TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Canada #StudentVisa

ካናዳ በእ.ኤ.አ. 2024 የዓለም አቀፍ ተማሪዎች ቪዛን (የምትቀበላቸውን ተማሪዎች ቁጥር) ትቀንሳለች። ይህም ለሁለት ዓመታት ይቀጥላል።

ሀገሪቱ በ2024 ዕድገቷን ለማረጋጋት ስትል የምትቀበለው 360,000 ዓለም አቀፍ ተማሪዎችን ብቻ እንደሆነ ይፋ አድርጋለች።

የካናዳ ኢሚግሬሽን ስደተኞችና ዜግነት ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የዓለም አቀፍ ተማሪዎች ቁጥር እየጨመረ ነው ብሏል።

አንዳንድ ተቋሞች ገቢያቸውን ለማሳደግ በሚል የቅበላ መጠናቸው በከፍተኛ ሁኔታ ጨምረዋል እንዲሁም ብዙ ተማሪዎች ለስኬታማነት ተገቢውን ድጋፍ ሳያገኙ ወደ ካናዳ እየመጡ ነው ሲል አስረድቷል።

ዓለም አቀፍ ተማሪዎች ለካናዳ ማኀበራዊ፣ ኢኮኖሚያና ባህላዊ ለውጥ አንድ አካል ናቸው ሲል ገልጿል።

ይሁን እንጂ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች ወደ ካናዳ መምጣት ፦
* በጤና አገልግሎት
* በቤት አቅርቦት ላይ #ጫና እየፈጠረ መጥቷል ነው የተባለው።

በመሆኑም፣ " ተማሪዎችን ከሕገ ወጦች ለመከላከልና የሀገሪቱን የሕዝብ ቁጥር ተመጣጣኝ ለማድረግ አዲስ ሕግ አስፈልጓል " ነው ያለው፡፡

የካናዳ ኢሚግሬሽን ስደተኞችና ዜግነት ሚኒስትር ማርክ ሚለር፣ " አዲሱ ሕግ ለሁለት ዓመት ይቆያል። በ2024 የ360,000 ማመልከቻ ብቻ እንቀበላለን " ብለዋል፡፡

" ይህም ከባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት በ35% ይቀንሳል" ብለዋል ሚለር፡፡

" ከመጠን በላይ እየጨመረ የመጣው የዓለም አቀፍ ተማሪዎች ቁጥር በካናዳ ያልተረጋጋ እድገት እያሳዬ " ነው ያሉት ሚኒስትሩ፣ ይህን ችግር ለመቅረፍም ከየግዛት አስተዳዳሪዎች ጋር መምከራቸውን አስታውቀዋል፡፡

ካናዳ እጅግ በርካታ ኢትዮጵያውያን ለትምህርት እንዲሁም ለስራ ከሚመርጧትና ለመሄድም ጥረት ከሚያደርጉባት ሀገራት አንዷ እንደሆነች ይታወቃል።

More : https://t.iss.one/ThiqaMediaEth/185

@tikvahethiopia @thiqamediaeth