TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አቶ ጌታቸው አሰፋ‼️

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) 11ኛ ድርጅታዊ ጉባኤውን ከነገ ጀምሮ በሀዋሳ ያደርጋል። አራቱ የኢህአዴግ እህት ድርጅቶችም ከድርጅታዊ ጉባኤው በፊት የፓርቲዎቻቸውን ሊቀ መንበር፣ ምክትል ሊቀ መንበር፣ የማዕከላዊ እና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫን አካሂደዋል።

የኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) መጠሪያውን ወደ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) በተመሳሳይ መልኩ የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ደግሞ ወደ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) መቀየራቸው ይታወሳል። ሁለቱ ፓርቲዎች ከስማቸው ባሻገር የአርማ ለውጥም አድርገዋል። በሌላ በኩል ሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሓት) እና የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) የቀድሞ ስማቸውን እና አርማቸውን ይዘው ቀጥለዋል።

ኦዴፓ፣ አዴፓ እና ዴኢህዴን በርካታ የቀድሞ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባሎቻቸውን በአዲስ እና ወጣት አባሎች ተክተዋል። ይህ በእንዲህ
እንዳለ ህውሓት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አድርጎ የመረጣቸው ግለሰቦች ነባር እና ከሞላ ጎደል የድርጅቱ ታጋዮች መሆናቸው አነጋጋሪ ሆኖ ቆይቷል።

በተለይ ደግሞ የቀድሞው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ #ጌታቸው_አሰፋ ከዐሥራ አንዱ የድርጅቱ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት መካከል አንዱ ሆነው መመረጣቸው ብዙዎች ህወሓት #ከለውጡ ራሱን ገሽሽ እያደረገ ስለመሆኑ እንደ አንድ ማሳያ አድርገው ወስደውታል።

ለመኾኑ አቶ ጌታቸው አሰፋ ወደ ሥራ አስፈጻሚ መምጣታቸው አሁን ባለው የለውጥ አውድ ምን ፖለቲካዊ ትርጉም ይሰጣል?

በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ለቢቢሲ የሰጡት የህወሓት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና የቀድሞ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ የነበሩትን አቶ #ጌታቸው_ረዳን እንዲህ ብለዋል፦

''ጌታቸው አሰፋ #ጎበዝ መሪ መሆኑን አውቃለሁ። ጎበዝ #ኢህአዴግ መሆኑን አውቃለሁ። ጎበዝ #ህወሓት መሆኑን አውቃለሁ። ህወሓት ሲወስን በሚዲያ #ሃሜት ላይ ተመሥርቶ አይደለም የሚወስነው'' በማለት በቀድሞው የደኅንነት ሹም አቶ ጌታቸው አሰፋ ላይ የሚቀርቡ ወቀሳዎችን አጣጥለዋል።

አቶ ጌታቸው ጨምረውም ''ይፋዊ መግለጫ ሳይኖር ሚዲያዎች ሃሜት ሲያወሩ ነበር። ሃሜት ላይ ተወስነን ውሳኔ የምናስተላልፍ ቢሆን ኖሮ ሃገር #ይጠፋል። ክስ ስለመመስረቱም የማውቀው ነገር የለም። አቶ ጌታቸው አሰፋን ፈልጎ ህውሓት ጋር የመጣ አካል የለም።'' በማለት አቶ ጌታቸው አሰፋ ላይ ክስ አለመመሥረቱን አመላክተዋል።

አቶ ጌታቸው አያይዘው እንደሚሉት ከሆነ አቶ ጌታቸው አሰፋ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆኖ የመመረጥ ፍላጎት አልነበራቸውም።

''ማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ መግባትም አልፈለገም፤ ሲሪየስሊ [አጥብቆ] ነው የተከራከረው። ጉባኤው ግን ከማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ እንዲገባ ወሰነ። ማዕከላዊ ኮሚቴው ደግሞ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ውስጥ መግባት አለበት ብሎ ወሰነ።'' ይላሉ አቶ ጌታቸው ረዳ።

"አቶ ጌታቸው አሰፋ በጉባኤው ላይ ለመሳተፍ ወደ ሀዋሳ ይሄዳሉ ወይ?" ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ አቶ ጌታቸው ረዳ ሲመልሱ ''የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል በጉባኤው እንዲሳተፍ ይጠበቃል። እንደማንኛው የኮሚቴ አባል ሀዋሳ ላይ ልታይዋቸው ትችላላችሁ።

እንደማንኛውም የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ተሳትፎ ማድረግ ስላለብን አንዳንዶቻችን ያው መንገድ ላይ ነን። ለምሳሌ አውሮፕላን ካመለጠኝ ልቀር እችላለሁ'' ብለዋል።

ይህ አገላለጽ 'አቶ ጌታቸው አሰፋ ላይገኙ ይችላሉ' የሚለውን ያመላክት እንደሆነ ከቢቢሲ የተጠየቁት አቶ ጌታቸው ረዳ፣"እኔ የእያንዳንዱ ሰው ስኬጁል አላወጣም። ሁላችንም ተበትነን ነው ወደ ሀዋሳ እየሄድን ያለነው፤ ጌታቸውም በራሱ ጊዜ ስኬጁሉን አሬንጅ ያደርጋል፤ ካገኘሁት እነግራችኋለሁ" ሲሉ በቀልድ የታጀበ ምላሽ ሰጥተዋል።

ነገ በሚጀመረው የኢህአዴግ 11ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ላይ የድርጅቱ ሊቀ መንበር ማን ሊሆን ይችላል ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ ''አሁን ያሉት ሊቀ መንበር ላለፉት 5 ወይም 6 ወራት ሲያገለግሉ ቆይተዋል። እስካሁን የሠሩት ሥራ ተገምግሞ ለውጥ ማድረግ ያስፈልገናል ወይስ አያስፈልገንም የሚለው የጉባኤው ውሳኔ ነው የሚሆነው'' በማለት መልሰዋል።

ህወሓት ማንን በእጩነት ለማቅረብ እንደተሰናዳ የተጠየቁት አቶ ጌታቸው ረዳ ፓርቲዎች እንደማይመርጡ አስረድተዋል። ''ህወሓት፣ ብአዴን
ወይም ኦህዴድ ዕጩዎችን አያቀርቡም። ፓርቲዎች አይደሉም ዕጩዎችን የሚጠቁሙት። ከ180ዎቹ የኢህአዴግ ምክር ቤት አባላት ግለሰቦችን ለሊቀ መንበርነት ለጉባኤው ጥቆማዎችን ይሰጣሉ። ከዚያም ምርጫ ይካሄዳል። ድምጽ ያገኘ ያሸንፋል።'' ብለዋል።

በግንባሩ ጉባኤ ላይ ሊነሱ የሚችሉ ዋና ዋና ጉዳዮች ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ የተጠየቁት አቶ ጌታቸው፤ ''የዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ አፈጻጸም ላይ መቀዛቀዝ ይታያል።

ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት እሱን እንዴት አድርገን ነው በፍጥነት የምናስቀጥለው የሚለው ትልቁ አጀንዳ ነው። ወደ ሃገር እንዲገቡ የተደረጉ ተፎካካሪ፣ ተቃዋሚ የሚባሉ ፓርቲዎች ወደ ሃገር ከገቡ በኋላ አንዳንዱ 'አሸንፌ ነው የመጣሁት' ይላል። ሌላኛው 'ወደሽ ሳይሆን ተገደሽ ነው የተቀበልሺኝ' ይላል። ይህ ዓይነት ስሜት የሚፈጥረው #የሰላም እና #የመረጋጋት ዝብርቅርቅ አለ። ይህን ለመሰሉ ጉዳዮች ጉባኤው #ምላሽ ይሰጣል። ይህ የሁላችንም አጀንዳ ነው'' ብለዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሀዘን መግለጫ⬆️የመቀለ ዩኒቨርሲቲ በዶክተር ደረጀ አሰፋ ድንገተኛ ሞት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል። ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ቤተሰቦቻቸው መፅናናትን ተመኝቷል።

▪️ዶ/ር ደረጀ የቀድሞው የደህንነት ሀላፊ አቶ #ጌታቸው_አሰፋ ወንድም ነበሩ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አቶ #ጌታቸው_አሰፋ ተይዘዋል ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው። የቀድሞ የደህንነት ሀላፊ እስካሁኗ ሰዓት ድረስ በፖሊስ ቁጥጥር ስር አልዋሉም።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ያሬድ ዘሪሁን‼️

ፖሊስ በያሬድ ዘሪሁን ላይ ያቀረበውን የክስ ማመልከቻ ለፍርድ ቤት አሰምቷል።

ፖሊሲ እንዳለው አቶ ያሬድ ዘሪሁን አሁን በቁጥጥር ስር ካልዋለው የቀድሞ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገለግሎት የቀድሞ ኃላፊ #ጌታቸው_አሰፋ ጋር #በመመሳጠርነ ቀጥተኛ ትዕዛዝ በመቀበል በዜጎች ላይ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈፅመዋል፡፡

ዜጎችን አፍነው በመውሰድና በማሰር ብልታቸው ላይ ውሃ በማንጠልጠል ራቁታቸውን ቆሻሻ ውስጥ በመጣል ጉንዳን እንዲበሉ አድርገዋል ብሏል ፖሊስ፡፡

መርማሪ ፖሊስ እንዳለው በተፈፀመባቸው ድብደባ ብዛትም የሞቱ ዜጎችም አሉ፡፡ ግለሰቦች ወደ ኤርትራ ሄደው ህገ ወጥ መሳሪያ እንዲያስገቡ በማቀነባበር ህዝብ እንዲሸበርና ተጠርጣሪዎች ላይ እንዲሳበብ ማድረግ
በሚል ወንጀል እንደጠረጠራቸውም ፖሊስ አስታውቋል። ተጨማሪ ምርመራ ለማድረግ 14 ቀን እንዲሰጠው ፍርድቤቱን ጠይቋል ፡፡

ተጠርጣሪው አቶ ያሬድ በበኩላቸው ከህግ አማካሪያቸው ጋር መገናኘት እንደሚፈልጉ በመግለፅ ለሚቀጥለው ማክሰኞ ቀጠሮ ይሰጠኝ ሲሉ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።

በተጨማሪም ከማንም ጋር እንዳልገናኝ እየተደረኩ ነው፤ አንድ ክፍል ውስጥ ብቻዬን ነው የታሰርኩት ሲሉም ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ አቅርበዋል።

መርማሪ ፖሊስ በበኩሉ ተጠርጣሪው ከማንም ጋር እንዳልገናኝ እየተደረኩ ነው፤ አንድ ክፍል ውስጥ ብቻዬን ነው የታሰርኩት ሲሉ ያቀረቡትን ያስተባበለ ሲሆን፥ ተጨማሪ 14 ቀን የምርመራ ጊዜ እንዲፈቀድለት ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

የግራ ቀኙን የተመለከተው ፍርድ ቤቱም ተጠርጣሪው ከህግ ባለሙያ ጋር እንዲገናኙና የተጠየቀው የ14 ቀን ቀጠሮ ላይ ብይን ለመስጠት ለፊታችን ማክሰኞ 8 ሰዓት ቀጠሮ ሰጥቷል።

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የቀድሞ የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ሀላፊ አቶ #ጌታቸው_አሰፋ እስካሁን በፖሊስ ቁጥጥር ውስጥ እንዳልዋሉ ለመስማት ተችሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ጌታቸው አሰፋ‼️

አቶ #ጌታቸው_አሰፋ በትግራይ ክልል #እንደተሸሸጉ መንግስት መረጃው አለው - ጠቅላይ አቃቢ ህግ
.
.
.
የቀድሞ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው አሰፋ በትግራይ ክልል ተሸሽገው እንደሚገኙ መንግሥት መረጃ እንዳለው ነገር ግን እሳቸውን በሕግ ቁጥጥር ሥር ለማዋል ሲባል ጥይት #በመታኮስ የሌላ ሰው ሕይወት እንዲጠፋ ፍላጎት እንደሌላው ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ ለፓርላማ አሳወቁ።

ዋና ጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉ የመሥሪያ ቤታቸውን የአምስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡበት ወቅት፣ በዜጎች ላይ አሰቃቂ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዲፈጸም በማድረግ የተጠረጠሩትን አቶ ጌታቸው አሰፋን በሕግ ቁጥጥር ሥር ለማዋል የክልሉ መንግሥት አሳልፎ እንዲሰጥ ጥያቄ ቢቀርብለትም ትብብር ለማድረግ ፈቃደኛ አለመሆኑን ተናግረዋል።

ከአቶ ጌታቸው ውጪ የክልሉ ተወላጅ ያልሆኑ ተጠርጣሪዎችንም ክልሉ ከለላ እንደሰጠና በሕግ ቁጥጥር ሥር ማዋል አለመቻሉን አስረድተዋል። ፓርላማው በዚህ ጉዳይ ላይ አቋም ይዞ ለጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚገባም ጠይቀዋል።

ይሁን እንጂ አንዳንድ የምክር ቤቱ አባላት በጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉ ማብራራያ አልተደሰቱም።
መንግሥትም ሆነ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በዚህ ጉዳይ ላይ ፈራ ተባ ሊሉ እንደማይገባ የተናገሩ አንድ የምክር ቤት አባል፣ በደል የፈጸሙ ተጠርጣሪዎችን መንግሥት በሕግ እንዲጠየቁ ማድረግ ሳይችል ስለሕግ የበላይነት ማውራት እንደማይችል ገልጸዋል።

ምንጭ፦ አሀዱ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ጌታቸው አሠፋ‼️

የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ በአቶ #ጌታቸው_አሰፋ ጉዳይ 'እየተወያየ እንዳልሆነ' የኮሚቴው አባል አቶ አማኑኤል አሰፋ ገልፀዋል፡፡ አቶ አማኑኤል "ፖለቲካዊ ችሎት ላይ አልተቀመጥንም፡ ከዚህ የሚበልጥ ብዙ አጀንዳዎች አሉን" ሲሉ በFB ገፃቸው ፅፈዋል፡፡

Via Mili Haileselassie
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአቶ #ጌታቸው_አሰፋ ጉዳይ፡ ፖለቲካዊ ወይስ ሕጋዊ መፍትሄ?
.
.

የትግራይ ክልል አሳልፌ #አልሰጥም ቢል በቀጣይ ምን ሊከሰት ይችላል?

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ አቶ ጌታቸውን ለመያዝ ሰው #መግደል የለብንም ማለታቸው ይታወሳል። አቶ #አብረሃም አቶ ጌታቸውን ለመያዝ የኃይል እርምጃ ሊወሰድ እንደማይገባ ይናገራሉ።

"አንድን ሰው ለመያዝ ተብሎ ወደ ጦርነት ይገባሉ ብዬ አላስብም የፌደራል መንግሥትም ፖለቲካውን ለማስተካከል ሲል ዝምታን ይመርጣል ፤ የትግራይ ክልልም የራሱን ህዝብ የራሱን ደህንነት ይጠብቃል ብየ አስባለሁ።" ይላሉ።


https://telegra.ph/የአቶ-ጌታቸው-አሰፋ-ጉዳይ-ፖለቲካዊ-ወይስ-ሕጋዊ-መፍትሄ-01-07
የፊታችን ሀሙስ ሰልፍ ሊደረግ ነው...

#ጌታቸው_አሰፋ ሽልማት እንጅ #እስር አይገባውም' በሚል መሪ ቃል የፊታችን ሀሙስ በመቐለ ከተማ #ሰላማዊ_ሰልፍ እንደሚያደርግ የትግራይ ወጣቶች ማህበር አስታውቋል።

Via ELU/ድምጺ ወያነ/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በእነ አቶ #ጌታቸው_አሰፋ መዝገብ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጥሪ የተደረገላቸው አቶ ጌታቸው አሰፋ፣ አፅበሃ ግደይ፣ አሰፋ በላይና ሲሻይ ልዑል በጥሪው መሰረት ባለመቅረባቸው ጉዳያቸው በሌሉበት እንዲታይ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የወንጀል ችሎት ትዕዛዝ ሰጠ፡፡

ከዚህ ቀደም በነበረው ችሎት አቃቤ ሕግ ካሉት ምስክሮች 29ኙ የሕግ ምስክሮች ጥበቃ እንዲደረግላቸው ያቀረበውን አቤቱታ በወቅቱ ችሎቱ ለዳኞች ብቻ ጥበቃ ትዕዛዝ ቢሰጠም ሕጉ ይህን ስለማይፈቅድ ስም ዝርዝሩን ለማቅረብ መቸገሩን አቃቤ ሕግ በችሎቱ ባቀረበው አቤቱታ ገልጿል፡፡

ችሎቱም ጥበቃ የሚደረግላቸው ሰዎች ስም ዝርዝር አቃቤ ሕግ እንዲያቀርብ የተሰጠውን ትዕዛዝ ባለመፈጸሙ እስካሁን ጥበቃ የተደረገለት ምስክር የለም ብሏል፡፡

ከሐምሌ 18/2011ዓ.ም ጀምሮ ምስክሮችን ለመስማት የተያዘው ቀጠሮ እንደተጠበቀው ሆኖ፣ የችሎቱ መደበኛ ሥራ እስከ ሐምሌ 15 የሚቀጥል በመሆኑ፣ ችሎቱ ነሐሴ 7 እና 8ን ለተጨማሪ የምስክርነት መስሚያ ቀናት ይዟል፡፡ ተይዘው ጉዳያቸው በፍርድቤት እየታየ ያሉት ተከሳሾች በሒሳብ ደብተራቸው ያላቸውን ገንዘብ እና በቁጠባ ያጠራቀሙትን ገንዘብ በእግድ ምክንያት እስካሁን ለማንቀሳቀስ መቸገራቸውን ለችሎቱ አስረድተዋል፡፡ ችሎቱም ገንዘቡ በሌላ መዝገብ ከታገደ በዚህ መዝገብ ጉዳዩ በቀጥታ ባለመኖሩ የሚሰጥ ትዕዛዝ እንደማይኖር ገልጿል፡፡ ስለጉዳዩም ተከሳሾቹ ጠበቆቻቸውን ቢያማክሩ የተሻለ እንደሚሆን ለችሎቱ አስረድተዋል፡፡

Via waltainfo
@tsegabwolde @tikvahethiopia