TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኦነግ ሰራዊት አባላት‼️

ከ1 ሺህ በላይ የሚሆኑ የኦነግ ሰራዊት አባላት ወደ ተዘጋጀላቸው #ካምፕ ገብተዋል።

የሰራዊት አባላቱ ጦላይን ጨምሮ በኦሮሚያ ክልል በተዘጋጁ የተለያዩ ካምፖች በመግባት #ስልጠና እየወሰዱ ነው።

ከኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የሰራዊት አባላቱ፥ የተደረገላቸው የሰላም ጥሪና እየታየ ያለው የፖለቲካ ለውጥ ለሃገርና ህዝብ ጥቅም በሰላማዊ መንገድ እንዲታገሉ እንዳደረጋቸው ተናግረዋል።
በሃይል ትግል ማድረጉም ለህዝቡ ስለማይጠቅም ሰላማዊ የትግል መንገድ መምረጣቸውንም ነው የተናገሩት።

ከዚህ በተቃራኒው የትጥቅ ትግልን አማራጭ በማድረግ በሃይል የሚንቀሳቀስ ቡድን አካሄድ ተቀባይነት እንደሌለውም ገልጸዋል፤ ለውጡን ለማስቀጠል መናበብና መመካከር አስፈላጊ መሆኑን በመጥቀስ።

ከዚህ ባለፈም የበርካቶች ህይወት ያለፈበትን ትግል ማደናቀፍ እንደማይገባ የጠቀሱት አባላቱ፥ የአንድ ሃገር እድገትን ለማረጋገጥ በሰላማዊ መንገድ መታገል አስፈላጊ መሆኑንም አንስተዋል።

በትጥቅ ትግል ላይ ለሚገኙ ሌሎች ጓዶቻቸውም ትጥቃቸውን ፈተው ሰላማዊ ትግሉን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርበዋል።
የጦላይ ስልጠና ማዕከል አስተባባሪ ኮሚሽነር ፀሃይ ነጋሽ በበኩላቸው አባላቱ በህገ መንግስቱ፣ በፌደራሊዝሙና በሃገራዊ ለውጡ ዙሪያ ስልጠና እየወሰዱ መሆኑን ገልጸዋል።

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Adigrat

በጦርነቱ ምክንያት ከ70 ከመቶ በላይ ውድመት የደረሰበት " የዓዲግራት አዲስ የመድሃኒት ፋብሪካ " አግግሞ እስከ 110 የሚደርሱ የተለያዩ በሽታዎች የሚፈውሱ መድሃኒቶች በማምረት ላይ እንደሚገኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የፋብሪካው ዋና ስራ አስፈፃሚ ሃይለ ገ/ሚካኤል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፥ የመድሃኒት ፋብሪካው ጦርነቱ በጀመረ ማግስት በኤርትራ ወታደሮች ቁጥጥር ስር ውሎ ነበር።

በእነዚህ የኤርትራ ወታደሮችም 7 ሰራተኞቹ በሞት መነጠቁንና በርካቶችም መቁሰላቸውን አስታውሰዋል፡፡

የመድሃኒት ፋብሪካው ከህዳር እስከ የካቲት 2013 ዓ.ም ባሉት ሶስት ወራት የኤርትራ ወታደሮች እንደ #ካምፕ ሲገለገሉበት እንደነበር ገልጸዋል።

" ወታደሮቹ ማሽነሪዎች ጨምሮ የተለያዩ የፅህፈት ቤት እቃዎች ዘርፈው መውሰዳቸውንና መውሰድ ያልቻሉት ፈንጅ በማጥመድ አጋይቶውታል " ብለዋል፡፡ 

ፋብሪካው ሚያዝያ ወር 2013 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ወታደሮች ቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ በተነፃፃሪ የጥበቃ ከለላ ስር የተወሰኑ የጥገና ስራዎች ጀምሮ ነበር ሲሉ ገልጸዋል።

ነገር ግን በውቅቱ በነበረው የተወሳሰበ ውግያና የፀጥታ መድፍረስ ሳይሳካለት ቀርቶ 1500 ቀዋሚና ጊዚያዊ ሰራተኞቹ ለመበተን መገደዱን አመልክተዋል።

ፋብሪካው ከጥቅምት 2015 የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ማግስት የጥገና ስራዎች በማካሄድ ከፌደራል የመድሃኒትና የምግብ ቁጥጥር ባለስልጣን መልሶ ለማምረት የሚያስችለው የብቃት ማረጋገጫ ማግኘቱ አቶ ሃይለ ገልፀዋል፡፡

ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-05-11

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia