TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#TechZone

ውፍረትን እና ቦርጭን መቀነስ ይፈልጋሉ? 0929088890
ያሉበት ድረስ ከነፃ ማድረሻ ጋር!              
ሙሉ ከወገብ በላይ(ቦዲ) - 899ብር
የቦርጭ ብቻ -599  ብር
ሙሉ በሙሉ ቦርጭን በአጭር ጊዜ የሚያጠፋ እና
ማራኪ-ቁመና የሚያላብስ ።
ተጨማሪ : የቴሌግራም አድራሻችን ይጎብኙ
( ክልል ከተሞች እንገኛለን ) @አ.አ = ቦሌ መዳሃንያለም
" የሚመጡ እንግዶችን ደህንነት ለመጠበቅ ዝግጅት ተጠናቋል " - ፌዴራል ፖሊስ

በ "አንድ ሚሊዮን ዳያስፖራ ወደ ሀገር ቤት " ጥሪ መሰረት ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ እንግዶችንን ደህንነት ለመጠበቅ የሚያስችል አስፈላጊው ሁሉ ዝግጅት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

ፌዴራል ፖሊስ በአዲስ አበባ ከተማ ሆነ በሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎች የሚመጡ እንግዶችን ደህንነት ለመጠበቅ የሚያስችል ዝግጅት አስቀድሞ ማድረጉን ገልጿል።

የጸጥታና ደህንነት ተግባሩን የኮማንድ ፖስቱ የጸጥታ መዋቅር ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን የሚያከናውን ሲሆን ጥምር የጸጥታ ሃይሎች አስቀድሞ የጸጥታ ስጋት የሆኑ ነገሮችን በመለየት እንግዶቹ በሚንቀሳቀሱበት ስፍራ ምንም አይነት ችግር እንዳይገጥማቸው በቂ ዝግጅት ማድረጋቸውን ፖሊስ አሳውቋል።

እንግዶቹ ለሚያጋጥማቸው ማንኛውንም ነገር መረጃ ለመስጠትና አስቀድሞ መረጃ ለማግኘት የሚችሉባቸውን አድራሻዎች ከፌደራል ፖሊስና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ማህበራዊ ገጾች ማግኘት ይችላሉ።

እንግዶች በስፋት ወደ ሀገር ሲገቡ ደግሞ አድራሻዎቹን የማሳወቅ ስራ እንደሚሰራ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ መግለፁን ኢዜአ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#Update

ሀይቅ፣ ቢስቲማና ለሚ ከተሞች ተቋርጦባቸው የነበረውን የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘታቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳውቋል።

@tikvahethiopia
Turkey 🤝 Africa

የቱርኩ ፕሬዜዳንት ሪሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን እና የሱማሊያው ፕሬዜዳንት ሞሀመድ አብድላሂ ፈርማጆ ወይይት አካሄዱ።

3ኛው የቱርክ-አፍሪካ ትብብር ጉባኤ በኢስታንቡል እየተካሄደ ይገኛል።

ከጉባኤው ጎን ለጎን የቱርክ እና የሱማሊያ መሪዎች ተገነኝተው ውይይት እንዳደረጉ ተሰምቷል፤ የውይይቱን ይዘት በተመለከተ የተባለ ነገር የለም።

@tikvahethiopia
#Update

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ከፕሬዜዳንት ኤርዶጋን ጋር ተወያዩ።

ከቱርክና አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን፣ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድና የልዑካን ቡድናቸው ከፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት ዛሬ አካሂደዋል።

ዶ/ር ዐቢይ ፥ " የሁለቱ ሀገራት ታሪካዊ ግንኙነት ሁሌም በመከባበር ላይ የተመሠረተ ነው። ትብብራችን በገንቢ ተሳትፎ ላይ በመመሥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል " ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የተመድ ሰብዓዊ መብቶች ም/ቤት ልዩ ስብሰባ በመካሄድ ላይ ይገኛል። ስብሰባውን በቀጥታ ለመከታተል ይህን ይጫኑ : https://media.un.org/en/asset/k11/k119r483hu @tikvahethiopia
#UN_Human_Rights_Council

ለተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት የቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ጸድቋል።

በአውሮፓ ህብረት ጠያቂነት የቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ዛሬ በተካሄደው ልዩ ስብሰባ ነው የፀደቀው።

የውሳኔ ሃሳቡ በ21 ድጋፍ እና በ15 ተቃውሞ የጸደቀ ሲሆን 11 ሃገራት ድምጽ ከመስጠት ታቅበዋል።

ለተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት የቀረበው ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ምን ይዟል ?

በአውሮፓ ህብረት አማካኝነት ቀርቦ የፀደቀው የውሳኔ ሀሳብ በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈፀሙ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን የሚመረምር ዓለም አቀፍ ባለሞያዎች ቡድን በኢትዮጵያ እንዲሰማራ የሚጠይቅ ነው።

የውሳኔ ሀሳቡ ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከተመድ ሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ጋር በጥምረት ያደረጉት ምርመራ ውጤት መነሻ አድርጎ ተጨማሪ ምርመራ የሚያደርግ ዓለም አቀፍ የባለሙያዎች ቡድን እንዲሰማራ የሚጠይቅ ነው።

ዓለም አቀፍ መርማሪ ቡድኑ በኢትዮጵያ የአንድ ዓመት ቆይታ እንዲኖረው የሚጠይቅ ሲሆን የሚላከው ቡድን ከሚያደርገው ምርመራ በተጨማሪ ፦
- የሽግግር ፍትህ ተግባራዊ የሚያደርግበትን፣
- ዕርቅና ተጠያቂነት የሚሰፍንበት
- ሰብዓዊ መብት ጥሰት የደረሰባቸው ማገገም እንዲችሉ ምክረ ሃሳብና የቴክኒክ ድጋፍ የመስጠት ኃላፊነት እንዲኖረው ይጠይቃል።

@tikvahethiopia
#Update

የኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት #መርሳ እና #ግራናን በመቆጣጠር ወደፊት እየገሠገሠ መሆኑን የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አሳውቋቃ።

የአትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት በቆቦ ግንባር ቀደም ብሎ የዞብል ከፍተኛ ቦታዎችን ተቆጣጥሮ የነበረ ሲሆን፣ በራያ ሰሜናዊ አቅጣጫ ያሉትን ከፍተኛ ቦታዎችን ጨምሮ ተቆጣጥሯል፡፡

በዞብል ደቡብ አቅጣጫ ደግሞ የጉራ ወርቄ አካባቢዎችን ተቆጣጥሮ የነበረው የወገን ጦር አሁን ደግሞ የጉራ ወርቄ ከፍተኛ ሰንሰለታማ ቦታዎችን ሙሉ በሙሉ በማጽዳት፣ ቀደም ብሎ የተቆረጠውን የወልድያ መቀሌ መሥመር አሰፋፍቶ፣ ወደ ወልድያ በቅርብ ርቀት እየገሠገሠ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ባለፈው ውጫሌ ከተማን ነጸ ያወጣው የወገን ጦር፣ በዚሁ ግንባር የውጫሌ ወረዳን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር የውርጌሳ፣ የሊብሶ፣የግራና፣ የመርሳ፣ የኪሌ፣ከተሞችንና በሰሜን ወሎ የሐርቡ ወረዳን ከፍተኛ ሰንሰለታማ ተራሮችን በእጁ አስገብቷል።

በእነዚህ የማጥቃት እንቅስቃሴዎች ጀግኖቹ የወገን ጥምር ጦር በንሥሮቹ አየር ኃይላችን በመታገዝ ጠላትን ከመርሳ በስተጀርባ ቆርጦ በመግባት፣ በውጫሌና ውርጌሳ መካከል የነበረውን ጠላት ሙለሉ በሙሉ ደምስሰውታል፤ ምርኮኛና ቁስለኛም አድርገውታል ብሏል የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት።

የመንግስት ኮሚኒኬሽን ፥ የአካባቢ ኅብረተሰብ ከወገን ጥምር ጦር ጋር በመቀናጀት፣ እግሬ አውጪኝ ብሎ የሚሸሸውን ጠላት ከየጢሻው እየመነጠረ በመደምሰስ አኩሪ ጀብድ ፈጽሟል ብሏል።

አክሎም " ጠላት የዘረፈውን ንብረትና ተተኳሾቹን ፈጽሞ ይዞ እንዳይወጣ አድርጎታል፡፡ የወገን ጥምር ጦር በወልድያና ሐራ ከተሞች መካከል የሚገኘውንና መውጫ ያጣውን ጠላት ለመደምሰስ፣ በተቀናጀና በተደራጀ መንገድ ወደ ፊት እየገሠገሠ ነው " ሲል አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#Update

በቱርክ፣ ኢስታንቡል እየተካሄደ ከሚገኘው የቱርክ - አፍሪካ ትብብር ጉባኤ ጎን ለጎን የቱርክ ፕሬዜዳንት ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ጋር የሚያደርጉትን የጎንዮሽ ውይይት ቀጥለዋል።

ፕሬዜዳንት ሪሲፕ ጣይብ ኤዶጋን እስካሁን ፦

- ከሀገራችን 🇪🇹 ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ
- ከጎረቤት ሀገር ሱማሊያ ፕሬዜዳንት ሞሀመድ አብዱላሂ ፈርማጆ
- ከናይጄሪያ ፕሬዜዳንት ሙሀመድ ቡሃሪ
- ከሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ
- ከኮሞሮስ ህብረት ፕሬዝዳንት አዛሊ አሱማኒ
- ከመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ፋውስቲን አርሴንጀን ቱዋዴራ
- ከሞሪታኒያው ሞሃመድ ኦልድ ጋዙዋኒ
- ከሊቢያ ፕሬዝዳንታዊ ምክር ቤት መሪ መሀመድ ዩነስ መንፊ ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UN_Human_Rights_Council ለተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት የቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ጸድቋል። በአውሮፓ ህብረት ጠያቂነት የቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ዛሬ በተካሄደው ልዩ ስብሰባ ነው የፀደቀው። የውሳኔ ሃሳቡ በ21 ድጋፍ እና በ15 ተቃውሞ የጸደቀ ሲሆን 11 ሃገራት ድምጽ ከመስጠት ታቅበዋል። ለተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት የቀረበው ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ምን ይዟል ? በአውሮፓ ህብረት…
" የተላለፈውን ውሳኔ አትቀበልም፤ አታስፈፅምም፤ የትኛውንም አይነት ትብብር አታደርግም " - ኢትዮጵያ

የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የተመድ የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት በኢትዮጵያ ዙሪያ ያካሄደውን ልዩ ስብሰባና በምክር ቤቱ የጸደቀውን የውሳኔ ሀሳብ አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል።

በመግለጫው፥ ኢትዮጵያ ም/ ቤቱ አንዳንድ አገራት የፖለቲካ አጀንዳ ማስፈጸሚያና መጠቀሚያ መሆኑ እጅጉን እንዳሳዘናት ገልጿል።

የኢትዮጵያ መንግስት የም/ቤቱ ልዩ ስብሰባ እንዳይካሄድ ሲገልጽና ሲቃወም የነበረ ቢሆን ይሄንን ችላ በማለት ስብሰባው መካሄዱን አመልክቷል።

ስብስባው ምክር ቤቱ ያጸደቀውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ቢሮና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የጋራ ሪፖርት ግኝት ያላከበረና የናቀ መሆኑን አስታውቋል።

የተመድ የሰብአዊ መብቶች ም/ቤት በኢትዮጵያ ዙሪያ ያካሄደውን ልዩ ስብሰባ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት፣ የግዛት አንድነትና ነጻነት የሚገዳደር ነው ብሏል።

ኢትዮጵያም ያለ ፍላጎቷና ፈቃዷ በተደረገው ልዩ ስብሰባ የተላለፈውን ውሳኔ እንደማትቀበል፣ እንደማትፈጽምና የትኛውንም አይነት ትብብር እንደማታደርግ አሳውቋል።

ኢትዮጵያ ከብሔራዊ ጥቅሟና ፍላጎቷ ውጪ የፖለቲካ ፍላጎታቸውን ለመጫን የሚከናወኑ ማንኛውም ድርጊቶችን እንደማትቀበል አስገንዝቧል።

በሰብአዊ መብት ስም በአገራት ላይ የሚደረግ ጣልቃ ገብነትና ፖለቲካዊ ጫና ሊቆም ይገባል ብሏል።

በእውነትና መርህ ላይ ተመስርተው ልዩ ስብሰባውንና የውሳኔ ሀሳቡን በመቃወም ከኢትዮጵያ ጎን በመቆም አጋርነታቸውን ላሳዩ አገራት ምስጋና አቅርባለች።

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ሕግ የዜጎች ሰብአዊ መብቶች እንዲጠበቁና እንዲከበሩ ያሉባትን ግዴታዎች ለመወጣት አሁንም በቁርጠኝነት እንደምትሰራ ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

@tikvahethiopia
#BeuDelivery

የልዩ ቅናሾቻችን ተጠቃሚ በመሆን የIphone 13 ተሸላሚ ይሁኑ!

በውድድሩ ለመሳተፉ እነዚህን መመሪያዎች ይከተሉ :
1. የ beU Delivery መተግበሪያን ያውርዱ ⬇️ https://onelink.to/97ekcy
2. የወደዱትን ምግብ ከልዩ ቅናሾቻችን ወይም ምርጫዎ ከሆነው ሬስቶራንት ይዘዙ
3. የመወዳደሪያ ትኬትዎን ከምግብዎ ጋር ይቀበሉ
4. ውጤቱን በቴሌግራም ቻናላችን ይከታተሉ @beUEthiopia

ለተጨማሪ መረጃ 9533 ይደውሉ!
#Germany #Ethiopia

የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር አውር ስቴፓን ጋር ተወያይተዋል፡፡

አምባሳደር ስቴፓን በውይይቱ ወቅት ጀርመን ለኢትዮጵያ የ80 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ እንደምታደርግ ይፋ አድርገዋል፡፡

የገንዘብ ድጋፉ ኢትዮጵያ ለምታከናውናቸው ፦
- የምግብ ዋስትና ፕሮግራም፣
- ለመልካም አስተዳደር፣
- ለመሬት አጠቃቀም፣
- ለግብርና ሜካናይዜሽን እንዲሁም ድርቅን ለመቋቋም ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች ይውላል ተብሏል፡፡

ምንጭ ፦የገንዘብ ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UN_Human_Rights_Council ለተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት የቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ጸድቋል። በአውሮፓ ህብረት ጠያቂነት የቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ዛሬ በተካሄደው ልዩ ስብሰባ ነው የፀደቀው። የውሳኔ ሃሳቡ በ21 ድጋፍ እና በ15 ተቃውሞ የጸደቀ ሲሆን 11 ሃገራት ድምጽ ከመስጠት ታቅበዋል። ለተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት የቀረበው ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ምን ይዟል ? በአውሮፓ ህብረት…
#ETHIOPIA

በአውሮፓ ህብረት 🇪🇺 አማካኝነት የቀረበው እና በተ.መ.ድ. የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ትላንት የፀደቀው ረቂቅ የውሳኔ ሀሳብ የትኞቹ ሀገራት ደገፉ ? ተቃወሙ ? ድምፀ ተአቅቦ አደረጉ ?

ለA/HRC/S-33/L.1 ድጋፍ የሰጡ ሀገራት ዝርዝር :-

🇦🇷 አርጀንቲና
🇦🇲 አርሜንያ
🇦🇹 አውስትሪያ
🇧🇸 ባሀማስ
🇧🇷 ብራዚል
🇧🇬 ቡልጋሪያ
🇨🇿 ቼክ ሪፐብሊክ
🇩🇰 ዴንማርክ
🇫🇯 ፊጂ
🇫🇷 ፈረንሳይ
🇩🇪 ጀርመን
🇮🇹 ጣልያን
🇯🇵 ጃፓን
🇲🇭 ማርሻል አይላንድስ
🇲🇽 ሜክሲኮ
🇳🇱 ኔዘርላንድስ
🇵🇱 ፖላንድ
🇰🇷 ደቡብ ኮሪያ
🇺🇦 ዩክሬን
🇬🇧 ዩናይትድ ኪንግደም እና ሰሜን አይርላንድ
🇺🇾 ኡራጋይ

ለA/HRC/S-33/L.1 ድጋፋቸውን ያልሰጡ ሀገራት ዝርዝር :-

🇧🇴 ቦሊቭያ
🇧🇫 ቡርኪና ፋሶ
🇨🇲 ካሜሮን
🇨🇳 ቻይና
🇨🇮 ኮት ዲቫር
🇨🇺 ኩባ
🇪🇷 ኤርትራ
🇬🇦 ጋቦን
🇮🇳 ህንድ
🇳🇦 ናሚቢያ
🇵🇰 ፓኪስታን
🇵🇭 ፊሊፒንስ
🇷🇺 ሩሲያ
🇸🇴 ሶማሊያ
🇻🇪 ቬኔዝዌላ

ድምፀ ተአቅቦ ያደረጉ ሀገራት ዝርዝር :-

🇧🇭 ባህሬን
🇧🇩 ባንግላዴሽ
🇮🇩 ኢንዶኔዥያ
🇱🇾 ሊቢያ
🇲🇼 ማላዊ
🇲🇷 ማውሪታኒያ
🇳🇵ኔፓል
🇸🇳 ሴኔጋል
🇸🇩 ሱዳን
🇹🇬 ቶጎ
🇺🇿 ኡዝቤኪስታን

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Update

Turkey 🤝 Africa

የቱርክ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን በቱርክ አፍሪካ ትብብር ጉባኤ ላይ ንግግር አድርገዋል።

በንግግራቸው ላይ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች ፦

- ወደ 19ኛው ክፍለ ዘመን ስንመለስ ከአፍሪካ ጋር ጥልቅ ግንኙነት አለን።

- አፍሪካን ለመደገፍ ቁርጠኞች ነን።

- ትብብራችን በእኩልነት ላይ የተመሰረተ እንጂ ኢምፔሪያሊዝም ወይም ኦሬንታሊዝም አይደለም።

- በ2020 ከአፍሪካ ጋር የነበረን የንግድ ልውውጥ 5.4 ቢሊዮን ዶላር ነበር።

- በዚህ አመት በአፍሪካ ያደረግነው ኢንቨስትመንት 6 ቢሊየን ዶላር ደርሷል።

- በአሁን ሰዓት የቱርክ ኩባንያዎች በመላው አህጉሪቱ በአሁኑ 25,000 አፍሪካውያንን ቀጥረዋል።

- በወረርሽኙ ወቅት ቱርክ ለ 44 የአፍሪካ ሀገራት ድጋፍ ልካለች።

- አብረን ታላቅ ለመሆን መጣር አለብን።

- ዓለም ከ5 በላይ ነው በመሆኑም አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት (UNSC) ውስጥ መወከል አለባት።

- ግንኙነታችንን የበለጠ በማጠናከር ለወደፊት ቦታችን መታገል አለብን።

በኢስታንቡል እየተካሄደ በሚገኘው 3ኛው የቱርክ - አፍሪካ ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች እየተካፈሉ ይገኛሉ።

@tikvahethiopia