TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#የመጀመሪያው ቀን⬆️

ፌስቡክን በአንድነት እና በፍቅር መልዕክቶች እናጥለቅልቅ ብለን በጀመርነው ዘመቻችንን በሺዎች የሚቆጠሩ የቤተሰባችን አባላት በገፃቸው ላይ የዛሬውን መልዕክት ለጥፈውታል። ምስጋና ይድረሳችሁ!

50 ሺ መጥፎ የሚያወሩ ሰዎችን እኛ 100 ሺ ሆነን ፍቅር እና አንድነት እናስተምራቸዋለን!

ነገ በሁለተኛው ቀን ሁለተኛውን መልዕክት እያሰራጨን ፌስቡክን በፍቅር እንቆጣጠረዋለን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አረንጓዴ የፖለቲካ ፓርቲ‼️

በኢትዮጵያ #የመጀመሪያው አረንጓዴ የፖለቲካ ፓርቲ ዕውን ሊሆን ነው። በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና በማህበራዊ ፍትህ ላይ ያተኮረ የመጀመሪያውን አረንጓዴ የፖለቲካ ፓርቲ (Green Party) ለማቋቋም ጊዜያዊ አስተባባሪ ፓርቲ መሰየሙን ዋዜማ ራድዮ ዘግቧል።

ከአስተባባሪዎቹ አንዱ #ውባለም_ታደሰ (ዶር) እንዳሉት የተለያዩ ታዋቂ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ #ምሁራን የተካተቱበት ይህ ፓርቲ በሀገሪቱ የሚታየውን ስር የሰደደ ድህነትና ማህበራዊ ፍትህ ዕጦት ለመቅረፍ አረንጓዴ ፓርቲ መፍትሄ አለው ብሎ ያምናል።

ፓርቲው #ብሄርም ሆነ #አካባቢ የማይገድበው ሁሉን አቀፍ መሆኑንና ለማናቸውም ኢትዮጵያውያን በሩ ክፍት መሆኑን አስተባባሪዎቹ ለዋዜማ ሬድዮ ገልፀዋል።

ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴው በቅርቡ መስራች ጉባዔ እንደሚያደርግና በምርጫ ቦርድም #የመመዝገብ እቅድ አለው።

አረንጓዴ ፓርቲ በታዳጊ ሀገሮች እምብዛም የተሳካለት ባይሆንም ባደጉት ሀገሮች በተለይ በጀርመን አናሳ ተፅዕኖ ፈጣሪ በመሆን ይታወቃል። ብዙውን ጊዜም ከሌሎች አውራ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በማበር አጀንዳውን ያስፈፅማል። 

ምንጭ፦ ዋዜማ ሬድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአንጌላ መርክል #የመጀመሪያው ምርመራ ውጤት ከኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ነጻ መሆናቸው አረጋግጧል። በቀጣይ ቀናት ተጨማሪ ምርመራዎች ይደርግላቸዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የቦሪስ ጆንሰን ተተኪ ተመረጡ። የብሪታንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ሊዝ ትረስ አዲሷ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተመርጠዋል። ትረስ እድሜያቸው 47 ሲሆን የቦሪስ ጆንሰን ተተኪ ሆነዋል። ሶስተኛዋ የሀገሪቱ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትርም እንደሆኑ ተገልጿል። ትረስ ተፎካካሪያቸው የነበሩት ሪሺ ሱናክን ሲሆኑ ያሸነፉት 57.4% ድምፅ በማግኘት እንደሆነ ዶቼ ቨለ ዘግቧል። @tikvahethiopia
#UK #China

ሪሺ ሱናክ የዩናይትድ ኪንግደም ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊሆኑ ነው።

ሊዝ ትረስ በተሾሙ በሰባት ሳምንት ስልጣን በቃኝ ያሉ ሲሆን እሳቸውን ለመተካት በተደረገው ውድድር ሪሺ ሱናክ አሸናፊ ሆነዋል።

ሱናክ ፤ የዩናይትድ ኪንግደም #የመጀመሪያው " እስያዊ " ዝርያ ያላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናሉ።

ጠ/ሚ ቦሪስ ጆንሰንን ለመተካት ከሰባት ሳምንታት በፊት በተደረገ ፉክክር ሪሺ ሱናክ ተወዳድረው የነበረ ቢሆንም በሊዝ ትረስ ሊሸነፉ ችለዋል።

ሊዝ ትረስ ' ግብር እቀንሳለሁ፤ ንግድን አሳልጣለሁ " ያሉት አዲስ ፖሊሲ ፍጹም ያልተጠበቀ የገበያ ምስቅልቅልና ብሔራዊ ጦስ ይዞባቸው መጥቶ ነው ሥልጣን እንዲለቁ የሆኑት።
 
ለ45 ቀናት ያህል ስልጣን ላይ የቆዩት ሊዝ ትረስ በዩናይትድ ኪንግደም ታሪክ ለአጭር ጊዜ የቆዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተመዝግበዋል። 

በሌላ መረጃ ፥  የቻይና ገዥ የሆነው ኮሚኒስት ፓርቲ ትላንት ባደረገው ጉባኤ ዢ ዢንፒንግን ዋና ጸሓፊ አድርጎ መምረጡን ተከትሎ ለ3ኛ ጊዜ ስልጣናቸው ተራዝሟል።

የፓርቲው #ዋና_ጸሃፊ በሃገሪቱ የመሪነት ቦታ የሚያስገኝ ሲሆን መጋቢት በሚደረገው የብሄራዊ ህዝቦች ጉባኤ በይፋ ስልጣናቸው ይጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ቢቢሲ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ በፕሪቶሪያው የ #ሰላም_ስምምነት መሰረት የህወሓት ታጣቂ ኃይሎች #የመጀመሪያው_ዙር የተሀድሶና መልሶ የማቋቋም መርሀ ግብር ዛሬ ከመቐለ ከተማ በቅርብ ርቀት በምትገኘው ኩሓ በይፋ መጀመሩን ኢፕድ ዘግቧል።

በመርሃ ግብሩ ማስጀመሪያ ወቅት ላይ መንግስት በትግራይ ያሉ ታጣቂዎችን ከልማት አጋሮች ጋር በመተባበር ወደመደበኛ ህይወታቸው እስኪመለሱ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አሳውቋል።

Photo Credit : EPA

@tikvahethiopia