TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የስራ ማቆም አድማ⬇️

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ‹‹ላለፉት ስምንት ዓመታት ላነሳናቸው ፍትሐዊ የሆኑ ከሙያ ዕውቅና፣ ከደመወዝና ከጥቅማ ጥቅም ጋር ለተገናኙ ጥያቄዎች በቂና ወቅታዊ ምላሽ አላገኘንም፤›› በማለት፣ ከሰኞ ነሐሴ 21 ቀን 2010 ዓ.ም. ጠዋት ጀምሮ የሥራ ማቆም #አድማ እንደሚያደርጉ አስታወቁ፡፡

በዚህም መሠረት #ከሰኞ ጠዋት አንድ ሰዓት ጀምሮ ከአምቡላንስ፣ ከቪአይፒና ከወታደራዊ በረራዎች ውጪ አናስተናግድም ሲሉም፣ ለባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ጽሕፈት ቤት ባስገቡት ደብዳቤ አስታውቀዋል፡፡

ተቆጣጣሪዎቹ ሰኔ 11 ቀን 2010 ዓ.ም. ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ባስገቡት ደብዳቤ በአፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጣቸው፣ ምላሽ ካላገኙ ግን ሥራቸውን #እንደሚለቁ ማስታወቃቸው ይታወሳል፡፡

©ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ ውሳኔዎች !

- የሴርያው ቡድኖች የቡድን ልምምዳቸውን #ከሰኞ ጀምሮ እንዲጀምሩ ፈቃድ ሰጥተዋል።

- ከግንቦት 17 ጀምሮ ጂሞች ፣ የመዋኛ ስፍራዎች እንዲሁም የስፖርት ማዕከላት አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉ።

- ሲኒማ እና ቲያትር ቤቶች ከሰኔ 8 ጀምሮ ስራ እንደሚጀምሩ ተገልጿል።

Via @tikvahethsport (ቲክቫህ ስፖርት)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

በኤሌክትሪክ ሞተር ከሚሰሩት #በስተቀር የተገጣጠሙ የቤት አውቶሞቢሎች፣ የባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች እና የተገጣጠሙ ሞተር ሳይክሎችን ጨምሮ " ቅድሚያ የማይሰጣቸው " ተብለው የተለዩ 38 ዓይነት ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ እግድ ተጥሏል።

እግዱ መጣሉን ያሳወቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ነው።

ይኸው እግድ የተላለፈው የህገወጥ የምንዛሬ ገበያውን ይበልጥ ለማውረድ በማሰብ መሆኑ ተገልጿል።

የእግዱ መተግበር በአማካኝ ግማሽ ያህል የውጭ ምንዛሬን ሊያስቀር ይችላል ተብሏል።

#ከሰኞ ጀምሮ ተግባራዊ መሆን የሚጀምረው እገዳ የሚቆየው ላልተወሰነ ጊዜ  ሲሆን እገዳ የተጣለባቸውን ምርቶች ለማስገባት የውጭ ምንዛሬ መጠየቅ እንደማይቻል የብሄራዊ ባንክ አሳውቋል።

ወደ አገር እንዳይገቡ አገዳ የተጣለባቸው ምርቶች ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia