TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Tigray

የትግራይ ክልል ወቅታዊ ጉዳዮች ፦

- የኢትዮጵያ የፌዴራል መንግስት በትላንትናው ዕለት የተናጠል በሰብዓዊነት ላይ የተመሰረተ የተኩስ አቁም ካወጀ በኃላ በተለያዩ ሀገራት የተሰጡ አስተያየቶች።

- UNICEF ያሰማው ክስ።

- በኔትዎርክ መቋረጥ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ወላጆች እና ትግራይ ክልል ውስጥ ቤተስብ ያላቸው ዜጎች ጭንቀት።

-የአሜሪካ ትግራይን ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለች እንደምትገኝ መግለጿ።

- የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምስራቅ አፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር ሳራ ጃክሰን ስለ ትግራይ ጉዳይ የሰጡት አስተያየት።

- የህወሓት ኃይሎች ሽረን መያዛቸው፣ የኤርትራ ሰራዊት ከሽረ መውጣቱ።

- የህወሓት ኃይሎች በሰጧቸው አስተያየቶች ላይ የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ያወጣው ጠንከር ያለመግለጫ።

- የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት በትግራይ ጉዳይ አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ ስለቀረበለት ጥሪ።

.
.
.
ሌሎችም ጉዳዮች!

(ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት የተዘጋጁ)

ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Tigray-Update-06-29-2
#UAE

ዩኤኢ የሪፐር ድሮኖች እንዲሁም የተዋጊ ጄቶችን ግዢ ልትተወው ነው ?

የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ (UAE) ከ23 ቢሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ገንዘብ አሜሪካን ሰራሽ ኤፍ-35 ተዋጊ ጄቶችን ፣ ሪፐር ድሮኖችንና ሌሎች እጅግ የዘመኑ ጥይቶችን ለመግዛት ያላትን ስምምነት ልትተወው መሆኑን ዎል ስትሪት ጆርናል ዛሬ ዘግቧል።

የባህረ ሰላጤዋ የአሜሪካ አጋር የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ (UAE) የአሜሪካ የደህንነት መስፈርቶች በጣም ከባድ ናቸው የሚል ቅሬታ ማቅረቧን ስማቸው ያልተገለፀ የአሜሪካ ባለስልጣናትን ዋቢ በማድረግ ዎል ስትሪት ጆርናል አስነብቧል።

ጉዳዩን በተመለከተ የኤፍ-35 ኮንትራክተር ሎክሄድ ማርቲን ኮርፕ (LMT.N)፣ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያቤት እንዲሁም የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ወዲያው ምላሽ አልሰጡም።

ሮይተርስ ፥ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቴስ 50 ኤፍ-35 ጄቶች እና እስከ 18 ሰው አልባ አውሮፕላኖችን (ድሮኖች) ለመግዛት ከአሜሪካ ጋር ስምምነት መፈራረማቸውን ጉዳዩን ከሚያውቁ ሰዎች በጥር ወር መስማቱን ገልጿል።

ለአሜሪካ በጣም ቅርብ ከሆኑ የመካከለኛው ምስራቅ አጋሮች አንዷ የሆነችው የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ (UAE) በሎክሄድ ማርቲን የተሰሩትን ኤፍ-35 የጦር ጄቶች ለመግዛት ፍላጎቷን ስትገልጽ ነበር ፤ በተለይ በ2020 ከእስራኤል ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መመስረቷ ኤፍ-35 የጦር ጄቶችን በእጇ እንድታስገባ እንደሚያግዛት ሲነገር ነበር።

እስራኤል በመካከለኛው ምስራቅ ብቸኛ የኤፍ- 35 የጦር ጄቶች ተጠቃሚ ናት።

@tikvahethiopia
#UAE

ዛሬ UAE ውስጥ በድሮን መሆኑ በተገመተ ጥቃት ቢያንስ 3 ሰዎች ሲገደሉ ፤ 6 ሰዎች ቆስለዋል።

የዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ (UAE) ባለሥልጣናት የደሃቢ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አካል በሆነው ስፍራ የሚገኙ 3 የነዳጅ ማጠራቀሚያ ታንከሮች በድሮን መሆኑ የተገመተ ጥቃት የደረሰባቸው መሆኑን ተናግረዋል።

የአገሪቱ መንግሥት ዜና አገልግሎት ባለሥልጣናቱን ጠቅሶ እንዳስታወቀው በደረሰው ጥቃት ቢያንስ ሶስት ሰዎች የሞቱ ሲሆን ሌሎች ስድስት ደግሞ መቁሰላቸው ተመልክቷል፡፡

ከሟቾቹ መካከል 2 ህንድ እና 1 የፓኪስታን ዜጋ እንደሚገኙበት ተነገሯል፡፡

ፖሊስ ሁኔታው እየተጣራ መሆኑን ቢገልጽም የየመን ሁቲዎች ዛሬ ሰኞ በሰጡት መግለጫ ወደ ዩናይትድ አረብ ኤምሬት (UAE) ጠልቆ የሚገባ ጥቃት የሰነዘሩ መሆናቸውን ቢያስታውቁም ስለ ሁኔታው ግን ዝርዝር መግለጫ አልሰጡም፡፡

ሁቲዎች ዩናይትድ አረብ ኤምሬት ላይ ተጨማሪ ጥቃት ሊፈፅሙ እንደሚችሉም አስጠንቅቀዋል።

የዩናይትድ አረብ ኤምሬት (UAE) እ.ኤ.አ. ከ2015 ጀምሮ የየመን ሁቲዎችን የሚወጋውና በሳኡዲ አረብያ የሚመራው የጦር ህብረት አባል መሆንዋ ይታወቃል፡፡

ዘገባውን ቪኦኤ አሶሼይትድ ፕሬስ እና አጃንስ ፍራንስ ፕሬስን ዋቢ አድርጎ ያዘጋጀው ሲሆን በተጨማሪ የአልጀዚራ መረጃ ተካቶበታል።

@tikvahethiopia
#UAE

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዩኤኢ ይገኛሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካን ቡድናቸው ለይፋዊ የስራ ጉብኝት በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ፣ አቡ ዳቢ ይገኛሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር የጋራ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

ምንጭ፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UAE የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዩኤኢ ይገኛሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካን ቡድናቸው ለይፋዊ የስራ ጉብኝት በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ፣ አቡ ዳቢ ይገኛሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር የጋራ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል። ምንጭ፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት @tikvahethiopia
#UAE #ETHIOPIA

የኢትዮጵያ ጠ/ሚር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ ጦር ምክትል አዛዥ ሼክ መሐመድ ቢን ዛይድ በኡቡ ዳቢ ውይይት አድርገው ነበር።

ውይይቱ በትብብር በጋራ ስለሚሰሯቸው ስራዎች እንዲሁም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ማጠናከር ላይ ያተኮረ እንደነበር ዋም ዘግቧል።

መሪዎቹ በምሥራቅ አፍሪካ ሰላም ለማውረድ የሚደረገውን ጥረት ጨምሮ በቀጠናዊ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ተወይይተዋል።

ዶክተር ዐቢይ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ሼክ መሐመድ ቢን ዛይድ ለኢትዮጵያ ህዝብ ሰላም፣ መረጋጋት እና አንድነትን ተመኝተዋል።

ልማትን ለማሳካት ፣ የህዝቦችን መልካም የወደፊት ተስፋ ለመገንባት የመረጋጋት ፣ የሰላም ፣ የአብሮ መኖር እና የመተሳሰብ ምሰሶዎች ላይ ጠንካራ መሰረት መገንባት እንደሚያስፈልግ ሀገራቸው ያላትን ጽኑ እምነት ገልፀዋል።

ሼክ መሐመድ ቢን ዛይድ ፤ የኢትዮጵያ መንግስት የ " ሁቲ አማፅያን " በሀገራቸው ላይ የፈፀሙትን ጥቃት በማውገዝ ላሳየው አቋምና ከዩኤኢ ጎን በመሆን አጋርነቱን በመግለፁ አመስግነዋል።

በሌላ በኩል እኤአ በየካቲት ወር በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ስኬትን እና መልካም እድልን ተመኝተዋል።

ዶ/ር ዐቢይ በበኩላቸው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ላላት አቋም እና ለኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት ስለምታደርገው ድጋፍ ምስጋናቸውንና አድናቆታቸውን ገልጸው ለተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ቀጣይ እድገትና ልማት ተመኝተዋል።

በተጨማሪም የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ከሌሎች ሀገራት ጋር ያላት ግንኙነት በጥበብ እና ሚዛናዊ በሆነ ዲፕሎማሲ ላይ የተመሰረተ እና በተለያዩ የዓለም ሀገራት መረጋጋትንና በተለይ በቀውስ ወቅት ሰላምን ለማስፈን ጥረት እያደረገች ያለውን ግንኙነት እና የጋራ ችግሮችን ለመፍታት ከአገራት ጋር ያላትን ትብብር አድንቀዋል።

ዶ/ር ዐቢይ ፥ የተባበሩት አረብ ኤምሬት የጸጥታ እና የግዛት አንድነቷን ለማስጠበቅ በምትወስዳቸው እርምጃዎች ሁሉ ኢትዮጵያ አጋርነቷን እንደምትገልፅ አረጋገጠዋል።

የሽብር ጥቃቱ ለቀጣናው ሰላምና ደህንነት ከፍተኛ ስጋት የሚፈጥር፣ በቀጠናው ሚካሄደውን የሰላም ጥረት የሚያዳክም እና ሁሉንም ዓለም አቀፍ እና ሰብአዊ ደንቦችን እና ህጎችን የሚጥስ መሆኑንም ገልፀዋል።

ዛሬ ወደ ዩ.ኤ.ኢ ያቀናው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የመሩት የልዑካን ቡድን የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶ/ር አብርሃም በላይ ፣ የብሔራዊ መረጃ እና ደሕንነት አገልግሎት መሥሪያ ቤት ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ፣ የሰለም ሚኒስትር ብናልፍ አንዱአለም ፣ የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ፣ የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል የተካተቱበት ነው።

ይህን ዝርዝር መረጃ ያገኘውነው የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ መንግስት ከሚቆጣጣረው ከዋም ነው።

@tikvahethiopia
#UAE

ታሪካዊ ነው የተባለው ጉብኝት ዩኤኢ ውስጥ እየተካሄደ ነው።

ዛሬ የእስራኤል ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ገብተዋል። ዩኤኢ ሲድርሱም እጅግ የሞቀ አቀባበል እንደተሰረገላቸው ነው ለማወቅ የተቻለው።

ታሪካዊ ነው የተባለ የሰላም ጉብኝት እያካሄዱ ነው ተብሏል።

ፕሬዜዳንቱ በሼክ መሀመድ ቢንዛይድ የተጋበዙ የመጀመሪያው የእስራኤል ፕሬዝዳንት መሆናቸው ተገልጿል።

የእስራኤሉ ፕሬዜዳንት ፤ ሼክ መሀመድ ቢንዛይድ በቤተ መንግስታቸው ላደረጉላቸው አቀባበል እና መስተንግዶ አመስግነው ፤ መካከለኛው ምስራቅ አዲስ ዘመን ውስጥ ገብቷል ብለዋል። ለዚህም ልዑሉና ሌሎች መሪዎች ግንኙነታቸውን መደበኛ ለማድረግ ላደረጉት ጥበባዊ እና ደፋር ውሳኔ አመስግነዋል።

በሼክ መሀመድ ቢንዛይድ እና አይዛክ ሄርዞግ መካከል የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ማጠናከር ላይ ባተኮሩ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ምክክር መደረጉ ተሰምቷል።

በእስራኤል የአሜሪካው አምባሳደር ቶም ኒድስ ጉብኝቱን በተመለከተ " ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ ወደ ተባበሩት አረብ ኤሜሪትስ ላደረጉት ታሪካዊ ጉብኝት እንኳን ደስ አሎት ! ዲፕሎማሲ ይህንን ይመስላል " ብለዋል።

@tikvahethiopia
#UAE 👉 #EGYPT #ETHIOPIA #ISRAEL

ባለፉት ቀናት የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ የኢትዮጵያን ጠቅላይ ሚኒስትር እና ከፍተኛ ባለልስጣናት፣ የግብፅ ፕሬዜዳንትን እንዲሁም የእስራኤል ፕሬዜዳንትን በሀገሯ ተቀብላ አድተናግዳለች።

ሀገሪቱ በቅድሚያ ያስተናገደችው የግብፁን ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲን ሲሆን በመቀጠል ደግሞ የኢትዮጵያን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድን ዛሬ ደግሞ የእስራኤል ፕሬዜዳንት አይዛክ ሄርዞግን ነው።

ከሁሉም መሪዎች እና ባለስልጣናት ጋር ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል። የዛሬው የእስራኤሉ ፕሬዜዳንት ጉብኝት ግን ታሪካዊ መሆኑ ተነግሯል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#UAE

ጠ/ሚ መሀመድ ሁሴን ሮብሌ ዩኤኢ ይገኛሉ።

የሶማሊያ ጠ/ሚር መሀመድ ሁሴን ሮበል በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ የስራ ጉብኝት ላይ እንደሚገኙ አል ዓይን ኒውስ ዘግቧል።

ጠ/ሚ ሮብሌ በትናንትናው ዕለት ወደ አቡዳቢ ያቀኑ ሲሆን ከአገሪቱ አመራሮች ጋር በመወያየት ላይ መሆናቸውን ዘገባው ይገልፃል።

ባለፉት ቀናት የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ የግብፅ ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ፣ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድን እንዲሁም ትላንት የእስራኤል ፕሬዜዳንት አይዛክ ሄርዞግን ተቀብላ አስተናግዳለች።

ከየሀገራቱ መሪዎች ጋርም በተለያዩ ጉዳዮች መክራለች።

ፎቶ : #SomaliPM

@tikvahethiopia
#UAE #Turkey #Kenya

የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የሁለት ቀናት ጉብኝት አድርገዋል።

ኤርዶጋን ጉብኝቱ ስኬታማ ነበር ብለዋል።

ሁለቱ ሀገራት አስራ ሶስት ስምምነቶችን የተፈራረሙ ሲሆን ስምምነቶቹ በሀገራቱ መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያዳብርና ኢንቨስትመንቶችን የሚያሳድግ እንዲሁም ግንኙነታቸውን የበለጠ የሚያጠናክር መሆኑ ተነግሯል።

በሌላ መረጃ የጎረቤት ሀገር #ኬንያ ፕሬዜዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ዛሬ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ይገኛሉ። ፕሬዝዳንት ኬንያታ ከአቡዳቢ አልጋወራሽ እና ከዩኤኢ ምክትል ጦር አዛዥ ከሆኑት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ውይይታቸው በአካባቢያዊ ፣ በአህጉራዊ እና በዓለም አቀፋዊ አጀንዳዎች ዙሪያ እንደነበር አል አይን ኒውስ ዘግቧል።

የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ባለፈው ጥር ወር እንዲሁም አሁን ባለንበት የየካቲት ወር ውስጥ በአጠቃላይ የስድስት ሀገራት መሪዎችን ማለትም ፦
- የግብፅ ፕሬዜዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ
- የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ
- የእስራኤል ፕሬዜዳንት አይዛክ ሄርዞግ
- የሶማሊያ ጠ/ሚር መሀመድ ሁሴን ሮበል
- የቱርክ ፕሬዜዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን
- የኬንያ ፕሬዜዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በሀገሯ አስተናግዳ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መክራለች።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ተጨማሪ " 30.3 ሜትሪክ ቶን " የምግብ አቅርቦት ወደ ትግራይ ክልል ላከች። የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ 5,700 ሴቶችና ህጻናትን ጨምሮ ከ7,100 በላይ ሰዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ 30.3 ሜትሪክ ቶን የምግብ አቅርቦትን የጫነ አምስተኛ አይሮፕላን ወደ ትግራይ ክልል መዲና መቐለ ከተማ ልካለች። ሀገሪቱ ድጋፉ እየጨመረ የመጣውን የአካባቢውን ነዋሪዎች ፍላጎት…
#UAE

የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ (UAE) ተጨማሪ የ30 ሜትሪክ ቶን የምግብ አቅርቦት ወደትግራይ ክልል መዲና መቐለ ልካለች።

ከጥቂት ቀናት በፊት ሀገሪቱ ፤ 30.3 ሜትሪክ ቶን የምግብ አቅርቦትን የጫነ አምስተኛ አይሮፕላን ወደ ትግራይ መላኳ ይታወሳል።

መረጃው በዱባይ በእግሊዘኛ ቋንቋ የሚታተመው Khaleej Times ነው።

@tikvahethiopia
#UAE

የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ፕሬዝዳንት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

ሼክ ኸሊፋ ቢን ዛይድ አል ናህያን በዛሬው ዕለት ነው በ73 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለያታቸው የተሰማው።

በፈረንጆቹ 1948 የተወለዱት ሼክ ኸሊፋ ከ2004 ጀምሮ ሀገራቸውን በፕሬዝዳንትነት በማገልገል ላይ ነበሩ፡፡

የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የፕሬዝዳንቱን ሞት ተከትሎ ለቀጣዮቹ 40 ቀናት የሀገሪቱ ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ ወስናለች፡፡

በቀጣዮቹ ሶስት ቀናት ስራ ዝግ እንደሚሆንም መገለፁን አል ዓይን ኒውስ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
ከዓለም ዙሪያ ፦

#ካናዳ ፦ የካናዳው ጠ/ሚ ጀስቲን ትሩዶ አነስተኛ የእጅ ሽጉጥ መግዛትም ሆነ መታጠቅ እንዲከለከል ጠይቀዋል። የትሩዶ መንግሥት በጠቅላላው የእጅ ሽጉጥ መግዛት ሆነ ቤት ማስቀመጥ በሕግ እንዲያስቀጣ ረቂቅ እያወጣ ነው። ረቂቁ እንደሚለው ካናዳዊያን የእጅ ሽጉጦቻቸውን ባይነጠቁም ከዚህ በኋላ አዲስ መግዛት ግን አይችሉም። ትሩዶ ይህን ሐሳብ ያፈለቁት በአሜሪካዋ ቴክሳስ ግዛት አንድ አፍላ ታጣቂ 19 ሕፃናትን ተኩሶ ከገደለ በኋላ ነው።

➡️ #እስራኤል #UAE ፦ እስራኤል እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ የነፃ ንግድ ስምምነት ተፈራርመዋል ፤ ይህ እስራኤል ከአረብ ሀገር ጋር ያደረገችው የመጀመሪው ትልቅ ስምምነት ነው።

➡️ #ሴኔጋል ፦ የሴኔጋል ፖሊስ በአንድ ሆስፒታል ውስጥ በደረሰው እና የ11 ህጻናት ህይወት ከቀጠፈው የእሳት አደጋ ጋር በተያያዘ ለመጀመሪያ ጊዜ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ማዋሉ ተሰምቷል።

➡️ #ሩስያ ፦ በያዝነው ዓመት 70ኛ ዓመታቸውን የሚደፍኑት የሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በጤና እክል ምናልባትም በካንሰር ህመም እየተሰቃዩ ሳይሆን አይቀርም የሚሉ ያልተረጋገጡ የመገናኛ ብዙኃን ሪፖርቶች እየወጡ ናቸው። የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ግን ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ታመዋል መባሉን ሀሰት ሲሉ አስተባበሉ። ላቭሮቭ ፕሬዚዳንት ፑቲን በየቀኑ በአደባባይ እንደሚታዩ እና እንደማኛውም ጤነኛ ሰው የህመም ምልክት አያታይባቸውም ብለዋል።

➡️ #ሶማሊያ ፦ የሶማሊያ ባይዶዋ ከተማ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐመድን ለመቀበል በዝግጅት ላይ ነች። ከተማዋ ፕሬዝዳንቱ ፈርማጆን አሸንፈው ዳግም የፕሬዜዳንትነት መንበሩን ከተረከቡ በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚጎበኟት ከተማ ትሆናለች።

#ቢቢሲ #ቲአርቲ #ሲጂቲኤን #SNTV

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች እና ትምህርት ቤቶች ተሸለሙ። በዛሬው ዕለት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን እና ትምህርት ቤቶችን መሸለማቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። የፎቶ ባለቤት ፦ የጠ/ሚ ፅ/ቤት @tikvahethiopia
#Update #UAE

በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ 273 ተማሪዎች የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መንግስት ሙሉ ስኮላርሺፕ መስጠቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ መናገራቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት ዛሬ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ወስደው ከግማሽ በላይ ውጤት ካስመዘገቡ ተማሪዎች ውስጥ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ 273 ተማሪዎች እውቅና በሰጡበት ወቅት ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተማሪዎቹ " እንኳን ደስ ያላችሁ " ካሉ በኋላ የተሰጣቸውን ፈተና በአግባቡ መስራት በመቻላቸው " ኢትዮጵያን የሚያግዙ 273 ተማሪዎች ተገኝተዋል በዚህም ደስታ ይሰማናል" ብለዋል፡፡

ተማሪዎቹ እጅግ ዘመናዊ በሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን እንደሚከታተሉና ለኢትዮጵያ እና አፍሪካ የሚደርሱ እንዲሆኑም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ተማሪዎቹ በርትተው ተምረው ሀገራቸውን ሳይረሱ የሚጠቅሙ እንዲሆኑም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሳስበዋል።

ዶ/ር ዐቢይ ሁሉም ተማሪ ጥበብን እንዲሻ እና ሀገሩን ለመለወጥ እንዲሰራ ጠይቀዋል፤ በተለይ " ለእውነት የቆመ ተማሪ ነገ ሃገሩን ይለውጣል፤ እናንተ የላቀ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎችም እውነትን የምትሹ መሆን አለባችሁ እንደዛ ሲሆን ደግሞ ሀገርን የምትገነቡ ትሆናላችሁ " ብለዋል።

#ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia