#MoH
የጤና ባለሞያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ከታህሳስ 21 እስከ ታህሳስ 27 ድረስ ይሰጣል።
በህክምና ፣ ነርሲንግ ፣ ጤና መኮንን ፣ ፋርማሲ ፣ ሜዲካል ላብራቶሪ ቴክኖሎጂ፣ ሚድዋይፈሪ፣ አንስቴዥያ፣ ዴንታል ሜድስን እና ሜዲካል ራዲዮሎጂ ቴክኖሎጂ ሙያዎች ተመርቀው የጤና ሚኒስቴር የሚሰጠውን የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ ለተመዘገቡ የጤና ባለሙያዎች ፈተናው የሚሰጠው ከታህሳስ 21-27/2014 ዓ.ም ድረስ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር ገልጿል።
ሚኒስቴሩ ፥ ተፈታኞች አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቦ የፈተናውን ፕሮግራም በቅርብ ቀን እንደሚያሳውቅ ገልጿል።
@tikvahethiopia

4 የፌዴራል ፖሊስ አባላት ላይ ክስ ተመሰረተ።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተገን በማድረግ ህገወጥ እስር በመፈፀምና በማስገደድ 260 ሺ ብር የተቀበሉ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ላይ የሙስና ወንጀል ክስ ተመስርቷል፡፡
የዐቃቤ ሕግ ክስ እንደሚያስረደዳው ከሆነ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የአስተዳደር ልማት ዘርፍ በሹፌርነትና በጉዳይ አስፈጻሚነት የሥራ መደብ ላይ የሚሰሩት፦
1ኛ.ረ/ኢ/ር ፍቃዱ ዘዉዴ
2ኛ.ረ/ኢ/ር ይስሀቅ ዳካ
3ኛ.ረ/ኢ/ር ደሴ ደጆ ዳዊት ዳዲና በልዩ ወንጀል ተካፋይነት ግብረ አበር የሆነው ዳዊት ዳዲ ጥቅምት 23/2014 ዓ.ም በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 09 ዲያፍሪክ ሆቴል አካባቢ የግል ተበዳይ በባለቤትነት በሚያስተዳድረው የንግድ መደብር በመግባት 4ኛ ተከሳሽ የመረጃ መረብ ደህንነት አገልግሎት ባልደረባ በመምሰል ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተከሳሾች የፌ/ፖሊስ አባልነታቸውን ሽፋን በማድረግ ምርመራ የማከናወንና ተጠርጣሪ የመያዝ የሥራ ድርሻ ሳይኖራቸውና ምንም አይነት ትዕዛዝ ሳይሰጣቸው የግል ተበዳይን በወቅታዊ ጉዳይ ትፈለጋለህ በማለት ለሥራ በተሰጣቸው መኪና ጭነውት ከወሰዱት በኋላ 1 ሚሊዮን ብር እንዲሰጣቸው ጠይቀው በኢዮጵያ ንግድ ባንክ ባልቻ አባ ነፍሶ ቅርንጫፍ 260 ሺ ብር ወደ 1ኛ ተከሳሽ የቁጠባ ሂሳብ እንዲያስገባ በማድረግ የተከፋፈሉ በመሆኑ በ1996 ዓ/ም የወጣዉን የወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ሀ፣ 33ና የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣዉን አዋጅ ቁጥር 881/07 አንቀፅ 9(2) ስር የተመለከተዉን በመተላለፍ በፈፀሙት ስልጣንን ያለአግባብ መገልገል የሙስና ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡
ተከሳሾች ዛሬ በችሎት ቀርበው ክሱ የተነበበላቸው ሲሆን በክሱ ላይ መቃወሚያ ካላቸው እንዲያቀርቡ ለመጠባበቅ ለታህሳስ 7/2014 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተይዟል፡፡
ምንጭ፦ፍትህ ሚኒስቴር

#Djibouti
በሶማሊ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ የተመራው የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ልዑክ ጂቡቲ ይገኛል።
ልዑኩ ሄሪቴጅ ኢንስቲትዩት በተባለው አለም አቀፍ የጥናትና ምርምር ተቋም አማካኝነት በየአመቱ የሚያዘጋጀው መድረክ ላይ እየተሳተፈ ነው።
መድረኩ በዋናነት በምስራቅ አፍሪካ ወቅታዊ የሆኑ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና በቀጠናው ውህደት ላይ ትኩረቱ ያደረገ ሲሆን የጅቡቲ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጌሌ ናቸው በንግግር የከፈቱት።
የጅቡቲ እና የሶማሊያ ሪፐብሊክ ባለስልጣናት እንዲሁም የኬንያ የቀድሞ ጁብሊ ፓርቲ መሪ ሌሎች ሙሁራን ተገኝተዋል።
የዘንድሮው መድረክ "በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ ያሉ ችግሮች የመረጋጋት ተስፋን ይጎትታሉ?" በሚል ርዕስ ነው የተካሄደ ሲሆን ከተለያዩ የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የተውጣጡ እውቅ ምሁራን ፅሁፎች አቅርበው ውይይት ተደርጓል።
በመድረኩ በኢትዮጵያ ያለው ነባራዊ ሁኔታ በቀጠናው ያለው አንደምታ ተዳሷል።
የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ፥ " ወራሪውና አሸባሪው ህወሓት በኢትዮጵያ የከፈተው ወረራ ቀጠናውን ለማተራመስ የተነሳ ስለሆነ የቀንዱ ሀገራት በጋራ ሊመክቱ ይገባል " ብለዋል።
አክለው ፥ " ጠ/ ሚ ዐቢይ አህመድ በማንኛውም ሀገር ላይ ጣልቃ ገብነት እንዳይኖርና አሸባሪው ህወሓት በምስራቅ አፍሪካ ያደርግ የነበረውን ጣልቃ ገብነትና የማተራመስ ስትራቴጂን ተከላክለው መልካም የሆነ ጉርብትና በሀገራት መካከል እንዲኖር አድርገዋል " ብለዋል
በተጨማሪ በመድረኩ ላይ አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድና ልዑካቸው የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የኢትዮጵያውያን ብቻ ነው በማለት የኢትዮጵያን ድምፅ አሰምተዋል።

#Somalia
ለዓመታት በአልሸባብ ስር የነበሩ አካባቢዎች በዳናብ ኮማንዶዎች ነፃ መደረጋቸው ተሰምቷል።
በአሜሪካ የሰለጠኑት የሶማሊያ ጦር አባላት [ዳናብ] በሞቃዲሾ አቅራቢያ በታችኛው ሸበሌ ክልል የሚገኙ መንደሮችን ጨምሮ ጋምቤሬይ፣ ዳዋካሌ እና ጌዲያን ከአልሸባብ ነፃ ማድረጋቸው ተሰምቷል።
ከላይ የተጠቀሱትን አካባቢዎች አልሸባብ ለዓመታት ሲቆጣጠራቸው ነበር።
በሌላ በኩል የወታደራዊ ምንጮችን ዋቢ በማድረግ የዘገበው ጋሮዌ ትላንት የዳናብ ኮማንዶዎች ታችኛው ሸበሌ ክልል ባካሄዱት የታቀደ የፀረ-አልሸባብ ዘመቻ በትንሹ 5 ታጣቂዎችን ገድለው መሸሸጊያ ቦታቸውን አውድመውታል።

ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia ፦
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 4 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 4,779 የላብራቶሪ ምርመራ 125 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።
የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 153 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።
#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

#UN
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ም/ቤት በኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ላይ በዚህ ሳምንት ልዩ ስብሰባ እንደሚያደርግ የተሰማ ሲሆን ም/ቤቱ ስብሰባውን የሚያደርገው ከአውሮጳ ህብረት የቀረበለትን አስቸኳይ ጥያቄ ከተቀበለ በኃላ መሆኑ ታውቋል።

#ETHIOPIA
የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ም/ቤትን አንዳንድ ሀገራት ኢትዮጵያን በተመለከተ የራሳቸውን የፖለቲካ አጀንዳ ለማራመድ እየተጠቀሙበት ነው ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ይህ ሁኔታ እጅግ እንዳሳዘነውም ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
የተመድ የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽንና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ተፈፅመዋል በተባሉ ጥሰቶች ላይ በጋራ ጥናትና ምርመራ አድርገው የጋራ ሪፖርት ማውጣታቸውን መግለጫው አስታውሷል።
መንግስት ይህ የድርጅቶቹ የጋራ ሪፖርት ውጤትን ተቀብሎ ከፍተኛ የሚኒስትሮች ግብረሃይል አቋቁሞ ምክረ ሀሳቦችን ለመተግበር እየሰራ መሆኑን ጠቁሟል።
ይህ በሆነበት ሁኔታ አንዳንድ የUN የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አባል ሀገራት ኢትዮጵያን በተመለከተ የራሳቸውን የፖለቲካ አጀንዳ በመያዝና ይህንንም አጀንዳቸውን በምክር ቤቱ በኩል ለመፈፀም ምክር ቤቱ በጉዳዩ ላይ ልዩ ስብሰባ እንዲያደርግ በመጥራት ላይ መሆናቸውን አንስቷል።
ይህ ሁኔታ የኢትዮጵያን መንግስት በእጅጉ እንዳሳዘነው ነው ያስታወቀው።
ይልቁንም ም/ ቤቱ አሸባሪው የህወሃት ቡድን በአማራ እና አፋር ክልሎች የፈፀማቸውን እጅግ ዘግናኝ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን አጀንዳ አድርጎ ሊወያይና ሊያወግዘው በተገባ ነበር ብሏል።
የምክር ቤቱ አባል ሀገራት ይህንን የተወሰኑ ሀገራትን የፖለቲካ ፍላጎት ያነገበን ልዩ ስብሰባ እና ውጤቱን በጥብቅ እንዲቃወሙ ሚኒስቴሩ በአጽንኦት ጠይቋል።
ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ መንግስት በዓለም አቀፉ ህግ መሰረት ሰብዓዊ መብቶችን ለማክበር፤ ለማስከበርና ለማሟላት ያለውን ቁርጠኝነት ለሰብዓዊ መብቶች ም/ቤት አባላትና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዳግም ለማረጋገጥ ይወዳል ሲል አስገንዝቧል።
ምንጭ፦የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር/ኤፍቢሲ

#America
" ህወሓት ወታደራዊ ዘመቻውን እንዲያስፋፋም ሆነ አዲስ አበባ እንዲገባ አሜሪካ በምንም ሁኔታ አበረታታ አታውቅም" - የአሜሪካ መንግስት
ከሰሞኑን የህወሓት ቡድን ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ በክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው በሰጡት ቃለ ምልልስ ወቅት ስለ አሜሪካ የተናገሩትን ንግግር በተመለከተ የአሜሪካ መንግስት ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ምላሽ ሰጥቷል።
አቶ ጌታቸው ረዳ በቃለ ምልልሱ ወቅት ፥ " የአሜሪካን አቋም ለመረዳት ከባድ ነው ። አንዳንዴ በሁለታችንም ላይ ማዕቀብ እንደሚጥሉ እያስፈራሩ ሰላም እንድናወርድ ይስገድዱናል፤ መልሰው ህወሓት አዲስ አበባ ከገባ ደም መፋሰስ ይኖራል ይሉናል ፤ በተመሳሳይ ጊዜ አዲስ አበባ የምትገቡ ከሆነ ሊፈጠር የሚችለውን ረብሻ ለማስቀረት እንዲቻል ሌሎች ፓርቲዎችን ጠርታችሁ አንድሁኑ ይሉናል፤ አሜሪካውያኑ ህወሓት አ/አ ቢገባ እንደድሮው ግትር ይሆናል የሚል ፍራቻ አላቸው ይሁን እንጂ አሜሪካ ውስጥ ያለው አስተሳሰብ ወጥ አለመሆኑን ማወቅ ጥሩ ነው " ሲሉ ነው የተናገሩት።
በዚህ ጉዳይ የአሜሪካ መንግስት ተከታዩን ምላሽ ሰጥቷል ፦
" ህወሓት ወታደራዊ ዘመቻውን እንዲያስፋፋ ሆነ ወደ አዲስ አበባ እንዲገባ አሜሪካ በምንም ሁኔታ አበረታታ አታውቅም።
እኛ ለሁሉም ወገኖች በአደባባይ ሆነ በግልም የአሜሪካ አቋም ኢትዮጵያ ውስጥ ላለው ግጭት ወታደራዊ መፍትሄ እንደሌለው በተደጋጋሚ ግልፅ አድርገናል።
የኛ ፍላጎት ህወሓት ለቆ እንዲወጣና ትግራይ ላይ ያለው የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት የከበባ እግድ ሊባል የሚችል ሁኔታ አብቅቶ ማየት መሆኑን ልዩ ልዑኩ ፌልትማን ህዳር 14 አሳውቀዋል።
የእኛ ግብ ግጭቱ እንዲያቆም ፣ የመብቶች ጥሰት እና ሁከት እንዲያበቃ ፣ ድርድር ያለቅድመ ሁኔታ እንዲጀመር ያልተገደበ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት እንዲኖርና ያንን ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታዎች እንዲመቻቹ፤ ሁሉን አቃፊ የሆነ ብሄራዊ ውይይት እንዲጀመር የመጀመሪያውም የመጨረሻውም ብቸኛውም መንገድ ዴፕሎማሲ እንዲሆን መደገፍ ነው። "

#እንድታውቁት
በተሽከርካሪ የፍጥነት መገደቢያ መሳሪያ አተገባበር ላይ ማሻሻያ ተደርጓል።
ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ አዳዲስ ተሽከርካሪዎች ከሌሎች ቅድመ-ሁኔታዎች በተጨማሪነት የፍጥነት መገደቢያ መሳሪያ የማስገጠምና በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት መገጠሙን የሚያረጋገጥ ማስረጃ የማቅረብ ግዴታ የነበራቸው መሆኑ ይታወቃል።
ይሁንና በአተገባበሩ ላይ እየታየ ያለውን ብልሹ አሰራር እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፈተሽ እና ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት የሚያስችል አሰራርና አደረጃጀት ተጠናቆ ተግባራዊ እስኪደረግ ድረስ እንዲሁም የፍጥነት መገደቢያ መሳሪያው ሊገጠምባቸው የሚገባቸውን ተሽከርካሪዎች ዓይነትና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በጥናት ምላሽ መስጠት የሚያስፈልግ በመሆኑ ለጊዜው አዲስ ተሽከርካሪዎችን ወደ ኢትዮጵያ የሚያስገቡ ባለንብረቶች በማምኛውም ጊዜ መሳሪያውን መግጠም እንዳለባቸው እንዲያውቁት ተብሏል።
የግዴታ ስምምነት እየፈረሙና አስፈላጊ ሰነዶቻቸውን በአባሪነት እንዲያያይዙ ተደረጎም በተሽከርካሪዎቹ ላይ የፍጥነት መገደቢያ መሳሪያ መግጠም ሳያስፈልጋቸው አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አሳውቋል።

" በሀሰተኛ ገፆች እንዳትታለሉ " - ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች በሳፋሪኮም ስም ተመሳስለው በተከፈቱ ሀሰተኛ ገፆች እንዳይታለሉ በላከልን መልዕክት አሳውቋል።
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ትክክለኛ የማህበራዊ ገጾች አድራሻ በትዊተር እና ፌስቡክ 𝐒𝐚𝐟𝐚𝐫𝐢𝐜𝐨𝐦𝐄𝐭 ሲሆን ሊንክዲን ላይ ደግሞ 𝐒𝐚𝐟𝐚𝐫𝐢𝐜𝐨𝐦 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐜𝐨𝐦𝐦𝐮𝐧𝐢𝐜𝐚𝐭𝐢𝐨𝐧 𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨𝐩𝐢𝐚 𝐏𝐋𝐂 ነው የሚለው።
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ነን ለሚሉ ሌሎች የሐሰት ገጾች መረጃዎች አያጋሩ ሲልም አሳውቋል።

" ... ጥፋቱን ካደረሱ መካከል በዩኒቨርሲቲው የተማሩ ተማሪዎች አሉበት " - የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት
የወሎ ዩኒቨርሲቲን በአጭር ጊዜ ወደ መማር ማስተማር ስራ ለማስገባት እንደሚሰራ ተገልጿል።
ህወሓት ባደረሰው ዝርፊና ውድመት ወሎ ዩኒቨርሲቲ 10 ቢሊዮን ብር የሚገመት ጉዳት እንደደረሰበት ተገልጿል።
የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት ዶ/ር መንገሻ አየነ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 በሰጡት ቃል ፥ " ህወሓት ተሳቢ መኪና አቅርቦ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ያሉትን ትልልቅ የቴክኖሎጂ ቁሳቁሶች ፣ ላብራቶሪ ቁሳቁሶች ፣ የወርክሾፕ፣ የኢንጂነሪንግ ፣ የቴክኖሎጂ ፣ የህክምናና ጤና ሳይንስ ፣ የተፈጥሮ ሳይንስ ፣ የግብርና ኮሌጅ ቁሳቁሶችን ነቅሎ ጭኖ ወስዷል " ብለዋል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንት ዶ/ር መንገሻ ፥ " ይህ የጥፋት ኃይል ዩኒቨርሲቲው በሚሊዮን ሚቆጠር ገንዘብ አውጥቶ የገነባቸውንና በጣም የሚጠቅሙ ቁሳቁሶች ዘርፎ መውሰድ አይደለም የሚገርመው ፤ መውሰድ ያልቻለውን ኢንስታሌሽን ( የኤሌክትሪክ ፣ የኢንተርኔት ፣ የወርክሾፕ) በአጠቃላይ በጣጥሶ ከሱ ቁጥጥር ውጭ የሆኑትን / በቀላሉ ትራንስፖርት ማድረግ የማይችላቸውን ባሉበት እንዲወድሙና ተቋሙ ወደፊት እንዳይጠቀምበት አድርጎ ነው የሄደው " ብለዋል።
ወሎ ዩኒቨርሲቲ በሀገሪቱ እጅግ ዘመናዊ የሚባል የአይሲቲ መሰረተልማት ካሉት ተቋማት አንዱ ሲሆን ህወሓት ወደ ዳታ ማዕከል በመግባት የሚጠቅሙ ኮምፒዩተሮችና መነቀል የሚችሉትን ትልልቅ ባትሪዎችንና ቺፖችን ነቅሎ ወስዷል።
ኢንስታሌሽን ጋር የተገናኙ ትልልቅ ቁሳቁሶች ባሉበት ዳግም አገልግሎት እንዳይሰጡ አድርጎ ማውደሙን ዶ/ር መንገሻ ተናግረዋል።
በአጠቃላይ በሁሉም ካምፓሶች ብዙ ጉዳት የደረሰ ሲሆን በገንዘብ ሲተመን 10 ቢሊዮን ብር ይደርሳል።
ጥፋቱን ካደረሱ የህወሓት ቡድን አባላት መካከል በዛው በዩኒቨርሲቲው የተማሪ ተማሪዎች መኖራቸውን ፕሬዜዳንቱ ተናግረዋል።
ዶ/ር መንገሻ ፥ " በጣም የሚገርመው እኛው ተቋም የሰለጠኑ የተማሩ፣ የመጀመሪያ ፣ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን የያዙ ተማሪዎች አሳብዶ እዚህ ቡድን ውስጥ አስገብቶ ይህን ተቋም በማፍረስ ሂደት ላይ አስተዋጽኦ እንደነበራቸው በአካባቢው የነበሩ እራሳቸው እኛ እዚህ ተምረናል እያሉ ለፀጥታ ኃይሎች ቃል በቃል እንደነገሯቸው የኛ የፀጥታ ኃይሎች ምስርክነታቸውን ነግረውናል።
በጣም ሰፋ ያለ ቡድን ጠመንጃ የያዘ ቡድን ፣ መፍቻ የያዘ ቡድን እንደገና ጀሌ ቡድን በወረፋ እየመጣ ትልልቅ ተሳቢ መኪናዎችን ይዞ እየገባ መካኒክ እሱ የሚፈታውን ወደተሳቢ መኪና የሚጭን ጀሌ ጉልበት ያለው ጫኝ ይሄ ሁሉ ተደራጅቶ የመጣ ኃይል መሆኑን ነው በአካባቢው የነበሩ የተቋሙ የፀጥታ አባላት የአይን ምስክር ሆነው የነገሩን " ብለዋል።
ወሎ ዩኒቨርሲቲ ወደ ቀደመው የመማር ማስተማር ስራ እንዲገባ ለማድረግ የመንግስት ፣ የክልል እና የአካባቢው አስተዳደር እንዲሁም ዓለም አቀፍ ተቋማት እደሚተባበሩን እርግጠኛ ነን ያሉት ዶ/ር መንገሻ " በእኛ ግምት መማር ማስተማሩን በአጭር ጊዜ ውስጥ መልሰን እናስጀምራለን" ብለዋል።
ወሎ ዩኒቨርሲቲ ከ30 ሺህ ላይ ተማሪዎችን ሲያስተምር የነበረ የ2ኛ ትውልድ ዩኒቨርሲቲ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንት ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

TIKVAH-ETHIOPIA
#Niger ትላንትና ቅዳሜ በምዕራብ ኒጀር ከቡርኪነፋሶ በኩል በአጀብ የገቡ የፈረንሳይ ወታደሮች ከተቃዋሚዎች ጋር በፈጠሩት ግጭት ቢያንስ 2 ሰዎች ሲገደሉ 18 መቁሰላቸውን የኒጀር መንግስት አስታውቋል። የፈረንሳይ ጦር ሰራዊት ደግሞ ፥ ወታደራዊ አጀቡ በገጠመው ተቃውሞ የተነሳ ከቡርኪናፋሶ ለአንድ ሳምንት ያህል መውጣት አቅቶት እንደነበርና በዛው መቆየቱን ገልጿል። የፈረንሳይ ወታደሮች አሸባሪዎች የሚወስዱትን…
" እስከ ቀጣዩ ሰኔ ወር ድረስ በምእራብ አፍሪካ አገራት ያለውን አብዛኛውን ጦር ወደ ፓሪስ የመመለስ እቅድ ተይዟል " - ኢማኑኤል ማክሮን
የፈረንሳይ ጦር ከ9 ዓመት በኋላ ከምዕራብ አፍሪካ አካባቢ ሊወጣ ነው።
ፈረንሳይ በምዕራብ እና መካከለኛው አፍሪካ አገራት አክራሪ ጽንፈኞች የሽብር ድርጊቶችን እየፈጸሙ በመሆኑ ይሄንን ድርጊት ለማስቆም በሚል ወደ አካባቢው ጦሯን አስገብታ ነበር።
ማሊ ፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ኒጀር እና ቻድ ደግሞ ከአምስት ሺህ በላይ የፈረንሳይ ጦር የሰፈረባቸው ሀገራት ናቸው፡፡
ፈረንሳይ ጦሯን በምን ምክንያት እንደምታስወጣ በግልጽ አላሳወቀችም።
በማሊ በሶስት ካምፖች ሰፍሮ ያለው የፈረንሳይ ጦር አሁን ላይ ቱምቡክቱ ላይ ካለው ወታደራዊ ጣቢያ ውጪ ቀሪው ጓዙን በመጠቅለል ላይ ነው።
የፈረንሳይ ፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እስከ ቀጣዩ ሰኔ ወር ድረስ በምእራብ አፍሪካ አገራት ያለውን አብዛኛውን ጦር ወደ ፓሪስ የመመለስ እቅድ መያዙን ተናግረዋል፡፡
በሳህል አካባቢ ሰፍሮ የነበረው የፈረንሳይ ጦር አካባቢውን ለቆ ሲወጣ የአውሮፓ ህብረት አባል አገር ሌላ ጦር በአካባቢው ሊሰፍር እንደሚችል ፕሬዘዳንት ማክሮን ተናግረዋል።
የአውሮፓ አገራት ሰላም አስከባሪ ጦር ወደ ሳህል ቀጠና የሚሰማራው ከምዕራብ አፍሪካ አገራት ወደ አውሮፓ በመሻገር የሽብር ድርጊቶች እንዳይፈጸሙ ያለመ ነው ተብሏል፡፡
የማሊና ቡርኪናፋሶ ዜጎች በተለያዩ ከተሞች የፈርንሳይ ጦር አገራቸውን ለቀው እንዲወጡ የሚጠይቁ ሰላማዊ ሰልፎች መካሄዳቸው ይታወሳል።
ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ / ሲጂቲኤን

#TechZone
ውፍረትን እና ቦርጭን መቀነስ ይፈልጋሉ? 0929088890
ያሉበት ድረስ ከነፃ ማድረሻ ጋር!
ሙሉ ከወገብ በላይ(ቦዲ) - 899ብር
የቦርጭ ብቻ -599 ብር
ሙሉ በሙሉ ቦርጭን በአጭር ጊዜ የሚያጠፋ እና
ማራኪ-ቁመና የሚያላብስ ።
ተጨማሪ : የቴሌግራም አድራሻችን ይጎብኙ
( ክልል ከተሞች እንገኛለን ) @አ.አ = ቦሌ መዳሃንያለም
ውፍረትን እና ቦርጭን መቀነስ ይፈልጋሉ? 0929088890
ያሉበት ድረስ ከነፃ ማድረሻ ጋር!
ሙሉ ከወገብ በላይ(ቦዲ) - 899ብር
የቦርጭ ብቻ -599 ብር
ሙሉ በሙሉ ቦርጭን በአጭር ጊዜ የሚያጠፋ እና
ማራኪ-ቁመና የሚያላብስ ።
ተጨማሪ : የቴሌግራም አድራሻችን ይጎብኙ
( ክልል ከተሞች እንገኛለን ) @አ.አ = ቦሌ መዳሃንያለም