ይገባል "

🇺🇳 የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ 🗣

" ፕሬዝዳንት ፑቲን በ #ሰብኣዊነት_ስም ጦርህን ወደ ሩሲያ መልስ። ይህንን ካላደረክ ውጤቱ በክፍለ ዘመኑ ታይቶ የማይታወቅ ጦርነት ሊያስከትል ይችላል "

🇺🇸 የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን 🗣

" ሩሲያ #በዩክሬን ላይ በምትፈጽመውን ወረራ ለሚደርሰው ጥፋትና ውድመት ዓለም ሩሲያን ተጠያቂ ሊያድርግ ይገባል። የዓለም ህዝብ በሩሲያ ጥቃት ጉዳት የሚደርስባቸው ዩከሬናውያንን በጸሎት ያስባል። "

🇬🇧 የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን 🗣

" ሩሲያ ደም አፋሳሹን መንገድ መርጣለች፤ ቀጣይ እርምጃ ምን መሆን አለበት በሚለው ላይ ከዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያይተናል። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የዩክሬን ቀውስ አስከፊውን የዓለም ጦርነት ይዞ እየመጣ ይሆን ? 🇷🇺 የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን 🗣 " ዶንባስ ክልል ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ተጀምሯል። የወታደራዊ ዘመቻው ዋነኛ ዓላማ ላለፉት 8 ዓመታት በኬይቭ በሚገኘው መንግስት የዘር ጭፍጨፋ ሲፈፀምባቸው የነበሩ ሰዎችን ነፃ ማውጣት ነው። " 🇺🇦 የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ 🗣 " ሩሲያ በማንኛውም ቀን አውሮፓ ውስጥ #ትልቅ_ጦርነት…
የነዳጅ ዋጋ📈

የነዳጅ ዋጋ በበርሜል ከ100 ዶላር በላይ አሻቅቧል።

የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በምሥራቃዊ ዩክሬን ላይ “ወታደራዊ ዘመቻ” መጀመሩን መግለጻቸውን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ቢቢሲ ዘግቧል።

በዚህም ሳቢያ በ7 ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የነዳጅ ዘይት ዋጋ በበርሜል ከ100 ዶላር በላይ አሻቅቧል።

ውጥረት እና ግጭቱ የሚቀጥል ከሆነ የነዳጅ ዋጋ ከዚህም በላይ #መጨመሩን እንደሚቀጥል ተነግሯል።

የነዳጅ ዘይት ዋጋ ውዝግቡ በተባባሰባቸው ባለፉት ቀናት ውስጥ በየዕለቱ እየጨመረ ሄዶ ነው አሁን ከ100 ዶላር በላይ የደረሰው።

ከነዳጅ በተጨማሪ የወርቅ ዋጋም ባለፉት ዓመታት ከታየው በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል።

ሩስያ ከሳዑዲ አረቢያ በመቀጠል በዓለም ሁለተኛዋ የነዳጅ ዘይት አምራች ሀገር ናት።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የነዳጅ ዋጋ📈 የነዳጅ ዋጋ በበርሜል ከ100 ዶላር በላይ አሻቅቧል። የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በምሥራቃዊ ዩክሬን ላይ “ወታደራዊ ዘመቻ” መጀመሩን መግለጻቸውን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ቢቢሲ ዘግቧል። በዚህም ሳቢያ በ7 ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የነዳጅ ዘይት ዋጋ በበርሜል ከ100 ዶላር በላይ አሻቅቧል። ውጥረት እና ግጭቱ የሚቀጥል ከሆነ የነዳጅ ዋጋ ከዚህም በላይ…
የሩስያ እና ዩክሬን ፍጥጫ #እንደኛ ባሉ አዳጊ ሀገራት ላይ ሊያሳድር የሚችለው ተፅእኖ ምንድነው ?

[በዓለም አቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት የቀረበ]

- #የምግብ_ዋጋ_መናር : ኢትዮጵያ ስንዴ የምትገዛባቸው ሶስት ዋና ዋና ሀገራት ሩስያ፣ ዩክሬን እና አውስትራሊያ ናቸው። በተለይ ሩስያ እና ዩክሬን በአለም ላይ ካለው የስንዴ ገበያ አንድ አራተኛውን ይሸፍናሉ። ዩክሬን 40 % የሚሆነውን የስንዴ ምርቷን ለመካከለኛው ምስራቅ እና እንደ ኢትዮጵያ ላሉ አዳጊ ሀገራት በሽያጭ ታቀርባለች። ታድያ ይህ አቅርቦት በጦርነት ምክንያት ሲስተጓጎል የምርት/ምግብ አቅርቦት መስተጓጎሉ አይቀርም። ይህም በአንዳንድ ሀገራት የሚታየውን የዋጋ ግሽበት አባብሶ ህዝባዊ ቁጣ ሊቀሰቅስ ይችላል።

- #የነዳጅ_ዋጋ_መጨመር : የሩስያ እና ዩክሬንን ፍጥጫ ተከትሎ አሁን ላይ የነዳጅ ዋጋ ከ100 ዶላር በላይ እንዳሻቀበ የሚወጡ ሪፖርቶች ያሳያሉ፣ ይህ ዋጋ ከዚህም በላይ በፍጥነት ሊጨምር ይችላል የሚል ግምት አለ። ሩስያ በአለም ላይ የተፈጥሮ ጋዝ እና ነዳጅ በማምረት ከፍተኛውን ድርሻ ከሚይዙ ሀገራት መሀል ትመደባለች። ታድያ ይህ ግጭት የአለም የነዳጅ ዋጋን እጅጉን እያናረው ይገኛል፣ ይህም በተለይ እንደ ሀገራችን ላሉ ነዳጅ ገዢ ሀገራት እጅጉን ፈታኝ ግዜ እንደሚያመጣ ግልፅ እየሆነ ነው።

- #የእርዳታ_መቀነስ : ብዙ ግዜ እንደሚታየው አንድ ቦታ ላይ ትልቅ ችግር ሲከሰት ትኩረት ወደዛ ይዞራል። ለምሳሌ በሶርያ፣ የመን፣ ኢራቅ፣ አፍጋኒስታን ወዘተ ችግሮች ሲከሰቱ ከረጂ ሀገራት የሚገኘው ድጋፍ እዚህም፣ እዛም ይከፋፈል እና ይቀንሳል። አሁን ደግሞ ሀገራችን በጦርነት እና ድርቅ ምክንያት ከፍተኛ አለም አቀፍ ድጋፍ የምትሻበት ግዜ ነው፣ ነገር ግን ይህ እየተባባሰ የመጣ ፍጥጫ ትኩረት እንዳያሳጣን ስጋት አለ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የሩስያ እና ዩክሬን ፍጥጫ #እንደኛ ባሉ አዳጊ ሀገራት ላይ ሊያሳድር የሚችለው ተፅእኖ ምንድነው ? [በዓለም አቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት የቀረበ] - #የምግብ_ዋጋ_መናር : ኢትዮጵያ ስንዴ የምትገዛባቸው ሶስት ዋና ዋና ሀገራት ሩስያ፣ ዩክሬን እና አውስትራሊያ ናቸው። በተለይ ሩስያ እና ዩክሬን በአለም ላይ ካለው የስንዴ ገበያ አንድ አራተኛውን ይሸፍናሉ። ዩክሬን 40 % የሚሆነውን የስንዴ ምርቷን…
#Update

ዩክሬን ከሩሲያ ጋር ያላትን ግንኙነት አቋረጠች።

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ዩክሬን ከሩሲያ ጋር ያላትን ሁሉንም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዳቋረጠች ተናግረዋል።

በዩክሬን ላይ በተከፈተው ጦርነት በበርካታ ስፍራዎች ላይ ጥቃቶች እየተፈጸሙ መሆናቸው እየተገለፀ ነው።

እንደ ቢቢሲ ዘገባ ኪየቭ እና ካርኪቭን ጨምሮ በተለያዩ የዩክሬን ግዛቶች የሚሳኤል ጥቃቶች እና ፍንዳታዎች ተዘግበዋል።

ቭላድሚር ፑቲን ረፋድ ላይ በሰጡ መግለጫ ሩሲያ ዩክሬንን ወራ የመቆጣጠር እቅድ እንደሌላት በመግለጽ ወታደሮቿ መሳሪያ እንዲያስረክቡ ጠይቀዋል።

ዩክሬን በበኩሏ ሩሲያ "ሙሉ ወረራ" ፈፅማለች ብላለች።

በግጭቱ እስካሁን የበርካታ ሰዎች ህይወት የጠፋ ሲሆን የኬየቭ ነዋሪዎች ደግሞ ከተማቸውን ጥለው እየሸሹ ናቸው።

ምዕራባውያን ሩሲያ ከባድ የሆነ ማዕቀብ ይጠብሻል እያሉ እየዛቱ ይገኛሉ።

@tikvahethiopia
ሄሜቲ ሞስኮ ምን ይሰራሉ ?

የጎረቤታችን ሀገር ሱዳን ሉአላዊው የሽግግር ም/ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ጄነራል መሐመድ ሃምዳን ዳጋሎ (ሄሜቲ) ሩስያ፣ ሞስኮ ይገኛሉ።

የሄሜቲ የሩስያ ጉብኝት በምዕራባውያን ሀገራት እና በሱዳን ወታደራዊ ክንፍ መካከል ውጥረት ባለበት እንዲሁም በዩክሬን ጉዳይ ምዕራባውያን ሩስያን በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለማግለል ማዕቀብም ለመጣል እየዛቱ ባሉበት ወቅት ነው።

ሄሜቲ በትዊተር ገፃቸው ላይ ጉብኝታቸው በሱዳን እና በሩሲያ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማስፋት እና ትብብርን ለማጠናከር ያለመ መሆኑን ገልፀዋል።

የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ካሊድ ፋራህ አሁን ከፍተኛ ውጥረት ባለበት ጊዜ ሄሜቲ ወደ ሩሲያ የተጓዙበት ጉዳይ ላይ አስተያየት የሰጡ ሲሆን በዩክሬን ጉዳይ በምዕራቡ ዓለም እና በሩሲያ መካከል ካለው ግጭት ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለው ተናግረዋል።

ካሊድ ፋራህ ፥ "ይህ ጉብኝት ሁለቱ ወዳጅ ሀገራት (ሱዳን እና ሩሲያ) ያላቸውን ወዳጅነት በሁሉም መስክ እና ሁኔታ ለማጠናከር ካለው ፍላጎት አንፃር የመጣ ነው። ሁለቱ ሀገራት ታሪካዊ እና የቆየ ግንኙነት አላቸው። ይህ ጉብኝት አስቀድሞ የታቀደ ነበር ፤ በዩክሬን ውስጥ ካለው ነገር ጋር ምንም ግንኙነት የለውም " ብለዋል።

ጡረታ የወጡት ሜጀር ጄኔራል እስማኤል ማዞብ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ደግሞ ጉብኝቱ በዋናነት በንግድ እና በኢንቨስትመንት ላይ ያተኮረ ይመስላል ብለዋል። የልዑካን ቡድኑ የሱዳን የፋይናንስ፣ የማዕድን፣ የግብርና ሚኒስትሮችን ያካተተ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

@tikvahethiopia
#Bank_of_Abyssinia

ለነገ ያለሙትን ትልቅ ግብ ለማሳካት ዛሬ በትንሹ በሙዳይ የቁጠባ ሂሳብ ይጀምሩ።

ይህ ልዩ የተቀማጭ ሂሳብ ገበሬዎች፤ ነጋዴዎችን፣ ባለሱቆች፤ እንዲሁም ሌሎች በአነስተኛ ስራዎች ላይ የተሰማሩ ሰዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው። በሙዳይ ይቆጥቡ፣ ህልምዎን ዕውን ያድርጉ!

የአቢሲንያ ባንክን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻነል ይቀላቀሉ! https://t.iss.one/BoAEth
#TsehaiFamiles

ለወላጆች 'ፀሐይ ለቤተሰብ' የተሰኘ የኦላይን ትምህርት መስጫ ፕላትፎርም ይፋ ሆነ።

ዊዝ ኪድስ ወርክሾፕ ፀሐይ ለቤተሰብ https://www.t4f.et የተሰኘ አዲስ የቤተሰብ የኦላይን ትምህርት መስጫ ፕላትፎርም በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ አስተዋውቋል።

ፀሐይ መማር ትወዳለች በተሰኘው የሕጻናት ፕሮግራሙ የሚታወቀው ዊዝ ኪድስ ወርክሾፕ በኢትዮጵያዊቷ እንስት በብሩክታዊት ጥጋቡ ከ17 ዓመታት በፊት የተመሰረተ ነው።

በዛሬው ዕለት አዲስ የተዋወቀው ፕሮግራም ቤተሰቦች ልጆቻቸውን እንዴት ማሳደግ እንዳለባቸው ትምህርት የሚያገኙበት ሲሆን በፕላትፎርሙ ከሚሰጠው ትምህርት በተጨማሪ ምዘናዎችንም ያካተተ መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል።

በተለይ እድሜያቸው ከዜሮ ዓመት እስከ 7 ዓመት ለሆኑ ህጻናት የቤተሰቦች አስተዳደግ ላይ ሥልጠና ይሰጣል የተባለው ይህ ፕላትፎርም በነጻ እንዲሁም በክፍያ ያሉ ሥልጠናዎችን አካቷል።

ዊዝ ኪድስ ወርክሾፕ ከዚህ በተጨማሪ ጥበብ ለሴቶች እንዲሁም ወጣቶቹ ተመራማሪዎች የተሰኙ ሌሎች ፕሮጀክቶችን ያካተተ ሲሆን በመሰረታዊነት ሕጻናትና ቤተሰብ ላይ ትኩረቱን አድርጎ ይሰራል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#PP የገዢው ብልፅግና ፓርቲ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በአሁን ሰዓት ስብሰባውን እያካሄደ ነው። ስብሰባው በዐበይት ሀገራዊ ጉዳዮችና በልዩ ልዩ የፓርቲ አጀንዳዎች ላይ እንደሚወያይ የፓርቲው ፕሬዝዳንት እና የኢትዮጵያ ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ገልፀዋል። @tikvahethiopia
#Update

የገዢው ብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ተጠናቀቀ።

ለሁለት ቀናት የተካሄደው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ በወሳኝ ሀገራዊ እና የፓርቲ ሥራዎች ላይ ተወያይቶ በቀጣይ ስለሚከናወኑ ተግባራት አቅጣጫ ማስቀመጡን ፓርቲው አስታውቋል።

@tikvahethiopia