TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Balderas

በትላንትናው ዕለት ከእስር የተፈቱት የባልደራስ ለእዉነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች እነ አቶ እስክንድር ነጋ፣ አቶ ስንታየሁ ቸኮል፣ ወ/ሮ ቀለብ (አስቴር) ስዩም በዋና ጽ/ቤት አቀባበል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

መከላከያ ሰራዊት ሲጠቀምባቸው የነበሩ የማዕረግ ምልክቶች ላይ ማሻሻያ አድርጓል።

በምልክቶቹ ውስጥ ጋሻና አንበሳን ጥቅም ላይ ማዋሉን ነው የተገለጸው።

ማሻሻያ ያስፈለገው የሠራዊቱ ማዕረግ አገራዊ ይሁን ወታደራዊ ታሪካዊ ይዘት ያለውና የሠራዊቱንም ባህሪ ሊገልፅ የሚችል ሆኖ እንዲዘጋጅ በማስፈለጉ መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahethiopia
#Update

በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው የፊልድ ማርሻል ወታደራዊ ማዕረግ ለጀነራል ብርሃኑ ጁላ ተሰጠ።

በተጨማሪ ፦

• 4 ሌትናል ጀነራሎች ወደ ሙሉ ጀነራልነት፣
• 14 ሜጀር ጀነራሎች ወደ ሌትናል ጀነራልነት፣
• 24 ብርጋዴር ጀነራሎች ወደ ሜጀር ጀነራልነት፣
• 58 ኮሎኔሎች ወደ ብርጋዴር ጀነራልነት በአጠቃላይ 100 ከፍተኛ የጦር አመራሮች እድገት ተሰጥቷል።

ሹመቱ በጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶክተር ዐቢይ አህመድ አቅራቢነት በኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በኩል ነው የተሰጠው።

የማዕረግ እድገት ያገኙ ከፍተኛ መኮንኖች ሙሉ ዝርዝር : https://telegra.ph/Tikvah-01-08

#PMOfficeEthiopia

@tikvahethiopia
#Tigray

በትግራይ ክልል ተፈናቃዮች በተጠለሉበት ካምፕ ላይ ተፈፀመ በተባለ የአየር ጥቃት 56 ሰዎች ሲገደሉ በደርዘን የሚቆጠሩት መቁሰላቸውን ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የእርዳታ ሰራተኞች እንደነገሩት ሮይተርስ ዘግቧል።

የአየር ጥቃቱ የተፈጸመው በክልሉ ሰሜናዊ ምዕራብ በምትገኘውና የኤርትራ ድንበር አቅራቢያ ባለች ደደቢት ከተማ በሚገኝ ትምህርት ቤት አርብ ዕለት መሆኑንም የእርዳታ ሰራተኞቹ ገልጸዋል።

ቅዳሜ የእርዳታ ሰራተኞች ለሮይተርስ እንደተናገሩት የሟቾች ቁጥር በአካባቢው ባለስልጣናት መረጋገጡን ነው።

የረድዔት ድርጅት ሰራተኞች ህፃናትን ጨምሮ ሆስፒታል ውስጥ ያነሷቸውን የቆሰሉ ሰዎችን ፎቶግራፍ ለሮይተርስ መላካቸው ተገልጿል።

የ ' ሽረ ስሁል አጠቃላይ ሆስፒታል ' ከጎበኙት የረድኤት ሰራተኞች መካከል አንደኛው እንደገለጹት መጠለያ ካምፑ በርካታ በእድሜ አዛውንትናና ህፃናት ያሉበት ነው።

ትምህርት ቤቱ እንዴት እና ለምን ጥቃት እንደደረሰበት ግልፅ አይደለም።

ሮይተርስ ጥቃቱ በገለልተኛ ወገን አልተረጋገጠም ብሏል።

ከኢትዮጵያ መንግስት በኩል ስለጉዳዩ ለመጠየቅ ቢሞክርም እንዳልተሳካለት ፅፏል።

ከዚህ በፊት የኢትዮጵያ መንግስት ብዙ ጊዜ ሲቪሎችን እንደማያጠቃ መግለፁን ሮይተርስ አስታውሷል።

UNOCHA ባወጣው መግለጫ ከታህሳስ 10-ታህሳስ 15 ድረስ በትግራይ ላይ በተፈጸሙ የአየር ጥቃቶች በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት መደረጉን አስፍሯል።

ታህሳስ 21/2014 ዓ.ም ባወጣው ሪፖርት ከጥቅምት ወር ወዲህ ከተከሰቱት በጣም አስከፊ፣በርካታ ሞቶች ሪፖርት የተደረጉበትና በተከተታይ የተፈጸመ ነው ብሏል።

በርካታዎቹ ጥቃቶች ሪፖርት የተደረጉት በአላማጣ፣ ኮረም፣ ማይጨው፣ መኮኒና ሚላዛት መሆኑን ጠቅሷል።

#ሮይተርስ

@tikvahethiopia
#USA

አሜሪካ በአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮዋ በኩል ፥ በትግራይ እየተካሄደ ያለው የአየር ድብደባ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት ማድረሱ ተቀባይነት የለውም ስትል መግለጫ አውጥታለች።

አሜሪካ ፥ ጦርነቱ ባስቸኳይ እንዲቆም፣ ሁሉን አቀፍ ብሄራዊ ዉይይት እንዲጀመር እና ያለ ምንም እንቅፋት ርዳታ ለተቸገሩ የኢትዮጵያ ማህበረሰቦች ሁሉ እንዲደርስ ጥሪያችንንም እናቀርባለን ብላለች።

@tikvahethiopia
የሴራ በዓል በቁሊቶ ከተማ እየተከበረ ነው።

በደቡብ ክልል የሀላባ ብሔር የዘመን መለወጫ ሴራ በዓል በቁሊቶ ከተማ እየተከበረ እገኛል።

በዓሉ እየተከበረ ያለው በሲምፖዝየም ሲሆን የብሔሩ ባህላዊ አስተዳደር መተዳደሪያ ደንብ የሆነውን ሴራን መሰረት አድርጎ የሚከበር እንደሆነ ተጠቁሟል።

በዘመን መለወጫ በዓሉ ላይ የዞኑና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም ከየወረዳው የተውጣጡ የብሔሩ ተወካዮች እየተሳተፉ ነው።

የሴራ በዓል በወረዳ ደረጃ በየዓመቱ እና በዞን ደረጃ ደግሞ በየሁለት ዓመቱ የሚከበር ነው።

ምንጭ፦ ኢዜአ

@tikvahethiopia
ድል ለሀገራችን ኢትዮጵያ❤️

ሀገራችን ከስምንት አመታት ቆይታ በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫው በመመለስ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ዛሬ ምሽት 4:00 ላይ ታደርጋለች።

ብሄራዊ ቡድናችን በምድቡ የመክፈቻ ጨዋታ ኬፕ ቨርዴን የሚገጥም ይሆናል።

ቡድናችን ውድድሩ ሳይጀምር ቀደም ብሎ ካሜሮን በመግባት ጠናካራ ልምምድ ሲያደርግ መቆየቱ አይዘነጋም።

በካሜሩን የሚገኙ የቲክቫህ አባላት በቀጥታ ከስፍራው መረጃዎችን @tikvahethsport በኩል ይልኩላችኃል።

መልካም እድል ለብሄራዊ ቡድናችን !

@tikvahethsport
#UPDATE

በጎንደር ከተማ የሰዓት እላፊ ገደብ ተነስቷል።

በታሪካዊቷ የጎንደር ከተማ በአስቸካይ ጊዜ አዋጅ ተጥለዉ የነበሩ ክልከላዎች ዉስጥ የሰዓት ገደቡ ተነስቷል።

ከምሽቱ 4.00 እስከ 11.30 የነበረዉ ክልከላ የተነሳ እና 24 ሰዓት በሰላም ሁሉም አካል ፣ ተሸከርካሪም ጭምር መንቀሳቀስ እንደሚቻል ትላንት ተወስኗል።

ሌሎች ክልልከላዎች ግን የሚቀጥሉ ይሆናል።

በዚህም መሰረት ፦

• ከተፈቀደለት የጸጥታ አካሉ ዉጭ መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው።
• ማንኛዉም ሰዉ መሳሪያ/ተተካሽ/ ይዞ ወደ መጥጥ ቤት ይዞ መግባት ሆነ መዝናናት በጥብቅ የተከለከለ ነው።
• እንግዶችን ሆነ ማንኛዉንም ሰዉ ማዋከብ መረበሽ የተከለከለ ነው።
• አግባብነት የሌለዉ ዋጋ በማናቸዉም ሽያጮች አገልግሎቶች መጨመር የተከለከለ ነዉ።
• ማንኛዉም ሰዉ የሚመለከታቸዉ የጸጥታ አካላት መታወቂያ እንዲያሳይ ሲጠየቅ የማሳየት #ግዴታ አለበት።
• የብሎክ አደረጃጀት ጥበቃዉ የማይቃረጥና ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።
• በፀጥታ አካሉ አማካኝነት የኬላ ፍተሸ የድነገተኛ ፍተሻ ተጠናክረዉ የሚቀጥሉ ይሆናል።

የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲከበር ዘንድ ሁሉም ሰዉ ከፀጥታ አካሉ ጎን እንዲቆም ፤ ከአቅም በላይ የሆኑ የጸጥታ ችግሮች ሲገጥሙ በአቅራቢያ ለሚገኘዉ የፖሊስ ጣቢያ ሪፖረት ማድረግ ወይም በየአካባቢዉ ለሚገኝ የፀጥታ አካል ሪፖርት በማድረግ የመተባበር ኃላፊነቱን እንዲወጣ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

መረጃው ከጎንደር ከተማ አስተዳደር ኮማንድ ፖስት የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
#DStvEthiopiaPoloTeam

ዲኤስቲቪ ኢትዮጵያ እንደ እግር ኳሱ ሁሉ የኢትዮጵያን ባህላዊ ስፖርት በመደገፍ ረጂም ዘመናትን አስቆጥሯል። የራሱን የገና ጨዋታ ቡድን በማዋቀርም በጃንሜዳ የሚከናወነውን ዓመታዊ የኢትዮጵያ ገና ጨዋታ ውድድር ሲካፈል ቆይቷል።

ዛሬ በጃንሜዳ በድምቀት የተከናወነው የዚህ ዓመቱ የገና ጨዋታ ውድድር በዲኤችገዳ አሸናፊነት ተጠናቋል።

የኢትዮጵያ ስፖርት ኮሚሽን ተወካይ፣ የገና ጨዋታ ፌደሬሽን ኃላፊዎች ና የዲኤስቲቪ ተወካዮች ለአሸናፊዎቹ የሜዳሊያ ሽልማት አበርክተዋል።የተራራ ቡና እና የዲኤች ገዳ ዱቄት ስጦታም ተበርክቶላቸዋል።

ዲኤስቲቪ ባህላዊ የኢትዮጵያ ስፖርት እንዲያድግ ወደፊትም ድጋፉን ይቀጥላል።

#DStvEthiopia
#GenaChewata
#PoloSport2022
የአፍሪካ ህብረት (AU) የታሳሪዎችን መፈታት በደስታ እንደሚቀበል አስታወቀ።

የአፍሪካ ህብረት ዋና ፀሀፊ ሙሳ ፋኪ ማሀመት ትላንት ቅዳሜ ባወጡት መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት የፖለቲካ እስረኞችን መፍታቱን በደስታ እንደሚቀበሉት አሳውቀዋል።

ዋና ፀሀፊው ፥ የታሳሪዎቹ መፈታይ በሀገሪቱ የፖለቲካ ንግግር ለማድረግ እንዲሁም ለብሄራዊ እርቅ አስፈላጊ እርምጃ ነው ብለዋል።

@tikvahethiopia