TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኢሠፓ

በደርግ ዘመነ መንግስት ገዢ ፓርቲ የነበረውን የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲን (ኢሠፓ) ዳግም ለማቋቋም የተሰባሰቡ ግለሰቦች፤ የምስረታ ሰነዶቻቸውን ለምርጫ ቦርድ አስገብተው ጊዜያዊ የምዝገባ ፈቃድ ለማግኘት እየተጠባበቁ መሆኑን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድም የፓርቲው የምስረታ ሰነዶች እንደደረሱት አረጋግጧል።

ኢሠፓን ከ30 ዓመታት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ ለመመለስ የተሰባሰቡት ግለሰቦች፤ የምስረታ ሰነዶችን ለምርጫ ቦርድ ያስገቡት ባለፈው ሰኔ ወር መጨረሻ መሆኑን የፓርቲው አደራጆች ገልጸዋል።

ከአደራጆቹ መካከል የሆኑ እና ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ግለሰብ ለኢትዮጵያ ኢንሳይደር በሰጡት ቃል ፤ " የሚያስፈልጉ መስፈርቶችን በሙሉ አሟልተን [ለቦርዱ] አስገብተናል " ብለዋል።

" በአዲስ መልክ ተመልሶ ይመሰረታል " የተባለለትን ኢሠፓን በማደራጀት ላይ ከሚገኙት ውስጥ #የቀድሞው የፓርቲ አባላት ይገኙበታል ተብሏል።

ከእነዚህ የቀድሞ አባላት ውስጥ በኢሠፓ #በከፍተኛ_አመራርነት ያገለገሉ እንዳሉበት እኚሁ አደራጅ ቢገልጹም ማንነታቸውን ከመግለጽ ግን ተቆጥበዋል። 

" የቀድሞዎቹ የኢሠፓ አመራሮች በእስር ቤት ያለፉ ሰዎች ናቸው። ከስህተታቸው ብዙ ትምህርት ተምረዋል " የሚሉት አደራጁ፤ ግለሰቦቹ እንደገና በሚቋቋመው ፓርቲ የሚኖራቸው ሚና ከኋላ ሆነው ልምዳቸውን የማካፈል መሆኑን አስረድተዋል።

በአደራጆቹ ስብስብ ውስጥ ከቀድሞዎቹ የኢሠፓ አመራሮች እና አባላት በተጨማሪ #ወጣቶችም መካተታቸውን መግለፃቸውን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር በድረገፁ አስነብቧል።

@tikvahethiopia