TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አብዲ ኢሌ⬆️

የሶማሌ ክልልን ለአስር ዓመታት ገደማ ያስተዳደሩት #አብዲ_ሙሃመድ_ዑመር ያለመከሰስ መብታቸው በትላንትናው ዕለት ተገፏል።

የሶማሌ ክልል ምክር ቤት ትላንት ባካሄደው መደበኛ ያልሆነ ጉባዔ ነው አብዲ ሙሃመድ ዑመርን ጨምሮ የሰባት አባላቱ ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ የወሰነው።

ምክር ቤቱ የግለሰቦቹን መብት ያነሳበት ምክንያት በቅርቡ በክልሉ ከተነሳው አለመረጋጋት ጋር ተያይዞ እንደሆነም አስታውቋል።

የአባላቱን ያመለከሰስ መብት የማንሳት ውሳኔውንም ምክር ቤቱ #በሙሉ ድምጽ እንዳፀደቀው ነው የተገለፀው።

ከዚህ በፊት የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ ሙስጠፋ ሙሀመድን ዑመርን የክልሉ ጊዜያዊ ፕሬዝደንት አድርጎ መሾሙ አይዘነጋም።

ክልሉን ለበርካታ ዓመታት የመሩትን አቶ አብዲ ሙሐመድ ኡመርን በመተካት ለሁለት ሳምንታት ክልሉን በፕሬዚዳንትነት ሲመሩ የቆዩት አቶ አህመድ አብዲ ሞሐመድ፤ አቶ ሙስጠፋ ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት ሆነው እንዲቀጥሉ የፓርቲው ሕገ-ደንብ እንደሚፈቅድላቸው ገልጸው ነበር።

©ቢቢሲ

📌አብዲ ኢሌ ትላንት ያለመከሰስ መብታቸው ተገፎ ዛሬ በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል።
@tsegbwolde @tikvahethiopia