TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#MinistryOfRevenues

በሰበታ የሚገኘው ቢኤምቲ የኬብል ፋብሪካ ሀሰተኛ ደረሰኝ በማቅረብ 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ኪሳራ ሊያሳውቅ ሲል መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ። ድርጅቱ ወደ 670 ሚሊዮን ብር የግብር ዕዳ አለበት ያለው ሚኒስቴሩ፣ ቢኤምቲ ሀሰተኛ ደረሰኝ ከሚያመርቱ ድርጅቶች ደረሰኝ ከመግዛቱ በተጨማሪ ሌሎች ግብር ከፋዮች የከፈሉትን ብር በተመላሽ ሊወስድ ሲሞክር በመሥሪያ ቤቱ ሠራተኞች መያዙ ተነግሯል።

Via አዲስ ማለዳ ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ ጤፍን ጨምሮ በሌሎች የግብርና ግብዓት ምርቶች ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ መሆናቸውን የሚወስነዉ መመሪያዉ ተግባራዊ መደረግ እንደጀመረ ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል። የገንዘብ ሚኒስቴር በአገር ውስጥ የሚመረቱ እና ከውጭ አገር የሚገቡ እቃዎች እንዲሁም በአገር ውስጥ የሚሰጡ አገልግሎቶች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ መሆናቸውን አረጋግጧል። ከሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ መደረግ በተጀመረው…
#ያንብቡ #ኢትዮጵያ

ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ የሚሆኑ እቃዎችን ለመወሰን የወጣው መመሪያ ፤ ' መመሪያ ቁጥር 1006/2016 ' ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል።

መመሪያው ተግባራዊ የተደረገው ዝቅተኛ ገቢ ያለው የህብረተሰብ ክፍል መሰረታዊ የሆኑ የምግብ አቅርቦቶችን ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ ሆኖ እንዲገዛ ለማድረግና የወጪ ጫናውን ለማርገብ ጠቀሜታ ስላለው መሆኑ ተገልጿል።

ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ የሆኑ እቃዎች እና አገልግሎቶች ዝርዝር ምንድናቸው ?

ከዚህ በታች የተዘረዘሩ በአገር ውስጥ የሚመረቱ እና ከውጭ አገር የሚገቡ እቃዎች እንዲሁም በአገር ውስጥ የሚሰጡ አገልግሎቶች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ ናቸው።

1ኛ. እህልና ጥራጥሬ
ጤፍ
ስንዴ
ገብስ
በቆሎ
ማሽላ
ዘንጋዳ
ዳጉሳ
አጃ
አተር ፣ ባቄላ ፣ ምስር፣ አኩሪ አተር፥ ሽምብራ፣ ግብጦ፥ ጓያ እና የመሳሰሉት ጥራጥሬዎች፤
የእነዚህ ዱቄት

2ኛ. የግብርና ግብአቶች
ማዳበሪያ
ጸረ-ተባይ ኬሚካል
የእንስሣት መድሃኒት
የመድሃኒት መርጫ

3ኛ. የበሰሉ ወይም የተዘጋጁ ምግቦች / መጠጦች
👉 እንጀራ
👉 ዳቦ
👉 ወተት

4ኛ. በካፒታል ሊዝ ስምምነት የሚቀርቡ የካፒታል እቃዎች

5ኛ. የወባ መከላከያ አጎበር ፤ ኮንዶም እና ለውሃ ማከሚያ የሚሆኑ ኬሚካሎች

#MinistryofFinance
#MinistryofRevenues

@tikvahethiopia