TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
አቶ ጃዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባ ዛሬ ባወጡት መግለጫ ምን አሉ ? • የአርቲስት ሃጫሉ ግድያን ተከትሎ "በተሳሳተ መንገድ ለእስር ተዳርገው" ላለፉት 18 ወራት በእስር መቆየታቸውን ገልፀዋል። • እስራቸው " ፖለቲካዊ " እንደነበር ገልፀዋል። ለእስር የተዳረግነው ገዢው ፓርቲ በምርጫ የተሻለ ድምጽ እንዲያገኝ ከፖለቲካዊው ምኅዳር ገለል እንድንል ታስቦ ነው ብለዋል። • በኦሮሚያ፣ ትግራይ፣ ቤኒሻንጉል…
#OFC

በቅርቡ ከእስር የተፈቱት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አመራሮች እነ አቶ ጃዋር መሀመድ ፣ አቶ በቀለ ገርባ እና ሌሎችም በአዲስ አበባ በሚገኘው የፓርቲው ፅ/ቤት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ኦፌኮ ፤ አሁንም በእስር ላይ ያሉ የቀሩ አባላቱ ከእስር እንዲፈቱ ፣ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አመራሮችና ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ በድጋሚ ጥሪውን አቅርቧል።

@tikvahethiopia
ውሸት ነው !

"ለኢትዮጲያ ብሄራዊ ውይይት አመቻች ኮሚሽን ኮሚሽነርነት አብላጫ ድምፅ ያገኙ እጩዎች ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ እየተዘዋወረ ያለው መረጃ ፍጹም ውሸት ነው" - አቶ ሄኖክ ስዩም (የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፅ/ቤት ምክትል ዋና ፀሀፊ)

@tikvahethiopia
ለፓርላማ የተመራው የክልል መለያ ተሽከርካሪዎች ሰሌዳ እንዲነሳ የሚያደርገው ረቂቅ አዋጅ ምንድነው ?

(ከሪፖርተር ጋዜጣ)

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ወጥነት ያለው ብሔራዊ የተሽከርካሪ ሰሌዳ አሠራር ለመዘርጋት አልሟል፡፡

በሚኒስቴሩ የሕግ አማካሪ አቶ አበጀ ማሞ 🗣

• " ለተወካዮች ምክር ቤት የተመራው ረቂቅ አዋጅ ከፀደቀ በኋላ የክልል መለያ የያዙ የተሽከርካሪ ሰሌዳዎች ተግባራዊ የሚሆኑት አዲስ ብሔራዊ ሰሌዳ ይፋ እስኪደረግ ብቻ ነው "

• " ተሽከርካሪ ዓለም አቀፍ ቁስ ነው፣ አንድ መኪና ከዚህ ተነስቶ ኬንያም ሆነ ሱዳን ሲሄድ የአገሮቹ መንግሥት ግራ ሊጋቡ አይገባም። ኢትዮጵያ ውስጥ በቅርቡ ተግባራዊ የሚደረገው የሰሌዳ ዓይነት የሚገልጸው ተሽከርካሪነታቸውን ብቻ ይሆናል "

• " በሚኒስትሮች ምክር ቤት የፀደቀው ይኼ ረቂቅ አዋጅ፣ የክልል መለያ በሰሌዳዎች ላይ እንዲኖር የሚያዘውን አባሪ እንዲሻር ቢያደርግም፣ በቀጣይ የሚኖረውን የሰሌዳ ዓይነት አይደነግግም፡፡ ' ምን ዓይነት ሰሌዳ ይደረግ? ' የሚለው ከአዋጁ መፅደቅ በኋላ በሚደረግ ጥናት ይወሰናል። ሰሌዳው ግን ' የኢትዮጵያ ሰሌዳ ' ነው የሚባለው "

• " አሁን ባለው የሰሌዳ አሠራር ምክንያት ተሸርካሪዎች ከክልል ወደ ክልል ሲንቀሳቀሱ 'ሥጋት' እና 'ፍራቻ' በውስጣቸው ሊፈጠር አይገባም። አሁን ባለው የአገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ ይኼንን ዓይነቱን ችግር መፍቻ አንዱ መፍትሔ ብሔራዊ ሰሌዳን መተግበር ነው። "

• " የተሽከርካሪ ሰሌዳው ከየት እንደወጣ ወይም የት እንደተመዘገበ የሚገልጽ መለያ ሙሉ ለሙሉ ይቀራል ማለት አይደለም። ነገር ግን ወደፊት በሚወጣው አዲስ አተገባበር ሰሌዳው የወጣበትን ቦታ የሚገልጸው መለያ የሚቀመጠው 'በተቻለ መጠን' የትራፊክ ፖሊሶችና የትራንስፖርት ተቆጣጣሪዎች ብቻ እንዲያውቁት በሚያስችል መንገድ ነው "

ያንብቡ : https://telegra.ph/ETH-01-23
ውሸት ነው !

አንጋፋው የኢትዮጵያ የሙዚቃ ሰው ክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ " ህይወታቸው አለፈ " እየተባለ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጃ ነጭ ውሸት ነው።

በማህበራዊ ሚዲያው በፌስቡክ፣ ዩትዩብ፣ ቴሌግራም፣ ትዊተር በመሳሰሉት ለገንዘብ ፣ ተከታይ ፣ ላይክ እና ኮሜት ለማፍራት ሲባል ብቻ እንዲህ ያለ ፀያፍ ድርጊት መፈፀም ከአንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ የማይጠበቅ ፍጹም ያፈነገጠ ስነምግባር ነው።

ከዚህ ቀደም በበርካታ በሀገራችን የሚከበሩ እና ታዋቂ ሰዎች ላይ ተመሳሳይ በህይወት እያሉ ሀሰተኛ መረጃ ሲሰራጭ እንደነበር ይታወቃል።

የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ዛሬ ላይ በህይወት የሌሉት በእናታችን ክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና ላይ የተሠራጨው ሀሰተኛ መረጃ አንዱ ነበር።

ውድ የቲክቫህ አባላት ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሚፃፍ ሁሉ እውነት አይደለምና የምታዩትን ነገር ደጋግማችሁ ለማረጋገጥ እንድትሞክሩ እንዲሁም ደግሞ እርግጠኛ ያልሆናችሁበትን መረጃ ለወዳጆቻችሁ ከማጋራትም እንድትቆጠቡ አደራ እንላለን።

መሰል ሀሰተኛ መረጃዎችን ባጋራን ቁጥር የሰዎችን ህይወት እየረበሽን መሆናችንን፤ ይህ ስራ ለሚሰሩት ደግሞ የገንዘብ ምንጭ መሆናችንን አውቀን መቆጠብ ይኖርብናል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ነገ በአዲስ አበባ የሚዘጉ መንገዶች ! ነገ የታላቁ ሩጫ ይካሄዳል። የ2014 ዓ/ም ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በሰላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታ ዝግጅት መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል። የሩጫ ውድድር የሚካሄድባቸው መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ስለሚሆኑ አሽከርካሪዎች አመራጭ መንገድ እንዲጠቀሙ ተጠይቋል፡፡ የ2014 ታላቁ ሩጫ መነሻውን መስቀል አደባባይ አድርጎ የሚጀምር ሲሆን በአዲስ አበባ ስታዲዮም፣…
" ውድድሩ በሰላም ተጠናቋል " - አ/አ ፖሊስ

ለ21ኛ ጊዜ በአዲስ አበባ የተካሄደው የታላቁ ሩጫ ውድድር በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

መነሻ እና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ያዘጋጀው 21ኛው የሩጫ ውድድር በሰላም ተጠናቋል፡፡

ፖሊስ ፥ " የታለቁ ሩጫ ውድድር በሠላም መጠናቀቁ ኢትዮጰያ ሰላም አይደለችም የሚል መረጃ የሚያሰራጩ አካላትን መረጃቸው ትክክለኛ ያልሆነና ሀሰተኛ መሆኑን ያረጋገጠ ከመሆኑም ባሻገር ከተማችን አዲስ አበባ አስተማማኝ ሰላም የሰፈነባትና መሰል ፕሮግራሞችን ለማዘጋጀት ምቹ መሆኗን የሚያሳይ ነው " ብሏል።

በመጪው ሳምንት አገራችን 35ኛውን የአፍሪካ ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ የምታስተናግድ ስለሆነ ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።

የዛሬው ውድድር በሠላም እንዲጠናቀቅ ድጋፍ ላደረጉ አካላትና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡ የፀጥታ አካላት የአዲስ አበባ ፖሊስ ምስጋና አቅርቧል።

ፎቶ : ሶሻል ሚዲያ ፣ ኤፍ ቢ ሲ፣ Heddo Siebs

@tikvahethiopia
#AU #SUDAN

የአፍሪካ ህብረት (AU) ኮሚሽን ሊቀ መንበር የሆኑት ሙሳ ፋኪ መሀመት ትላንት አዲስ አበባ ከገቡት የሱዳን ሉአላዊ የሽግግር ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ጄነራል መሐመድ ሃምዳን ዳጋሎ (ሄሜቲ) ጋር ተወያይተዋል።

ሊቀመንበሩ ፤ ውይይቱ የነበረው አሁን ላይ በሱዳን ስላለው አሳሳቢ ሁኔታ መሆኑን ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA የሱዳን ሉአላዊ የሽግግር ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ጄነራል መሐመድ ሃምዳን ዳጋሎ ኢትዮጵያ ገብተዋል። ጄነራል መሐመድ ሀምዳን ዳጋሎ አዲስ አበባ ሲደርሱ የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ እና የብሄራዊ ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ጥሩነህ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ጄነራል መሐመድ ሃምዳን ዳጋሎና የልዑካን ቡድናቸው በኢትዮጵያ በሚኖረው ቆይታ…
#GeneralDagallo

ጄነራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ (ሄሜቲ) በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር እንዲሁም ከሌሎች አመራሮች ጋር መገናኘታቸውን ገልፀዋል።

ጄነራሉ ባጋሩት ፎቶ : ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፣ ከኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና ከሀገር መከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ ጋር መገናኘታቸውን ያሳያል።

ሄሜቲ ጉብኝቱን በተመለከተ ፥ " ... አዲስ አበባን በመጎብኘቴ እና የዚህችን ውብ ሀገር መሪዎች በወንድማማችነት መንፈስ በማግኘቴ ደስተኛ ነኝ። ይህም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ጥልቀት እና ጥንካሬ ያረጋግጣል " ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ለፓርላማ የተመራው የክልል መለያ ተሽከርካሪዎች ሰሌዳ እንዲነሳ የሚያደርገው ረቂቅ አዋጅ ምንድነው ? (ከሪፖርተር ጋዜጣ) የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ወጥነት ያለው ብሔራዊ የተሽከርካሪ ሰሌዳ አሠራር ለመዘርጋት አልሟል፡፡ በሚኒስቴሩ የሕግ አማካሪ አቶ አበጀ ማሞ 🗣 • " ለተወካዮች ምክር ቤት የተመራው ረቂቅ አዋጅ ከፀደቀ በኋላ የክልል መለያ የያዙ የተሽከርካሪ ሰሌዳዎች ተግባራዊ የሚሆኑት…
#Update

" የክልል መለያን የያዙ ሰሌዳዎችን የሚያስቀር ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ተመራ በሚል በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሠራጨ ያለዉ መረጃ የተሳሳተ ነዉ " - አቶ ካሳሁን ጎፌ

ሪፖርተር ጋዜጣ " የክልል መለያ ተሽከርካሪዎች ሰሌዳን " በተመለከተ ዛሬ አንድ ዘገባ በፊት ገፁ ይዞ ወጥቶ ነበር። (ከላይ በ Reply) ማግኘት ይቻላል።

ጋዜጣው በዘገባው ላይ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የህግ አማካሪ አቶ አበጀ ማሞን ተጨማሪ ዝርዝር ማብራሪያ ይዞ ነው የወጣው።

ከደቂቃዎች በፊት የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ በተረጋገጠ የፌስቡክ ገፃቸው ላይ ፥ " የክልል መለያን የያዙ ሰሌዳዎችን የሚያስቀር ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ተመራ በሚል በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሠራጨ ያለዉ መረጃ የተሳሳተ ነዉ " ብለዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው አራተኛው መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ የመንገድ ትራንስፖርት ረቂቅ አዋጅ ላይ አስፈላጊዉን ግብዓቶችን በማካተት እንዲፀድቅ ወደ ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት መምራቱን አስታውሰዋል።

ሆኖም ግን ከረቂቅ አዋጁ ይዘት ዉጭ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የክልል መለያ ከተሽከርካሪዎች ሰሌዳ ላይ እንዲነሳ የሚያደርግ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ መመራቱን የሚገልጽ ዜና እየተዘገበ ስለመሆኑ አረጋግጠናል ብለዋል።

አቶ ካሳሁን ጎፌ ፥ " በመጀመሪያ መረጃዉ የተሳሳተ እና ከረቂቅ አዋጁ ይዘት ዉጭ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን " ያሉ ሲሆን " በቀድሞ አዋጁ የነበረዉ የተወሰኑ ክልሎችን ታርጋ ዝርዝር የያዘ አባሪ በዚህ ረቂቅ አዋጅ የቀረዉ መንግስት ተጨማሪ ክልሎች ሲወጡ በየጊዜዉ በአዋጁን ማሻሻል ሳያስፈልገዉ ተግባራዊ ለማድረግ እንዲችል ታስቦ መሆኑ ታዉቆ የክልል መለያ ሰሌዳን ከተሸከርካሪዎች ላይ የማንሳት የረቂቅ አዋጁ ሀሳብና ይዘት አካል እንዳልሆን ሊታወቅ ይገባል " ሲሉ አስረድተዋል።

አክለው " ረቂቅ አዋጁ የመንገድ ትራንስፖርትን አስመልክቶ የፌዴራሉንና የክልል አስፈጻሚ አካላት የተሰጣቸውን ሥልጣንና ተግባር በማያሻማ ሁኔታ የሚያስቀምጥ ከመሆኑም በላይ ለሀገራችን ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ዕድገት የመንገድ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ የበለጠ ለማጎልበት ዘርፉ አስተማማኝ፤ የተቀናጀ፤ ዘመናዊና ደኅንነቱ የተረጋገጠ ሆኖ እንዲራመድ የሚያስችል ሲሆን በቅርቡም ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ቀርቦ ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር ሰፊ ዉይይት ተደርጉበት አስፈላጊዉ ማሻሻያ ተደርጎበት እንደሚጸድቅ ይጠበቃል " ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#GeneralDagallo ጄነራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ (ሄሜቲ) በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር እንዲሁም ከሌሎች አመራሮች ጋር መገናኘታቸውን ገልፀዋል። ጄነራሉ ባጋሩት ፎቶ : ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፣ ከኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና ከሀገር መከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ ጋር መገናኘታቸውን ያሳያል። …
" ከሱዳን ጋር ተቀራርበን መስራት እንደሚገባን መግባባት ላይ ደርሰናል " - ዶ/ር አብርሃም በላይ

ከሱዳን ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተቀራርበን መስራት እንደሚገባን መግባባት ላይ ደርሰናል ሲሉ የአገር መከላከያ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ ገልፀዋል።

የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ጄኔራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ በኢትዮጵያ የነበራቸውን የሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት አጠናቀው ዛሬ ወደ አገራቸው ሲመለሱ ዶክተር አብርሃም አሸኛኘት አድርገውላቸዋል።

የጄኔራል ዳጋሎን የኢትዮጵያ ቆይታን በተመለከተ ዶክተር አብርሃም ለኢዜአ እንደገለጹት ፤ በኢትዮጵያ እና በሱዳን የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሂዷል።

“አብረንና ተቀራርበን መስራት እንደሚገባን ተግባብተናል” ሲሉም ገልጸዋል።

ትናንት አዲስ አበባ የገቡት ጄኔራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል።

ጄኔራሉ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪ ከአገር መከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይ እና ከኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ጋር መወያየታቸው ይታወሳል።

#ኢዜአ

@tikvahethiopia
25 ሱደናውያን ከእስር ተለቀቁ።

የጄኔራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎን የኢትዮጵያ ጉብኝትን ተከተሎ ኢትዮጵያ 25 ሱዳናዊያንን ከእስር ለቀቀች፡፡

የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ጄኔራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ በኢትዮጵያ የነበራቸውን የሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት አጠናቀው ወደ ካርቱም ተመልሰዋል፡

ኢትዮጵያ 25 ሱዳናዊያን እስረኞችን መፍታቷን የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይል ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ሱዳናዊያን እስረኞቹ የተፈቱት ጄኔራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ ኢትዮጵያን መጎብኘታቸውን ተከትሎ ነው መሆኑን አል ዓይን ዘግቧል።

እስረኞቹ የተፈቱት ሁለቱ ሀገራት የጋራ ድንበር ጉባኤ ከአንድ ወር በፊት በብሉናይል እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች መካከል የሰላም እና የደህንነት ጉባኤ ካደረጉ በኋላ በተስማሙት መሰረት ነው፡፡

ዛሬ የተፈቱት ሱዳናዊያን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዋና ከተማ አሶሳ ማረሚያ ቤት ታስረው የነበሩ እንደሆነም ተገልጿል፡፡

Credit : አል ዓይን ኒውስ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ ቤተሰቦች ስለ አንፋጋው የኢትዮጵያ የሙዚቃ ሰው ምን አሉ ?

ፍርድዮስ ዩሱፍ ለኤፍ ኤም 97.1 ሬድዮ የተናገሩት ፦

" ... አሊ በራ ሞተ ምናምን እያሉ በየጊዜ ያወጣሉ። ነገር ግን የትላንትናው በጣም እኛንም የጎዳ ያሳዘነን ነው።

ከትላንት ወዲያ ነው ከሆስፒታል የወጣው ፤ በጤንነት ጥዋት ላይ ደግሞ የሚገርመው በእግሩ እኔ ሄዳለሁ አብራችሁኝ ሂዱ ብሎ በመኪና ይዘነው ሄደን ባንክ ሄዶ ለእራሱ የሆነ ትራስዛክሽን ሰርቶ ነው የመጣው።

እንግዲህ ይህ ሰው ዊልቸር ላይ የለም፤ ወይም ደግሞ አልጋ ላይ የለም። በእግሩ ጥዋት ሄዶ ነው የተመለሰው።

እዛው ነው ያደርነው (የአሊ መኖሪያ ቢሾፍቱ) ። ለሊት ላይ ብቻ ስልክ ይጮሃል ምንድነው የተፈጠረው ? እንደተለመደው ሞተ ሊሉኝ ነው ስል በጣም በጣም ከማልጠብቀው ሰው ነው ፌስቡክ ላይ ፖስት ሲያደርግ ሳይ ለማን ነው RIP የምትሉት ኧረ ባካችሁ አንሱ እሱ በጤና ነው ያለው እያልኩኝ ለሊት ሙሉ አልተኛሁም።

ይሄ ነገር ተደጋገመ ፤ ያልተጣራ መረጃ እየለጠፉ ቤተሰብን ያሳዝናሉ ፣ ይሄነገር ባህል ሆነብን እንዴ ? ብቻ አላውቅም በጣም ተደጋጋመ ነገር ግን የትላንት ማታው በጣም ያሳዘነን ነው። ከዚህ ቢቆጠቡ ይሻላል በጣም ደስ የማይል ነገር ነው እያደረጉ ያሉት።

...አሊ ቢራ እጅግ በጣም ጥሩ ሁኔታ ላይ ጥሩ ጤንነት ላይ ነው ያለው። ፀልዩለት ! ሰው ሲፖስት ደግሞ ዝም ብለው ከእስር እያነሱ የሚፖስቱት ደግሞ ቢቆጠቡ። ቤተሰብ አለ፣ ስንት የሚሰማው ሰው አለ ስለዚህ በዚህ ላይክ እና ሼር ለማግኘት ብላችሁ እንዲህ አይነት ነገር የምታደርጉ ብትቆጠቡ እላለሁ። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba እድሳት የተደረገለት የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ህንፃ በነገው እለት እንደሚመረቅ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል። ይህ ታሪካዊ እና የከተማዋ ምልክት የሆነ ህንፃ ከ57 ዓመት በኋላ ለእድሳት የበቃ መሆኑና የከተማዋ የዘመናት ጉዞ አሻራ የያዘ ታላቅ ቅርስ ጭምር መሆኑ ተገልጿል። የከተማው አስተዳደር ፤ ህንፃውን እጀግ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ እንዲታደስ ማድረጉን ገልጾ ለተገልጋይ…
#Update

እድሳት ሲደረግለት የቆየው የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ህንፃ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል።

ለእድሳቱ ከ2.2 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ መሆኑ ተሰምቷል።

ህንፃው ከ57 ዓመታት በኋላ ነባር ገፅታውን ሳይለቅ ነው መሰረታዊ እድሳት የተደረገለት።

ህንፃው አዳዲስና ደረጃቸውን የጠበቁ አገልግሎቶችን በውስጡ ያካተተ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ፦
- የህፃናት መዋያ፣
- ቤተ-መፃሕፍት፣
- የስልጠናና የምርምር ክፍሎች፣
- ክሊኒክ፣
- የቴአትር አዳራሽ፣
- የስብሰባ አዳራሾች፣
- የመኪና ማቆሚያ፣
- አረንጓዴ ስፍራዎችና የከተማ ግብር ናሙናዎች ይገኙበታል።

የከተማዋ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከነገ ሰኞ ጀምሮ ለህዝብ ክፍት እንደሚደረግ እና መጎብኘት እንደሚቻል አሳውቀዋል።

ፎቶ : አ/አ ከንቲባ ፅ/ቤት

@tikvahethiopia