TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
25 ሱደናውያን ከእስር ተለቀቁ።

የጄኔራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎን የኢትዮጵያ ጉብኝትን ተከተሎ ኢትዮጵያ 25 ሱዳናዊያንን ከእስር ለቀቀች፡፡

የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ጄኔራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ በኢትዮጵያ የነበራቸውን የሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት አጠናቀው ወደ ካርቱም ተመልሰዋል፡

ኢትዮጵያ 25 ሱዳናዊያን እስረኞችን መፍታቷን የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይል ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ሱዳናዊያን እስረኞቹ የተፈቱት ጄኔራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ ኢትዮጵያን መጎብኘታቸውን ተከትሎ ነው መሆኑን አል ዓይን ዘግቧል።

እስረኞቹ የተፈቱት ሁለቱ ሀገራት የጋራ ድንበር ጉባኤ ከአንድ ወር በፊት በብሉናይል እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች መካከል የሰላም እና የደህንነት ጉባኤ ካደረጉ በኋላ በተስማሙት መሰረት ነው፡፡

ዛሬ የተፈቱት ሱዳናዊያን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዋና ከተማ አሶሳ ማረሚያ ቤት ታስረው የነበሩ እንደሆነም ተገልጿል፡፡

Credit : አል ዓይን ኒውስ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ ቤተሰቦች ስለ አንፋጋው የኢትዮጵያ የሙዚቃ ሰው ምን አሉ ?

ፍርድዮስ ዩሱፍ ለኤፍ ኤም 97.1 ሬድዮ የተናገሩት ፦

" ... አሊ በራ ሞተ ምናምን እያሉ በየጊዜ ያወጣሉ። ነገር ግን የትላንትናው በጣም እኛንም የጎዳ ያሳዘነን ነው።

ከትላንት ወዲያ ነው ከሆስፒታል የወጣው ፤ በጤንነት ጥዋት ላይ ደግሞ የሚገርመው በእግሩ እኔ ሄዳለሁ አብራችሁኝ ሂዱ ብሎ በመኪና ይዘነው ሄደን ባንክ ሄዶ ለእራሱ የሆነ ትራስዛክሽን ሰርቶ ነው የመጣው።

እንግዲህ ይህ ሰው ዊልቸር ላይ የለም፤ ወይም ደግሞ አልጋ ላይ የለም። በእግሩ ጥዋት ሄዶ ነው የተመለሰው።

እዛው ነው ያደርነው (የአሊ መኖሪያ ቢሾፍቱ) ። ለሊት ላይ ብቻ ስልክ ይጮሃል ምንድነው የተፈጠረው ? እንደተለመደው ሞተ ሊሉኝ ነው ስል በጣም በጣም ከማልጠብቀው ሰው ነው ፌስቡክ ላይ ፖስት ሲያደርግ ሳይ ለማን ነው RIP የምትሉት ኧረ ባካችሁ አንሱ እሱ በጤና ነው ያለው እያልኩኝ ለሊት ሙሉ አልተኛሁም።

ይሄ ነገር ተደጋገመ ፤ ያልተጣራ መረጃ እየለጠፉ ቤተሰብን ያሳዝናሉ ፣ ይሄነገር ባህል ሆነብን እንዴ ? ብቻ አላውቅም በጣም ተደጋጋመ ነገር ግን የትላንት ማታው በጣም ያሳዘነን ነው። ከዚህ ቢቆጠቡ ይሻላል በጣም ደስ የማይል ነገር ነው እያደረጉ ያሉት።

...አሊ ቢራ እጅግ በጣም ጥሩ ሁኔታ ላይ ጥሩ ጤንነት ላይ ነው ያለው። ፀልዩለት ! ሰው ሲፖስት ደግሞ ዝም ብለው ከእስር እያነሱ የሚፖስቱት ደግሞ ቢቆጠቡ። ቤተሰብ አለ፣ ስንት የሚሰማው ሰው አለ ስለዚህ በዚህ ላይክ እና ሼር ለማግኘት ብላችሁ እንዲህ አይነት ነገር የምታደርጉ ብትቆጠቡ እላለሁ። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba እድሳት የተደረገለት የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ህንፃ በነገው እለት እንደሚመረቅ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል። ይህ ታሪካዊ እና የከተማዋ ምልክት የሆነ ህንፃ ከ57 ዓመት በኋላ ለእድሳት የበቃ መሆኑና የከተማዋ የዘመናት ጉዞ አሻራ የያዘ ታላቅ ቅርስ ጭምር መሆኑ ተገልጿል። የከተማው አስተዳደር ፤ ህንፃውን እጀግ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ እንዲታደስ ማድረጉን ገልጾ ለተገልጋይ…
#Update

እድሳት ሲደረግለት የቆየው የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ህንፃ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል።

ለእድሳቱ ከ2.2 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ መሆኑ ተሰምቷል።

ህንፃው ከ57 ዓመታት በኋላ ነባር ገፅታውን ሳይለቅ ነው መሰረታዊ እድሳት የተደረገለት።

ህንፃው አዳዲስና ደረጃቸውን የጠበቁ አገልግሎቶችን በውስጡ ያካተተ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ፦
- የህፃናት መዋያ፣
- ቤተ-መፃሕፍት፣
- የስልጠናና የምርምር ክፍሎች፣
- ክሊኒክ፣
- የቴአትር አዳራሽ፣
- የስብሰባ አዳራሾች፣
- የመኪና ማቆሚያ፣
- አረንጓዴ ስፍራዎችና የከተማ ግብር ናሙናዎች ይገኙበታል።

የከተማዋ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከነገ ሰኞ ጀምሮ ለህዝብ ክፍት እንደሚደረግ እና መጎብኘት እንደሚቻል አሳውቀዋል።

ፎቶ : አ/አ ከንቲባ ፅ/ቤት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ማስታወሻ📌ዛሬ ውይይት የተካሄደበት ረቂቅ በጀቱ ነገ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በተገኙበት ይፀድቃል። *ዛሬ ጥዋት ኦነግ፣ኦብነግ እና አርበኞች ግንቦት 7 ከሽብርተኝነት ዝርዝር ውስጥ በይፋ ተሰርዘዋል። #ነገ ዓርብ ዶክተር አብይ ምክር ቤት ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። @tsegabwolde @tikvahethiopia
#ONLF

ኦብነግ ከሶማሊያ የሽብርተኛ ድርጅት ዝርዝር ውስጥ ተሰረዘ።

የሶማሊያ ካቢኔ እ.ኤ.አ. በ2017 ( የቀድሞው ካቢኔ ) የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) ን “አሸባሪ ድርጅት” ሲል ያሳለፈው ውሳኔ ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ ሽሮታል።

ኦብነግ ከ5 ዓመት በኃላ ከሽብረተኛ ድርጅትነት ተሰርዟል።

ካቢኔው የኦብነግ ኮማንደር አብዲከሪም ሼክ ሙሴን ወደ ኢትዮጵያ ተላልፎ መሰጠትንም “ህገወጥ” ሲል ገልጿል።

አብዲከሪም ሼክ ሙሴ እ.ኤ.አ. በ2018 በኢትዮጵያ ከመጣው ለውጥ ጋር ተያይዞ በኢትዮጵያ መንግስት ከእስር ነፃ መደረጋቸው ይታወሳል።

የዛሬው የሶማሊያ ካቢኔ ውሳኔ በ23 ድምጽ ድጋፍ ፣ በ1 ተቃውሞ እና በ1 ድምፀ ተአቅቦ ነው የፀደቀው።

ኦብነግ በትዊተር ገፁ በጠቅላይ ሚኒስትር መሀመድ ሁሴን ሮብሌ እና በካቢኔያቸው ዛሬ የተላለፈውን ውሳኔ በደስታ መቀበሉን ገልፆ ውሳኔውን " ታሪካዊ ነው " ብሎታል።

ኢትዮጵያ እንደ እ.ኤ.አ. በ2018 የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ)ን ከሽብርተኛ ድርጅቶች ዝርዝር መሰረዟ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA😷

የ24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 👉 4,805
• ቫይረሱ የተገኘባቸው 👉 374
• ህይወታቸው ያለፈ 👉 8
• ከበሽታው ያገገሙ 👉 825
• ፅኑ ታማሚዎች 👉 364

ዛሬ ፣ ትላንት እና ከትላንት በስቲያ አጠቃላይ 1,505 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ 32 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

@tikvahethiopia
#ይበቃል

ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ያሉ ዜጎቻችን ፍትህን እንዲያገኙ የሚጠይቅ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ እየተካሄደ መሆኑን ተመልክተናል።

ዘመቻው ሳዑዲ ያሉ ዜጎቻችን እምነበረድ ላይ ለብሰው የሚተኙትን ጥቁር ፌስታል በመልበስ አጋርነት የሚገለፅበት ነው።

ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ በርካታ ዜጎቻችን እጅግ አስከፊ በሆነ ሁኔታ ውስጥ እንዳሉ ይታወቃል።

የሳኡዲ አረቢያ መንግስት መሰረታዊ የእስረኛ አያያዝ ህግን እንዲተገብር፣ ፍትሃዊ የሆነ ምላሽም እንዲሰጥ የሚጠየቅበት የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ነው እየተካሄደ ያለው።

#ይበቃል
#ጥቁር_ፌስታል

#الحرية_للسجناء_الاثيوبيين
#العدالة_للسجناء_الاثيوبيين

Credit : Ali Amin & Social Media

@tikvahethiopia
" መኪናው በግምት 200 ሜትር ከሚሆን ገደል ውስጥ ነው የገባው። ... በደረሰው አደጋ 20 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ 6 ሰዎች ቆስለዋል " - ኢንስፔክተር ሲሳይ አበራው

ከባሕር ዳር ከተማ ወደ ሰቆጣ ሲጓዝ በነበረ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ20 ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡

ለግዳጅ ከባሕር ዳር መነሻውን ያደረገው የሕዝብ ማመለሻ አውቶብስ በደረሰበት አደጋ ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ፣ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው እንዳሉም ታውቋል፡፡

የድሃና ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት የመንገድ ትራፊክ ደኅንነት ክፍል ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ሲሳይ አበራው ለአሚኮ በሰጡት ቃል ፥ ለግዳጅ ከባሕር ዳር የወጣው የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ በመንገድ ላይ ያገኛቸውን ሰዎች ጭኖ ሲጓዝ አደጋው እንደደረሰ ተናግረዋል።

አደጋው የደረሰው መለያ ቁጥሩ 11300፣ የጎን ቁጥሩ 2527 የሆነ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

ጉዳቱ የደረሰው ከአምደወርቅ ወጣ ብሎ አቦ መገጠንያ መንገድ በምትባል ሥፍራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በግምት 200 ሜትር ከሚሆን ገደል ውስጥ መግባቱንም ተናግረዋል፡፡ በደረሰው አደጋም 20 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ 6 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ነው የተናገሩት፡፡

ከአደጋው ከተረፉ ሰዎች ጋር ቆይታ እንዳደረጉ የተናገሩት ኃላፊው ከእብናት ወደ አምደ ወርቅ ሲጓዝ ብዙ ሰው እንደነበርና ከአምደወርቅ ሲያልፉ ግን ሰው ያልነበረባቸው ወንበሮች እንደነበሩ ነግረውኛል ነው ያሉት፡፡

ለአደጋው ምክንያት ፍጥነት እና የመንገዱ መጎዳት ሳይሆን እንዳልቀረም ተናግረዋል፡፡ ጉዳቱ ከፍተኛ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

ምንጭ፦ አሚኮ

@tikvahethiopoa