TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ProfessorAsratWeldeyes

በደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ " ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ " በዛሬው ዕለት ይመረቃል፡፡

የምረቃ ስነስርዓቱ የፌደራል፣ የክልል፣ የዞንና የከተማ አስተዳደሩ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት እንደሚካሄድ ከዩኒቨርስቲው የተገኘው መረጃ ይመለክታል፡፡

Credit : የደብረ ብርሃን ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
#Benishangul

በዛሬው ዕለት የበርታ ብሔረሰብ ምክር ቤት 8ኛ መደበኛ ጉበዔውን በኩርሙክ ወረዳ አካሂዶ ነበር።

በዚህ ጉባዔው የብሔረሰቡ መጠሪያ ሥያሜ 👉ቤኒሻንጉል እንዲሆን መወሰኑ ተሰምቷል።

ሥያሜውን ለመቀየር የተጠናዉ ጥናት በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ቀርቦ ውይይት እንደተደረገበት ተገልጿል።

በጥናቱ ዙሪያ ከተደረገው ሰፊ ዉይይት በኃላ ምክር ቤቱ የብሔረሰቡን መጠሪያ ሥያሜ ቤኒሻንጉል እንዲሆን ወስኗል ነው የተባለው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

በደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ የፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ካምፓስ እንዲሁም የሐኪም ግዛው ማስተማሪያ ሆስፒታል ምረቃ ፕሮግራም ተካሂዷል።

በምርቃት ስነስርአቱ የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ዶክተር ይልቃል ከፋለን ጨምሮ የክልልና የፌደራል ከፍተኛ ስራ ኃላፊዎች ተገኝተው ነበር።

ፎቶ : የደብረ ብርሃን ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Benishangul በዛሬው ዕለት የበርታ ብሔረሰብ ምክር ቤት 8ኛ መደበኛ ጉበዔውን በኩርሙክ ወረዳ አካሂዶ ነበር። በዚህ ጉባዔው የብሔረሰቡ መጠሪያ ሥያሜ 👉ቤኒሻንጉል እንዲሆን መወሰኑ ተሰምቷል። ሥያሜውን ለመቀየር የተጠናዉ ጥናት በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ቀርቦ ውይይት እንደተደረገበት ተገልጿል። በጥናቱ ዙሪያ ከተደረገው ሰፊ ዉይይት በኃላ ምክር ቤቱ የብሔረሰቡን መጠሪያ ሥያሜ ቤኒሻንጉል እንዲሆን…
" በርታ " የብሄረሰቡን መጠሪያ ለምን መቀየር አስፈለገ ?

ዛሬ በተካሄደ የበርታ ብሔረሰብ ም/ቤት ጉባኤ የብሔረሰቡ መጠሪያ ስያሜ "ቤኒሻንጉል" ተብሎ አንዲጠራ ወሳኔ አሳልፏል።

በቤ/ጉ ክልል ኮሚኒኬሽን ገፅ እንደሰፈረው ዛሬ እንዲቀየር የተደረገው መጠሪያ ብሔረሰቡ ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ በ ' ህወሃት ' አስገዳጅነት ይጠራበት እንደነበር ይገልጻል።

ዛሬ ግን የብሔረሰቡ ስያሜ "ቤኒሻንጉል" ተብሎ እንዲጠራ ተወስኗል።

በዚሁ መረጃ ላይ በዛሬው ጉበዔ ለምክር ቤቱ " የበርታ ብሔረሰብ ስያሜ ለመቀየር የቀረበ የህዝብ ዉሳኔ መነሻና ሳይንሳዊ ትንታኔ " በሚል ርዕሰ በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን የተጠና ጥናት ቀርቦ ዉይይት ተደርጎበታል።

ከዉይይት በኃላ ምክር ቤቱ የብሔረሰቡ መጠሪያ ስያሜ "ቤኒሻንጉል" ተብሎ እንዲጠራ ወሳኔ አሳልፏል።

@tikvahethiopia
#ይቅርታ

" ባቀድነው ልክ ውጤታማ ባለመሆናችን የ ኢትዮጵያ ህዝብን ይቅርታ እጠይቃለሁ " - የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ፀሀፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከአፍሪካ ዋንጫው ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ ጠየቀ።

ዛሬ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ውበቱ አባተ እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ፀሀፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን የኢትዮጵያን የካሜሩን አፍሪካ ዋንጫ ቆይታ አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

የፌዴሬሽኑ ዋና ፀሀፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን " ባቀድነው ልክ ውጤታማ ባለመሆናችን የ ኢትዮጵያ ህዝብን ይቅርታ እጠይቃለሁ " ብለዋል።

አክለውም ፥ " የአሰልጣኙን ኮንትራት እናከብራለን ፣ እስከ ኮንትራቱ መጨረሻ አብሮን ይቀጥላል ብለን እናምናለን " ሲሉ ተናግረዋል ።

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በበኩላቸው ፥ " ስንሄድም ስንመጣም በኢትዮጵያ አየር መንገድ ነው አልተደበቅንም ፣ ብሄራዊ ቡድኑ ኩራት ነው ፣ በ ማህበራዊ ገፆች እንደተመለከትነው ድንጋይ ይዞ የተቀበለን ሰው የለም " ብለዋል።

" እስከ መስከረም 30/2015 ከ ፌዴሬሽኑ ጋር ኮንትራት አለኝ " ያሉት አሰልጣኙ እስከዛው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ነኝ " ሲሉ ተናግረዋል።

ብሄራዊ ቡድኑ ከ8 ዓመታት በኃላ ወደ አፍሪካ ዋንጫው ቢመለስም ምድቡን ማለፍ ሳይችል በመቅረቱ የመጀመሪያ ተሰናባች ሆኖ ከቀናት በፊት ወደ ሀገሩ መመለሱ ይታወቃል።

More : @tikvahethsport
#DrTedrosAdhanom

ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የዓለም ጤና ድርጅትን እንዲመሩ በድጋሚ እጩ ሆነው ቀረቡ፡፡

ዶ/ር ቴድሮስ በራሱ በዓለም ጤና ድርጅት ቦርድ ነው በድጋሚ እጩ ሆነው የቀረቡት፡፡

ይህም በመጪው ወርሃ ግንቦት 2022 ለሚካሄደው የዋና ዳይሬከተርነት ምርጫ በብቸኛነት የቀረቡ እጩ ያደርጋቸዋል።

ዶ/ር ቴድሮስ ምርጫውን አሸንፈው ድርጅቱን በድጋሚ በዋና ዳይሬክተርነት የመምራታቸው እድል ሰፊ ስለመሆኑ ይነገራል፡፡

#AlAIN

@tikvahethiopia
#ተጠናቋል

የእንጦጦ ፖርክ የመኪና ማቆሚያ የግንባታ ስራ መጠናቀቁ ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በቅርቡ ስራ የጀመረው የእንጦጦ ፖርክ የመኪና ማቆሚያ የግንባታ ስራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት መሆኑን አሳውቋል።

ይህ ኘሮጀክት በአጠቃላይ ሶስት የመኪና ማቆሚያ ግንባታዎችን የያዘ ሲሆን ሁለቱ በእንጦጦ ፖርክ ዋና መግቢያ በር እንዱሁም ሶስተኛው በሱሉልታ መግቢያ በኩል የተገነቡ ናቸው፡፡

እነዚህ የመኪና ማቆሚያዎች 14,063 ሜትር ስኩዌር ስፋት ያላቸው ሲሆን በአንድ ጊዜ 450 መኪኖችን ማቆም የሚችሉ ናቸው፡፡

@tikvahethiopia
#Ethiopia #Kenya #Egypt

ከቀናት በፊት እዚህ ኢትዮጵያ የነበሩት የአሜሪካው ባለስልጣን ኬንያ ሄደው ከፕሬዜዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር ተወያይተዋል።

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ዴቪድ ሳተርፊልድ ከኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር በናይሮቢ ባደረጉት ውይይት ሁለቱም አካላት በኢትዮጵያ የሚታየዉ ጦርነት እንዲያበቃ ጥረታቸዉን እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።

ሳተርፊልድ ፤ ፕሬዝዳንት ኬንያታ በኢትዮጵያ መንግስት እና በTPLF መካከል ያለውን ግጭት ለማስቆም ላደረጉት ቁርጠኝነት አመስግነዋል።

ሳተርፊልድ ለኬንያዉ ፕሬዚዳንት "የእርስዎ ሚና (የኢትዮጵያን ግጭት ለማስቆም በመርዳት) በጣም ጠቃሚ እንደነበረ እናምናለን። ኬንያ በአፍሪቃ ቀንድ አካባቢ እየተጫወተች ያለውን ሚናም እናደንቃለን። በኢትዮጵያ የእናንተን እርዳታ እና ድጋፍ እንጠይቃለን። በዚያች አገር የሰራችሁት ሥራ እንዲባክን አንፈልግም" ብለዋቸል።

ኬንያታ በበኩላቸዉ ኬንያና ኢትዮጵያ ጥሩ አጋር መሆናቸውን ጠቁመው በሀገሪቱ ያለው የውስጥ ግጭት የተፈጠረውን እድገት የሚሸረሽር በመሆኑ እንዲቀጥል መፍቀድ እንደሌለበት ጠቁመዋል።

"ጠንካራና የተረጋጋች ኢትዮጵያ ለኛ ጠቃሚና አስፈላጊ ነች። ለዚህም ነው ግጭቱ እልባት እንዲያገኝ የምንችለውን ሁሉ ለማድረግ ቁርጠኛ አቋም የያዝነው" ብለዋል።

ከኢትዮጵያ ግጭት በተጨማሪ ፕሬዝዳንት ኬንያታ እና ሳተርፊልድ በሱዳንና በሶማሊያ ስላለው የሰላምና የፀጥታ ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።

በሌላ መረጃ፦ ዴቪድ ሳተርፊልድ ዛሬ ግብፅ የገቡ ሲሆን የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሹክሪ እንደተቀበሏቸው የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል። በምን ጉዳይ እንደተወያዩ የተገለፀ ነገር የለም።

ምንጭ፦ የኬንያ ፕሬዜዳንት ፅ/ቤት (ዶቼ ቨለ) እና የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የቡርኪና ፋሶ ወታደራዊ ሃይል በሀገሪቱ ብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ለይ ቀርቦ ስልጣን መቆናጠጡን አሳውቋል። መግለጫውን በቴሌቪዥን ቀርበው የሰጡት ወጣት የጦሩ ቃል አቀባይ ናቸው። ጦሩ ፤ ሕገ መንግሥቱ መታገዱን ፣ በመላ ሀገሪቱ የሰዓት እላፊ መታወጁን፣ ሁሉም የሀገሪቱ ድንበር መዘጋቱን ገልጿል። ፕሬዝዳንት ሮች ካቦሬ በወታደሮቹ እንደታሰሩ ናቸው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ…
#BurkinaFaso

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተ.መ.ድ) የቡርኪናፋሶ ጦር በአስቸኳይ ያሰራቸውን የሀገሪቱን ፕሬዜዳንት እንዲፈታ በጥብቅ አሳስቧል።

በቡርኪናፋሶ የተደረገውን መፈንቅለ መንግስት የአፍሪካ ህብረት ፣ ECOWAS እና አሜሪካ አውግዘዋል።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠ ፕሬዜዳንት ላይ የመፈንቅለ መንግስት መደረጉን ህብረቱ እንደሚያወግዝ ገልፀዋል።

ECOWAS በተመሳሳይ መፈንቅለ መንግስቱን በጥብቅ አውግዟል።

አሜሪካ በበኩሏ በቡርኪናፋሶ ያለው ሁኔታ እንደሚያሳስባት ገልፃ በአስቸኳይ የሲቪል አስተዳደር ወደቦታው እንዲመለስ አሳስባለች።

ፕሬዜዳንት ሮች ካቦሬ በወታደሮች እንደታሰሩ ናቸው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የዓለም ጤና ድርጅት ሥራ አመራር ቦርድ የኢትዮጵያ መንግሥት በድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ላይ ያቀረበውን አቤቱታ አሁን ላለማየት መወሰኑን / እንደሚያዘገይ መወሰኑን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል። ቦርዱ ዛሬ አልወያይበትም ብሎ ወደ ጎን የገፋው የኢትዮጵያ መንግሥት ዶ/ር ቴድሮስ የሕወሃት ደጋፊ እንደሆኑ እና በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ሐሰተኛ መረጃ እንደሚያሰራጩ ጠቅሶ…
#ETHIOPIA

የዓለም ጤና ድርጅት ስራ አስፈፃሚ ቦርድ በድርጅቱ የኢትዮጵያ ተወካይ ንግግር እንዳያደርጉ መከልከሉ ተቀባይነት እንደሌለው ኢትዮጵያ ገልፃለች።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፤ ኢትዮጵያ የድርጅቱን ዋና ዳይሬክተርን የስነ ምግባር ጥሰት በተመለከተ ቦርዱ እንዲመረምር በይፋ ቅሬታ ማቅረቧን አስታውሷል።

ምንም እንኳ ቀደም ሲል የአፍሪካ እና ሌሎች ወዳጅ ሀገራትን በማስተባበር ዋና ዳይሬክተሩን እጩ አድርጋ በማቅረብ እና የወዳጅ አፍሪካ ሀገራትን በማንቀሳቀስ ብታስመርጣቸውም በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በህወሓት አማካኝነት ጦርነት ሲነሳ ግን የግለሰቡ ትክክለኛ ማንነት መገለጡንና ከሀገራቸው ይልቅ ህወሓትን መምረጣቸውን አመልክቷል።

የተመረጡበትን ሀላፊነት የቡድኑን ፕሮፓጋንዳ ለማሠራጨት እንደተጠቀሙበት ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።

ይህ ድርጊት ከድርጅቱ የስምግባር መርህ ጋር የሚጣረስ ድርጊትን ስራ አስፈፃሚ ቦርዱ እንዲመረምር ኢትዮጵያ በይፋ ብታመለክትም ቦርድ ጥያቄውን ተቀብሎ ከመመልከት ይልቅ ይብስኑ የኢትዮጵያ ተወካይ ይህን ጉዳይ እንዳያብራሩ መከልከሉን ገልጿል።

በአባል ሀገር ላይ እንዲህ ዓይነቱን ድርጊት መፈፀሙ ተቀባይነት እንደሌለው ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ምንጭ፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣ ኤፍቢሲ

@tikvhaethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሰሜን_ኮሪያ ሰሜን ኮሪያ ሁለት የተጠረጠሩ የአጭር ርቀት ባላስቲክ ሚሳኤሎችን (SRBM) በመዲናዋ ፒዮንግያንግ ከሚገኝ አውሮፕላን ማረፊያ መተኮሷን የደቡብ ኮሪያ ጦር ማሳወቁን ሮይተርስ ዘግቧል:: ጃፓን በተመሳሳይ መወንጨፉን ሪፖርት አድርጋ ድርጊቱን የሰላም እና የፀጥታ ጠንቅ ነው ስትል አውግዛለች። ቻይና በበኩሏ ሁሉም ወገኖች የቀጠናውን መረጋጋት እንዲያስጠብቁ ስትል አሳስባለች:: ዛሬ ሰሜን ኮሪያ…
#NorthKorea

ሰሜን ኮሪያ ዛሬ ማክሰኞ 2 ተጨማሪ የክሩዝ ሚሳዬሎችን በመተኮስ መሞከሯን የደቡብ ኮሪያ ጦር አስታወቀ፡፡

ይህ በአዲሱ የአውሮፓውያን ዓመት አምስተኛው የሚሳዬል ሙከራ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

የደቡብ ኮሪያ ጦር ዝርዝሩ እየተጠና መሆኑን አስታውቋል፡፡

ሰሜን ኮሪያ በአዲሱ ዓመት ውስጥ ብቻ ባደረገቸው 5 ሙከራዎች 8 ሚሳዬሎችን መተኮሷ ተገልጿል፡፡

እ.ኤ.አ. በ1950 የተካሄደውን የኮሪያ ጦርነት ስምምንት መሠረት አሜሪካ በደቡብ ኮሪያ ወደ 28ሺ ወታደሮችን አስፍራለች፡፡

አሜሪካ ፤ የሰሜን ኮሪያ ሚሳኤል ሙከራዎቹን በማወገዝ አሳሳቢ መሆናቸውንም እየገለጸች ሲሆን በተከታታይ የእንነጋገር ጥሪዋን ስታሰማ መቆየቷን የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" 5 ተማሪዎች እና 1 በንግድ ስራ የተሰማራ ግለሰብ ታግተዋል " - የፌደራል የደኅንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል በኦሮሚያ ክልል ፣ ምስራቅ ወለጋ 5 ተማሪዎች እና አንድ በንግድ ስራ የሚተዳደር ግለሰብ በድምሩ 6 ሰዎች ታግተዋል። የፌደራል የደኅንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል እገታውን ሸኔ እንደፈፀመ ገልፆ የታገቱትን ግለሰቦች ለማስለቀቅ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አሳውቋል። ግብረ ኃይሉ ፥ ታጋቾቹ…
#Update

በምስራቅ ወለጋ የታገቱትን 5 ተማሪዎች እና 1 በንግድ ስራ ላይ የተሰማራን ግለሰብ ለማስለቀቅ የመንግስት ፀጥታ አካላት እርንጃ እየወሰዱ ነው ተብሏል።

የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሚኒኬሽን ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ፥ " ሸኔ ነው እገታውን የፈፀመው የታገቱትን ሰዎች ለማስለቀቅ የመንግስት ፀጥታ ኃይሎች እርምጃ በመውሰድ ላይ ይገኛሉ። የሚወሰደውን እርምጃ ተከትሎ የሚመጣውን ውጤት ወደፊት እናሳውቃለን " ብለዋል።

በሌላ በኩል ኃላፊድ ትላንት በሰጡት መግለጫ በህ/ተ/ም/ቤት አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው ሸኔ /እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እያለ ነው የሚጠራው / በኦሮሚያ ክልል
° 163 ትምህርት ቤቶችን ማውደሙን
° ከ756 ትምህርት ቤቶች መጻሕፍት ማቃጠሉን፣
° ኮምፕተሮችን እና ሌሎች ንብረቶችን በመዝረፍ ትውልዱ እንዳይማር ማድረጉን ገልጿል።

በዚህ የቡድኑ ድርጊት ብቻ 325 ሺ ተማሪዎች ከትምህርት ውጭ መሆናቸውን እና 5 ሺህ 227 መምህራን ከስራ ገባታሳ ውጪ መሆናቸውን ኃላፊው ተናግረዋል።

በስህተት ወደ ሸኔ የተቀላቀሉና ወጣቶች የቡድኑን ድርጊት በመረዳት በሰላም እስጃቸውን የሰጡ ስለመኖራቸው አሁንም ደግሞ እጅ እንዲሰጡ የክልሉ መንግስት ጥሪ አቅርቧል።

" በአሸባሪ ድርጅትነት የተፈረጀን ቡድን በሰላም እጅ ስጡ ማለት " የሚያመጣው ስጋት የለውም ወይ ተብለው ከሬድዮ ጣቢያው የተጠየቁት አቶ ኃይሉ አዱኛ ፥ " ባለፈው የወጣው አዋጅ ቡድኑን እንደ ቡድን ነው በአሸባሪነት የፈረጀው ያ ማለት ግን አሁን የተደረገው ጥሪ ለቡድኑ አይደለም። በተሳሳተ መንገድ ቡድኑን የተቀላቀሉ ንፁሃን የትግል መስመሩ እውነተኛ መስሏቸው የተቀላቀሉ፣ በውሸት ትርክት የተቀላቀሉ ወጣቶች ሊኖሩ ስለሚችሉ ለእነሱ እድል ለመስጠት ነው የተሰጠው " ሲሉ መልሰዋል።

@tikvahethiopia