TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
እስር ላይ ከነበሩት ጋዜጠኞች መካከል ጋዜጠኛ እና አክቲቪስት ኢያስፔድ ተስፋዬ ዛሬ ከእስር ተፈቷል።
ኡቡንቱ የተባለው ሚዲያ መስራችና ጋዜጠኛ እያስፔድ ተስፋዬ ዛሬ ከቀትር በኋላ ነው ከእስር እንደተፈታ ሚዲያው የገለፀው።
ጋዜጠኛ እና አክቲቪስት እያስፔድ 43 ቀናት በእስር ሲቆይ ፖሊስ አንድም ጊዜ ፍርድ ቤት እንዳላቀረበው እና ክስም እንዳልመሠረተበት ሚዲያው ገልጿል።
በትላንትናው ዕለት ጋዜጠኛ መዓዛ መሀመድ ከእስር መፈታቷ ይታወቃል።
ሌሎች በእስር ላይ ከሚገኙ ጋዜጠኞች መካከል ተራራ ኔትዎርክ የተባለው ሚዲያ መስራች ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ የአሐዱ ሬዲዮ ባልደረባ ጋዜጠኛ ክብሮም ወርቁ ስለመፈታታቸው የተባለ ነገር የለም።
@tikvahethiopia

#Somaliland በሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ የሚመራ ከፍተኛ የልኡካን ቡድን ዛሬ ማለዳ ወደ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ማቅናቱ ተነግሯል። ፕሬዝዳንቱ ከኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በተደረገላቸው ይፋዊ ግብዣ መሰረት ነው ወደኢትዮጵያ እንደሚመጡ የተገለፀው። በሌላ በኩል ፥ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢሳ ካይድ የሚመራ የልዑካን ቡድን ከፕሬዜዳንቱ ሙሴ ቢሂ አብዲ ቀደም…
የፕሬዜዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ የኢትዮጵያ ቆይታ ፦
በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ግብዣ ወደ ኢትዮጵያ እንደመጡ የተነገረላቸው የሶማሊላንድ ፕሬዤዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ ወደ ሀርጌሳ ተመልሰዋል።
ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ በኢትዮጵያ ቆይታቸው የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የስራ እንቅስቃሴን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ ላይ የሲዳማ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ደስታ ሌዳሞ፣ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተሳትፈው ነበር።

#ጥምቀት የኢፌዴሪ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ዛሬ ባወጣው መግለጫ የጥምቀት በዓል በሰላም ተከብሮ በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊ ዝግጅት መደረጉን አሳውቋል። የበዓሉ ታዳሚዎችና እንግዶች ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆንና በዓሉን በሰላም እንዲከበር ግብረ ኃይሉ ከወትሮው በተለየ መልኩ በቂ ዝግጅት በማድረግ ስምሪት ወስዶ ወደ ተግባር መግባቱን ገልጿል፡፡ ግብረኃይሉ ፥ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች…
" የ2014 ዓ/ም የጥምቀት በዓል በሰላም ተጠናቋል " - የፀጥታና ደህንነት የጋራ-ግብረ ኃይል
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ -ግብረ ኃይል የጥምቀት በዓል በሰላም መጠናቀቁን አስታውቋል።
የጋራ-ግብረ ኃይሉ አዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማን ጨምሮ በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች በዓሉ በሰላም ተከብሮ መጠናቀቁን ገልጿል።
ለበዓሉ በሰላም መጠናቀቅ ሕዝበ ክርስቲያኑ፣ የሃይማኖት አባቶች ፣ የደብር ኃላፊዎች፣ ወጣቶችና ሴቶች እንዲሁም በዓሉን ለማስተባበር በየደረጃው የተዋቀሩ ኮሚቴዎች ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ግብረ-ኃይሉ ምስጋና አቅርቧል።
በተመሳሳይም ይህ ታላቅ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ ኃላፊነታቸውን በብቃት ለተወጡት የግብረ-ኃይሉ አባላት ምስጋና ቀርቧል።

#ETHIOPIA
የተመድ ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጎተሬዥ በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ መልዕክተኛ ክቡር ኦሊሲንጎ ኦቦሳንጆ በኢትዮጵያ ባለው ግጭት ዙሪያ በመቐለ እና በአዲስ አበባ ያደረጉትን ግብኝት ተከትሎ የስልክ ውይይት አድርጌያለሁ ሲሉ አስተውቀዋል።
ሰላም ለማስፈን የሚያስችል ተጨባጭ ጥረት በመኖሩ ተደስቻለሁ ብለዋል፡፡
" ኦሊሴንጉ ኦባሳንጆ በኢትዮጵያ መንግሥትና ህወሓት ግጭቱን ለማስወገድ እያደረጉ ስላሉት ጥረት ገለጻ አድርገውልኛል” ያሉት ዋና ጸሀፊው ግጭቱና ጥቃቱ እንዲያበቃ አሁን ፖሊካዊና ዲፕሎማሲያዊ እልባት ለመስጠት የሚያስችል ትክክለኛ እድልና አጋጣሚ ስለመኖሩ ተስፋ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡
ጉተሬዥ ከአንድ ዓመት በላይ በመላው ኢትዮጵያና በአካባቢው በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለጉዳት ከዳረገው ግጭት በኋላ አሁን ሰላም ለማስፈን የሚያስችል ተጨባጭ ጥረት በመኖሩ ተደስቻለሁ ብለዋል፡፡
በአንዳንድ የሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች አሁንም የሚካሄደው ውጊያ ለሰላም ሂደቱ መራር ፈተና መሆኑን የገለጹት ዋና ጸሀፊው በሁሉም ወገኖች ዘንድ መተማመን የሚፈጥሩ ጠንካራ እምርጃዎች እየተወሰዱ ነው ብለው ተስፋ ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡
ጎተሬዥ አሁንም ሰላምን ለማስፈን ትክክለኛው አቅጣጫ ሁሉም ወገኖች ግጭቱን ማቆሙ ያላባቸው መሆኑን ያቀረብኩትን ጥሬዬን እንደገና አቀርባለሁ ብለዋል፡፡
የተባበሩት መንግሥታት ኢትዮጵያ ውስጥ በኢትዮጵያውያን ባለቤትነት የሚመራ ሁሉን አቀፍ ብሄራዊ የሰላም የደህንነትና የእርቅ ሂደትን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም ሁሉም ወገኖች ለሰላሙ ሂደት በቅንነትና በቁርጠኝነት እንዲሳተፉ የሚያደርገውን ጥረት መቀጠል አለበት ማለታቸውን ቪኦኤ ዘግቧል።

#Update ዴቪድ ሳተርፊልድ እና ሞሊ ፊ ሳዑዲ አረቢያ ይገኛሉ። በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ኃላፊ የሆኑት ሞሊ ፊ እና የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ ትላንት ሳዑዲ አረቢያ ገብተዋል። የሳውዲ አረቢያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑል ፋይሰል ቢን ፋርሃን ሁለቱን የአሜሪካ ባለስልጣናት ተቀብለው አነጋግረዋል። በውይይታቸው ወቅት በሳዑዲ አረቢያ እና…
#Update
ሞሊ ፊ እና ሳተር ፊልድ በሱዳን ውይይት አድርገዋል።
በቀናት በፊት ሳዑዲ አረቢያ የነበሩት በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ኃላፊ የሆኑት ሞሊ ፊ እና የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ ሱዳን ገብተው በሱዳን ጉዳይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት አድርገዋል።
ሁለቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት በቀጣይ በአዲስ አበባ ተገኝተው ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) የሰላም ማስከበር ዘመቻ ኃላፊ ጅን ፔሬ ላክሮክስ እንደገለጹት በአብየ ሚገኘውን የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሃይል የተመተካቱ ሂደት በቀጣይ ወር ይጀምራል፡፡
ሱዳን በአብየ ያለው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ጦር እንዲወጣ ጥያቄ አቅርባ የነበረ ሲሆን ጥያቄዋም በተመድ ተቀባይነት ማግኘቱ ይታወሳል፡፡
ሱዳን የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ጦር ይወጣ ያለችው በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል በድንበር ጉዳይ አለመግባባት ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ ነው፡፡
ኃላፊዋ ላክሮክስ ይህን ያሉት ከሱዳን ሉአላዊ የሽግግር ም/ቤት ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አልቡርሃን ጋር ባደረጉት የስልክ ወይይት ነው ተብሏል፡፡
የሽግግር ም/ቤቱ እንደገለጸው አልቡርሃን ከተመድ ኃላፊ ጋር ያደረጉት ውይይት የተመድ ኢንትሪም ሴኩሪቲ ፎርስ ፎረ አብየ ውስጥ ያሉት የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ወታደሮችን በሱዳን መንግስት በተጠየቀው መሰረት ለመተካት የመከረ ነበር፡፡
በስልክ ወይይቱ ወቅት ላክሮክስ የመተካቱና የመተካቱ ስራ በፈረንጆቹ ቀጣይ የካቲት ወር እንደሚጀመርና እስከ ፈረንጆቹ መጋቢት 2022 እንደሚቀጥል ማረጋገጣቸው ተዘግቧል፡፡
ምንጭ፦ አል ዓይን

" ዝም አላልም ለምን፣ እንዴት የሚሉትን የሚያጣራ የህግ አካል ይዞታል ቀጣይ የሚኖሩ ሂደቶችን የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን " - ሐጅ ዑስማን ዑመር
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከትላንት በስቲያ የከተራ በዓል በሚከበርበት ወቅት በባህር ዳር ከተማ የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ፅ/ቤት ትንኮሳ መፈፀሙን ገልፆ የደረሰውን ጉዳት የክልሉ መንግስት በአስቸኳይ አጣርቶ ትንኮሳውን እና አደጋውን ያደረሱትን ግለሰቦች ለህግ አቅርቦ ተገቢውን ፍትህ እንዲያሰፍን አጥብቆ ጠይቋል።
ምክር ቤቱ ባሰራጨው አጭር መልዕክት ፥ " መንግስት በክልሉ ሙስሊም ላይ በየጊዜው የሚደርሱት መሠል ተደጋጋሚ ትንኮሳዎች እና የመብት ጥሰቶችን በማስቆም የዜጎችን ሰላም የማስከበር ኃላፊነት እንዲወጣ ጥሪ እናቀርባለን " ብሏል።
በተመሣሳይ የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጸሐፊ ሐጅ ዑስማን ዑመር በጥምቀት በአል ዋዜማ በአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ቢሮ ላይ የተደረገው የቢሮውን የብሉኬት አጥርን የማፈራረስና የተለያዩ ክብረ ነክ ስድቦች መሳደብ እጅግ ሊወገዙና ተከባብሮና ተቻችሎ በመኖር ብቻ ሀገር እንደሚገነባ ፅኑ እምነት ያላቸው የእምነቱ ተከታዮች ድርጊቱን ሊያወግዙ እና በዚህ አፀያፊ ተግባር የተሳተፉ አካሎችን ወደ ህግ ማቅረብ እንዳለባቸው አጥብቀው አሳስበዋል።
ከተፈፀመው ድርጊት ጋር በተያያዘም " ዝም አላልም ለምን፣ እንዴት የሚሉትን የሚያጣራ የህግ አካል ይዞታል ቀጣይ የሚኖሩ ሂደቶችን የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን " ብለዋል።

የአፍሪካ ኅብረት 35ኛ የመሪዎች ጉባኤ በቀጣይ ሳምንት በአዲስ አበባ ይካሄዳል።
ዛሬ ሳምንታዊ መግለጫ የሰጡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ፥ " ጉባኤው ኢትዮጵያ ሠላም አይደለችም የሚለውን የጠላት ሃሳብ ከመሰረቱ ነቅሎ የሚጥል ነው " ብለዋል።
ጉባኤውን ከማስቀረት ባለፈ የአፍሪካ ኅብረት መቀመጫን ከኢትዮጵያ ለማንሳት ዘርፈ ብዙ ጥረቶች ሲደረጉ መቆየታቸውን አምባሳደር ዲና ሙፍቲ አንስተዋል።
ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ያላትን ሚና ከግምት በማስገባት በተሠራ ሰፊ የዲፕሎማሲ ሥራ ግን ጉባዔው አዲስ አበባ እንዲካሄድ ተወስኗል ብለዋል።
አፍሪካውያን ተጽእኖ ፈጣሪዎች እንዲሁም ታዋቂ ሰዎችም በዲፕሎማሲው ሥራ የራሳቸው አበርክቶ ነበራቸውም ብለዋል።
የጉባኤው ዋና አጀንዳ አልሚ ምግብ ላይ መሆኑን የገለጹት ቃል አቀባዩ፥ ጉባኤው የተሳካ እንዲሆን ግብረ-ኃይል ተቋቁሞ ሰፊ ዝግጅት እየተደረገ ነው ሲሉ አሳውቀዋል።
#ኤፍቢሲ

" ድሬዳዋ የአብሮነት የፍቅር የሰላም ከተማ ! "
በድሬዳዋ የተከበረው የጥምቀት በዓል በከተማው በሚገኙ የተለያዩ የእምነት ተከታዮች ወንድማዊ ፍቅር የደመቀ ነው ሲል ድሬዳዋ ፖሊስ አሳውቋል።
ድሬዳዋ ፖሊስ ከከተራ በዓል ጀምሮ ህዝበ ክርስቲያኑ ታቦታቱን አጅበው ወደ ጥምቀተ ባህሩ ሲያቀኑ ድካም ለተሰማቸው ህዝበ ክርስቲያን ቀዝቃዛ ውሃ እንዲሁም የሚበሉ ልዩ ልዩ የምግብ አይነቶችን አዘጋጅቶ በመስጠት ህዝበ ሙስሊሙ ያሳየው ተሳትፎ የቀደመውን የአብሮነት መንፈስ ገልጦ አሳይቷል ሲል ገልጿል።
በዛሬው ዕለት ታቦታቱ ካደሩበት ጥምቀተ ባህር ወደ መንበራቸው ሲመለሱ በከተማው በሚገኙ ሁሉም አካባቢዎች ህዝበ ሙስሊሙ እንዲሁም የተለያዩ የእምነት ተከታዮች በዓሉ በሠላም እንዲከበር ጥበቃ ከማድረግ በላይ ገንዘብ በማዋጣት ለበአሉ ድምቀት በየአካባቢያቸው ባነር በማሠራት ኩኪስና ልዩ ልዩ ጣፋጭ ምግቦች በማዘጋጀት እንዲሁም የታሸገ ውሃ በማቅረብ ፍቅራቸውን በገሀድ አሳይተዋል።
በአብሮነትና በፍቅር መንፈስ ተከብሮ ያለፈውን የዘንድሮ የጥምቀት በዓል በሁሉም የከተማው ነዋሪ ዘንድ ልብን በሀሴት የሞላ እንደነበር ድሬዳዋ ፖሊስ ገልጿል።
የዘንድሮ የጥምቀት በዓል በድሬዳዋ ከተማ በብዙ ፍቅር በመልካም አብሮነት እጅግ በላቀ ሠላም የተከበረ ሲሆን ነገ እና ከነገ በስቲያ ከባህረ ጥምቀቱ ወደ መንበራቸው የሚመለሱ ታቦታት በደመቀ ፍቅር ወደ መንበራቸው እንደሚገቡ ይጠበቃል።
ድሬዳዋ የአብሮነት እና የፍቅር ከተማ መሆኗን በርካቶች ያለምንም መንገራገር በልበ ሙሉነት የሚናገሩት ጉዳይ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የአብሮነት እና የፍቅር ከተማነቷ ተቀዛቅዟል ለሚሉ ሠዎች የዘንድሮ ጥምቀት በዓል የቀደመው ፍቅር እና አብሮነት እንዳለ ሁነኛ ምሳሌ ሆኖ ተጠናቋል ሲል ድሬዳዋ ፖሊስ ገልጿል።