TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" የአሜሪካ ትኩረት በኢትዮጵያ የሚካሄደውን ጦርነት ወደ ፍፃሜው ማምጣት ነው " - ኔድ ፕራይስ

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል ሀገራቸው አሜሪካ ትኩረቷ በኢትዮጵያ የሚካሄደውን ጦርነት ወደ ፍፃሜው ማምጣት ነው ብለዋል።

በሰሜን ኢትዮጵያ በተከሰተው ግጭት የተንሰራፋውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፣ ረገጣና ስቃይ ለማስቆም ከሁሉ የተሻለው መንገድ ጦርነቱ መቋጫ የሚያገኝበትን መንገድ መፈለግ እንደሆነ ኔድ ፕራንስ ተናግረዋል።

ለዚህ አሜሪካ ልዩ ትኩረት ለሰጠችው ጉዳይ ጠንካራ ዴፕሎማሲ እየተከተለች ነው ብለዋል።

ኔድ ፕራስ ፥ " ጠንካራ ዴፕሎማሲ እየተከተልን ነው። በመሪዎች ደረጃ የተካሄደው የስልክ ውይይት የዚህ አካል ነበር። አምባሳደር ፌልትማን እና የአሁኑ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ስታርፊልድ በዚህ ውስጥ በጥልቀት ተሰማርተዋል። ከቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዜዳንት ኦሊሴንጉ ኦባሳንጆ ጋር በቅርበት በመስራት ላይ ነን " ሲሉ ገልፀዋል።

ቃል አቀባዩ ፕራስ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድን ጋር የመነጋገር እድል እንዳገኙ አንስተዋል። ንግግሩ አንዱ የዲፕሎማሲው አካል ነው ብለዋል።

ኔድ ፕራስ አሁን ያለው ሁኔታ በግጭት ውስጥ ላሉት ወገኖች መልካም እምነትን ለማሳየት እድል ይሰጣል ብለን እናምናለን ያሉ ሲሆን ውጊያ አቁመው ወደ ድርድር ጠረጴዛ ሊመጡ ይህ ደግሞ ግጭቱ እንዲዘጋ ሊያደርገው ይችላል ሲሉ ማመልከታቸውን ዶቼ ቨለ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#Balderas

የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ዛሬ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቶ ነበር።

ፓርቲው በመግለጫው የተለያዩ ጉዳዮችን ያነሳ ሲሆን ከነዚህ መካከል የሰሜኑ ጦርነት እና የእነ አቶ ስብሃት ነጋ ክስ ማቋረጥ ጉዳይ አንዱ ነበር።

ፓርቲው የሰሜኑ ጦርነት መነሻ ህወሓት የጀመረው ቅድመ ጥቃት እንደሆነ እረዳለሁ ብሏል።

የፌዴራል መንግስቱ በርካታ የአፈፃፀም ችግሮች ቢኖሩበትም ያደረገው የመከላከል ጦርነት ፍትሃዊ እንደሆነ ባልደራስ እንደሚያምን አሳውቋል።

በዚህም ፓርቲው ፖለቲካዊ ድጋፍ ከማድረግም ባለፈ በአካል ቦታው ድረስ በመሄድ ቁሳዊ እገዛ ማድረጉን አስታውሷል።

ነገር ግን መንግስት " ምዕራፍ አንድ " ያለውን ዘመቻ የኢትዮጵያን ሉኣላዊነት ሳያረጋግጥ ማቆሙ ትልቅ አደጋ ያዘለ መሆኑን ፓርቲው መገምገሙን ገልጿል።

ዘመቻውን ያቆመበት አመከንዮ ከማስረዳት አኳያ ሆነ እሱን ተከትሎ ከህዝብ ከሚነሳው ተጨባጭ ስጋት ዙሪያ በቂ ምላሽ አልሰጠም።

ባልደራስ ፓርቲ ፥ " መንግስት ' ተከድተናል ' ለሚለው የኢትዮጵያ ህዝብ እያሳየ ያለውን ንቀት ማስተካከል ይገባዋል። ህወሓት አሁንም የሀገሪቱን አንድነት ሊፈታተን በሚችል ወታደራዊ ቁመና ላይ ይገኛል። የዘመቻው ፍፃሜ የኢትዮጵያ አንድነት አደጋ ላይ የሚጥለውን የህወሓት ወታደራዊ አቅምን በመስበር መቋጨት ይገባል። " ብሏል።

በተጨማሪም የህወሓት የፖለቲካ እና የጦርነቱ ዋነኛ ቀስቃሽ የሆኑ ጉዳያቸውን በህግ ጥላ ስር ሆነው እየተከታተሉ የነበሩ እስረኞችን ሰሞኑን መፍታት መጀመሩ የህግ የበላይነትን የጣሰ ውሳኔ ሆኖ ማግኘቱን ባልደራስ በመግለጫው ላይ ገልጿል።

ያንብቡ : telegra.ph/Tikvah-01-13

@tikvahethiopia
#አቢሲኒያ_ባንክ

አቢሲንያ ባንክ ከቪዛ ካርድ ጋር በመተባበር ሀገራችን ኢትዮጵያ ከካሜሩን ጋር ዛሬ ሀሙስ ጥር 5 ቀን 2014 ዓ/ም የሚያደርጉትን ፍልሚያ በጊዮን ግሩቭ ጋርደን በግዙፍ እስክሪን አብረን እንመልከት ይሎታል።

ምግቡ መጠጡ ሙዚቃው ሁሉም ተሰናድቶል። ዝግጅቱ ከቀኑ11:00 ሰዓት ጀምሮ ክፍት የሚሆን ሲሆን፣ ጨዋታው 1፡00 ሰዓት ላይ ይጀምራል፡፡

#መግቢያበነፃ

ቪዛ ካርድ የቶታል ኢነርጂስ አፍሪካ ዋንጫ ኦፊሻል ስፖንሰር !

የአቢሲንያ ባንክን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻነል ይቀላቀሉ! https://t.iss.one/BoAEth
በጦቢያ የቤተሰብ ቀን ልዩ ፌስቲቫል !

ውድ የጦቢያ ቤተሰቦች እሁድ ጥር 8/2014 " በጊዮን ግሮቭ ጋርደን ዎክ " ከቀኑ 6ሰአት ጀምሮ

- በማርሽ ባንድ ኢትዮጵያን ይዘምራሉ!
- በድንቅ ገጣሚያን የግጥም ጥምዎን ያረካሉ!
- በፍራሽ አዳሹ ፍራሽዎ ይታደሳል!
- በመረዋ ኳየር የተቀነባበረ ስልተ ድምፅ ይደመማሉ!
- በኢትዮጵያነት የውዝዋዜ ቡድን አዲስ ስራዎች ይዝናናሉ። በዚህ ሁሉ ውስጥ ኢትዮጵያችን አለች!!

#በነፃ_ሃሳብና_በሰከነ_መንፈስ_ኢትዮጵያንና_ኢትዮጵያዊነትን_እናድምቅ!

የመግቢያ ትኬቱ በሁሉም የቡና ባንክ ቅርንጫፎች ይገኛል።
ለመረጃ 0919787878
#ETHIOPIA

ዛሬ የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት መግለጫ አውጥቶ ነበር።

በዚህም መግለጫው ላይ TPLF ለትግራይ ህዝብ ሰብዓዊ ድጋፍ እንዳይቀርብ እንቅፋት ሆኖ መቀጠሉን አስገንዝቧል።

የመንግስት ኮሚኒኬሽን ፥ " እንደ ዓለም ጤና ድርጅት አይነት ለሁሉም ሰው በእኩል ቆመናል የሚሉ አለምአቀፍ ተቋማት ግን አሸባሪው ቡድን የአማራና አፋር ክልሎችን በወረረበት ወቅት ሀስፒታሎችንና የጤና ጣቢያዎችን ሲዘርፍና ሲያወድም ንፁሃንን ሲደፍርና ሲገድል የሽብር ቡድኑን ድርጊት ሲያወግዙ አልተደመጡም " ብሏል።

" ይልቁንም መንግስት ወደ ትግራይ ክልል እርዳታ እንዳይገባ እያደረገ ነው በሚል የአሸባሪው ቡድን የሚያሰማውን ፕሮፖጋንዳ ተቀብለው እያስተጋቡት ይገኛል። ይህ በመንግስት ዘንድ ፍፁም ተቀባይነት የለውም " ሲል አሳውቋል።

የመንግስት ኮሚኒኬሽን ፥ " አሁንም ለአንድ ወገን ባጋደለው አቋማቸው በመጽናት የሽብር ቡድኑ ወደ ትግራይ የሰብአዊ እርዳታ እንዳይገባ እንቅፋት መሆኑን በግልጽ አለማንሳታቸው በተዛባ አመለካከታቸው መጽናታቸውንና ውግንናቸው ለህዝብ ጥቅም ሳይሆን ለፖለቲካ አጀንዳ መሆኑን ያመለክታል " ሲል ገልጿል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ለትግራይ ክልል ህዝብ የዕለት ደራሽ ዕርዳታ ያለ ምንም መስተጓጎል እንዲቀርብ ለማስቻል በየጊዜው ከአጋር አካላት ጋር ምክክሮችን በማድረግ እየሠራ ይገኛል ሲል አሳውቋል።

* ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopoa
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም እና ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ ባለንበት ማረሚያ ቤት በትግረኛ ቋንቋ ስልክ ለማውራት እና በማረሚያ ቤት በተለያየ ቦታ ላይ የታሰርነው ተገናኝተን ለመወያየት ይፈቀድልን ሲሉ ባቀረቡት አቤቱታ ላይ ማረሚያ ቤት አስተዳደር አስተያየት እንዲሰጥበት ታዘዘ። አቶ ተክላይ አብርሐ ፖስፖርቴንና መንጃ ፍቃዴን ለማሳደስ ለዩንቨርስቲ መታወቂያ ላላቸው ቤተሰቦቼ ውክልና እንድሰጥ ይፈቀድልኝ…
#Update

በስልክ በትግረኛ ቋንቋ ለማውራት እና ማስታወሻ ደብተር እንድንይዝ ይፈቀድልን ሲሉ ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም ባቀረቡት አቤቱታ ላይ ማረሚያ ቤቱ መልስ ሰጥቷል።

በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ልደታ ምድብ 1ኛ የፀረ ሽብርና የህገመንግስት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ለዛሬ የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር በ6 ተከሳሾች በተነሱ አቤቱታዎች ላይ መልስ እንዲሰጥ በያዘው ቀጠሮ ችሎቱ የተሰየመ ሲሆን አቤቱታ አቅርበው ከነበሩ ስድስት ተከሳሾች ውስጥ 11 ኛ ተከሳሽ ወ/ሮ ሙሉ ገ/እግዛብሔር ክሳቸው በመቋረጡ አቤቱታቸው ታልፏል።

በዛሬው ቀጠሮ 8ኛ ተከሳሽ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም እና 19 ኛ ተከሳሽ ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ በህመም ምክንያት በችሎት ያልቀረቡ ሲሆን 20ኛ ተከሳሽ አሰፉ ሊላይ 43 ኛ ተከሳሽ ተክላይ አብርሐ እና 44 ኛ ተከሳሽ ዘሚካኤል አንባዬ ግን ቀርበዋል።

የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር የቀድሞ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዬ የነበሩት ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም በትግረኛ ቋንቋ ስልክ ለማውራት ስለተከለከልን እንዲፈቀድልት ይታዘዝልን ስትል ያቀረበችው አቤቱታን በተመለከተ ማረሚያ ቤቱ በስልክ ማውራትም የተከለከለው ለሀገሪቷ ደህንነት ክትትል ስለሚደረግ መሆኑን በጽሁፍ ምላሽ ሰጥቷል።

በተጨማሪም የማስታወሻ ደብተር ተከልክለናል ሲሉ ባቀረቡት አቤቱታ ላይ ማረሚያ ቤቱ ከፍርድ ቤት ማህተም ካለበት ሰነድ ውጪ መያዝ የተከለከለው በደህንንነት መከታተያ ስርአት መሰረት መሆኑን ምላሽ ሰጥቷል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/UPDATE-01-13-3

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ
#ተራዝሟል

የኢፌዲሪ የህዘብ ተወካዮች ም/ቤት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1265/2014 ማጽደቁ ይታወሳል፡፡

በዚሁ መሠረት የዕጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ ከታህሳስ 26/2014 - ጥር 6/2014 ዓ.ም ድረስ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ምክር ቤቱ እስካሁን ዕጩ ኮሚሽነሮችን ለመጠቆም ዜጎች ያሳዩት ተነሳሽነትና እያደረጉ ያሉት ተሳትፎ የሚያበረታታ ነው ብሏል።

ይሁንና ኮሚሽኑ ከሚኖረው ከፍተኛ ሀገራዊ ኃላፊነት አንፃር ተጨማሪ ዕጩዎችን ህዝቡ እንዲጠቁም እንዲሁም የአገሪቱን ብዝሃነት ታሳቢ በማድረግና በተለያዩ ምክንያቶች መጠቆም ላልቻሉ ዜጎች ዕድሉን ለመስጠት የዕጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ እስከ ጥር 13/2014 ዓ.ም ድረስ የተራዘመ መሆኑን ገልጿል።

ለመጠቆም በም/ቤቱ ድህረ ገጽ
https://www.hopr.gov.et/web/guestpublicatons-acticles ወይም በ FB ገጽ https://www.facebook.com/hoprpariament ላይ የተቀመጠውን አድራሻ ይጠቀሙ፡፡

(የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት)

@tikvahethiopia
#ሹመት

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ፥ ካናዳ ሞንትሪያ በሚገኘው የዓለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ምክር ቤት የኢትዮጵያ ተወካይ ሆነው በማገልገል ላይ የነበሩትን አቶ ጌታቸው መንግስቴን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አድርገው ሾመዋል።

አቶ መንግስቱ ንጉሴን ደግሞ የኤር ናቪጌሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አድርገው መሾማቸውን ተቋሙ አስታውቋል።

አቶ ጌታቸው መንግስቴ፤ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙት ረዘም ላለ ጊዜ ተቋሙን በዋና ዳይሬክተርነት ሲያገለግሉ የነበሩት ኮሎኔል ወሰንየለህ ሁነኛውን በመተካት ነው።

#አልዓይን

@tikvahethiopia
#COOP #MICHU

የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ከክፍያ ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂስ ጋር በመተባበር ምቹ የተባለ አዲስ ያለዋስትና ብድር ማግኘት የሚያስችል ዲጂታል ቴክኖሎጂ አስተዋውቋል።

በሀገሪቱ የመጀመሪያ የሆነው ምቹ ዲጂታል ዋስትና አልባ የብድር አገልግሎት በዋስትና ምክንያት የብድር አገልግሎት ማግኘት የማይችሉትን በዝቅተኛና መካከለኛ ንግድ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችን በእጅጉ ይጠቅማል ተብሎ ይታመናል።

ምቹ የብድር መጠየቂያ እና ማግኛ መተግበሪያ ሲሆን አጠቃቀሙም በሞባይል ስልክ ላይ በመጫን ነው፡፡

ብድር ጠያቂው በመተግበሪያው ላይ ጥያቄው ያቀርባል፣ ብድሩን ለማግኘት የሚጠየቁ መስፈርቶች ይሞላል መተግበሪያው በደቂቃዎች ውስጥ ውጤቱን ያሳውቃል ተብሏል፡፡

ጥቃቅን፣ አነስተኛ እና መካከለኛ የሥራ መስኮች ያለ ዋስትና ብድሩ የቀረበላቸው ሲሆን እንደ ስራው ዓይነትና የመመለሻ ጊዜ የብድር መጠኑ ከ30 ሺ ብር እስከ 150 ሺ ብር ይደርሳል።

ምንጭ፦ የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA ዛሬ የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት መግለጫ አውጥቶ ነበር። በዚህም መግለጫው ላይ TPLF ለትግራይ ህዝብ ሰብዓዊ ድጋፍ እንዳይቀርብ እንቅፋት ሆኖ መቀጠሉን አስገንዝቧል። የመንግስት ኮሚኒኬሽን ፥ " እንደ ዓለም ጤና ድርጅት አይነት ለሁሉም ሰው በእኩል ቆመናል የሚሉ አለምአቀፍ ተቋማት ግን አሸባሪው ቡድን የአማራና አፋር ክልሎችን በወረረበት ወቅት ሀስፒታሎችንና የጤና ጣቢያዎችን ሲዘርፍና…
#ETHIOPIA

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በኢትዮጵያ ጉዳይ የግላቸውን አቋም እንዳያንጸባርቁ ኢትዮጵያ ጠየቀች፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ ትናንትና ረቡዕ በሰጡት መግለጫ ላይ የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት በትግራይ ክልል ላሉ ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ እንዳይደርስ አግዷል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

መንግስት በራሱ ዜጎች ላይ ምግብ፣ መድሃኒት እና ሌሎች የህይወት አድን ድጋፎችን እንዳያገኙ እገዳ ጥሏል ሲሉም ነበር ዋና ዳይሬክተሩ የተናገሩት፡፡

ይህን ተከትሎ በመንግስታቱ ድርጅት የኢትዮጵያ ተጠሪ ጽህፈት ቤት በትዊተር ገጹ ፖለቲካዊ ውግንና አላቸው ያላቸው ዶ/ር ቴድሮስ ኢትዮጵያን ከተመለከቱ ጉዳዮች ራሳቸውን እንዲያርቁና ገለልተኛ እንዲሆኑ ጠይቋል፡፡

የተሰጣቸውን ዓለም አቀፋዊ ሚና ከመወጣት ይልቅ ከፖለቲካዊ እና ግለሰባዊ ፍላጎት የመነጨ ውግንናቸውን እያንጸባረቁ ነው ያለው ጽህፈት ቤቱ የተመድ ኤጀንሲዎች ስራም በዚሁ ምክንያት እየተስተጓጎለ ይገኛል ብሏል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ ኢትዮጵያን ከተመለከቱ የትኞቹም ጉዳዮች ራሳቸውን እንዲያርቁም ነው በተመድ የኢትዮጵያ ተልዕኮ ጽ/ቤት የጠየቀው፡፡

ኢትዮጵያ በጦርነቱ ምክንያት የጤና ተቋማት ሲወድሙ ምንም አላለም በሚል የዓለም ጤና ድርጅትን መውቀሷ ይታወሳል።

ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AFCON2021 ⚽️ ኢትዮጵያ 🇪🇹🇨🇲 ካሜሮን 🗓 ዛሬ ጥር 5 / 2014 ዓ/ም ⌚️ ማታ 1:00 🏟️ ፖል ቢያ ስታድየም 📍 ካሜሩን - ያዉንዴ 🖥 ሱፐር ስፖርት / ስካይ ስፖርት እና ኢቲቪ መዝናኛ ድል ለሀገራችን ኢትዮጵያ ! #HanaG. More : @tikvahethsport
#AFCON2021

ሀገራችን ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫው የመጀመሪያ ጎሏን አስቆጠረች።

ኢትዮጵያ ከካሜሮን ጋር ፍልሚያዋን እያደረገች ትገኛለች።

ጨዋታው ከተጀመረ ጥቂት ደቂቃዎች የተቆጠረ ሲሆን በዳዋ ሆቴሳ አማካኝነት በዘንድሮ ውድድር የመጀመሪያ ጎል አስቆጥራለች።

ጨዋታው 1 ለ 1 በሆነ ውጤት ቀጥሏል።

በስፖርት ገፃችን ተከታተሉ : @tikvahethsport
TIKVAH-ETHIOPIA
#AFCON2021 ሀገራችን ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫው የመጀመሪያ ጎሏን አስቆጠረች። ኢትዮጵያ ከካሜሮን ጋር ፍልሚያዋን እያደረገች ትገኛለች። ጨዋታው ከተጀመረ ጥቂት ደቂቃዎች የተቆጠረ ሲሆን በዳዋ ሆቴሳ አማካኝነት በዘንድሮ ውድድር የመጀመሪያ ጎል አስቆጥራለች። ጨዋታው 1 ለ 1 በሆነ ውጤት ቀጥሏል። በስፖርት ገፃችን ተከታተሉ : @tikvahethsport
#AFCON2021

#ኢትዮጵያ እና #ካሜሮን መካከል እየተደረገ የሚገኘው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ፍልሚያ የመጀመሪያ አጋማሽ 1 ለ 1 በሆነ ውጤት ተጠናቋል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በመጀመሪያ አጋማሽ አስደሳችና እጅግ ማራኪ የሚባል እንቅስቃሴ አሳይታለች።

በዘንድሮ ውድድርም የመጀመሪያ ጎል አስቆጥራለች።

ድል ለእናት ሀገራችን ኢትዮጵያ ይሆን ዘንድ እንመኛለን።

More : @tikvahethsport
#ETHIOPIA

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቅርቡ በአዲስ አበባ ለሚካሄደው 35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እየተደረገ ባለው ዝግጅት ዙሪያ ከህብረቱ አባል ሀገራት ጋር መክሯል።

ሚኒስቴሩ እንዳስታወቀው ለአፍሪካ ሀገራት አምባሳደሮች እና ዲፕሎማቶች ለጉባኤው እየተደረገ ስላለው ዝግጅት ማብራሪያ ተሰጥቷል።

ለጉባኤው ስኬት የሚያስፈልጉ ሁሉንም ነገሮች ከማዘጋጀት ባለፈ የተሳታፊዎች ጤንነት መጠበቅን ለማረጋገጥ የኮቮድ-19 ምርመራ እና ክትባት መስጫ የጤና ማእከላት በመንግስት መቋቋማቸውን ነው የገለፀው። 

የአፍሪካ ሀገራት ለኢትዮጵያ ላሳዩት አጋርነትም ምስጋናውን አቅርቧል። 

በዛሬው የጉባኤውን ዝግጅት አስመልክቶ በተደረገው ገለፃ ላይ ስለተነሱት ጉዳዮችም ለየሀገሮቻቸው መንግስታት እንዲያሳውቁም አሳስቧል።

ምንጭ፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

@tikvahethiopia