TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" በቦረና ዞን የሞቱ እንስሳት ቁጥር 70 ሺህ ተሻግሯል " በቦረና ዞን በተከሰተው ድርቅ ምክንያት የሞቱ እንስሳት ቁጥር ከ70 ሺ ማለፉን የዞኑ አርብቶ አደር ልማት ኃላፊ ዶ/ር ቃሲም ጉዮ አስታወቁ። ድርቁ ከእንስሳት ሞት ባሻገር በሰዎች ህይወት ላይ ማህበራዊ ጉዳት እያደረሰ መሆኑንም አመልክተዋል። ዶ/ር ቃሲም ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ፥ " 70,185 ከብቶች ሞተዋል ፤ 117,462 እራሳቸው መነሳት…
#BORANA

• " ነፍሴን ካወቅኩ ጀምሮ ግን እንደዚህ አይነት ድርቅ አይቼ አላዉቅም " - የ88 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋው አቶ አብጃሀታኒ ሞሉ

• " ምን እንደሚገጥመንም ፈጣሪ (ዋቃ) ብቻ ነዉ የሚያወቀው " - ወ/ሮ ደቦ ዋቅቶላ

ወይዘሮ ደቦ ዋቅቶላ አካባቢቸውን ለቀው ወደ ሌላ ስፍራ ለስደት ከሄዱ አርብቶ አደሮችን መካከል ሲሆኑ ቀበሌያቸው በድርቅ በመጎዳቱ ለእንስሳቱ ዉሃና ሳር ለሰዉም የሚሆን ምግብ በመጥፋቱ እንስሳቶቹን እየነዱ ወደ ድሬ ወረዳ መሰደዳቸውን ለሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያ ኤፍ ኤም 91.5 ተናግረዋል።

ወ/ሮ ደቦ፥ " ምን እንደሚገጥመንም ፈጣሪ (ዋቃ) ብቻ ነዉ የሚያወቀው " ብለዋል፡፡

የ88 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋው አቶ አብጃሀታኒ ሞሉ በበኩላቸው፥ ከዚህ በፊትም አልፎ አለፎ ድርቅ ይመጣል፣ ነፍሴን ካወቅኩ ጀምሮ ግን እንደዚህ አይነት ድርቅ አይቼ አላዉቅም ብለዋል።

" ከእኔ ብቻ 132 ከብቶች አልቀውብኛል " የሚሉት እኚህ አባታችን " አሁን ደግሞ እኔና በአካባቢዬ ያሉ ሰዎች እየተራብን ነዉ፣ በቦረና ሰማይ ላይ ደመናም አይታይም ስለዚህ ፈጣሪ፣ ህዝብና መንግስት ተረባርበዉ ካልደረሱልን እንኳን እንስሳት እኛም በረሀብ ልናልቅ ስለሆነ መላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲረዳን ጥሪዬን አቀርባለሁ " ብለዋል፡፡

በቦረና ዞን በድርቅ በተመቱት 5 ወረዳዎች ከሌሎች እንስሳት በተለየ መልኩ አህያዎች በራሳቸዉ ያሉበትን አካባቢ በመልቀቅ ደመና ወዳለበት እየጠፉ ሲሆን ይህም የተለመደ የአህያ ልዩ ባህሪይ በመሆኑ በርካታ አርብቶ አደሮች አህያዎቻቸውን ፍለጋ ተሰማርተዋል።

በቦረና ዞን በድርቅ በተመቱ አካባቢዎች በየቦታው የሞቱ እንስሳቶች ቅሪት ፣ በህይወት ያሉትም በጣም ተዳክመው አጥንታቸው ከቆዳቸው ጋር ተጣብቆ ይታያል።

ከሀዩ ኤፍ ኤም የተወሰደ።

@tikvahethiopia
#Borana #Dawa

የIOM WASH ቡድን በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን እና ሶማሊ ክልል ዳዋ ዞን የተከሰተውን ድርቅ ለመከላከል ይረዳ ዘንድ ለህብረተሰቡ የውሃ ማጓጓዝ ስራ መስራት መጀመሩን ገልጿል።

IOM በዚህ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት በከባድ ድርቅ ለተጎዱ እና አስተማማኝ የውሃ ምንጭ ለሌላቸው ማህበረሰቦች ውሃ የማድረስ ስራ እየሰራ መሆኑን አመልክቷል።

ይህንን ተግባር ለማከናወን የጀርመን የፌደራል የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ልግስና ድጋፍ ማድረጉ ተገልጿል።

በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን እና በሶማሊ ክልል በዳዋ ዞን በከፋ ድርቅ ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ እንስሳት መሞታቸው ሰዎችም በውሃ እጥረት ለከፋ ችግር መጋለጣቸው መገለፁ ይታወቃል።

@tikvahethiopia
#BORANA

" የዱር እንስሳቱ ለሞትና ስደት ተዳርገዋል " - ቦረና ብሄራዊ ፓርክ

በቦረና የተከሰተው ድርቅ በአካባቢው በሚኖረው ማህበረሰብ እንዲሁም በቤት እንስሳት ላይ ያደረሰውን ተፅእኖ ከዚህ ቀደም ተደጋጋሚ መረጃ መለዋወጣችን አይዘነጋም።

ድርቁ ወገኖቻችንን እና እንስሳቶቻችን ክፉኛ እየጎዳ ሲሆን አሁን ደግሞ እንደተሰማው በድርቁ ሳቢያ በቦረና ብሄራዊ ፓርክ ውስጥ የሚገኙ የዱር እንስሳት ለከፍተኛ የውሃና የምግብ ችግር ተዳርገዋል። 

የዱር እንስሳቱ ለከፍተኛ የውሃ እና የምግብ ችግር በመዳረጋቸው ለሞትና ስደት መዳረጋቸውን የፓርኩ አስተዳደር ለኢዜአ ገልጿል።

በርካታ ቁጥር ያላቸው የሜዳ አህያ፣ ከርከሮዎችና ሌሎችም መሞታቸውን ሪፖርት ተደርጓል።

የዱር እንስሳቱ ሞትና ስደት ፓርኩ ባሉት አምስት ክፍሎች ወይም ብሎኮች ውስጥ የሚታይ ሲሆን በፓርኩ ከሚገኙት የዱር አንስሳት መካከል በተለይም ግሪዝ ዜብራ፣ አጋዘን እና ከርከሮ በድርቁ ሳቢያ ህልውናቸው ጥያቄ ውስጥ መግባቱ ተገልጿል።

በአካባቢው የሚገኙ አንዳንድ አርሶ አደሮች በሞተር ታግዘው ከመሬት ወስጥ በሚያወጡበት ውሃ ለዱር እንስሳቱ ውሃ ሲሰጡ ነው የቆዩት።

የዱር እንስሳቱ አደጋ ውስጥ በመሆናቸው መንግስት እና የሚመለከታቸው አካላት አስቸኳይ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

የድርቁ ችግር በዚሁ ከቀጠለ በፓርኩ ባሉት በርካታ የዱር እንስሳት የመኖር ህልውና ላይ አደጋ ጋርጧል ብለዋል።

በቦረና ብሔራዊ ፓርክ ግሬዝ ዜብራ፣ አጋዘን፣ የሜዳ አህያ፣ ሰጎን፣ ቀጭኔ እና አንበሳን ጨምሮ ሌሎች ከ286 በላይ የአእዋፋት ዝርያዎች ይገኛሉ። 

የቦረና ብሔራዊ ፓርክ በ2005 ዓ.ም ህጋዊ እውቅናን አግኝቶ የተቋቋመ ሲሆን 5 ክፍሎች ወይም ብሎኮች እንዳሉት የኢዜአ ዘገባ ያሳያል።

@tikvahethiopia
#Borana

የኢትዮጵያጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ ከፍተኛ ባለስጣናት በቦረና ዞን ያቤሎ ወረዳ ጉብኝት እያደረጉ ነው።

የጠ/ሚ ፅ/ቤት ጉብኝቱ ፥ " በድርቅ የተጎዱ ማህበረሰቦችን ተግዳሮቶች በጥልቀት ለመገምገም " እንደሆነው ገልጿል።

ፅ/ቤቱ የዝናብ ውሀ እጥረት መከሰቱ የእንስሳት መኖ እጥረት እና የውሃ አቅርቦት ውስንነትን ጨምሮ በርካታ ፈታኝ ሁኔታዎችን ማስከተሉን አሳውቋል።

በሌላ መረጃ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ያቤሎ ኢፋ ቦሩ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤትን መጎብኘታቸው ተገልጿል።

@tikvahethiopia
#Oromia #Borana📍

" የድርቁ ሁኔታ ምንም መሻሻል አላሳየም " - የቦረና ዞን የግብርና ፅ/ቤት

• በድርቁ ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ ከብቶች አልቀዋል።

• ወደ 262 ሺ ከብቶች ሞተዋል።

• 280 ሺህ በላይ ከብቶች በሰው ጉልበት ነው የሚነሱት።

የቦረና ዞን የግብርና ፅ/ቤት የእንሳት ሃብት ልማት አስተባባሪ ዶ/ር ቃሲም ጉዮ በቦረና ያለው የድርቅ ሁኔታ ምንም መሻሻል እንዳላሳየ ለቪኦኤ በሰጡት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል።

ዶ/ር ቃሲም ጉዮ ፥ " የተለያየ ድጋፍ ቢደረግም ሁኔታው እንደዛው ነው እየቀጠለ ያለው። ስለዚህ የድርቁ ሁኔታ ሄዶ ሄዶ መሃሉንም አልፎ ወደ መጨረሻ አካባቢ ነው ያለነው " ብለዋል።

በድርቁ ምክንያት ወደ 262 ሺ ከብቶች የሞቱ ሲሆን ወደ 280 ሺህ በላይ ከብቶች በሰው ጉልበት ነው ከመሬት የሚነሱት ሲሉ አክለዋል።

በግምት ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ ከብቶችን ቦረና ዞን አጥቷል።

ዶክተር ቃሲም ጉዮ በድርቁ ምክንያት የምግብ እጥረት ማጋጠሙን የገለፁ ሲሆን ለህበረተሰቡ ሆነ ለእንስሳት ዘርፈ ብዙ ድጋፍ እየተደረገ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በድርቅ ከብቶቻቸው ያለቁባቸው የዞኑ ነዋሪዎች የሚደረገው ድጋፍ አሁንም በቂ ባለመሆኑ መንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ፣ ግለሰቦች ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ... እንስሳት የሚበሉትን አጥተው አብዛኛዎቹ አልቀዋል፤ ከእንስሳትም አልፎ ለሰው ህይወትም እየሰጋን ነው " - አቶ ጎዳና ሎራ #NakorMelkaVoA በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን የድሬ ነዋሪ የሆኑት አቶ ጎዳና ሎራ ባለፈው ዓመት መዝነብ የነበረበት የመኸር እና ክረምት ዝናብ ባለመዝነቡ በሰዎች እና በእንስሳት ላይ ጉዳት መድረሱን ገልፀው ፤ ተጨማሪ ጉዳት ለመከላከል ርብርብ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።…
#Oromia , #Borana📍

በድርቅ ምክንያት 30 ከብቶቻቸውን ያጡት የድሬ ወረዳ ነዋሪው ጎዳና ሎራ (ለቪኦኤ የሰጡት ቃል) ፦

" እኛ የቦረና ህዝብ ከከብት ውጪ ሌላ ምንም ነገር የለንም። ያሉን ከብቶች በድርቅ ምክንያት አልቀውብናል።

አሁን በነፍስ ያሉት ሞተው ካለቁብን ህይወታችን በጨለማ ተጋረደ ማለት ነው። አሁን ባለው ሁኔታ በህይወት ያሉ ከብቶች እንኳን ዋጋ የላቸውም።

ድሮ በ10 ሺህ ብር የሚሸጥ ከብት 2 ሺህ ብር እያወጣ አይደለም። በችግር ላይ ነን። ህዝቡ ምንም የለውም። በፊት ፍየል ነበር አሁን ህዝቡ እሱን እየሸጠ ከብቶቹን ለማዳን እየተረባረበ ስለሆነ እነሱም አልቀዋል።

መንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ሁሉ በመተባበር ከቦረና ህዝብ ጎን መቆም ያስፈልጋል አለበለዚያ አሁን የተከሰተው ድርቅ ለሰው ህይወትም አስጊ ነው። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
🌧 ቦረና 🌧 ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ አስከፊ ድርቅ ውስጥ የነበሩ አካባቢዎች ዝናብ ጥሏል። ይህም ነዋሪዎች ላይ ደስታን ፈጥሯል። ከሰሞኑን በእነዚህ አከባቢዎች ላይ የሚኖሩ ነዋሪዎች ፈጣሪያቸውን በማመስገን ከብቶቻቸው የዝናብ ዉሃ ሲጠጡ የሚያሳይ ፎቶ እና ቪዲዮ በማሕበራዊ ሚዲያ እያጋሩ ይገኛሉ። ቃላቸውን ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ክፍል የሰጡት የቦረና ዞን ኤልዋዬ ወረዳ ነዋሪው አባ ሾባ ሞሉ ዝናብ…
#BORANA

ከሰሞኑን በከፍተኛ ድርቅ ውስጥ የነበሩ የቦረና አካባቢዎች ዝናብ አግኝተዋል።

ነዋሪዎች ክብር ለፈጣሪ ይሁንና ፈጣሪያቸውን በማመስገን ከብቶቻቸው የዝናብ ዉሃ ሲጠጡ ሚያሳዩ ፎቶ እና ቪዲዮ በማሕበራዊ ሚዲያዎች እያጋሩ ይገኛሉ።

ከሰሞኑ ዝናብ ጋር በተያያዘ አቶ ሙስጠፋ ከዲር በኦሮሚያ የቡሳ ጎኖፋ ጽ/ቤት ሀላፊ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ የተናገሩት ፦

" በሁሉም ወረዳዎች ላይ ዝናብ ዘንቧል። በቂ ባይሆንም በቦረና ወረዳ፣ ምዕራብ ጉጂ እና ምዕራብ ባሌ ዘንቧል።

ጅማሬው ጥሩ ይመስላል። የአየር ትንበያ ዝናብ እንደሚዘንብ ያሳያል። አሁን ያለው ዝናብ የነበረውን ችግር ይፈታል ባንልም፣ ዉሃ ያገኛሉ።

ነገር ግን የሰው እርዳታ ብያንስ ለሚቀጥሉት ሶሰት፣ አራት ወራት ሊቀጥል ይገባል።

ዝናብ ስለጣለ ብቻ እህል አይበቅልም ፣ ሰብል አይዘራም። ስለዚህ የማሕበረሰቡ እርዳታ መቋረጥ የለበትም።

በወንዝ አከባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎችም ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው ፤ ከብቶቹን ለጊዜው በማቆያ ውስጥ እንዲያገግሙ ማድረግ አለባቸው። "

@tikvahethiopia